No summary available.
ታህሳስ 12 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የአዱስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ነ/ፈጅ ፈያራ ገለታ ቀረቡ ተጠሪ፡- የአዱስ አበባ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበላ 16/17 አስተዲደር ጽ/ቤት የቀረበ የለም፡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የውሃ አገልግልት ሂሳብ ክፍያን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በቀበላ ማህበራዊ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የአመልካች ክስ ይዘትም ባጭሩ፡- ተጠሪ በቀድሞ ወረዲ 07/ቀበላ 27 አስተዲደር በቤት ቁጥር 436 ነዋሪና ባለቤት የነበሩት አቶ ግርማ ወ/ሚካኤል በ15/07/1950 በውል ከአመልካች መስሪያ ቤት ጋር ባደረጉት የውል ስምምነት አገልግልት እያገኙና የውሃ ሂሳብ ሲከፍለ የቆዩ መሆኑን የተጠቀሰውን ቤት ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት ወርሶ በቀድሞው ባለሃብት እግር በመተካት የውሃ አቅርቦት አገልግልት ሲጠቀም የቆየ ቢሆንም የህዲር ታህሳስና ከሐምል 1992 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 1993 ዓ.ም ድረስ የተጠቀመበትን የውሃ ፍጆታ ክፍያ አለመክፈለን ገልጾ ብር 556.79 (አምስት መቶ ሃምሳ ስድስት ብር ከሰባ ዘጠኝ ሳንቲም) እንዱከፍል ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃሚያና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርቧል። በመልሱም አመልካች ክስ ለመመስረት የሚያስችለው የውል ወይም የሕግ ግንኙነት የላለው መሆኑን ክሱም በይርጋ የሚታገድ መሆኑንና ሂሳቡ ካልተከፈለ ደንበኝነቱን ሳያቋርጥ ቆይቶ ክስ መመስረቱ አግባብ አለመሆኑን ጠቅሶ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የቀበላ ማህበራዊ ፍርድ ቤትም የተጠሪን የክርክር ነጥቦች ሙለ በሙለ ውድቅ በማድረግ ተጠሪን ለክሱ ኃላፉ አድርጏ ለክሱ መሰረት የሆነውን ገንዘብ (ብር 556.79) እንዱከፍል በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኙን ለአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የውሃ ፍጆታ ክፍያ ጥያቄ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) መሰረት ተቀባይነት የለውም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሽሮታል። ጉዲዩ በሰበር አቤቱታ የቀረበለት የአዱስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችልትም በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት የአመልካችን አቤቱታ ሳይቀበለው ቀርቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ጳጉሜ 05 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈት ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024 ድንጋጌና የደንብ ቁጥር 31/1994 ለጉዲዩ አግባብነት የላላቸው መሆኑን በመዘርዘር ውሳኔው እንዱሻር እና ተጠሪ የውሃ ፍጆታ ሂሳቡን እንዱከፍል ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚየሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው ነው ተብል በመታዘዙ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጏለት ቀረቦ በነገረ ፈጁ አማካኝነት የፁሐፍ መልሱን ሰጥቷል። የአመልካች ነገረ ፈጅም የመልስ መልሱን አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ዋናው የህግ ትርጉም የሚያስፈልገው ጉዲይ፡- የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ድንጋጌ ለውሃ ፍጆታ ሂሳቡ(ገንዘብ) አግባብነት አለው? ወይስ የለውም? የሚለው ነው። ለዚህ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይቻል ዘንድ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ድንጋጌን በሚገባ መረዲት ያስፈልጋል።
የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024 በጠቅላላው ሲታይ በሕግ የሕሉና ግምት የሚሸፈን የፍሬ ነገር ነጥብ (Legal Presumptions) የሚመለከት ሲሆን ዓይነቱም ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2025 እና 2026 ድንጋጌዎች ጋር ተዛምድ ሲታይ ውስን የሆነ የማስተባበያ ማስረጃ የሚቀርብበት (not freely rebuttable or rebuttable but in a limited way) የሕግ የህሉና ግምት ነው። የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024 የተለያዩ የክፍያ አይነቶችን የሚዘረዝር ሆኖ በጠቅላላው ሲታይ ግን በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሉከፈለ የሚገቡ ክፍያዎች (እዲዎች) በዚሁ የሁለት አመት ጊዜ ውሰጥ ሳይጠየቁ የቀሩ እንደሆኑ ክፍያውን (እዲውን) የመክፈል ኃላፉነት ያለበት ወገን የተባለውን ክፍያ (እዲ) እንደከፈለ የሕግ ግምት እንደሚወሰድበት ያስገነዝባል። ድንጋጌው የውሃ ፍጆታ ሂሳቡን ለይቶ አላስቀመጠም።
ለተያዘው ጉዲይ ቀጥተኛ አግባብነትና ተፈጻሚነት ያለው ድንጋጌ ተብል በተጠሪ የሚጠቀሰውን በስር የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ሆነ ሰበር ሰሚ ችልት ተቀባይነት ያገኘው በፍ/ሕ/ቁጥር 2024 ድንጋጌ በፉደል (ረ) ስር የተመለከተው የክፍያ ግምት ሲሆን ሙለ ይዘቱም በሚከተለው መልኩ የተቀመጠ ነው።
ቁ. 2024 በሁለት አመት የተወሰነ ጊዜ እዲው እንዱከፈል መጠየቅ ከሚገባበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ሳይከፈል የቀረ ገንዘብ እንደተከፈለ የሚቆጠረው፡- (ረ) በብድር ለተሰጠ፣ የገንዘብ ወለድና በጠቅላላውም የዓመት ጊዜ ተወስኖለት በየዓመቱ ወይም ከዚህ ባነሰ የጊዜ ውሳኔ ውስጥ ሉከፈል የሚገባው ዕዲ የሆነ እንደሆነ ነው። የዚሁ ድንጋጌ የእንግሉዝኛ ቅጂም፡- Art. 2024 presumption of payment after two years The following debts shall be deemed to have been paid where two years have elapsed since they fell due: (f) interest on loans and generally any sum payable annually or at shorter periodical intervals. በሚል ተቀምጧል።
ከላይ ከተጠቀሰው ድንጋጌ ይዘት እና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው የድንጋጌው መጀመሪያ ፕራግራፍ የመክፈያ ጊዜያቸው ከደረሰ ጊዜ አንስቶ ሁለት አመት ያለፊቸው እዲዎች (ክፍያዎች) እንደተከፈለ ይቆጠራለ የሚል ሲሆን በተከታይ የተዘረዘሩት ንዐስ ድንጋጌዎች ደግሞ የሚወሰንባቸውን የክፍያ (እዲ) ዓይነቶችን የሚዘረዝር ነው። በድንጌጋው ፉደል (ረ) ስር የተመለከተው ሲታይ በብድር የተሰጠ ወይም ለማናቸውም የአከፊፈል ሁኔታ በየአመቱ ወይም ከአመት ባነሰ ጊዜ እየተከፈለ እንዱያልቅ ጊዜ ተቆርጦለት የተሰጠ ገንዘብ ላይ የሚታሰብ ወለድ እዲው ከበሰለበት ወይም በየተወሰነ ጊዜ የሚከፈል ገንዘብ ከሆነ ደግሞ ገንዘቡ ተከፍል ማለቅ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ሁለት ዓመት ያለፈ እንደሆነ በእነዚህ ክፍያዎች (እዲዎች) ላይ ሉጠየቅ የሚችለው የወለድ ክፍያ እንደተከፈለ የሕግ ግምት የሚወሰድ መሆኑን ያሳያል። በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ስር የተመለከተው ድንጋጌ ተፈጻሚነት የሚኖረው በብድር ለተሰጠ የገንዘብ ወለድ ላይ ሲሆን ዋናው የብድር ገንዘብን የማይጨምር መሆኑን የድንጋጌው ይዘትና አቀራረጽ ያስገነዝባል።
ምክንያቱም ድንጋጌው ዋናውን የብድር ገንዘብ የሚጨምር ቢሆን ኖሮ የብድር ገንዘብና ወለድ በማለት ያስቀምጠው ነበር እንጂ ለብቻው ነጥል የብድር ገንዘብ ወለድን በማለት አይጽፈውም ነበር። ይህ ስለመሆኑም ይህ ችልት በሰመ/ እና የሰ/መ/ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2(1) መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል። በመሆኑም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ድንጋጌ አግባባነት የሚኖረው ለብድር ገንዘብ ወለድ እንጂ ለዋናው የብድር ገንዘብ አይደለም፣ የውሃ ፍጆታ ሂሳብም ብድር ባለመሆኑ ከመነሻውም ድንጋጌው አግባባነት ሉኖረው አይችልም።
ላላው ስለክፍያ ግምት የሚያወሳው ድንጋጌ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2023 ሲሆን ይህ ድንጋጌ የስድስት ወር ጊዜ ማለፈ ክፍያው እንደተፈጸመ ያስቆጥራል በሚል የተቀመጠ ነው። ይህ ድንጋጌ የስድስት ወር ማለፍ ገንዘቡ እንደተከፈለ የሚያስቆጥርባቸው ሁኔታዎችን ለይቶ አስቀምጧል።
በዚህ ድንጋጌ ስር የወርሃዊ የውሃ ፍጆታ ሂሳብ አልተመለከተም። በመሆኑም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2023 ድንጋጌ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው ሁኖ አግኝተናል። እንዱሁም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2022 ድንጋጌ ሲታይም የተከፈለው እዲ ወለድችን ወይም በተወሰነው ጊዜ የሚከፈለትን ላልች የክፍያ ድርሻዎችን የሚመለከት እንደሆነ የተከፊዩን አይነት ለይቶ ሳይገልጽ ለአንደ የክፍያ ደረሰኝ የሰጠ ባለገንዘብ ያለፈውንም ድርሻ እንደተቀበለ ይቆጠራል በማለት በንዐስ ቁጥር አንድ ድንጋጌ ያስቀመጠ ሲሆን ተጠሪ በዚህ ረገድ ያቀረበው ክርክርም ሆነ ማስረጃ የለም። በመሆኑም ጉዲዩ በዚህ ድንጋጌ መሰረትም ላታይ የሚገባው ሁኖ አልተገኘም።
ላላው ተጠሪ ለክርክሩ መሰረት ያደረገው የደንብ ቁጥር 31/1994 አንቀጽ 19(1) ድንጋጌን ነው። በዚህ ድንጋጌ መሰረት በክፍያ ምክንያት የውሃ አቅርቦት ከተቋረጠበት ቀን ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ደንበኛው የአገልግልት ክፍያ ካልፈጸመ የደንበኝነት ውለ ተሰርዞ ደንበኛው ለዋስትና ያስያዘው ተቀማጭ ገንዘብ ለአመልካች መስሪያ ቤት ገቢ የሚደረግበትን አግባብ ተመልክቷል።
ድንጋጌው በአመልካችና በደንበኛው መካከል ስለሚኖረው የወደፉት ግንኙነትና አመልካች ሉወስደው ስለሚችለው እርምጃ ከሚያሳይ በስተቀር ደንበኛው ለተጠቀመበት የውሃ አገልግልት ያልተከፈለ ሂሳብ ካለ አመልካችን ለመጠየቅ አይችልም የሚል መንፈስ የለውም። በመሆኑም ለዚህ ጉዲይ አግባብነት የላለው ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም የውሃ ፍጆታ ሂሳብ ከመሰረቱ ብድር አይደለም፣ የብድር ባህሪም የለውም። የውሃ ፍጆታ ሂሳብ አመልካች ለህብረተሰቡ በሚያቀርበው አገልግልት መሰረት የሚከፈል ሲሆን መሰረቱም ውል ነው። አመልካች ክስ ያቀረበው በክሱ ላይ በተመለከተው ቤት ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት እያስተዲደረው በመሆኑ በቤቱ ለተጠቀመበት ውሃ ተጠሪ ክፍያ እንዱፈጽም ነው። ተጠሪ ቤቱን በተጠቀሰው ሕግ ተረክቤ አላስተዲድርም የሚል ክርክር የላለው ሲሆን በቀድሞው ባለቤት ስም የገባው የውሃ ቆጣሪ ሲነሳም ችግሩ እንደደረሰበት ገልጾ ቆጣሪው እንዱመለስለት ጠይቆ ቆጣሪው የተመለሰለት መሆኑ በስር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል።
የተጠሪ ክርክር ከአመልካች ጋር የውሃ አቅርቦት ውል አልፈፀምኩም የሚል ሲሆን ከላይ እንደተመለከተው በስር ፍርድ ቤት ቤቱን በሕግ ተረክቦ የሚያስተዲድረው መሆኑ ካለመካደም በተጨማሪ የውሃ ቆጣሪውን አመልካችን ጠይቆ መውሰደ የተረጋገጠ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ ቁጥር 235 መሰረት ጉዲዩ እንደታመነ የሚቆጠር ነው። በመሆኑም የውሃ አቅረቦቱ ተጠሪ ቤቱን በሕግ አግባብ ተረክቦ የሚያስተዲድረው እስከሆነ ድረስ መብትና ግዳታው በሕግም ሆነ በውል ለተጠሪ መተላለፈ የተረጋገጠ በመሆኑ ተጠሪ ለውሃው ፍጆታ የማይጠየቅበት አግባብ የለም።
ክፍያውን ስለመክፈለ ደግሞ ተጠሪ ገልፆ የተከራከረው ነገር የለም። እንዱህ በሆነ ጊዜ ደግሞ ተጠሪ የክፍያ ግምት ተጠቃሚ የሚሆንበት ምክንያት የለም። በአጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች ለውሃ ፍጆታ አገልግልት ሂሳብ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) እና የደንብ ቁጥር 31/1994 ድንጋጌዎችን መሰረት ማድረጋቸው ያላግባባ በመሆኑ እና ተጠሪም በሕጉ አግባባ ለሚያስተዲድረው ቤት የውሃ ፍጆታ ክፍያውን ለመክፈል ከሕግና ከውል የመነጨ ግዳታ ያለበት በመሆኑ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሚያዝያ 05 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በከተማው ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ሐምል 17 ቀን 2001 ዓ.ም በትእዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 08/09 ቀበላ ማህበራዊ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 2602 ጥቅምት 18 ቀን 2001 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
የውሃ ፍጆታ ሂሳብ ይከፈለን ጥያቄ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2022 መሰረት የክፍያ ደረሰኝ ያልቀረበበት ከሆነ በይርጋ ደንብ የሚገዛ እንጂ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ስር በተመለከተው የሕሉና ግምት የሚሸፈን አይደለም ብለናል።
ተጠሪ ብር 556.79 (አምስት መቶ ሃምሳ ስድስት ብር ከሰባ ዘጠኝ ሳንቲም) ለአመልካች እንዱከፍል ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል። መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.