No summary available.
ህዲር 13 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች- ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካቾች - 1. የምሥራቅ ወለጋ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ነገፈጅ አቶ በቀለ መንገሻ ቀረቡ 2. የምስራቅ ወለጋ ዞን ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ነገረፈጅ ድንቀለም ይኖሩተጠሪ፣ አቶ ፀጋዬ ነጋ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የምስራቅ ወለጋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልትና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት ስላመለከቱ ነው ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት አንደኛው አመልካች በአዱስ ዘመን ባወጣው ጨረታ ተሣትፋ በማሸነፋና ላልች ፍርማሉቲዎችን በማሟላት ለጤና ኬላ የሚውለ መሣሪያዎችን ሳቀርብ ተከሣሹ ዋጋቸውን ሉከፍል ውል ተዋውለናል። ሆኖም ተከሣሹ /አንደኛ አመልካች ሀምላ 27 ቀን 1997 ዓ.ም ባደረግነው ውል መሰረት ላቀረብኩለት አስራ አራት ፍሪጅ ዋጋውን ከነተጨማሪ እሴት ታክሱ እንዱከፍለኝ ጠይቄ እስካሁን ያልከፈለኝ በመሆኑ ብር 340,621.96 /ሶስት መቶ አርባ ሺ ስድስት መቶ ሃያ አንድ ብር ከዘጠና አንድ ሣንቲም/ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ተጠሪ ክስ አቅርቧል። አንደኛ አመልካች በተከሣሽነት ቀርቦ ፍሪጁን ተረክቦ ለሁለተኛው ተጠሪ ያስረከበ መሆኑን ከገለፀ በኃላ ገንዘብ ያልከፈልነው ተጠሪ ያቀረበው ፍሪጅ በጨረታ ተወዲድሮ ያሸነፈበት ሣይሆን ላላ አይነት ፍሪጅ በማቅረቡ ነው በማለት መልስ ሰጥቷል። ሁለተኛው አመልካች በጨረታው ጣልቃ ገብ ተከራካሪ ሆኖ ቀርቦ ተጠሪው ‛Cibir Type ‛ የሚባል ፍሪጅ ማቅረብ ሲገባው ‛Zero applience‛ የተባለ ፍሪጅ ነው ያቀረበው ሉከፈለው አይገባም በማለት ተከራክሯል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራቀኙን ማስረጃ ከሰማ በኃላ ተጠሪ ባቀረበው የጨረታ ሰነድ ‛Zero applience‛ የሚባለውን ፍሪጅ በመሞላት የተወዲደረ በመሆኑ በውለ አስፈላጊው ሪፍሪጅሬተር የሚል አሻሚ ቃል ያለ በመሆኑ ተጠሪ ለማቅረብ የተስማማው ‛Zero applience‛ የተባለውን ፍሪጅ ነው ይህንን ፍሪጅ በውለ መሰረት ያቀረበ በመሆኑና አስራ አራት ፍሪጅ ከሣሽ /ተጠሪ/ ያስረከበ ስለሆነ ብር 340,621.95 ብር አመልካቾች ለተጠሪ እንዱከፍለ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል አንደኛ አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበዋል የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት የአንደኛ አመልካችን ይግባኝ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል አመልካቾች የሰበር አቤቱታ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አቅርበዋል። የክልለ ሰበር ችልት የግራቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የአመልካቾችን የሰበር አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል።
አመልካቾች መጋቢት 7 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ በጨረታው ያቀረበው ስፓስፉኬሽንና አመልካቾች እንድንረከበው የጠየቀው ዕቃ አንድ አይነት አይደለም ከዚህ በተጨማሪ በዋጋ ማቅረቢያው ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈልበት መሆኑን ሣያሣውቅ ከነተጨማሪ እሴት ታክሱ የዕቃውን ዋጋ እንድንከፍል ተወስኖለታል። ስለሆነም የክልለ ፍርድ ቤቶች በየደረጃው የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል ተጠሪ በበኩለ የአመልካቾች አቤቱታ የህግ ድጋፍ የላለው በመሆኑ የሰበር አቤቱታቸውን በመሰረዝ የሰበር ችልት እንዱያሰናብተኝ የሚል ይዘት ያለው መልስ ያቀረበ ሲሆን አመልካቾች የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ በጽሐፍ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራቀኙ በፅሐፍ ያቀረቡት ክርክር ይዘት በአጭሩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካቾች ተጠሪ ያቀረበውን አስራ አራት ፍሪጅ በሙለ ባለቤትነት በመቀበል ለተጠሪ የፍሪጁን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር እንዱከፍለ የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ለተያዘው ጭብጥ እልባት ለመስጠት በመጀመሪያ የሥር ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍሬ ጉዲይ ደረጃ የደረሱበትን መደምደሚያ ማየቱ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ያየው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ በጨረታ ሰነድ ሞልቶ ያቀረበው ‛Zero applience‛ የሚባለውን ፍሪጅ መሆኑን ሁለተኛው አመልካችም ‛Zero applience“ የሚባለው ፍሪጅ ተገቢውን አገልግልት መስጠት የሚችልና ከተያዘው በጀት ጋር ዋጋው ተመጣጣኝ መሆኑን ገልፆ ለጨረታ ኮሚቴው ደብዲቤ የፃፈ መሆኑን በመዘርዘር ተጠሪ የተዋዋለው ‛Zero applience‛ የተባለው ፍሪጅ በመሆኑና ይህንኑ ፍሪጅ በቁጥር አስራ አራት ያስረከበ በመሆኑ የፍሪጁን ዋጋ ከነተጨማሪ እሴት ታክስ አመልካቾች እንዱከፍል ወስኗል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት አመልካቾች ከተጠሪ ጋር ውል የተዋዋለት ‛Zero applience‛ የሚባለውን ፍሪጅ ለመግዛት መሆኑን በመግለፅ ትዕዛዝ ሰጥቷል የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ተጠሪ በውለ የተገለፀውን ዕቃ ያቀረበ መሆኑን በማረጋገጥ ውሣኔ ሰጥቷል።
አንደኛ አመልካች በአዱስ ዘመን ጋዜጣ ለጨረታ የወጣው ‛Cibir Type‛ የተባለውን ፍሪጅ ለመግዛት ነው የሚል ክርክር ያቀረበ ቢሆንም ተጠሪ በጨረታ ሰነደ ሞልቶ ያቀረበው ‛Zero applience‛ የሚባለውን ፍሪጅ ለማቅረብ እንደሆነ በየደረጃው ባለ የክልለ ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። ይህም ተጠሪ በሀራጅ ማስታወቂያው የተገለፀውን ፍሪጅ ሣይሆን ላላ አይነት ፍሪጅ ለተጠሪ ለማቅረብ የጨረታ ሰነደን ሞልቶ ሲያቀርብ አዱስ ድርድር እንዱደረግ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1694 መሰረት ሀሳቡን እንደገለፀ የሚያስቁጥር ሲሆን የጨረታ ኮሚቴው የሁለኛውን አመልካች ሃሳብና ስምምነት ከተቀበለ በኃላ ተጠሪን የጨረታው አሸናፉ መሆኑን በማረጋገጥ ውል መዋዋለ ተጠሪ ያቀረበውን አዱስ ድርድር የተቀበለና በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1695 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ውል የተዋዋለ መሆኑን የሚያሣይ ነው።
ስለሆነም ተጠሪ የጨረታ ሰነደን የሞላው ‛Zero applience ‛ የሚባለውን ፍሪጅ መሆኑና አመልካቾችም ይህንኑ አውቀውና አምነውበት ተጠሪን ዕቃውን እንዱያቀርብ ውል የተዋዋለ መሆኑና ተጠሪ በውለ መሰረት አሥራ አራት ‛Zero applience‛ ፍሪጅ ማስረከቡን ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተረጋገጠ በመሆኑ ተጠሪዎች ይህ በክልለ ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠው ፍሬ ጉዲይ ተገቢነት የለውም በማለት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ለሰበር ችልት በህገ መንግስቱ አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 የተሰጠውን ሥልጣን ያላገናዘበና የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም። ከዚህ በተጨማሪ አመልካቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ እንድንከፍል መወሰኑ አላግበብ ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር የአዋጅ ቁጥር 285/1994 ድንጋጌዎች እንደተሻሻለው ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባና የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
በአጠቃላይ አመልካቾች ከተጠሪ ጋር ባደረጉት ውል መሰረት የተረከቧቸውን አስራ አራት ሪፍሬጅሬተሮች ዋጋ ከነተጨማሪ እሴት ታክስ እንዱከፍለ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልትና ሰበር ችልት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልትና ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት
No topics extracted.