No summary available.
ህዲር 14 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጠሪዎች፡- 1ኛ አንዋር አብደራማን 2ኛ አብደልቃድር አብደራማን 3ኛ መሐመድ አብደራማን 4ኛ ከሉፍ አብደራማን 5ኛ አይሻ አብደራማን 6ኛ ሂቦ አብደራማን 7ኛ ሳሚያ አብደራማን 8ኛ ናሬሳ አብደራማን መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፤ ግራ ቀኙ ከቀጠሮ በፉት ካቀረቡት የጽሐፍ ክርክር ጋር መዝገቡን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ ግራ ቀኙ የመያዣ ውል አደራረግ ሥርዓትን አስመልክቶ ያቀረቡትን የህግ ክርክር የሚመለከት ነው።
የጉዲዩም መነሻ የአሁኑ ተጠሪዎች አባታችን ሳያውቀው በድብቅ የተደረገ የመያዣ ውል ስለሆነ ያስረክብልን ይሰረዝልኝ ይለቀቅልን የሚል ክስ በአሁን አመልካች ላይ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት በማቅረባቸው ሲሆን የአሁን አመልካችም ባንኩ ለዮሴፍ አብርሃም ለሰጠው የብድር ገንዘብ ከአባታቸው ጋር ሐምል 14 ቀን 1987 ዓ.ም በተደረገ የመያዣ ውል መነሻ እንጂ ከሳሾች እንደሚለት አይደለም በማለት ተከራክሯል።
ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም ጉዲዩን መርምሮ ይህ አከራካሪ የሆነ የመያዣ ውል በኦሮሚያ ከተማ አስተዲደር ተመዝግቦ እንደማይገኝ የከተማው አስተዲደር ምንም ዓይነት ማስረጃ እንደላለ አረጋጋጧል። አከራካሪ በሆነው የመያዣ ውል ላይ የተቀመጠውን ፊርማ የአባታቸው ስለ መሆኑ ማረጋገጥ እንዲይቻል ባንኩ የአሁን አመልካች ማገናዘብያ የሚሆን የተለያዩ ማስረጃ ለማቅረብ አልቻለም። ዋናውን የመያዣ ውል ማቅረብ ባለመቻለ ያቀረበው ኮፑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2011 ሥልጣን ባለው አካል ፉት ካልተረጋገጠ ተቀባይነት የለውም።
ስለሆነም የመያዣ ውለ በፍ/ብ/ስ/ሕ/ቁ 1723 መሰረት በአዋዋይ ፉት ያልተረጋገጠ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 3052 መሰረት በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ላይ ስላልተመዘገበ አደራረጉ የሕግ መስፈርትን አላሟላም በመሆኑም ውድቅ ነው። ካርታው ይመለስ በማለት ወስኗል።
ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤትም ጉዲዩን ተመልክቶ የተጠሪዎች አባት በህይወት እያለ እኔ ሳላውቀው ካርታ ይዞብኛል በማለት ከአሁን አመልካች ጋር ስለተከራከረ የመያዣ ውል ምዝገባ ሥርዓት አስፈላጊ አልነበረም በህይወት እያለ በመያዣ ውለ ላይ አልፈረምኩም በማለት ስለተከራከሩ ዋናው አከራካሪ ነጥብ ፈርመዋል ወይስ አልፈረሙም የሚለው ነበር ይህንን ነጥብ ለመለየት የአሁን አመልካች ዋናውን ሰነድ አላቀረበም የእራሱን ሰነድ በሥርዓት መያዝ ግዳታው ነው ያቀረበው ኮፑ ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚቻልበት መንገድ የለም።
የሚለውን ተችቶ በሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠውን ወሳኔ አጽንቷል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ከዚህ በላይ በአጭሩ እንደተገለፀወው በየደረጃው ባለት ፍ/ቤቶች የተሰጡት ውሳኔዎች መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በሚል ነው ያቀረበውም ምክንያት ዋናው የመያዣ ውል ሉገኝ ባይችልም ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ ኮፑ አቅርበናል። በዚህ ሰነድ ላይ የሰፈረን ፊርማ መካድ እንደማይቻል በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2011 ተደንግጓል። ይህ ድንጋጌ በአግባቡ አልተተረጏመም የሚለውን ነው።
ተጠሪዎችም ለዚህ የሰበር ቅሬታ መልሳቸውን በጽሐፍ ያቀረቡ ሲሆን በግራ ቀኙ መካከል ለተነሣው አከራካሪ ነጥብ መነሻ የሆነውን የኮፑ ሰነድ ጉዲይን አስመልክቶ የአሁን አመልካች በሰበር ቅሬታው ላይ ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት የተረጋገጠ ኮፑ አቅርቤያለሁ ለሚለው ክርክር ዋናውን ቅጅ ማቅረብ እንደማይቻል በዚህ ሰበር ደረጃም አረጋግጧል። ቢኖረው ኖሮ በሚመለከተው ማዘጋጃ ቤት ይቀመጥ ነበር እራሱም ዋናውን መያዝ ነበረበት ይህ ሁለ ሳይሆን በሰጡት ሰነድ ይወሰንልኝ ማለቱ አግባብ አይደለም በማለት ተከራክረዋል ።
እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው ተመልክተናል። እንደተመለከትነውም በዚህ ሰበር ደረጃ ግራ ቀኙ እንዲደረጉት ክርክር የአሁን አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ ጉዲዩን ለማስረዲት ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት የተረጋገጠ ኮፑ አቅርቦ እንደነበር የሚያስረዲ ሲሆን ይህንንም የሚያጠናክረው በሥር በሁለቱም ደረጃ በተደረገው ክርክር አመልካች በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2008 መሰረት አከራካሪ የሆውን የመያዣ ውል ሰነድ ኮፑ አቅርቦ እንደነበረ በሁለቱም ውሳኔዎች ተመዝግቦ የመገኘቱ ጉዲይ ነው።
የዚህን ክርክር ያስነሳው የመያዣ ውል ዋናው ኮፑ ቀርቦ ቢሆን ኖሮ ተጠሪዎች ሦስተኛ ወገን ናቸው እንኳ ቢባል ይህ የመያዣ ውል ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት እስከተረጋገጠ ድረስ የሰነደን ይዘቱና ፊርማን ጨምሮ በማናቸውም መንገድ ቢሆን ሉቃወሙት እንደማይችለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2009 ላይ ተመልክቷል ይህ ዋናው ሰነድ መቅረቡ ቀርቶ የዚህ ሰነድ ትክክለኛ ቅጅ ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት ተረጋግጦ ከቀረበ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2011 እንደተመለከተው በማስረጃ ዋጋነቱ እንደ ዋናው የተረጋገጠ የመያዣ ሰነድ የሚያገለግል እንጂ ክርክር የቀረበለት ፍ/ቤት ዋናውንና ቅጂውን ሁለቱንም በማስቀረብና በማስተያየት ቅጅው ያለውን የማስረጃ ዋጋ የሚመረምርበት የህግ አግባብ የለም በዚህ መንገድ የማረጋገጥ ተግባሩ አይከናወንም። ዋናውና መሰረታዊ የሆነው ጉዲይ ለማስረጃነት የቀረበው ኮፑ ከዋናው ጋር በማገናዘብ ሥልጣን ባለው አካል ፉት ትክክለኛ ግልባጭ ስለመሆኑ በኮፑው ላይ ተገልፆ የመገኘቱ ሁኔታ ነው።
No topics extracted.
በመሆኑም የመያዣ ውል ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት ተደርጎ ለማስረጃነቱ ዋናው ሰነድ ባልተገኘ ጊዜ በምትኩ ኮፑ ሲቀርብ የዚህ የዋናው ሰነድ ግልባጭ ስለመሆኑ እራሱ ሰነደ ሥልጣን በተሰጠው አካል ማረጋገጫ ተደርጏበት የሚናገርሆኖ ከተገኘ ከላይ በተጠቀሰው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2011 መሰረት በእራሱ በቂ ማስረጃ ሆኖ እያለ ለዚህ ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት ተረጋግጦ የቀረበን ኮፑ ብቸኛው ማረጋገጫ ዋናው ሰነድ እንደሆን ተደርጎ የተሰጠው ትርጉም መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት እንደቅደም ተከተለ በመ/ቁ 9452 በ19/12/2000 እና በመ/ በ29/18/2002 የሰጡትን ፍርድች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕቁ 348(1) መሰረት ሽረናል።
ሐምል 14 ቀን 1987 ዓ.ም በተፃፈ የተደረገው የመያዥ ውል በተጠሪዎች አባት ስለመደረጉ አመልካች በህግ መሰረት ያረጋገጠ ስለሆነ ዋጋ ያለው በመሆኑ በዚሁ በአንድ ላይ የተገለፀው ንብረት ካ ርታ ለተጠሪዎች ሉለቀቅ አይችልም ብለናል።
በዚህ ሰበር ችልት ግራ ቀኙ ላደረጉት ክርክር ወጪና ኪሣራውን በየእራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡን ዘግተናል።