No summary available.
ጥር 24 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ተስፊዬ አበበ ሥራ ተቋራጭ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- ማዕረጉ ወርቁ ሥራ ተቋራጭ - ጠበቃ ተካ ዲባ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው። የክርክሩ መነሻ በስር ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበው ክስ ነው። አመልካች ተጠሪ በምዕራብ አርሲ ዞን በገደብ አሣሣ ወረዲ ጥጆ ዋቄንጥረ ከሚባለው ሥፍራ የሚሰራውን የጤና ኬላ ለመገንባት በጨረታ ተወዲድሮ አሸንፎል።
ተጠሪ ይህንን ግንባታ ራሱ ለማከናወን ስላልፈለገ ህንፃውን እኔ ሙለ በሙለ እንድሰራለት በተወካዩ በኩል ተዋውሎል። እኔም ለተጠሪ ኮሚሽን ብር 5ዐ,ዐዐዐ /ሀምሣ ሺህ ብር/ ከፍዬ ውለን በተዋዋልንበት ሰኔ 25 ቀን 1999 ዓ.ም. የግንባታ ቦታውን አስረክቦኝ ሥራውን ሰርቻአለሁ።
ሆኖም ተጠሪ ለተሰራው ሥራ ከምዕራብ አርሲ ዞን ጤና መምሪያ የተከፈለውን ብር 24ዐ,ዐዐዐ /ሁለት መቶ አርባ ሺህ ብር/ ከተቀበለ በኋላ ለእኔ መስጠት ሲገባው ራሱ የወሰደ በመሆኑ ይህንን ገንዘብ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። ተጠሪ በበኩለ የእኔ ወኪል የዚህ አይነት ውል ለመዋዋል ሥልጣን የለውም። አመልካች የውክልና ሥልጣን ከላለው ሰው ጋር አደረግሁ የሚለው ውል ህግን የሚቀረን ነው። አመልካች ህንፃውን አንድም ቀን አልሰራም። የሚል ክርክር አቅርቧል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ በራሱም ሆነ በወኪል አማካኝነት በራሱ ለመገንባት ተጫርቶ ያሸነፈውን የህንፃ ሥራ ውል ለአመልካች አሣልፍ የመስጠት ሥልጣን የለውም። በውለ ላይ አሰሪው የህንፃው ባለቤት የምዕራብ አርሲ ዞን ጤና መምሪያ አልተስማማም። ስለሆነም አመልካች /ከሣሽ/ ያቀረበው ክስ ህጋዊ መሰረት የለውም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአመልካችን ይግባኝ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ግንቦት 17 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ በጨረታ ተወዲድሮ ያሸነፈውን ጤና ኬላ ሰራተኛ ቀጥሬና የሚያስፈልገውን የግንባታ ዕቃ አሟልቼ እንድሰራ በወኪለ አማካኝነት ውል በመፈረምና ብር 5ዐ,ዐዐዐ /ሀምሣ ሺህ ብር/ ኮሚሽን በመቀበል ተዋውሎል ውለን ስንዋዋል የአሰሪው የምዕራብ አርሲ ጤና መምሪያ ተቆጣጣሪ መሀንዱስ የነበረ ሲሆን ተቆጣጣሪ መሐንዱሱ ባለበት የግንባታውን ቦታ ተረካክበናል። ለስራው በተሰጠው ንድፍና ቢል ኦፍ ኳንቲቲ መሰረት ስራውን የሰራሁት እኔ ስሆን አሰሪውም የተሰራውን ሥራ ሲያፀድቅ ቆይቷል። ሰራተኛ ቀጥሬ የግንባታ ዕቃዎችን በራሴ ወጭ አቅርቤና አሟልቼ የሰራሁትን ሥራ ለአሰሪው በማስረከብ የክፍያ ሰርተፍኬት የተቀበለው ተጠሪ ወኪለ የግንባታውን ሥራ ለላላ ለማሳለፍ ስልጣን የለውም በማለት ያቀረበውን ክርክር በመቀበል የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ስለግንባታ ሥራ ውል የተደነገጉ መሰረታዊ የአሰራር መመሪያን የሚፃረርና የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ ውለ ሥልጣን በላለው ተወካይ በኩል የተደረገ ነው። አመልካች የግንባታ ሥራውን የሰራ መሆኑን የሚያስረደ ማስረጃዎችን ያላቀረበ መሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች ተገጋግጧል። ስለዚህ አመልካች ክርክሩን በማስረጃ በአግባቡ ሣያስረዲ በሰበር አቤቱታው አዱስ ክርክር ማቅረቡ ተገቢ አይደለም። የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ጥቅምት 22 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ አቅርበዋል።
አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ በሰበር አቤቱታው ያነሣቸውን የመከራከሪያ ነጥቦች በማጠናከር ተከራክሯል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ያቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ለግንባታ አስፈላጊ የሆነውን የግንባታ ዕቃ በማሟላትና ሰራተኛ በመቅጠር ለሰራሁት ሥራ ተጠሪ ክፍያውን ሉሰጠኝ ይገባል በማለት የቀረበው ክስ የህግ ድጋፍ እና መሰረት የለውም በማለት የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች በእኔና በተጠሪ መካከል ተደርጓል የሚለው ውል ተጠሪ በጨረታ ያሸነፈውን የህንፃ ሥራ ሙለ ለሙለ ለእኔ በመልቀቅ ሥራውን እንድሰራና ዋጋው መጨረሻ ለእኔ ሉከፈል ሰኔ 25 ቀን 1999 ዓ.ም. ተዋውለናል የሚል ክርክር ያቀርባል። ይህ የአመልካች ክርክር በአሰሪው /በምዕራብ አርሲ ዞን ጤና መምሪያ/ ፈቃድና ዕውቅና ተጠሪ የህንፃውን ሥራ ለእኔ አስተላልፍልኛል የሚል ይዘት ያለው አይደለም። የግንባታ ሥራ ውል በአሰሪው ዕውቅናና ፈቃድ ሙለ በሙለ ለላላ ሰው የሚለቀቅበት ወይም ለንዐስሥራ ተቋራጭ የሚሰጥበት ሁኔታ ማለትም ‛Nominated Assignment or Nominated sub contract“ የሚደረግበት ሁኔታ እንዲለና በእኛ አገር አስተዲደር መሥሪያ በቶች ጋር የተደረገን የሥራ ውል ሙለ በሙለ ለላላ ሰው ለመልቀቅ ወይም ለንዐስ የሥራ ተቀራጭ ለመስጠት የአስተዲደሩ መሥሪያ ቤት ፈቃድ አስፈላጊ እንደሆነ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 32ዐ2 ንዐስ አንቀፅ 1 እና ንዐስ አንቀፅ 2 ተደንግጓል። ከዚህ በተጨማሪ በአስተዲደሩ መስሪያ ቤት ሙለ ዕውቅናና ፈቃድ የህንፃ ሥራ ውለን ለላላ ሰው በሚለቀቅበት ጊዜ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 32ዐ5 የተደነገገው ውጤት የሚያስከትል መሆኑን በአስተዲደሩ ሙለ ዕውቅናና ፈቃድ ሥራው ለንዐስ ሥራ ተቋራጭ የተሰጠ ሲሆን በፍታብሓር ህግ ቁጥር 32ዐ6 የተደነገገውን ውጤት የሚያስከትል መሆኑ ተደንግጓል። የአስተዲደሩ መስሪያ ቤት ተቋራጩ ሥራውን ሙለ በሙለ ለላላ ሰው እንዱለቅ ለመፍቀድ ወይም ሥራውን በከፉል ለንዐስ ሥራ ተቋራጭ እንዱሰጥ ለመፍቀድ የሚችለው ውለን ለመዋዋል ሥልጣን ባለው ባለሥልጣን በኩል መሆን እንዲለበት በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 32ዐ2 ንዐስ አንቀፅ 2 በግልፅ ተደንግጓል። ከዚህ አንፃር ስናየው አመልካች ከተጠሪ ጋር ውል የተዋዋልኩት የአሰሪው /የምዕራብ አርሲ ዞን ጤና መምሪያ/ ተቆጣጣሪ መሀንዱስ ባለበት ስለሆነ የህንፃ ሥራ ውለን ለተጠሪ ለመልቀቅ የተስማማው በአሰሪው ዕውቅናና ፈቃድ ነው በማለት ያቀረበው ክርክር የህግ ድጋፍና መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ውለ በአመልካችና በተጠሪ መካከል በአግባቡ ተደርጓል ወይስ አልተደረገም የሚለው ጭብጥ ወደፉት የሚታይ ሆኖ በአመልካችና ተጠሪ መካከል ሰኔ 25 ቀን 1999 ዓ.ም. ተደርጓል ተብል የአመልካች መከራከሪያ የሆነው ውል በባህሪው ከአሰሪው ማለትም የአስተዲደር መሥሪያ ቤት ከሆነው የምዕራብ አርሲ ዞን ጤና መምሪያ ፈቃድ ውጭ የተደረገ የህንፃ ሥራን የመልቀቅ ውል / Unnominated Assignment of Contract of work / ነው። ተቋራጩ የአስተዲደር መሥሪያ ቤቱ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 32ዐ2 ንዐስ አንቀፅ 2 በሚደነግገው መሰረት ሣይፈቅድለት የህንፃውን ሥራ ሙለ በሙለ ለላላ ሰው ቢለቅ ውጤቱ ምን ይሆናል የሚለውን ጥያቄ መልስ ማግኘት ያለበት ነው። የሥራ ተቋራጩ ከአሰሪው ፈቃድ ውጭ ሥራውን ሙለ በሙለ ለላላ ሰው ቢለቅ ወይም ለንዐስ ሥራ ተቋራጭ ቢሰጥ፣ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 32ዐ5 እና በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 32ዐ6 የተደነገጉትን ህጋዊ ውጤቶች በተቋራጩና በልላ ሶስተኛ ወገን መካከል የሥራ ውልን ለመልቀቅ ወይም ንዐስ የሥራ ውል ለመዋዋል የተደረገው ውል በአስተዲደሩ መሥሪያ ቤት ላይ ግዳታ የሚያስከትልበት አይደለም። የአስተዲደሩ መስሪያ ቤት መብቱን የሚጠይቀውም ሆነ ግዳታውን የሚወጣው ለሥራ ተቋራጩ ሲሆን የአስተዲደሩ መሥሪያ ቤት ግንኙነት ከሥራ ተቋራጩ ጋር ብቻ የሚወሰን መሆኑን ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 32ዐ5 እና ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 32ዐ6 የተቃርኖ ንባብና ትርጉም ‛ Acontrario reading and Interpretation ‛ ለመገንዘብ ይቻላል።
ከላይ ከተገለፀው በተጨማሪ ተቋራጩ አሰሪ የሆነው የአስተዲደር መሥሪያ ቤት ሣይፈቅድለት ሥራውን ለመልቀቅ ያደረገው ውል ወይም ለንዐስ ተቋራጭ ጋር ያደረገው ንዐስ የሥራ ውል በአስተዲደሩ መሥሪያ ቤት ላይ መከራከሪያና መቃወሚያ ላሆን እንደማይችል በፍታብሓር ህግ ቁጥር 32ዐ4 ንዐስ አንቀፅ 1 በግልፅ ተደንግጓል። በተቃራኒው የሥራ ተቋራጩ የአስተዲደር መሥሪያ ቤቱ ሣይፈቅድለት የሥራ ውለን ለላላ ሰው ለመልቀቅ በመዋዋለ ወይም ንዐስ የስራ ውል መዋዋለ እንደ ጥፊት ተቆጥሮ የአስተዲደር መሥሪያ ቤቱ ውለን ለማፍረስ የሚያስችለው በቂ ምክንያት እንደሆነ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 32ዐ4 ንዐስ አንቀፅ 2 በግልፅ ይደነግጋል።
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስ አሰሪው የምዕራብ አርሲ ዞን ጤና መምሪያ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 32ዐ2 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት ሣይፈቅድ ተጠሪና አመልካች ሰኔ 25 ቀን 1999 ዓ.ም.
አደረጉት የተባለው ውል አመልካች በአሰሪው በምዕራብ አርሲ ዞን ጤና መምሪያ ላይ በቀጥታ መከራከሪያ አድርጎ ሉያነሣው የማይችል መሆኑ ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 32ዐ4 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ ለመገንዘብ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ አሰሪው የምዕራብ አርሲ ዞን ጤና መምሪያ የሥራው ተቋራጭ ከሆነው ከተጠሪ ጋር አድርጎት የነበረውን የህንፃ ሥራ ውል ለማቋረጥ የሚያስችለው በቂ ምክንያትና ጥፊት እንደሆነ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 32ዐ4 ንዐስ አንቀፅ 2 ድንጋጌ ለመረዲት ይቻላል። የአሰሪው ፈቃድና ስምምነት አለመኖር ከላይ ከተገለፀው ሁኔታ አልፍ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ተደርጓል የተባለውን ውል በመካከላቸው አስገዲጅነትና ምንም አይነት ህጋዊ ውጤት የማያስከትል ውል አያደርገውም። ስለሆነም በአመልካችና በተጠሪ መካከል ተደርጓል የተባለውን ውል በመካከላቸው አስገዲጅነትና ምንም አይነት ህጋዊ ውጤት የማያስከትል ውል አያደርገውም። ስለሆነም በአመልካችና በተጠሪ መካከል ሰኔ 25 ቀን 1999 ዓ.ም. ተደርጓል የተባለው ውል ላይ አሰሪው /የምዕራብ አርሲ ዞን ጤና መምሪያ/ ፈቃድና ስምምነቱን አለመስጠቱ ውለ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ምንም አይነት መብትና ግዳታ የማይፈጥር ፈራሽና ውጤት አልባ ያደርገዋል በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የህግ ትርጉምና ውሣኔ ከላይ በዝርዝር ያየናቸውን ድንጋጌዎች ይዘት መንፈስና ዓላማ እና የሚያስከትለትን ህጋዊ ውጤት ያላገዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪ ከአመልካች ጋር የጤና ኬላ ህንፃ ሥራ ውለን ለመልቀቅ የተደረገ ህጋዊ ውል ሰኔ 25 ቀን 1999 ዓ.ም. አላደረግሁም። የእኔ ተወካይ ይህንን ውል የተዋዋለው ከተሰጠው የውክልና ሥልጣን ውጭ ነው በማለት በሥር ፍርድ ቤት የተከራከረ ሲሆን የሥር ፍርድ ቤት ይህንን ምክንያት የአመልካችን ክስ ውድቅ ለማድረግ ጠቅሶታል። ሆኖም ተጠሪ ተወካይ ከውክልና ሥልጣኑ ውጭ ነው የተዋዋለው የሚለውን የህንፃ ሥራ የመልቀቅ ውል ተጠሪ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 21ዐ7 ድንጋጌዎች መሰረት የማፅደቅ ግዳታ አለበት ወይስ የለበትም? የሚለው ጭብጥ የበታች ፍርድ ቤቶች የግራ ቀኙን ክርክር ማስረጃና የግንባታ ሥራን ልዩ ባህሪ መሰረት በማድረግ ጭብጥ መመሥረትና መወሰን ይገባቸው የነበረ መሆኑን ከፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 248 ድንጋጌዎች ለመገንዘብ ይቻላል። የበታች ፍርድ ቤቶች ይህንን መሰረታዊ ጭብጥ ሣይመሰርቱና ውሣኔ ሣይሰጡበት አልፈዋል። ይህንን ጭብጥ በአግባቡ ለመወሰን፣ አመልካች ለተጠሪ በኮሚሽን መልክ ከፍየዋለው የሚለው ብር 5ዐ,ዐዐዐ /ሀምሣ ሺህ ብር/ ተጠሪ ተቀብሎል ወይስ አልተቀበለም? ተጠሪ የግንባታ ሥፍራውን ሙለ በሙለ ለአመልካች አስረክቦ ነበር ወይስ አልነበረም? ለጤና ኬላው ግንባታ የሚያስፈልገውን ሰራተኛ በመቅጠርና ለግንባታው አስፈላጊ የሆነውን ዕቃ በማሟላት ግንባታውን ያከናወነው አመልካች ነው ወይስ አይደለም? አመልካች የሰራው የግንባታ ሥራ አለ ከተባለ ተጠሪ አመልካች የሰራውን ሥራ አሰሪው የምዕራብ አርሲ ዞን ጤና መምሪያ እንዱረከበው በማድረግ ክፍያ እንዱፈፀምለት አሰሪውን ጠይቋል ወይስ አልጠየቀም የሚለት ነጥቦች ፍርድ ቤቱ በተከራካሪ ወገኖች የሚቀርቡ ማስረጃዎችንና እውነቱን ለማውጣት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 145/1/ በማስቀረብ ጭምር በማጣራት ውሣኔ ላሰጥባቸው የሚገቡ ነጥቦች ናቸው። በያዝነው ጉዲይ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለመወሰን አስፈላጊ የሆኑትን ከላይ የተገለፀውን ጭብጥ ሣይመሰርትና ፍሬ ጉዲዩን ሣያጣራ
No topics extracted.