No summary available.
የካቲት 7 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገብረሥላሴ ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ጌታ ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አልቀረቡም ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት የሰበር አቤቱታ ስላቀረበ ነው። የክርክሩ መነሻ አመልካች ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ነው። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በከሣሽነት ቀርቦ በሥር ተከሣሽ የነበረው ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 97/199ዐ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት የአዱስ አበባ ደቄት ፊብሪካን ለመሸጥ የሐራጅ ማስታወቂያ አውጥቶ ነበር። በሐራጅ ማስታወቂያው መሰረት ተወዲድሬ ጨረታውን በማሸነፋ ታህሣሥ 23 ቀን 1993 ዓ.ም በተፃፈ ሽያጭ ውል ፊብሪካውን በብር 42,5ዐዐ,1ዐዐ.99/አርባ ሁለት ሚሉዮን አምስት መቶ ሺ አንድ መቶ ብር ከዘጠና ዘጠኝ ሣንቲም/ ገዝቻለሁ። አከፊፈለን በተመለከተ ብር 1ዐ,625,025.5ዐ /አስር ሚሉየን ስድስት መቶ ሃያ አምስት ሺ ሀያ አምስት ብር ከሀምሣ ሣንቲም/ ተከፍሎል። ቀሪው ብር 31,825,ዐ25 /ሰላሣ አንድ ሚሉየን ስምንት መቶ ሃያ አምስት ሺ ሀያ አምስት ብር/ ተከሣሽ በሚሰጠው ብድር ለመክፈል የካቲት 17 ቀን 1993 ዓ.ም ከተከሣሽ /ተጠሪ/ ጋር የብድር ውል ተዋውለናል። ከተከሣሽ /ተጠሪ/ ለተወሰደው ብድር ከሣሽ ሰላሣ ሰባት መኪናዎችን በመያዣ ውል አስይዟል። ሆኖም የፊብሪካው ሽያጭ የባንኩን አሻሻጥ ደንብ የተከተለ አይደለም በማለት የባንኩ ኢንስፓክተሮች ሐምል 23 ቀን 1993 ዓ.ም ባቀረቡት ሪፕርት ፊብሪካው በተጠሪ በመያዣነት ያልተያዘ መያዣውም የተመዘገበ አይደለም ተብል የተከሣሽ /ተጠሪ/ ድርጅት ሥራ አስኪያጆችና የከሣሽ /አመልካች/ ድርጅት በወንጀል ተከሰው የከሣሽ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ በነፃ ተሰናብተዋል። ስለዚህ የሽያጭ ውል የማይፀናና ውል ለመዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፉት ያልተደረገ በመሆኑ የብድርና የመያዣ ውለ ፈራሽ ነው ተብል ይወሰንልን በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በተከሣሽነት ቀርቦ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የለውም። ሽያጩ እንዱፈርስ የመጠየቅ መብት ያለው የተሸጠው ንብረት ባለቤት የሆኑት አስር አለቃ ወ/ሃይማኖት ስርቋ እንጅ ከሣሽ /አመልካች/ ክስ የማቅረብ መብት የለውም። ከሣሽ /አመልካች/ የሽያጭ ውለ እንዱፈርስልኝ በማለት ጥያቄ ያቀረበው በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 447/1/ የተደነገገው የሁለት ወር ጊዜ ካለፈ በኋላ ነው። ጥያቄው በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 181ዐ የተደነገገው የሁለት ዓመት የይርጋ ገደብ ካለፈ በኋላ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ አቅርቧል።
አመልካች ተጠሪ/ ተከሣሽ/ ፊብሪካ የሸጠልን በመሆኑና የሸጠልኝ የፊብሪካ ላይ ሽያጭ ውል ሉፈፀም የማይችል በመሆኑ ክስ የማቅረብ መብት አለኝ። ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የማየት ሥልጣን አለው የሚል ሰፉ ክርክር አቅርቧል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ከሰማና ያቀረቡትን የጽሐፍ ክርክርና የሰነድ ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ክስ ተቀብል የማከራከርና ውሣኔ የመስጠት ሥልጣን አለው። ከሣሽ /አመልካች/ ክስ ለማቅረብ መብት አላቸው በማለት ብይን የሰጠ ሲሆን በተጠሪ በኩል የቀረበውን የሁለት ወር የይርጋ ጊዜ መቃወሚያ በመቀበል በአዋጅ ቁጥር 97/9ዐ አንቀጽ 6 ባንክ በመያዣ ሲሸጥ ከፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 394-449 የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንደአግባብነታቸው ተፈፃሚነት እንዲላቸው ይደነግጋል። ከሣሽ መብት የላለውን ንብረት ነው የሸጠልኝ በማለት በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 446 መሰረት ሽያጩ እንዱሰርዝ የሚያቀርቡት ጥያቄ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 447/1/ የተደነገገው የሁለት ወር ጊዜ ካለፈ በኋላ የቀረበ በመሆኑ ክሱ በይርጋ የታገደ ነው በማለት ብይን ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቧዋል። ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን በድምጽ ብልጫ አጽንቶታል።
አመልካች ታህሣሥ 1 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ከተጠሪ ጋር የተደረገው የፊብሪካ ሽያጭ ውልና የመያዣ ውለ ቀሪ እንዱሆንና የጠየቅሁት የባንክ ኢንስፓክሽን ተጠሪ ንብረቱን የሸጠው የመያዣ መብት ሣይኖረው ነው በማለት በጽሐፍ የሰጠውን ማረጋገጫ በማስረጃነት በመያያዝ ነው። ውለ ሕግን የሚቃረን ውል ከሆነ በይርጋ የማይታገድ በመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ለሕግ ተቃራኒ የሆነ ውል ቀሪ እንዱሆን የሚቀርብ ጥያቄ በይርጋ የማይታገድ መሆኑን ሣይገነዘብ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ ማጽናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው።በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 344 እስከ ፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 449 የተደነገጉት ድንጋጌዎች ለጉዲዩ ተፈፃሚ የሚሆኑት በመጀመሪያ ተጠሪ በንብረቱ ላይ የመያዣያ መብት ሲኖረው ነው። ተጠሪ በንብረቱ ላይ የመያዣ መብት ሣይኖረው የከፍተኛው ፍርድ ቤትም ሆነ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አብላጫው ድምጽ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 447/1/ን በመጥቀስ የሰጡት ውሣኔ የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት። ስለዚህ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ ሐምል 15 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ለአመልካች በአዋጅ ቁጥር 97/9ዐ መሰረት የደቄት ፊብሪካውን የሸጥነው የፊብሪካው ባለቤት ለሆኑት አስር አለቃ ወልደሀይማኖት ስቋር የሰጠነው ብድር ባለመከፈለና የፊብሪካውን ሕንፃ በመያዣነት በክልል 14 መስተዲድር ሥራና ከተማ ልማት ቢሮ አስመዝግበን ስለያዝነው ነው። ማሽነሪዎቹንና ተሽከርካሪዎቹን በተመለከተ በመያዣነት የያዛቸው አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ በሰጠን ውክልና መሰረት ሸጠናል።
ስለዚህ አመልካች በዚህ በኩል የሚያቀርበው ክርክር ተገቢ አይደለም ይህም በመሆኑ ለጉዲዩ የአዋጅ ቁጥር 97/9ዐ አንቀጽ 6 በሚደነግገው መሰረት ከፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 339 እስከ ፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 449 የተደነገጉት ድንጋጌዎች እንደአግባብነታቸው ተፈፃሚነት አላቸው። ስለሆነም የከፍተኛው ፍርድ ቤትም ሆነ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል።
ግራ ቀኙ ለሰበር ችልት በጽሐፍ ካቀረቡት ክርክር በተጨማሪ ችልቱ የአመልካችንና የተጠሪን የቃል ክርክር ሐምል 15 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የሰማ ሲሆን የቃል ክርክሩ ወደ ጽሐፍ ተቀይሮ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል። የአመልካችና ተጠሪ የቃል ክርክር በይዘቱ በጽሐፍ ካቀረቡት ክርክር ጋር ተመሣሣይነት ያለው ሲሆን አመልካች ሕገወጥ የሆነ ውል እንዱፈርስ የሚቀርብ ጥያቄ በጊዜ ገደብ አይታገድም የሚል መሰረታዊ የሕግ መርህ አለ።ለምሣላ በዚህ ዘመን የባሪያ ንግድ አይፈቀድም። ባሪያ ነግዲለሁ ብል ተዋውል ቢገኝ በሁለት ዓመት ይርጋ ታግዶል ልባል አይችልም የሽያጭ ውለ ሕገወጥ ስለሆነ። በዚህ ጉዲይም ተጠሪ የሱ ያልሆነውንና በአዋጅ ሉሸጠው የማይችለውን መሸጥ አይችልም። አንድ ውል ሕገወጥ ውል ነው የሚባለው በሕግ የተከለከለ ሲሆን ነው። ስለዚህ የይርጋ ክርክርና የይርጋ የሕግ ድንጋጌዎች በዚህ ጉዲይ ተጠቃሽነትም ሆነ ተፈፃሚነት የላቸውም የሚል ይዘት ያለው ሰፉ ክርክር አቅርቧል። ተጠሪ በበኩለ የሸጥነው በመያዣ የያዝነውን ንብረት ነው ገዥ ፊብሪካውንም ተረክበው እየተጠቀሙበት ይገኛለ። ውለ ሕገወጥ ነው መባለ ተገቢ አይደለም የሚል ይዘት ያለው መልስ በቃል ክርክር ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር በግራ ቀኙ በኩል የቀረበው የጽሐፍና የቃል ክርክር ይዘት ከላይ በአጭሩ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው የከፍተኛው ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የአመልካች ጥያቄ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 447/1/ በተደነገገው የጊዜ ገደብ ያልቀረበ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት የሰጡት ውሣኔና የሕግ ትርጉም ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው መሰረታዊ ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ሀ/ ሕገ ወጥ ውል /unlawfull contract/ ማለት በሕግ እንዱደረግ ያልተፈቀደ የሕግ ክልከላ ያለበት ውል ማለት ነው። አንድ ውል ሕገወጥ ውል ነው የሚባለው ተዋዋዮቹ የተዋዋለበት መሰረታዊ ጉዲይ ዓላማ በመሰረታዊና ሞራላዊ ይዘቱ ተዋዋይ ወገኖች ስምምነት በማድረግ መብትና ግዳታ እንዱፈጥሩበት በሕግ ያልተፈቀደ ወይም በሕግ ክልከላ የተደረገበት ሆኖ ሲገኝ ነው። ለምሣላ አመልካች እንዲለው በሕገ መንግሥቱም ሆነ በአገሪቱ የወንጀል ሕግ እንደዚሁም በዓለም አቀፍ የወንጀል ሕግ ማንኛውንም ሰብዓዊ ፍጡር በግዳታ አገልጋይነት መያዝ ወይም በሰው መነገድ የተከለከለ በመሆኑ ሰውን በግዳታ አገልጋይነት ለመያዝ ወይም በሰው ለመነገድ የተደረገ ውል በመሰረታዊ ባህሪውና ሞራላዊ ይዘቱ ሕገወጥ ውል /unlawfull contract/ ነው። አንድ ውል የተመሰረተበት መሰረታዊ ጉዲይ ‛object of contract“ በሕግ ክልከላ የተደረገበት በሆነ ጊዜ ውለ በሕግ ፉት እንደላለና ምንም አይነት ሕጋዊ ውጤት የማያስከትል /void contract/ ነው። አንድ ውል በማናቸውም ሰው ወይም አካል ፈቃድና ስምምነት ሕጋዊ ውጤት እንዱኖረው ማድረግ የማይቻልና በማናቸውም መንገድ ለማስተካከልና ሕጋዊ ውጤት እንዱያገኝ ለማድረግ የማይቻል በሆነ ጊዜ ውለ ከጅምሩ በሕግ ፉት እንዲልተደረገና እንደላለ ‛Null or void contract“ እንደሚሆን በዘርፈ ከተደረጉ ጥናቶች ለመገንዘብ ይቻላል።
በእኛ አገር የሕግ ሥርዓት አንድ ውል የፀና ውል ለመሆን ማሟላት ከሚገባው አንደኛው መሰረታዊ ነጥብ ውለ ሕጋዊ በሆነ ጉዲይ ላይ የተመሰረተ መሆን የሚገባው እንደሆነ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1678 ንዐስ አንቀጽ /ለ/ ይደነግጋል። ይህንን ነጥብ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1678 ንዐስ አንቀጽ ‛ለ“ የእንግሉዝኛው ቅጅ ‛The object of the contract is sufficiently defined and is possible and lawful“ በማለት ከአማርኛው ቅጅ በተሻለ አገላለጽ ይደነግጋል።
ከዚህ በተጨማሪ የውለ መሰረታዊ ባህሪና ጉዲይ በሕግ ያልተፈቀደና ክልከላ የተደረገበት በሆነ ጊዜ ማለትም ውለ ሕገወጥ /unlawful contract/ በሆነ ጊዜ በሕግ ፉት ውጤት እንደማያስከትል በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1716 ተደንግጓል። በውጤት ደረጃ ዳኞች የውለ መሰረታዊ ዓላማ ሕገወጥ መሆኑን ከውለ ቃል ወይም ውለ እንዱፈፀምለት የሚጠይቀው ተዋዋይ ካቀረበው ጽሐፍ በተረደበት በማናቸውም ጊዜ ውለ እንዱፈፀም የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ ለማድረግና አንቀበልም ለማለት የሚችለ መሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1718 በግልጽ ተደንግጓል። የውለ መሰረታዊ ዓላማ ወይም ጉዲይ በሕግ ያልተፈቀደና የተከለከለ ሆኖ ሲያገኙት ዳኞች ሕገወጥ /unlawful/ የሆነው ውል በቀረበላቸው በማናቸውም ጊዜ ሕጋዊ ውጤትና ተፈፃሚነት የለውም በማለት ለመወሰን እንደሚችለና ሕገወጥ የሆነውን ውል ውድቅ ለማድረግ በሕጉ የተደነገገው የይርጋ የጊዜ ገደብ መቃወሚያ ላሆን እንደማይችል ከላይ ከተጠቀስናቸው የሕግ ድንጋጌዎች ይዘት መንፈስና ዓላማ ለመገንዘብ ይቻላል።
ለ/ ውለ ሲደረግ በጠቅላላ የውል ሕግና በልዩ የውል ሕግ ድንጋጌዎች ወይም በላልች ህጎች የተደነገገውን መስፈርት የማያሟላና ጉድለት ያለበት ሆኖ መገኘቱ ውለ የሕጉን መስፈርት የማያሟላ ‛illegal contract“ ያደርገዋል እንጅ ውለን ሕገወጥ ውል /unlawfull contract/ ነው ብል ለመደምደም የሚያስችል አይደለም።
ከባለሀብቱ በቂ የሆነ የውክልና ሥልጣን ሣይኖረው ወይም ንብረቱን ለመሸጥ የሚያስችል መብት በላለው ሰው የተደረገ የሽያጭ ውል፣ ውለ በሕግ የተደነገጉ አስገዲጅ መስፈርቶችን የማያሟላ ነው የዚህ ጉድለት ውለን በፍርድ ቤት እንዱፈርስ መቃወሚያና ክርክር ላቀርብበት የሚችል /invalid contract/ የሚያደርግ አይደለም።
በሕገወጥ ውል /unlawful contract/ እና የሕጉን መስፈርት ሣያሟላ በተደረገ ውል /illegal contract/ መካከል በጽንሰ ሀሣብ ደረጃ ሰፉ ልዩነት እንዲለ በሥነ ሕግ ዙያ በተደረጉ ጥናቶች ብቻ ሣይሆን በብላክስ ልው መዝገበ ቃላት ውስጥ ‛The principal distinction between the terms of lawful and legal is the former contemplates the Substance of a law, the latter the form of law.. To say an act ‛lawful“ implies that it is authorized, sanctioned or at any rate not forbidden by law. To say it is ‛legal“ implies that it is done or performed in accordance with the forms and usage of law, or in a technical manner; in this sense illegal approaches the meaning of invalid“ በሚል መንገድ ተገልጾ እናገኘዋለን።
ከላይ የተገለጸውን የሕግ ጽንሰሀሳብ እና የፍታብሓር ሕግ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው የደቄት ፊብሪካ ሽያጭ ውል በመሰሪታዊ ባህሪው ሞራላዊ ይዘቱና ዓላማው በሕግ ክልከላ የተደረገበት ሕገወጥ ውል /unlawfull contract/ ነው ብል ለመደምደም አይቻልም። አንድ የማይንቀሣቀስ ንብረት ሀብቱን በሽያጭ የማስተላለፍ የውክልና ሥልጣን በባለሀብቱ ባልተሰጠው ሰው ወይም ንብረቱን በሽያጭ ለማስተላለፍ በማይችል ሰው ቢሸጥ ውለን በመሰረታዊ ባህሪው በሞራላዊ ይዘቱና ዓላማው ሕገ ወጥ ውል /unlawfull contract/ አያደርገውም። በአንጻሩ ይህ ጉድለት መኖሩ ቢረጋገጥ ውለ ባለሀብትነትን በሽያጭ ለማስተላለፍ የተደነገጉትን አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች የማያሟላ ‛Illegal or invalid contract“ የሚያደርገው ጉድለት ነው። አመልካች ተጠሪ ፊብሪካውን የሸጠልኝ ንብረቱ ላይ ሕጋዊ የመያዣ መብት ሣይኖረውና ንብረቱን በአዋጅ ቁጥር 97/1990 ለመሸጥ የሚያስችል መብት ሣይኖረው ነው።
ስለዚህ ውለ ሕገወጥ ውል /unlawfull contract/ በመሆኑ ከጅምሩ ውለ እንደላለ የሚቆጠር /null or void contract/ ነው በማለት የሚያቀርበው ክርክርም ከሕጉ መሰረታዊ ሀሣብ ጋር የማይሄድ ነው። የውል ሕግ ወይም ላልች የሕግ ማዕቀፍች የደነገጉትን መስፈርት ሣያሟላ የተደረገ ውል በሙለ /null or void contract/ና ሕገወጥ ውል ነው ከሚል መደምደሚያ ላይ ለመድረስ አይቻልም።
አንድ ውል ከጅምሩ እንዲልተደረገ /null or void contract/ የሚቆጠረው በማናቸውም መንገድ ሕጋዊ ውጤት ለማስገኘት የማይችልና ጉድለቱ ሉስተካከል የሚችልበት ምንም ዓይነት አማራጭ ወይም መንገድ የላለ ሆኖ ሲገኝ መሆኑን ‛An instrument or transaction which is wholly in effective, in operative and incapable of ratification and which thus has no force or effect so that nothing can cure it“ በሚል መንገድ ተገልፃ የምናገኘው ሲሆን የውለን ጉድለት በማቃናት ህጋዊ ውጤት እንዱኖረው ለማድረግ የሚቻልበት መንገድና ሁኔታ ሲኖር ውለ (null or void contract) ሣይሆን ጉድለት ያለበትና ፈራሽ ላሆን የሚችል ውል ‛voidable or invalid contract“ እንደሚሆን Variable exists when an imperfection or detect can be cured by an actor confirmation of him who could take advantage of it“ በሚል መንገድ በብላክስ ልው እና በላልች ጽሐፍች የተሰጡ ትንታኔዎችን በማየት ለመገንዘብ ይቻላል።
በእኛ አገር የህግ ሥርዓት አንድን ንብረት በሽያጭ ለማስተላለፍ መብት ወይም የውክልና ሥልጣን በላለው ሰው ሽያጭ ሲፈፀም የንብረቱ ባለቤት ሽያጩን ካፀደቀውና ከተቀበለው ውለ በሕግ ፉት የፀናና ውጤት ያለው እንደሚሆን ከፍ/ብሓር ሕግ ቁጥር 219ዐ- 2192 የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ይዘት መንፈስና ዓላማ በማየት ለመገንዘብ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ በሽያጭ ሉያስተላልፈው የሚችለው የባለሀብትነት መብት ከላለው ሰው ንብረት የገዛ ገዥ ንብረቱ የእኔ ሀብት ነው የሚል ሶስተኛ ወገን ሲመጣበት ሻጭ በዋቢነት /መድንነት/ እንዱቀርብለት ለመጠየቅ እንደሚችልና የሽያጭ ውለን ለማፍረስ የሚያስችለው በቂ ምክንያት እንደሆነ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2875፣የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2884፤ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2341 እና የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2342 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌዎችን በጣምራ በማንበብ ለመገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም አመልካች ተጠሪ በሽያጭ ሂደቱ ፈፅሞታል በማለት የሚዘረዝራቸው ጉድለቶች በተጠሪ ሙለ በሙለ የተካደና በፍርድ ያልተረጋገጠ መሆኑ እንዲለ ሆኖ ጉድለቱ መኖሩ ቢረጋገጥም እንኳን አመልካች እንደሚለው ውለን ከጅምሩ ሕገ ወጥ ውል/unlawfull contract/ ና ከጅምሩ እንዲልተደረገ የሚያስቆጥር (null or void contract) የሚያደርግ ሣይሆን የሽያጭ ውለን ጉድለት ያለበትና በፍርድ ቤት መቃወሚያና ክርክር ላቀርብበትና ፈራሽ ላሆን የሚችል ውል መሆኑን (voidable or invalid contract) የሚያሣዩ መሆናቸውን ከላይ ከዘረዘርነው የሕግ መሰረተ ሀሣብ የፍታብሓር ድንጋጌዎች ለመገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው የሽያጭ ውል በመሰረታዊ ባህሪው በሞራላዊ ይዘቱና ዓላማው ከሰው ከመነገድ ጋር የሚነፃፀርና ሕገወጥ ውል /unlawful contract/ ልባል የሚችል አይደለም። በሽያጭ ውለ ላይ አመልካች አለ በማለት የሚዘረዝራቸው ጉድለቶች ውለን ከጅምሩ እንዲልተደረገና ሕጋዊ ውጤት የላለው /null or void contract/ የሚያደርጉ አይደለም። አመልካች የሚዘረዝራቸው የሕግ ጉድለቶች መኖራቸው ቢረጋገጥ እንኳን ውለን ጉድለት ያለበትና በፍርድ ቤት ሉፈርስ የሚችል /voidable or invalid Contract/ ሉያደርግ የሚችል ጉድለት ነው። ስለሆነም አመልካች በጽሐፍና በቃል ባቀረቡት ክርክር የሽያጭ ውለ ሕገወጥ የሆነ ውል/unlawful contract/ በመሆኑ ከጅምሩ እንዲልተደረገ መቆጠር የሚገባው(null or void contract) ነው በማለት ያቀረበውን ክርክር ከላይ በዘረዘርናቸው ምክንያቶች አልተቀበልነውም።
2.የሽያጭ ውለ ሲደረግ በተጠሪ በኩል አልተሟለም በማለት አመልካች የሚያነሣቸው የሕግ መከራከሪዎች በተጠሪ የተካደና በፍርድ ያልተረጋገጡ መሆናቸው እንዲለ ሆኖ ጉድለቶቹ ሙለ በሙለ እውነት መሆናቸው ቢረጋገጥ እንኳ ውለን ለማፍረስ ምክንያት የሚሆኑ /avoidable contract) የሚያደርጉ ናቸው። በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1718 በግልጽ እንደተመለከተው ዳኞች ሕጋዊ ውጤትና ተፈፃሚነት የላለው መሆኑን ገልፀው አንድ ውል ተፈፃሚ እንዱሆን የሚቀርብን ጥያቄ ውድቅ የሚያደርጉት ውለ ሕገ ወጥ ውል /unlawfull contract/ ሆኖ ሲያገኙት ነው።
ውለን በፍርድ ቤት ተከራክሮ ለማፍረስ የሚቻል /invalid contract/ ከሆነ ውለ ጉድለት አለበት የሚለው ወገን ውለን ለማስፈረስ ጥያቄውን የሚያቀርብበትን የጊዜ ገደብ ሕግ አውጭው በሕግ ይደነግጋል።
ተጠሪ ለአመልካች የደቄት ፊብሪካውን የሸጥኩት በአዋጅ ቁ
No topics extracted.