No summary available.
ኀዲር 28 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ኃይላይ ተክላይ - ጠበቃ አቶ ገ/አምላክ ገ/ጊዮርጊስ ቀረቡ ተጠሪ፡- ሙቁር የጨው አምራቾች ኃላ/የተወ/የግል ማህበር ጠበቃ አቶ ሙለጌታ ገብሩ ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፤መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበው በተጠሪ ማህበር መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 16 ላይ ስለ ውዝግብ አፈታት በሚል የተቀመጠው የደንብ ክፍል በማህበሩ አባላት መካከል የተነሣን ክርክር ብቻ ለመሸፈን ታስቦ የተቀረፀ ነው ወይስ በአባለና በማህበሩ መካከል የሚነሳውንም ውዝግብ ሉጨምር የሚችል ነው? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ ጋር በተያያዘ የአንቀፁ የተፈፃሚነት ወሰን በሚመለከት አግባብነት ያለውን ትርጉም ለመስጠት ሲባል ነው።
የጉዲዩ መነሻ የአሁን አመልካች የማህበሩ አባል በማህበር ላይ በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረበው ክስ ሲሆን ይዘቱም ማህበሩ በንግድ ሕግ ባለበት ኃላፉነት መሰረት የማህበሩን የሂሳብ ሚዛን ለአባላት አላቀረበም፤ትርፍና ኪሣራም አላሳወቀም። በመሆኑም ማህበሩ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ያደረገውን እንቅስቃሴ የሚያሳዩ የሂሳብ ሪፕርት እንዱያቀርብ ትርፍና ኪሣራ ታይቶ ድርሻዬ ይሰጠኝ የሚል ነው።
የአሁን ተጠሪ በማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 16 ላይ ማህበር ነክ አለመግባባት በግልግል እንደሚታይ የተደነገገ ሲሆን ይህ ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን የለውም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል።
የአሁኑ አመልካችም የፍ/ቤቱን ሥልጣን አስመልክቶ በመተዲደሪያ ደንቡ ላይ በግልግል እንዱታይ የተስማማነው በማህበርተኞች መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን እንጂ በማህበሩ ላይ የቀረበውን ክስ የሚመለከት አይደለም። ስለሆነም ሥልጣኑ የፍ/ቤት ነው በሚል ይዘት ማስተባበያውን በቃል ክርክር አቅርቧል።
ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም በማህበርተኞች መካከል የሚነሱ ማህበር ነክ አለመግባባቶች የሚለው የመተዲዲሪያ ደንቡ አንቀጽ በማህበሩና በማህበርቶኞች መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን ሁለ የሚመለከት በመሆኑ በግልግል ከሚታይ በቀር ፍ/ቤቱ ክርክሩን ለማየት ሥልጣን የለውም የሚል ዲኝነት ሰጥቶበታል።
ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት ፍ/ቤትም በዚሁ ነጥብ ላይ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት በሥር ፍ/ቤት የተሰጠውን ብይን አጽንቷል።
ይህ ሰበር አቤቱታ የቀረበውም ክርክር ያስነሳው ጉዲይ በፍ/ቤት ቀርቦ ላታይ የሚችል ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ለመለየት በሥር በየደረጃው ያለ ፍ/ቤቶች በማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 16 የተመለከተውን የደንብ ክፍል በአግባቡ አልተረጏሙትም፤የሚል ሆኖ በምክንያትነትም ክርክሩ የተነሣው በማህበርተኞች መካከል ሳይሆን በማህበርተኛ እና በማህበሩ መካከል ስለሆነ ደንቡ ተፈፃሚ ላሆን የሚችል አይደለም። ጉዲዩ በፍ/ቤት ላታይ የሚችል ነው። በሚል የተጠቀሰው ይገኝበታል።
እንዱሁም ወጭና ኪሣራን አስመልክቶ የአሁን ተጠሪ አቅርቦት የነበረው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ ከተደረገ ተረቺ በመሆኑ የወጭና ኪሣራ መብታችን ሳይጠበቅ በአንፃሩ በሥልጣን ምክንያት የእኛን ክስ ውድቅ ሲያደርግ ለተጠሪ መብቱን መጠበቁና በተመሳሳይ መንገድ የእኛን መብት መንፈጉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 463 የተመለከተውን ድንጋጌ የሣተ የሕግ ስህተት ነው የሚለውንም ቅሬታ አቅርቧል።
ተጠሪም የሥር ፍ/ቤቶች ሥልጣንን አስመልክቶ የሰጡት ዲኝነት መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈፀመበት መሆኑን ለማስረዲት የበኩለን መልስ ዘርዝሮ ያቀረበ ሲሆን፤አመልካችም በመልሱ መልስ ላይ የጠበቃውን በጥብቅና ለመከራከር ያለውን የውክልና ሥልጣን የፀና አይደለም ስለሆነም መልሱ ዋጋ ያለው ባለመሆኑ የክርክሩ አካል ላሆን አይገባም የሚለውን ሁለ ጨምሮ የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን፤እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ለትርጉም መነሻ የሆነው፣በማህበሩ መተዲዲሪያ ደንብ አንቀጽ 16 ውዝግብ ለመፍታት በሚል ርዕስ በማህበርተኞቹ መካከል የሚነሱ ማህበር ነክ አለመግባባቶች በኢትዮጵያ የፍ/ብሓር ህግና የሥነ-ሥርአት ሕግ ስለግልግል በተመለከተው ደንብ መሰረት ይወስናል። ውሳኔው አስገዲጅና የመጨረሻ ነው ‛በሚል ከተቀመጠው አንቀጽ“ በማህበርተኞቹ መካከል የሚነሱ ማህበር ነክ አለመግባባቶች …“ የሚለው ሐረግ በቀጥተኛው የሐረግ ትርጉም (literal meaning) የሚገደብ ነው ወይስ የተነሳው አለመግባባት ማህበር ነክ መሆኑ እስከተገለፁ ድረስ ከማህበሩ የሚመነጭ ማህበር ነክ አለመግባባት በማህበርተኞቹ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን በማህበሩና በማህበርተኞቹ መካከል አለመግባባት መነሳቱ አይቀሬ በመሆኑ ‛በማህበርተኞች መካከል“ የሚለው ሐረግ በስፊት ታይቶ ሉተረጏም ይገባል ወይ? የሚለውን ጥያቄ ስለሚያስነሳ ለትርጉም በር በማይከፍት ሁኔታ የተቀረፁ አንቀጽ ሆኖ አልተገኘም።
No topics extracted.
የትርጉም ሥራ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ደግሞ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከሚመራበት ደንብ የመነጨ በመሆኑ እና ይህ ደንብም በማህበርተኞች ስምምነት የሚወጣ በመሆኑ እንደማናቸውም በሕግ ፉት የፀና ውል እንደሚተረጏመው ይህም ደንብ ስለውልች በጠቅላላው ሕግ በተቀመጠው የመነሻ አተረጓጏም መርህ ላታይ የሚችል ከመሆኑም በላይ ይህን መሰል ደንብ ለመተርጏም ሉመራን የሚችል የተለየ ሕግ እስከላለ ድረስ የስምምነት ዓይነት ምንም ይሁን ምን ስለውልች በጠቅላላው የተመለከቱት ደንቦች ተፈፃሚ እንደሚሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1676/1/ የተመለከተ በመሆኑ ጭምር ነው።
በመሆኑም ማህበር ነክ አለመግባባት በማህበርተኞች መካከል ብቻ የተወሰነ ሳይሆን በማህበሩና በማህበሩ አባላት መካከል ጭምር የሚነሳ በመሆኑ አንቀጹን ቃል በቃል ካየነው በማህበሩና በማህበርተኞች መካከል ከማህበሩ የመነጩ አለመግባባት የተነሣ እንደሆነ እንዳትና በማን ይታያል? የሚል ጥያቄ ከተነሣ በክፍተትነት የሚቀር በመሆኑ ይህንኑ በሚመለከት ጥያቄ ቢነሳ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1734 እንደተመለከተው በዚህ ነጥብ ላይ የማህበሩ አባላት የሐሳብ አንድነት (common interest of the members) ምን ላሆን ይችላል? እንዱሁም ማህበር ነክ አለመግባባት የሚል ጠቅላላ አነጋገር በዚሁ አንቀጽ ላይ ተጠቅሶ እያለ ከማህበሩ ሉመነጭ የሚችለውን የአለመግባባት ዓይነት ወሰን የሚያጠብ ‛በማህበርተኞች መካከል“ የሚል ቃል ቢገኝም ማህበርተኞቹ ማህበር ነክ አለመግባባት የሚለውን ቃል ሲጠቀሙ የነበራቸው ሐሳብ ምን ነበር? የሚለውን ሁለ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1735 ከተመለከተው አንፃር ማየት የሚያስፈልግ በመሆኑ ይህ ክርክር ያስነሳው አንቀጽ ከነዚህ ማዕዘኖች አኳያ ታይቶ ሉተረጏም የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል።
የማህበሩን መተዲደሪያ ደንብ ዝርዝር ይዘቱን ማየት እንደሚቻለው ማህበር ነክ ጉዲዮችን በተሟላ አኳኋን እንዱሸፈን ተደርጏ የተቀረፀ ሲሆን፤በስተመጨረሻ ከዚህ መሰል መተዲደሪያ ደንብ ሉመነጭ የሚችልን ውዝግብ እንዳት መፍታት እንደሚቻል አስቀድሞ ለማየት የደንቡ አካል በማድረግ በአንቀጽ 16 ላይ ከማህበሩ የመነጩን ማናቸውም ውዝግብ ለፍርድ ቤት በማቅረብ ፍትህ የማግኘት መብቱ በሕገ-መንግስቱም ሆነ አከራካሪ በሆነው በንግደ ሕጉ ላይ የተከበረ መሆኑ እየታወቀ ውዝግቡ በሕግ መሰረት በግልግል እንዱታይና ይህም በግልግል ታይቶ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ መሆኑን በመግለጽ ማካተታቸው ማናቸውም ጉዲይ በአማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዳ እንዱያልቅ ሐሳብ የነበራቸው መሆኑን የደንቡ ይዘት እና አቀራረጽ ስለሚያስረዲ፤
እንዱሁም ከማህበሩ የሚመጩት ውዝግቦች በማህበርተኞች መካከል ወይም በማህበሩና በአባላቱ መካከል ላሆን እንደሚችል እየታወቀ የውዝግቡን ዓይነት በሁለት በመክፈል በማህበሩና በአባላት መካከል ከሆነ ግን ወደ ፍ/ቤት እንዱሄድ አስበው ነው ለማለት የተለዩ የግምት መነሻ የሆኑ ምክንያቶች ባለመገኘታቸው፣ በማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 16 ላይ ማህበር ነክ ውዝግብ የሚለው አባባል በማህበሩና በአባላቱ መካከል ጭምር ሉነሳ የሚችልን ክርክር ሁለ የሚያጠቃልል ላሆን ይገባል በሚል የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዲኝነት በውል አተረጓጏም ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አልተገኘም።
በልላ በኩል የዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን ትርጉም ለመስጠት መነሻ ያደረገው በአመልካች የሰበር አቤቱታ እና በሥር ፍ/ቤት የተሰጠውን ትርጉም መሰረት በማድረግ እንጂ የተጠሪን መልስ በመመርኮዝ ባለመሆኑ፣ እንዱሁም ስለተጠሪ ሆኖ ለመከራከር ለጠበቃው የውክልና ሥልጣን ሰጡ የተባለት ሥራ አስክያጅ በማህበሩ ቃለ ጉባኤ ተሰጥቷቸው የነበረው የሥራ ዘመን አልቋል እንጂ በልላ ሥራ አስኪያጅ ተተክተዋል በማለት ባለመሆኑ፤ ይልቁንም አመልካች ያቀረቡት ማስረጃ በግልጽ እስካሁን ድረስ በልላ ሥራ አስኪያጅ የአለመተካታቸውን የሚያስረዲ በመሆኑ ከጥብቅና ውክልና ጋር በተያያዘ ያነሱት ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
ስለወጭና ኪሣራ ጉዲይ ማን እንደሚከፍል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 462 እንደተመለከተው ለይቶ ለመወሰን ሥልጣኑ የፍ/ቤቱ በመሆኑና ይህንኑ ሥልጣኑን በዘፈቀደ የተጠቀሙበት ለመሆኑ ጠቋሚ እና አስረጂ በሆነ አኳኋን የቀረበ ክርክር ባለመሆኑ ወጭና ኪሣራ ማን ይክፈል የሚለውን በመወሰን ረገድም የሕግ ስህተት የተፈፀመ ሆኖ ስላላገኘው የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
348 መሰረት አጽንተናል።
ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።