No summary available.
ህዲር 17 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች - ወ/ሮ ብርሃኔ አጥናፈ ጠበቃ መኮንን አራጋው ቀረቡተጠሪ - ኢንስፓክተር ዩሐንስ ተሲሳ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።
በከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ተጠሪ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 11 ቀን 2001 ዓ.ም ባቀረበው የክስ ማመልከቻ እና በተከሣሽ ማለትም በአሁን አመልካች መካከል በነበረን የተለየ ግንኙነት ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በብድር እንድሰጣት ጠይቃኝ አበድሬያታለሁ። ተከሣሽ ግንቦት 16 ቀን 2000 ዓ.ም የብድር ውል የፈረመች ሲሆን እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2001 ዓ.ም ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺ ብር/ ቀሪውን ብር 100,000 /መቶ ሺ ብር/ እስከ ሚያዚያ 5 ቀን 2002 ዓ.ም ሉከፍለ ተስማምተዋል። በውለ መሰረት ያልከፈለ በመሆኑ በብድር የወሰደትን ገንዘብ እንዱከፍለ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። አመልካች በተከሣሽነት ቀርባ ከከሣሽ ጋር እንደባልና ሚስት በመሆን አብረን ስንኖር መግባባት ስላልቻልን ለመለያየት ስንወሰን ገንዘብ ካልሰጠሽኝ በስተቀር በማለት በእኔና በንብረቴ ላይ አደጋ እንደሚያደርስ ስላስፈራራኝ ገንዘብ ሣልበደር በግዲጅ ገንዘብ እንደተበደርኩ አድርጌ ፈርሜለሁ ስለሆነም ከከሣሽ /ተጠሪ/ የተበደርኩት ገንዘብ ስለላለ እንድከፍል የምገደድበት ምክንያት የለም በማለት ተከራክረዋል። የሥር ፍርድ ቤት ሁለት ምስክሮችን ሰምቷል። አንደኛው ምስክር በመጀመሪያ አመልካችና ተጠሪ ሲከራከሩ እንደነበር ከዚያም ሣይስማሙ በመቅረታቸው ከጠበቃ ጋር ሄደው ሲጮሁ እንደነበርና አመልካች የእኔ ድርሻ ለተጠሪ እንዲይደርሰው ስትል እንደነበርና ተጠሪ የአንቺ ድርሻ እንዲይደርሰኝ ፈርሚ ሲል የነበረ መሆኑንና በመጨረሻ አመልካች ብር 200,000 ከተጠሪ ተበድሬለሁ በማለት እንደፈረመች በመቅረቱ ተጠሪ ለአመልካች ብር 200,000 እንዲልሰጣት የመሰከረ መሆኑን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በውሣኔው በግልፅ ያሰፈረ ሲሆን ሁለተኛው ምስክር አመልካችና ተጠሪ እንደባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ እንደነበር የብድር ውል በተፈራረሙበት ቀን አመልካች ተጠሪን ከድርሻየ ጋር እንድትደርስ ስትል ተጠሪ አብረን ያፈራነውን ንብረት ድርሻየን እንዲገኝ ነው በማለት ይናገር እንደነበር ከዚያ በኃላ አመልካች የብድር ውል የፈረሙለት መሆኑን በመግለፅ እንደመሰከረ ከከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ ለመገንዘብ ችለናል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ አመልካችን እንደባልና ሚስት በኖርንበት ጊዜ ያፈራነውን የጋራ ንብረት ስጭኝ በማለት ሲጠይቅ የነበረ መሆኑንና አመልካች ከተጠሪ በደረሰባት ግፉትና ተፅዕኖ የተበደረችው ገንዘብ ሣይኖር ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ ተበደሬአለሁ ብላ የፈረመች መሆኑ በአመልካች ማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ይህም በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1706 በተደነገገው ሁኔታ የተደረገ ውል በመሆኑ በህግ ፉት ውጤት የለውም በማለት የተጠሪን ክስ ውድቅ አድርጎታል። ተጠሪ ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቧል የክልለ ጠቅላይ ፍድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች በፈረመችው ብድር ውል መሰረት ተጠሪ ክስ ያቀረበበትን ገንዘብ ከነወለደ የመክፈል ግዳታ አለባት በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ቢሆንም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የአመልካችን አቤቱታ አልተቀበለውም።
አመልካች ሚያዚያ 20 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ እኔና ተጠሪ እንደባልና ሚስት በነበረን ግንኙነት አብረን የኖርን ሲሆን አስራ አንድ ዓመት የሆናት መክሉት ዩሐንስን ወልደናል። ሆኖም በመካከላችን በነበረው አለመግባባት ግንኙነታችንን ለማቋረጥ ስንወስን ገንዘብ ካልሰጠሽኝ በማለት በሥራው ምክንያት መንግስት ባስታጠቀው መሣሪያ በተለያየ ጊዜ እያስፈራራ ስላስቸገረኝ በብድር የወሰደኩት ገንዘብ ሣይኖር ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ እንደተበደርኩ በመግለፅ በፍራቻ ፈርሜለሁ ገንዘብ በወቅቱ ያልተበደርኩ መሆኔን በውለ ላይ በምስክርነት የፈረሙት የተጠሪ ሁለት ምስክሮች ለሥር ፍርድ ቤት አስረድተዋል። ስለሆነም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ ያላግባብ ተጨማሪ ማስረጃ በመቀበል የሰጠውና ህግን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በይግባኝ ሰሚው ችልት የተፈፀመውን የህግ ስህተት ሣያርም ማለፈ ተገቢ ባለመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩላቸው አመልካች ውለን ሲፈፅሙ የሀይል ተግባር የተፈፀመባቸው መሆኑን አላስረደም አመልካች የፍታብሓር ህግ ስለብድር በሚደነግገው መሰረት ገንዘብ በብድር የወሰደ መሆኑ በውለ ሰነድ የተረጋገጠ በመሆኑ ብድሩን ላለመክፈል የሚያቀርቡት ክርክር የህግ ድጋፍና መሰረት የለውም። ስለዚህ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ውድቅ እንዱያደርግልኝ የሚል ይዘት ያለው መልስ ሰጥተዋል። አመልካች ተጠሪ ማስፈራራትና ዛቻ የፈፀመው ውለ በተፈረመበት ቀን ሣይሆን ከዚያ በፉት አመልካች ላይ ከዚያ በፉት ሥነ ልቦናዊ ተፅኖ የሚያሣድሩ ተግባራትን በመፈፀም ነው አመልካች ያልተማርኩ በመሆኔና ተጠሪ የፕሉስ መኮንን በመሆኑ እኔን ስጋት ላይ የሚጥል ተግባር ሲፈፅም የቆየ ሲሆን ውለ በሚፈረምበት ወቅትም በእኔና በአመልካች መካከል ጭቅጭቅ የነበረ መሆኑ በማስረጃ ስለተረጋገጠ ውለን በሙለ ፈቃድና ፍላጎቴ ያላደረግሁት በመሆኑ ልገደድበት አይገባም በማለት የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር በግራቀኙ መካከል የተደረገው የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው በአመልካችና በተጠሪ መካከል ግንቦት 16 ቀን 2000 ዓ.ም ያደረጉት የብድር ውል ህጋዊ ውጤትና አስገዲጅነት አለው ወይስ የለውም የሚለው ጭብጥ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመመለስ አንድ ውል ህጋዊ ውጤት የሚኖረው በምን መንገድ ሲፈፀም ነው የሚለውን ነጥብ ማየት ያስፈልጋል። ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች በህግ ፉት የፀናና ህጋዊ ውጤት ሉኖረው የሚችለው በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1678 የተደነገጉትን ሶስት መሰረታዊ ሁኔታዎችን ሲያሟላ መሆኑን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1678 ‛የሚፀና ውል ነው ለማለት ሶስት ሁኔታዎች ያስፈልጉታል“ በማለት ሁኔታዎቹን ከ“ሀ“ እስ ‛ሐ“ በዝርዝር ደንግጓል።
በህግ ፉት የፀና ውል ለማቋቋም አስፈላጊ ከሆኑ ሁኔታዎች አንደኛ ውለ ችልታ ባላቸው ሰዎች መካከል የተደረገና ተዋዋዩቹ ጉድለት በላለው ሁኔታ የተስማሙበት ሲሆን እንደሆነ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1678 /ሀ/ በግልፅ ተደንግጓል። አመልካች ከተጠሪ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ ብድር የወሰደ መሆኑን በመግለፅ ግንቦት 16 ቀን 2000 ዓ.ም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በማጣሪያ ምስክርነት ጠርቶ ቃላቸውን የተቀበላቸው ጠበቃ ባዘጋጁት የብድር ውል ላይ በማጣሪያ ምስክሩ ቢሮ ውስጥ መፈረማቸውን አልካደም። አመልካች የሚከራከሩት በወቅቱ ብር 200,000 እንደተበደርኩ በሚገልፀው ሰነድ ላይ የፈረምኩት በሙለ ፍላጎቴና ፈቃዳ አይደለም።
ከተጠሪም ውለን በምፈርምበት ጊዜም ሆነ ከዚያ በፉት በብድር የወሰድኩት ገንዘብ የለም ። ብድሩን የፈረምኩት ተጠሪ ሰነደን ካልፈረምኩ በህይወቴና በንብረቴ ላይ የማይቀር አደጋ ወይም ጉዲት የሚያደርስብኝ መሆኑን በመግለፅ በተለያየ ጊዜ የማስፈራራትና የማስገደድ ተግባራትን ስለፈፀመብኝ ነው በማለት ነው።
የማስገደድ ወይም የሀይል ሥራና ተግባር ስለተፈፀመበት አንድ ሰው አንድን ውል ለመዋዋል የተስማማ በሆነ ጊዜ ለውለ የሰጠው ስምምነት ጉድለት ያለበት ስምምነት ተደርጎ እንደሚወስድና በህግ ፉት የፀና መብትና ግዳታ ለማቋቋም የማይችል ስለመሆኑ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1678/ሀ/ እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1706 እና የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1809 ድንጋጌዎችን በጣምራ በማንበብ ለመገንዘብ ይቻላል።
አንደኛው ተዋዋይ ወገን ላላውን ተዋዋይ ወገን ራሱን ወይም ወላጆቹን ወይም ተወላጆቹን ወይም ባልን ወይም ሚስትን ከባድና የማይቀር አደጋ በህይወቱ በአካለ በክብሩ ወይም በንብረቱ እንደሚያመጣበት ያሳመነው በመሆኑ ምክንያት ውለን ለመዋዋል የተስማማ እንደሆነ ውለን በማፍረስ በቂ ምክንያት እንደሆነ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1706 ንዐስ አንቀጽ 1 ይደነግጋል። እዚህ ላይ ላላውን ወገን ውል እንዱፈፅም የሚያስገድደው ሰው የማስገደድ ተግባሩን የፈፀመውና ላላውን ተዋዋይ ወገን ስጋት ላይ የሚጥለ ተግባራትን የፈፀመው ውለ በሚፈፀምበት ዕለት ወይም ከዚያ ውለ ከተፈፀመበት ዕለት በፉት ላሆን እንደሚችል ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 1706 ንዐስ አንቀጽ 1 እና ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 1706 ንዐስ አንቀጽ 2 ድንጋጌ የጣምራ ንባብ ለመረዲት ይቻላል።
አንደኛው ተዋዋይ ላላውን ተዋዋይ ወገን በውለ ካልተስማማ በህይወቱ ወይም በንብረቱ ላይ የማይቀር አደጋ የሚያደርስበት መሆኑን ለማሳመን የሚችለ የተለያዩ የማስገደጃና የማስፈራሪያ ተግባራትንና ዘዳዎች በመጠቀም በአእምሮው ተደላድል የነበረው ተዋዋይ ወገን ላለው ተዋዋይ ከባድና የማይቀር አደጋ ሉያደርስብኝ ይችላል በሚል ስጋት ውለን እንዱዋዋል ለማድረግ የሚችልባቸው በርካታ መንገድች አለ። እነዚህ ሁኔታዎች ውለ ከመደረጉ በፉት የተፈፀሙ መሆኑን አለመሆኑን አንደኛ ተዋዋይ ወገን ላላው ተዋዋይ ከባድና የማይቀር አደጋ ሉያደርስብን ይቻላል በሚል ስጋት ለውለ ስምምነቱን የሰጠ መሆኑን ዳኞች በመገደድ ስምምነቱን የሰጠውን ሰው እድሜውን ፆታውንና አኳኃኑን በማመዛዘን ውሣኔ መስጠት እንደሚገባቸው የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1706 ንዐስ አንቀጽ 3 ይደነግጋል።
አመልካች ከተጠሪ ብር 200,000 መበደራቸውን የሚገልፅ ውል ግንቦት 16 ቀን 2000 ዓ.ም የፈረሙት በእርግጥ ከተጠሪ ተበድረው የወሰደት በውለ መጠኑ የተገለፀው ገንዘብ ስላለ ነው?
ወይስ ተጠሪ የማይቀርና ከባድ አደጋ በህይወታቸውና በንብረታቸው የሚያደርስባቸው መሆኑን እንዱያምኑና ስጋት ላይ እንዱወድቁ ለማድረግ የሚችለ የተለያየ ተግባራትና ዘዳ በመፈፀሙ ነው?
የሚለውን ጭብጥ ለመወሰን በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረውን ልዩ ግንኙነትና ባህሪ የአመልካችን ፆታ የትምህርት ደረጃና የተጠሪውን ግላዊ ሁኔታና እና ሥልጣንና ኃላፉነት መመርመርና መመዘን እንደሚያስፈልግ ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 1706 ንዐስ አንቀጽ 3 ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ ለመገንዘብ እንችላለን።
ከላይ ያስቀመጥናቸውን መሰረታዊ ሁኔታዎች ስንመዝን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በማጣሪያ ምስክርነት የሰማቸው ሁለት ሰዎች አመልካች በተጠሪ ምንም አይነት የማስገደድ ተግባር ሣይፈፀምባቸው እኛ ባለንበት የብድር ውለን ፈርመዋል በማለት ውለ በተፈረመበት ወቅት ብቻ ስለነበረው ሁኔታ የሰጡትን የምስክርነት ቃል መሰረት በማድረግ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች አልተገደደም የሚል መደምደሚያ ላይ መድረሱ ከላይ የጠቀስነውን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1706 ንዐስ አንቀጽ 3 ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ጉዲዩን ያልመዘነና ያልመረመረ መሆኑን የሚያሣይ ሆኖ አግኝተነዋል።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውለ ከመፈፀሙ በፉት በተጠሪና በአመልካች መካከል የነበረውን ግንኙነትና የተጠሪ ምስክሮች አመልካችና ተጠሪ ወደ ሁለተኛው የማጣሪያ ምስክር ቢሮ ከመሄዲቸው በፉት ሲለዋወጡት የነበረው ሃሳብና ንግግርን መመዘንና መመርመር ይገባው ነበር አመልካችና ተጠሪ እንደባልና ሚስት አብረው ለረዥም ጊዜ የኖሩ እና የአስራ አንድ ዓመት ሴት ልጅ ወልደው ያሣደጉ መሆናቸው በግራቀኙ የተካደ ፍሬ ጉዲይ አይደለም እንደባልና ሚስት በመተማመን የኖሩት አመልካችና ተጠሪ በመካከላቸው በተፈጠረው አለመግባባት ግንኙነታቸውን ለማቋረጥ ለየብቻቸው ለመኖር ሲወስኑ በመካከላቸው አለመግባባትና ቅሬታ ተፈጥሮ የነበረ በመሆኑ የብድር ውለ ተፈረመ በተባለበት ግንቦት 16 ቀን 2000 ዓ.ም የዕርቅ ስምምነት ውል አድርገው የነበሩ መሆኑና በውለም በጋራ በቆየንበት ጊዜ የተፈራ የጋራ ሀብት በውርስ ወይም በስጦታ ያገኘነው ንብረት የለም በማለት ተስማምተው የነበረ መሆኑ አመልካችና ተጠሪ ካቀረቡት ክርክር ለመገንዘብ ችለናል። አመልካችና ተጠሪ ወደ ሁለተኛው የፍርድ ቤት የማጣሪያ ምስክር ቢሮ ከመሄዲቸው በፉት የእኔን ድርሻና ንብረት እንዲትወስድ እያለች አመልካች ትናገር የነበረ መሆኑና አመልካች ብር 200,000 ተበድሬያለሁ ብላ ከመፈረሟ በፉት ይከራከሩና ሃሳብ ይለዋወጡ የነበሩት ስለብድር ገንዘብ ሣይሆን ስለጋራ ንብረት እንደነበር የከፍተኛው ፍርድ ቤት የምስክርነት ቃላቸውን የሰማቸውና የሰጡትን የምስክርነት ቃል ተዓማኒነት ያለው መሆኑን በማረጋገጥ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በውሣኔው በግልፅ አስፍሯል። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች ብር 200,000 ተበድሬአለሁ ብላ ከመፈረሟ ውጭ በዕለቱ ተጠሪ በብድር የሰጣት ጥሬ ገንዘብ ቼክ ወይም ሐዋላ የላለ መሆኑ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ቃላቸውን የሰማቸው የተጠሪ ምስክሮችና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰማቸው የማጣሪያ ምስክሮች አረጋግጠዋል።
ተጠሪ መርማሪ ፕሉስ በመሆኑ አመልካችን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በሰማቸው የማጣሪያ ምስክሮች ፉት ውለን ፈርሚ ብል ለማስገደድ የሚሞክርበት ሁኔታ የለም ምክንያቱም ተጠሪ ድርጊቱ በህግ ፉት የሚያስትለውን ህጋዊ ውጤት ጠንቅቆ የሚያውቅ ከአመልካች የተሻለ የህግ ዕውቀትና ግንዛቤ ያለው በመሆኑ ከአመልካች ጋር እንዲባልና ሚስት ስንኖር ያፈራነው የጋራ ሀብት አለ ብል በህግ ፉት ተከራክሮ ለመፍታት የሚያስችለው ማስረጃ አለመኖሩን በመረዲት አመልካች የብድር ውል እንዱፈፅሙ ያደረገ መሆኑን ከላይ ከገለፅናቸው ሁኔታዎች ለመገንዘብ ይቻላል የብድር ውለ አመልካች ከሚኖሩበት ከተማ ውጭ መደረጉ የአመልካችን ክርክር የሚያጠናክር ነው። ስለሆነም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች ውለን ስትፈርም ተጠሪ አላስገደዲትም ወይም አላስፈራራትም የሚለውን የማጣሪያ ምስክሮች ቃል በመስማት ብቻ አመልካች የብድር ውለን ተጠሪ እንድትፈፅም አላስገደዲትም ከሚለው መደምደሚያ ላይ የደረሰው በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1706/3/ በሚደነግገው መሰረት ውለ ከመፈረሙ በፉት አመልካችና ተጠሪ ያደረጉትን የዕርቅ ስምምነት እንደዚሁም ወደ ሁለተኛው ማጣሪያ ምስክር ቢሮ ከመሄዲቸው በፉት ሃሳብ እየተለዋወጡ ሲከራከሩ የነበሩት በብድር ስለተወሰደ ገንዘብ ሣይሆን አብረው ሲኖሩ በጋራ ያፈሩት ንብረት አለ ወይም የለም በሚለው ነጥብ ላይ መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ የማያስገባ በመሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪ አመልካች የማስፈራራትና የማስገደድ ተግባራት የተፈፀመባት መሆኑን አላስረዲችም በማለት ያቀረበውን ክርክር ስንመለከተው አመልካች የብድር ውለ በህግ ፉት የማይፀናና ፈራሽ መሆኑን የማስረዲት ግዳታ እንዲለባቸው በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2001 ንዐስ አንቀጽ 2 የተደነገገ ቢሆንም በህግ ፉት የሚፀናና ጉድለት የላለበት የብድር ውል ያለ መሆኑን ለማስረዲት ተጠሪ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2001 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት ያቀረባቸው ምስክሮችና በአጠቃላይ ላልች የአካባቢ ሁኔታዎች አመልካች ከተጠሪ ብር 200,000 በሙለ ፍላጎትና ፈቃዲቸው ያልተበደሩና በተቃራኒው ተጠሪ አብረን ስንኖር ያፈራነው የጋራ ገንዘብ ያለኝ በመሆኑ በብድር መልክ ድርሻየን ፈርሚ በማለት የተለያዩ የማስገደጃና የማስፈራራት ተግባራትን በመፈፀም የብድር ስምምነቱን እንዱፈርሙ ያደረጉ መሆኑን የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የከፍተኛው ፍርድ ቤት የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1706 ንዐስ አንቀጽ 3 የተደነገጉትን ሁኔታዎች በማመዛዘን ከድምዲሜ ላይ የደረሰ በመሆኑ ተጠሪ በዚህ በኩል ያቀረቡትን ክርክር አልተቀበልነውም። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪ አመልካች የብድር ውለን ለማፍረስ በሁለት ዓመት ያልጠየቁ መሆኑን ገልፆ የተከራከረ ቢሆንም ይኸ የተጠሪ ክርክር ውለን ለመፈፀም እንቢ ለማለት የማይፈልገው ወገን ውለ የማይረጋ መሆኑን በማናቸውም ጊዜ መቃወሚያ ሉያደርገው እንደሚችል በግልፅ የሚደነገግውን የፍታብሓር ህገ ቁጥር 1809 መሰረት ያላደረገ በመሆኑ አልተቀበልነውም። በአጠቃላይ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት እና ሰበር ችልት በአመልካችና ተጠሪ በመካከላቸው የነበረውን ልዩና ጥብቅ ግንኙነት አመልካችና ተጠሪ በመካከላቸው የነበረውን ግንኙነት ለማቋረጥ ያደረጉትን ስምምነትና ውለ የአመልካች መኖሪያ በሆነው ቢሸፍቱ ከተማ ሣይሆን የተጠሪ መኖሪያና የሥራ ቦታ በሆነው አዲማ ከተማ የተደረገ መሆኑን የአመልካችን ፆታና የትምህርት ደረጃና የተጠሪን የትምህርት ደረጃ ሙያና ስልጣንና ሀላፉነት እንደዚሁም የብድር ውለን ከማፀፊቸው በፉት ሲከራከሩበት የነበረውን መሰረታዊ ጉዲይ የፍታብሐር ህግ ቁጥር 1706 ንዐስ አንቀጽ 3 በሚደነግገው መሰረት ሣያመዛዝኑ አመልካች ለተጠሪ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ ከነወለደ እንዱከፍለ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ሰበር ችልት እና የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንተነዋል።
አመልካችና ተጠሪ ግንቦት 16 ቀን 2000 ዓ.ም የተፈራረሙት የብድር ውለ ተጠሪ በሙለ ፈቃዲቸው ስምምነታቸውን ያልሰጡበት ጉድለት ያለውና በህግ ፉት የማይፀናና ውጤት የላለው ነው በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
No topics extracted.