No summary available.
ጥር 23 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ሂጦስ የገበሬዎች የህ/ሥ/ማህበር - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- የመሥራቅ ደቄትና ፊብሪካ - ‛ መዝገቡ የተቀጠረው ለጉዲዩ አወሳሰን እንዱረዲ ይቅረብ የተባለው የሥር የመጀመሪያ ደረጃ መዝገብ ቁጥር 6059 አለመቅረቡን አስመልክቶ ተገቢውን ትዕዛዝ ለመስጠት በሚል ነበር፤ ይሁን እንጂ ይኸው መዝገብ ዘግይቶም ቢሆን የቀረበ ስለሆነ ጉዲዩን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበው ግራ ቀኙ እንደአደረጉት የስንዳ ሽያጭ ውል ሳይፈፀም የቀረው በየትኛው ተዋዋይ ወገን ጉድለት ነው የሚለውን ነጥብ በውለ ከተመለከተው የሻጭና የገዥ መብትና ግዳታ፣ ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች እና ግራ ቀኙ ስለጉዲዩ ካቀረቡት ክርክርና ማስረጃ አንፃር ለይቶ ከሚያስከትለው ውጤት ጋር ተገቢውን ዲኝነት ለመስጠት ሲባል ነው።
ለዚህ የሰበር ጉዲይ መነሻ የሆነው የአሁን አመልካች የሂጦስ ገበሬዎች የህ/ሥ/ማህበር ያቀረበው ክስ ሲሆን፤ ይዘቱም ታህሳስ 26 ቀን 1997 ዓ.ም በተደረገ የስንዳ ግዥና ሽያጭ ውል መሰረት በየጊዜው ለማስረከብ ከገባነው 4000(አራት ሺህ) ኩንታል ስንዳ ውስጥ እስከ ጥር 27 ቀን 1997 ዓ.ም ድረስ በድምሩ 1020(አንድ ሺህ ሃያ) ኩንታል አስረክበናል። ለዚሁ ለተረከበው ገዥ ዋጋውን አልከፈለም።
እኛም የማስረከቡን ተግባር በማቆም ክፍያ እንዱፈፅም ብንጠይቀው እንደጥያቄው ባለመፈፀሙ ርክክቡ ዘገየ። የስንዳም ዋጋ በነዲጅ ዋጋ ጭማሪ የተነሣ ጨመረ። ይህንም የስንዳ ዋጋ ጭማሪ እራሱ በሰጠን ማስታወቂያ ጭምር አረጋግጧል። ስለሆነም በእራሱ የክፍያ ግዳታ ባለመፈፀም ተግባር ውለ ቀሪ ሆኖ ላስረከብነው የስንዳ ዋጋ ብር 168,300(አንድ መቶ ስድሳ ስምንት ሺህ ሦስት መቶ ብር) ከእነ ወለደ ጋር ይክፈል የሚል ነው። የአሁን ተጠሪ በተከሳሽነት የሰጠው መልስ የክፍያ ጥያቄ አቅርቦ አልተከለከለም። ውለ ከተደረገበት ስንዳውን እስከሚያስረክብበት ድረስ የነዲጅ ዋጋ ጭማሪ አልተደረገም ለማስረከብ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት አልቻልኩም በማለት የገለፃቸው ምክንያቶች በህጉ መሰረት እንደአቅም በላይ የሆኑ ምክንያቶች አይቆጠሩም። ስለሆነም ስንዳውን ለማቅረብ እንቢተኛ ሆኖ ያስረከበውን ስንዳ ዋጋ ክፍያ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት መልሷል።
እንደገናም የተከሳሽ ከሳሽ ሆኖ ተከሳሽ እንደውለ ለማስረከብ በገባው ግዳታ መሰረት ባለማስረከቡ ባልተረከብነው 2980 ኩንታል ልክ የስንዳ ዋጋ በዚያው ጭማሪ የብር 447,000(አራት መቶ አርባ ሰባት ሺህ ብር) በልዩነት ጉዲዩ ደርሶብናል። ስለሆነም ቀሪውን 2980 ኩንታል ያስረክበን፤ ወይም ይህንኑ የዋጋ ልዩነት በጉዲት ኪሣራ ይክፈለን የሚል አቤቱታ አቅርቧል።
የአሁን አመልካች ለዚሁ የተከሳሽ ከሳሽ አቤቱታ የሰጠው መልስ ፍሬ ቃል ለማስረከብ የገባሁት ስንዳ እኔ የማመርተውን ሳይሆን ከማህበሩ አባላት ወይም ከአርሶ አደሩ በግዥ የሚገኘውን ነው። ለተረከበው የስንዳ ዋጋ ባለመክፈለ ምክንያት የስንዳ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት የቀሪውን የማስረከብ ተግባር እንዱያቆም ተገዶል። በውለ አንቀጽ 13 አንደኛው ወገን የገባውን ግዳታ ሳይፈፅም ቢቀር ወይም ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥም ውለን ማፍረስ ይቻላል። ለተረከበው 1020 ኩንታል ስንዳ በወቅቱ ክፍያ ለመፈፀም ባለመቻለ ጊዜው ተራዘመ ጊዜው ሲራዘም የስንዳ ዋጋና የነዲጅ ዋጋ በመጨመሩ ለዚሁ ጭማሪ ምክንያት የሆነው እራሱ የተከሳሽ ከሳሽ ነው። ስለሆነም ለውለ መፍረስ ምክንያት የሆነው እራሱ በመሆኑ በተከሳሽ ከሳሽነት ያቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም። የጠየቀውም የጉዲት ኪሣራ መጠን በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በማለት ተከራክሯል።
ክርክሩ የቀረበለት ፍ/ቤትም ጉዲዩን ተመልክቶ የአሁን ተጠሪ የተረከበውን 1020(አንድ ሺህ ሃያ) ኩንታል ስንዳ ዋጋ ክፍያ ያልፈፀመ መሆኑን ስላመነ ዋጋውን ብር 168,300.00(አንድ መቶ ስድሳ ስምንት ሺህ ሦስት መቶ ብር) ከጥር 20 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር ለከሳሽ ይክፈል፤
በልላ በኩል የአሁን አመልካች ቀሪውን ስንዳ ላለማስረከብ በምክንያትነት የጠቀሰው የስንዳና የነዲጅ ዋጋ ጭማሪ ናቸው በሚል ስለመሆኑ እራሱ ለተከሳሽ በ10/6/97 ዓ.ም የፃፈው ደብዲቤ አስረጂ በመሆኑ ምክንያት ከክፍያ መዘግየት ጋር የሚያያዝ አይደለም፤ በተጨማሪም የክፍያ መዘግየት ለውል ማፍረስ ምክንያት የሚሆነው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1788 እንደተመለከተው የክፍያው መዘግየት የውለን መሰረታዊ ስምምነት የነካ ሲሆን ነው። በውላቸው አንቀጽ 8 ላይም የክፍያ መዘግየት የውለን መሰረታዊ ስምምነት የሚነካ መሆኑ አልተመለከተም። ስለሆነም የክፍያ መዘግየት ውለን ያፈርሳል የሚለውን ክርክር ፍ/ቤቱ አልተቀበለውም፤ በውለ መሰረት ቀሪውን 2980(ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ) ኩንታል ስንዳ ያስረክብ፤ ወይም ደግሞ በአሁን ጊዜ ለአንድ ኩንታል ብር 150.00(አንድ መቶ ሃምሣ ብር) ስለመጨመሩ በቀረበው መረጃ መሰረት ለ2980 ኩንታል ብር 447,000.00(አራት መቶ አርባ ሰባት ሺህ ብር) ተከሳሽ ለከሳሽ ይክፈል በማለት ወስኗል።
No topics extracted.
በዚህ ወሳኔ ቅር በመሰኘት የአሁን አመልካች ያቀረበው የይግባኝ ክርክር በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ተቀባይነት ባለማግኘቱ ለዚህ የሰበር መዝገብ መነሻ የሆነውን የሰበር አቤቱታ አቅርቧል።
ሁለቱም ወገኖች በዚህ በሰበር ሰሚ ችልት ደረጃ ያቀረቡት ክርክር ይዘት ከላይ ባጭር ባጭሩ በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡትን ለመግለፅ ከተጠቀሰው በይዘቱ የተለየ አይደለም።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርመረናል።
እንደመረመርነውም የአሁን አመልካች በከሳሽ ለውለ መፍረስ ምክንያት የሆነው ገዥ መሆኑ ታውቆ ውለ ይፍረስ ላስረከቡት ስንዳ ዋጋ ይክፈለኝ በሚል እና የአሁን ተጠሪም በተከሳሽ ከሳሽነት እንደ ውለ ቀሪውን ስንዳ ያስረክበኝ፤ የማያስረክብ ከሆነ በሻጭ ጉድለት ምክንያት የስንዳ ዋጋ በመጨመሩ የተነሳ የታየውን የዋጋ ጉድለት በጉዲት ኪሣራ ይክፈለኝ በሚል ይከራከሩ እንጂ ሁለቱንም ወገኖች የሚያከራክራቸውን ነጥብ ለይቶ ለጉዲዩ ውሳኔ ለመስጠት አከራካሪው ነጥብ አንድ ነው። ይኸውም እንደ ውለ ሉፈፀም ያልቻለው በየትኛው ተዋዋይ ወገን ጉድለት የተነሣ ነው የሚለው ነው። ከዚህም ጭብጥ በመነሳት በታመነው እና የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር መሰረት በማድረግ ከውላቸው አንቀጾች እና አግባብነት ካለው ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ እንደተመለከትነው ፡የአሁን ተጠሪ በሁለት ተከታታይ ጊዜ ለተረከበው 1020(አንድ ሺህ ሃያ ኩንታል) ስንዳ ዋጋ ያለመክፈለን የካደው ጉዲይ አይደለም ስላልጠየቀኝ እንጂ ጠይቆ ክፍያ አልተከለከለም የሚል ክርከር ያቅርብ እንጂ በውለ እንደተመለከተው በየጊዜው ለሚረከበው ስንዳ ዋጋውን የመክፈል ግዳታ የተጣለበት ከመሆኑ በቀር የመክፈል ግዳታው በክፍያ ጥያቄ ላይ የተመሰረተ አይደለም።
በመሆኑም ሻጭ በየጊዜው የተባለውን የስንዳ መጠን የማስረከብ ግዳታ ያለበትን ያህል ተጠሪም በገዥነት በየጊዜው ለሚረከበው የስንዳ መጠን ዋጋውን የመክፈል ተነፃፃሪ ግዳታ አለበት። ይህም የሻጭና የገዥ እንደቅደም ተከተለ በየጊዜው የተሸጠውን ነገር የማስረከብና ዋጋውን የመክፈል ግዳታቸው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በውላቸው ላይ ተመልክቷል። በመሆኑም ይህ በየጊዜው ለሚረከበው ስንዳ ዋጋ የመክፈል ግዳታ መዘግየቱ ካላከራከረ የገዥ ብቸኛ ግዳታ በሽያጭ ለተረከበው ስንዳ ዋጋ መክፈል እንደመሆኑ መጠን ይህ የክፍያ መዘግየት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1784 በተደነገገውም ቢሆን የውለን መሰረታዊ ስምምነት የነካ ነው ከሚባል በቀር የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን ትርጉም የሚከተል አይደለም። እንደውለ አነጋገር ክፍያ የመፈፀም ግዳታ በየጊዜው በሚደረገው ርክክብ መሰረት እንጂ ገዥ ክፍያ ሳይፈፀም በውል ማብቂያ ጊዜ አጠቃል የመክፈል መብት ያለው ይመስል ከፉል ክፍያ የውለን መሰረታዊ ስምምነት ሉነካ አይችልም ወደ ሚለው መደምደሚያ የሚያደርስ አይደለም። በተለይም ሻጭ የሚሸጠውን ስንዳ ከማህበሩ አባል ከላልች አርሶአደረሮች በመሰብሰብ በሽያጭ የሚያስተላለፍ መሆኑን ገልፆ ሲከራከር ለዚህ ማስተባበያ ክርክር ተጠሪ አለማቅረቡ በየጊዜው ለሚደረገው ርክክብ በወቅቱ ክፍያ የማግኘት መብትና ክፍያ የመፈፀም ግዳታ የውለ መሰረታዊ የስምምነት ክፍል መሆኑን አመላካች ነው።
በውላቸው አንቀጽ 8 ላይ ገዥው በየጊዜው ለሚረከበው ስንዳ ዋጋውን የመክፈል ግዳታ ያለበት በመሆኑና አንደኛው ወገን የገባውን ግዳታ ሳይፈፅም በቀረ ጊዜ ለውል ማፍረሻ ምክንያት እንደሆነ በውለ አንቀጽ 13 ላይ የተመለከተ በመሆኑ የገዥ ግዳታ አለመፈፀም ምን ውጤት እንደሚያስከትል በውላቸው ላይ የተቀመጠ ሲሆን፤ ይህ ስለመሆኑ በውላቸው በግልፅ አልሰፈረም እንኳ ቢባል በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2278 እንደተመለከተው የተሸጠን ነገር የተረከበ ገዥ የሽያጩን ዋጋ ወዱያውኑ የመክፈል ግዳታ ያለበት በመሆኑና የሽያጩ ዋጋ ያልተከፈለው ሻጭ የተሸጠውን ነገር ሳያስረክብ በእጁ የማቆየት መብት የሚሰጠው ለመሆኑ የዚሁ ድንጋጌ ግልባጭ ንባብ ስለሚያስረዲ በተለይም ግራ ቀኙ ከያዙት ውል አንፃር ለጉዲዩ ቀጥተኛ አግባብነት ባለው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2351(1) እንደተመለከተው ሻጭ በተከታታይ ለሁለት ጊዜ የተሸጠውን ስንዳ ሲያስረክብ በተጓዲኝ ገዥ የክፍያ ዋጋውን አለመክፈለን እንዲረጋገጠ፤ በተከታይ ለሚያስረክባቸውም ነገሮች ስለመከፈለ ተገቢውን ስጋት የሚያሳድርና በዚህም የተነሣ ውለን የማፍረስ መብት የሚሰጠው እንጂ ተጠሪ እንደሚለው ተገድ ቀሪውን ስንዳ እንዱያስረክብ ወይም ደግሞ ይህንኑ የማስረከብ ግዳታ የማይዋጣ ከሆነ የዋጋ ልዩነትን የመክፈል ግዳታ የሚጥልበት አይደለም።
በዚህ ሁለ ምክንያት ግራ ቀኙ እንደገቡት የሽያጭ እና ግዥ ውል እንዲይፈፀም ምክንያት የሆነውን የግዳታ መጓደል የፈፀመው ገዥ እንጂ ሻጭ ያለመሆኑ ግራ ቀኙ ባቀረቡት ክርክር ማስረጃ ማረጋገጡን የሥር ፍ/ቤት ተቀብል ሆኖም ይህ የክፍያ ግዳታ አለመሟላት ዋናውን የስምምነት አካል የነካ አይደለም በሚል መነሻ ለውለ መፍረስ ሻጭን ኃላፉ በማድረግ የሰጠው ትርጉም ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን ከላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች አፈፃፀም በአግባቡ ያላገናዘበ በመሆኑ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ዲኝነት መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እና ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍ/ቤት እንደቅደም ተከተለ በኮ/መ/ቁ 6059 በ8/8/2000 እና በኮ/መ/ ሐምል 09 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ እና ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሻሽል ተወስኗል።
የግራ ቀኙ የሽያጭ ውል በገዥ በኩል የሚጠበቀውን የክፍያ ግዳታ ባለመፈፀም ምክንያት መፍረሱ ስለተረጋገጠ ሻጭ የአሁን አመልካች በሽያጭ ላስረከበው 1020(አንድ ሺህ ሃያ) ኩንታል ስንዳ ዋጋ ብር 168,300.00(አንድ መቶ ስድሳ ስምንት ሺህ ሦስት መቶ ብር) ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር ገዥ /የአሁን ተጠሪ/ ይክፈል ብለናል።
ለስንዳው ሽያጭ እና ግዥ ውል መፍረስ ምክንያት ሆኖ የተገኘው ገዥ ለተረከበው 1020 ኩንታል ዋጋ ክፍያ በጊዜው ባለመክፈለ የተነሣ በመሆኑ እንጂ በሻጭ በኩል በታየ የግዳታ አለመፈፀም ምክንያት ባለመሆኑ ሻጭ የአሁን አመልካች ለገዥው ለአሁን ተጠሪ ቀሪ ስንዳውን የማስረከብም ሆነ ቢያስረክብ ታዩ የተባለውን የዋጋ ልዩነት በጉዲት ኪሣራ መልክ የመክፈል ግዳታ የለበትም ብለናል።
በዚህ ሰበር ደረጃ ግራ ቀኙ ያደረጉት ክርክር ላስከተለው ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
የሥር ፍ/ቤቶች መዝገቦች በመጡበት ሁኔታ ይመለሱ።