No summary available.
ህዲር 1 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፣ ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች - ዶ/ር ሰልሞን ነጋሽ ዶ/ር ዘውድነህ በየነ ቀረበተጠሪ - የባህርዲር ዩኒቨርሲቲ ሙላት ያዛቸው ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ ሰበር ችልት እንዱወሰን ለቀረበው አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ ቀደም ሲል በተደረገው ውል መሰረት የግልግል ዲኛ በፍ/ቤት ትዕዛዝ እንዱመረጥ አመልካች አቅርቦት የነበረውን ጥያቄ የሚመለከት ነው አመልካች ጥያቄውን ያቀረበው ለምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን ፍ/ቤቱ ተጠሪን አስቀርቦ መልስ እንዱሰጥ ከማድረጉ በፉት ጥያቄው በፍ/ቤት የሚስተናገድ አይደለም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 231 የተመለከተውን ድንጋጌ በመጥቀስ መዝገቡን ዘግቶአል ጉዲይ በይግባኝ የቀረበለት የአማራ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤትም ይግባኝ የተባለበት ትዕዛዝ ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሰርዞአል የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ግንቦት 14 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተደረገው ለአመልካች ክስ መሰረት የሆነው በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረገ ውል መሆኑ እስካላከራከረ ድረስ እንደውለ ጉዲዩ በግልግል ያልቅ ዘንድ የፍ/ቤትን እገዛ በመጠየቅ የቀረበው ክስ በማያስከሰስ ነገር ላይ የቀረበ ነው በማለት ሳይስተናገድ የመቅረቱን አግባብነት ለመመርመር ነው በመሆኑም በዚህ ረገድ ግራቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ትዕዛዝ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከፍ ሲል እንደተገለጸው አመልካች በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረተው በመሃከላቸው የተደረገውን ውል መነሻ በማድረግ ነው ውለ ነሐሴ 28 ቀን 2000 ዓ.ም የተደረገ የማማከር አገልግልት የመስጠት እንደሆነም በክርክሩ ተመልክቶአል በልላ በኩል ደግሞ የውለን አፈፃፀም በሚመለከት በመሃከላቸው አለመግባባት ቢፈጠር እና አለመግባባቱን በድርድር መፍታት ካልተቻለ ሁለቱ ወገኖች በሚያቋቁሙት የግልግል ዲኝነት እንደሚታይ ስምምነት ስለመደረጉ ግራቀኝ ወገኖች አልተካካደም አመልካች ወደክስ ያመራው ተጠሪ በውለ መሰረት ለመገዛት ፈቃደኛ አልሆነም በማለት ሲሆን የጠየቀው ዲኝነትም ተጠሪ በውለ በገባው ግዳታ መሰረት የግልግል ዲኛ እንዱመርጥ ይገደድልኝ የሚል ነው።
እንደሚታየው አመልካች እና ተጠሪ በመሃከላቸው ያቋቁሙትን መብት እና ግዳታ የሚገዛ ውል አድርገዋል። በፍ/ብ/ሕግ ቁ 1731 እንደተደነገገው በሕጉ አግባብ የተቋቋሙ ውለች ባቋቋሙዋቸው ሰዎች ላይ ሕግ ናቸው ከሣሽ የሆነው ወገን ተጣሰብኝ የሚለውን መብት ለማስከበር ዲኝነት የሚጠይቀው የመብቱን ምንጭ ወይም መሰረት ውል ወይም ህግ እንደሆነ በማረጋገጥ ስለመሆኑ የሚያከራክር አይደለም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 33/2/ አነጋገር ከሣሽ ከተከሣሽ ላይ የሚጠይቀውን ጥቅም ወይም መብት በማረጋገጥ አቤቱታውን ያቀርብ ዘንድ ይጠበቅበታል ሲባልም የመብቱ መሰረት ሕግ ወይም ውል መሆኑን በግልጽ ማሳየት አለበት ማለት ነው። በያዝነው ጉዲይ አመልካች ተጠሪ ይፈጽምልኝ የሚለው ግዳታ መሰረቱ ውለ እንደሆነ አሳይቶአል ተጠሪም ለአመልካች የሰበር አቤቱታ በሰጠው መልስ እንደገለጸው ስለውለ መደረግም ሆነ ስለይዘቱ የሚክደው ነገር የለም። ክርክሩ ተከሣሽ የመንግስት መሥሪያ ቤት በመሆኑ ጉዲዩን በግልግል እንዱጨርስ በሕግ አይገደድም የሚል እንደሆነም ከዚሁ መልሱ ይዘት ተገንዝበናል።
ክሱን በመጀመሪያ ደረጃ የቀረበለት የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የክሱን መዝገብ የዘጋው ተጠሪን ሳያስቀርብ እንደሆነ ከላይ ተገልጾአል። መዝገቡን ሉዘጋ የቻለውም አመልካች የክስ ምክንያት የለውም በማለት ነው ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት ፍ/ቤትም በተመሳሳይ ሁኔታ ይግባኙን ሰርዞአል በመሆኑም ይህ የሰበር ችልት በዚህ ደረጃ ሉያይ የሚገባው አመልካች ያቀረበው ክስ የክስ ምክንያት የለውም በማለት የተሰጠው ትዕዘዝ አግባብነት ያለው ነው ወይ? የሚለውን ጭብጥ በመሆኑ ተጠሪ በግልግል ዲኝነት ጉዲዩን እንዱጨርስ የሚለውን የሥረ ነገር ክርክር የምንመረምርበት አግባብ የለም። ወደያዝነው ጭብጥ ስንመለስም አመልካች በክሱ ላይ የገለጸው ጉዲይ /ነገር/ የክስ ምክንያት የላለው /የማያስከስስ/ ነው የሚባል ባለመሆኑ አቤቱታ የቀረበበት ትዕዛዝ በሕጉ አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል። ስለዚህም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍ/መ/ ሚያዚያ 21 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ እና በአማራ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት በፍ/ብ/መ/ ግንቦት 12 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
No topics extracted.
አመልካች ውለን መሰረት በማድረግ ያቀረበው ክስ የክስ ምክንያት የለውም በማለት ሳይስተናገድ መቅረቱ በአግባቡ አይደለም ብለናል። ስለዚህም የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክሱን ለተጠሪ እንዱደርስ በማድረግ እና ግራቀኝ ወገኖች በክሱ ስረ ነገር የሚያቀርቡትን ክርክር ከሰማ በኃላ ተገቢውን ይወሰን ዘንድ ጉዲዩ ይመለስለት በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 341/1/ መሰረት ወስነናል።
ግራቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።