No summary available.
የሰ/መ/ቁ/55229 ጥር 09 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ መሐዲ ዐመር ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የአርሲ ቅርንጫፍ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ ለሰበር የቀረበውን ጉዲይ በተመለከተ በመጀመሪያ ያየው የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ከሣሽ የነበሩት የአሁኗ አመልካች የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዕዲውን ሳይከፍል ከቀረ የገበሬ ማህበር ተረክቦ ለእኔ ያስተላለፈልኝ ማሽን ጉድለት የላለበት መሆን ሲገባው ከጉድለቱ ጋር ስላስተላለፈልኝ ተከሣሹ ባንክ ከእኛ የወሰደውን ብር 40,000 /አርባ ሺህ ብር/ መመለስ ይገባዋል በሚል ባቀረቡት ክስና ክርክር መሰረት ተከሣሹ ገንዘቡን ለከሣሽ መመለስ ይገባዋል በማለት የወሰነ ሲሆን በባንኩ /በአሁኑ ተጠሪ/ የይግባኝ አቤቱታ መነሻ ጉዲዩ ቀርቦለት የተመለከተው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ደግሞ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ መርምሮ ባንኩ የክስ መቃወሚያ አድርጏ ያቀረበውን የይርጋ ክርክር የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሳያየው አልፍ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ መክፈል አለበት ብል የወሰነው ያለአግባብ ነው። ከተነሣው የይርጋ ክርክር አንፃር ሲታይ ክሱ በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 1845 መሰረት በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ሽሮታል።
የአሁኗ አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኙን ሉያቀርቡ የቻለ ቢሆንም ጠቅላይ ፍ/ቤትም ጉዲዩን መርምሮ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ይግባኙን ሰርዞታል።
የሰበር አቤቱታው በዚህ ምክንያት የቀረበ ነው።
አመልካች ክሱ በ10 ዓመት ይርጋ ይታገዲል በሚል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው የሚለባቸውን ምክንያቶች ሚያዚያ 18 ቀን 2002 ዓ.ም. በተጻፈ ማመልከቻ ገልፀው አቅርበዋል።
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ ይታይ በመባለ ማመልከቻው ለተጠሪው ተልኮ ቀርቦ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጓል።
በተጠሪው በኩል በጽሐፍ በቀረበው መልስ ላይ አመልካችም የመልስ መልስ ሰጥተውበት ተከራክረዋል።
ይህ ችልትም ጉዲዩን መርምሯል።
የአሁኑ አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ላይ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪ በይግባኙ ያላነሳውን የይርጋ ክርክር እራሱ በማንሳት ውሣኔ ሰጥቷል በሚል የገለፁትን በተመለከተ ከዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጀምሮ የይርጋው ክርክር መቅረቡን ውሣኔው ስለሚያስረዲ ተቀባይነት የለውም።
በአሁኑ ተጠሪ በኩል የይርጋ ክርክር መቅረቡ ስለተረጋገጠ የአሁኗ አመልካች በተጠሪው ላይ ያቀረቡት ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል የተባለው በአግባቡ መሆን አለመሆኑ ሲመረመር፡የአሁኗ አመልካች ተጠሪው ለእኔና ለባለቤቴ መጭመቂያ ማሽን አስተላለፈልን የሚለት ነሐሴ 14 ቀን 1985 ዓ.ም. በተደረገ ውል ሲሆን ተጠሪው ከላላ ገበሬ ማህበር በዕዲ ምክንያት የተረከበውን ማሽን ስለዋጋው አከፊፈል በውለ ላይ በማመቻቸት ከፍለን የራሳችን በማድረግ እንድናስቀረው አስተላለፈልን በማለት የሚገልጹት ሽያጭ እንጅ ላላ ትርጉም የሚሰጠው አይደለም።
አመልካች በውል ተላልፍልኛል የሚለትን ማሽን እንደተረከቡ በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2291 መሰረት በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዱመረመር በማድረግ ጉድለት ያለበት ሆኖ ከተገኘ በዚሁ ሕግ ቁጥር 2292 መሰረት ለተጠሪው ማስታወቅ ነበረባቸው። ካስታወቁ በኋላም በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2298/1/ ላይ በተገፀው መሰረት ክስ ማቅረብ ይችለ የነበረው ካስታወቁበት ቀን አንስቶ እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ክስ ካላቀረቡ ዕቃው ጉድለት ያለበት ነው ብለው የመክሰስ መብታቸውን ያጣለ። አመልካች በማሽኑ ላይ ጉድለት ስለመኖሩ በሕጉ መሰረት በአጭር ጊዜ ለተጠሪው አስታውቀው በተወሰነው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ክስ ማቅረብ ቀርቶ የፈፀሙት አንድም ነገር ሣይኖር ከአሥራ ሁለት ዓመት ቆይታ በኋላ ተጠሪው ያስረከበን ማሽን ጉድለት ስላለበት የከፈልነውን ብር 40,000 /አርባ ሺህ ብር/ ይመልስልን የሚል ክስ አቅርበዋል። አሥር ዓመት ወደሚለው የይርጋ ክርክር መሄድ ሳያስፈልግ አመልካች ማሽኑን እንደተረከቡ በአጭር ጊዜ እንዱመረመር አድርገው ጉድለት ያለው ስለመሆኑ ለተጠሪው በማሳወቅ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ማሽኑ ጉድለት ያለበት ነው የሚለውን ክስ ያላቀረቡ ስለሆነ የመክሰስ መብታቸውን አጥተዋል።
የይርጋው ጊዜ ተቋርጦ ቆይቷል በሚል ያነሱትን ክርክር በሚመለከት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ጉዲዩን በይግባኝ በሚያይበት ጊዜ እንዱህ ዓይነት ክርክር ያላቀረቡ ሲሆን የይርጋው ጊዜ ተቋርጦ ቆይቷል የሚለውን ክርክር ያነሱት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ባቀረቡት ይግባኝ ላይ ነው።
No topics extracted.
ጠቅላይ ፍ/ቤቱም በሥር ፍ/ቤት ያልቀረበ አዱስ ክርክር በመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 329 መሰረት ላታይ የሚችል አይደለም ብል ሳይቀበለው ቀርቷል። ፍ/ቤቱ በዚህ ረገድ ፈጽሟል የሚባለው የሕግ ስህተት የለም።
በአጠቃላይ በዚህ ጉዲይ የአሁኗ አመልካች ተጠሪው አስተላልፍልን የነበረው ማሽን ጉድለት ስላለበት የከፈልነውን ገንዘብ ብር 40,000 ይመልስልን በሚል ያቀረቡት ክስ በይርጋ የታገደ ነው በሚል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አልተገኘም።
ው ሣ ኔ
የሰበር አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።