No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 521ዐ6 ህዲር 13/2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ/ማህበር ነ.ፈጅ አቶ ብርሃኑ ልኪሣ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ታደሰ አደሬ ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፤ መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ አንድ የተሸጠ የሚንቀሣቀስ ንብረት ከመሸጡ በፉት በነበረ የፍ/ቤት ዕገዲ ምክንያት ገዥው በባለቤትነት መብቱ መገልገል ሣይችል ቢቀር በሻጩ ላይ ሉኖር የሚችለው ኃላፉነት ምንድን ነው የሚለውን ነጥብ በሚመለከት በሻጭና በገዥ መካከል በተነሣው የሕግ ክርክር ላይ ያተኮረ ነው።
የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካች ላይ በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበው ክስ ባጭሩ፡ ሳምሶን ነጋሽ በሚባል ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን ፉያት የጭነት መኪና ሚያዚያ 28 ቀን 1998 ዓ.ም በብር 58,ዐዐዐ.ዐዐ ሸጦልኛል። ሆኖም የፍ/ቤት ዕግድ ስላለበት የንግድ ፈቃድ፣ ቦል እና ታርጋ በማውጣት እንደባለቤት በንብረት አገልግልት ማግኘት አልቻልኩም ጥቅም ተቋርጦብኛል።
ስለሆነም የተቋረጠ ጥቅም በወር 7ዐዐዐ.ዐዐ /ሰባት ሺህ ብር/ እንዱከፍለኝና ስመሐብትነቱንም ወደ እኔ ይዙርልኝ የሚል ክስ አቅርቦበታል።
የአሁን አመልካችም በተከሣሽነት ቀርቦ ባለቤትነትን የሚያረጋግጡ ሰነድችንና ሉብሬውን አስተላልፈናል። በከፍተኛው ፍ/ቤት ተሰጥቶ የነበረውን የዕግድ ትእዛዝ ያስነሳን ሲሆን በወረዲው ፍ/ቤት የነበረውን ግን ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ለማሰነሣት አልቻልንም የሚለውንና ከይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የውሣኔ ግልባጭ መረዲት እንደሚቻለውም በዕገዲ ምክንያት መኪናው ያለሥራ አልቆመም፤ ዕግድ ያለበት መሆኑንም እያወቀ ስለገዛ ኃላፉነት የለብንም የሚለትን ከኃላፉነት ጋር የተያያዙ ክርክሮችን ካቀረበ በኋላ ስለተቋረጠ ጥቅም መጠን አስመልክቶ ደግሞ የተቋረጠው ጥቅም መጠን በማስረጃ ያልተረጋገጠ በመሆኑ አይታመንም በማለት ግልጽ መልስ ሰጥቷል።
ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም ተቋረጠ ስለተባለው ጥቅም ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ ይችል ዘንድ ከበከልቻ ትራንስፕርት አክሲዩን ማህበር ማረጋገጫ እንዱቀርብ ካደረገ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ፣ ተከሣሽ የአሁን አመልካች ለተቋረጠ ጥቅም ኃላፉነት አይኖርብኝም ሲል ያቀረባቸው ምክንያቶች ተቀባይነት የላቸውም የተቋረጠ ጥቅምን በሚመልከት የትራንስፕርት አክሲዮን ማህበሩ ከሣሽ ከገለፀው መጠን በላይ ሆኖ ስለተገኘ ከሣሹ ያቀረበውን መጠን የሰላት መነሻ በማድረግ የሽያጭ ውለ ከተደረገበት ሚያዚያ 28 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ ስመ ሀብትነቱ ወደ ከሣሽ ዞሮ ሥራ እስከሚጀምርበት ጊዜ ድረስ በወር 7ዐዐዐ.ዐዐ /ሰባት ሺህ ብር/ ተከሣሽ ይክፈል ሲል ወስኗል።
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በይግባኝ ደረጃ የሁለቱንም ወገኖች ክርክር ከሰማ በኋላ የሽያጭ ውለ ከተደረገበት ከሚያዚያ 28 ቀን 1998 ዓ.ም በፉት ግንቦት 23 ቀን 1994 ዓ.ም የተሰጠ የዕግድ ትእዛዝ መኖሩን ከተረጋገጠ ሻጭ ቀድሞውኑ የዕግድ ትእዛዝ እንዲለበት ያውቃል።
ስመሀብት የማዛወር ግዳታ ባይኖርበትም ይህንን ዕገዲ እያወቀ መሸጡ፡ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ ነው በሽያጭ ውል ላይ ሻጭ አስፈላጊውን ትብብር ሁለ ያደርጋል በሚል መገለፁ በሻጭ ላይ ያለውን ከሕግ የመነጨ ግዳታን የሚያስቀር አይሆንም መኪናው ስለመቆሙ አልተረጋገጠም ቢልም ስመሐብትነቱ በገዥው ስም እስካልዞረ ድረስ ያለስራ እንደቆመ ይቆጠራል ስለሆነም ኃላፉ ነው መባለ ተገቢ ሲሆን፤ የደረሰውን የጉዲት መጠንንም ቢሆን በገለልተኛ ወገን የተረጋገጠው ከሣሹ ከጠየቀው በልጦ በመገኘቱ የተነሣ በከሣሽ በኩል የቀረበው መጠን መወሰደ ስህተት አይደለም የሚለትን መነሻ በማድረግ ውሣኔውን አጽንቷል።
የሰበር ቅሬታ የቀረበውም በእነዚህ በየደረጃው የተሰጡት ውሣኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመባቸው ናቸው ይታረምልን በሚል ሆኖ የመከራከሪያ ነጥቡም በሥር ፍ/ቤቶች አቅርቧቸው ከነበረው በይዘቱ የተለዬ አይደለም።
ተጠሪም በኃላፉነትም ሆነ በጉዲት ካሣ መጠን ረገድ የሰጠው ዲኝነት ሕግን መሰረት ያደረገ ነው ለሚለው ክርክሩ ውለን አብራርቶ አቅርቧል።
እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል። አመልካች በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2341/2/ ላይ በተመለከተው መሰረት ከኃላፉነት ለመዲን ሲል ገዥው በንብረቱ ላይ የዕገዲ ትእዛዝ ያለበት መሆኑን እያወቀ ገብቷል የሚለውን ክርክር ያቅርብ እንጂ ይህ ክርክር ለሻጭ ጠቃሚ የሚሆነው ገዥው ተከስተ ባለው ጉድለት ሣቢያ የሽያጭ ውል ይፍረስልኝ በሚል ክስ የቀረበበት እንደሆነ ስለመሆኑ በንዐስ ቁጥር 1 ላይ ተመልክቷል። የገዥ የአሁን ተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ ውል ይፍረስልኝ የሚል ሣይሆን ሻጭ ግዳታውን ከኪሣራ ጋር ይፈጽም የሚል ስለሆነ ቀጥተኛ አግባብነት የለውም። ገዥው የሚጠይቀው ዲኝነት አስገድድ ማስፈፀምም ይሁን የውል ይፍረስልኝ ጥያቄ ይህ የሻጭ መከራከሪያ ነጥብ በሁለቱም ዓይነት ዲኝነቶች ያገለግላል እንኳ ቢባል ገዥ የአሁኑ ተጠሪ ንብረቱን በገዛበት ጊዜ በፍ/ቤት በተሰጠ ዕገዲ ምክንያት ሻጩ የእኔ ነው ከሚለ ሦስተኛ ወገኖች መብት ሁለ ነፃ የሆነ መኪና ለገዥው ማስረከብ የማይችል መሆኑን ያውቅ ነበር ወይስ አልነበረም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ተይዞ በሥር ፍ/ቤት በማስረጃ የተረጋገጠ ጉዲይ አይደለም በዚህ ነጥብ ላይ ማስረጃችንም አልታየልንም የሚል የሰበር ክርክርም የለውም። ገዥ ያውቅ ነበር በሚል በአባባል ደረጃ ከመግለጽ አልፍ ይህንን አባባል በማስረጃ አስደግፍ ማስረዲት ይኖርበታል። በመሆኑም በዚህ ሰበር ደረጃም ቢሆን ገዥ ያውቅ ነበር በሚል ብቻ ተወስኖ የቀረበው ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
No topics extracted.
እንዱሁም አመልካች አከራካሪ የሆነው የዕግድ ትእዛዝ በእሷ መዝገብ ላይ ስላልተሰጠ፤
የወረዲው ፍ/ቤትም ስለእግድ ጉዲይ ሲጠየቅ ዕግድ የለም በሚል ስለአረጋገጠ እና ገዥውም ዕገዲ ያለበት መሆኑን አስቀድሞ የማረጋገጥ ግዳታ ነበረበት የሚለትን ነጥቦች በመጠቀስ ኃላፉነት የለብኝም ሲል ያቀረባቸው ክርክሮች ሻጩ የተሸጠው ንብረት ላይ የማያስነካ መብት ለገዥው ለማስተላለፍ አስፈላጊ ተግባሮችን ለመፈፀም ግዳታ ይኖርበታል በሚል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2281 እንዱሁም ውጤቱ የውል ማፍረስን ጉዲይ የሚመለከት ቢሆንም የገዠውን መብት በሚነካ ጉድለት ምክንያት ሻጭ የእኔ ነው ከሚለ ሦስተኛ ወገኖች መብት ሁለ ነፃ የሆነ ነገር ለገዥው የማስረከብ ግዳታ አለበት በሚል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2341 የተጣለበትን ከሕግ የመነጨ ግዳታ ያገናዘቡ ክርክሮች ባለመሆናቸው የሕግ መሰረት የላቸውም።
አከራካሪው መኪና በፍ/ቤት ዕግድ ምክንያት ያለ ሥራ ቆሟል ወይስ በሥራ ላይ ነበረ የሚለውን ጉዲይ አስመልክቶ አመልካች በሰበር ደረጃ የተብራራ ክርክር ያቀረበ ቢሆንም ይህ የፍሬ ነገር ጉዲይ ለሥር ፍ/ቤት በማስረጃ ተደግፍ ሉያጥር የሚችል እንጂ የሕግ ክርክርን የሚያስነሳ ሆኖ አላገኘነውም።
በዚህ ሁለ ምክንያት አመልካች በሸጠው ንብረት ላይ አስቀድሞ በነበረ የፍ/ቤት ዕገዲ ምክንያት በገዥው ላይ ደረሰ ለተባለው የጥቅም መቋረጥ ኃላፉ ነው በሚል በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አልተገኘም።
ሆኖም በዚሁ በሻጭ የግዳታ ጉድለት በገዥው ላይ ደርሷል የተባለውን የጉዲት መጠን በሚመለከት የተሰጠው ውሣኔ በተጓዲኝ ገዥ እንዱህ ያለ ጉዲይ ባጋጠመ ጊዜ እርሱም በተቻለ መጠን ሉደርስ የሚችለውን ለይቶ የመቀነስ ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ ከተመለከተው ድንጋጌ ጋር ተካቶ ላታይ የሚገባው ነጥብ ነው።
በዚህ ጉዲይ የመኪና ሽያጭ ውል የተደረገው ሚያዚያ 28 ቀን 1998 በሕግ ገዥው ጉዲት ደረሰበኝ ካሣ ይከፈለኝ ሲል ክስ ያቀረበው ደግሞ መጋቢት 26 ቀን 1999 ዓ.ም ነው። ጉድለት ያለበት ንብረት ወይም ደግሞ ሙለ የባለቤትነት መብት ለመገልገል የሚያስችል ጉድለት ያለበት ንብረት የተረከበ ገዥ ያለው የማስተካከያ መብት በፍ/ብ/ሕግ ከቁጥር 2336 ቀጥል ባለት ድንጋጌዎች ተቀምጧል። ገዥው ወዱያውኑ ክስ አቅርቦ ውለን ማስፈረስ ወይም ደግሞ ከቁጥር 2329 ጀምሮ ባለት ድንጋጌዎች የተጓደለው ነገር ተሟልቶ ይፈፀም ዘንድ ወዱያውኑ መጠየቅ ከዚህ ጋር ጎን ለጎንም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 236ዐ እንደተመለከተው ከላይ ከተመለከቱት የሕግ መፍትሄዎች በሻጭ ግዳታ መጓደል ምክንያት የደረሰበትን ጉዲት በገንዘብ አስልቶ መጠየቅ እንደሚገባው ተመልክቷል። በዚህ ጉዲይ ገዥው ይህንን በሕግ በተሰጠው መብቱ ሳይገለገል ለአንድ ዓመት ያህል እንደቆዩ መዝገቡ ያስረዲል። ይህንንም ማድረግ መብቱ የሆነውን ያህል ሉደርስ የሚችለውን ጉዲት በመቀነስ ረገድ ከባከነው ጊዜ አንፃር ደግሞ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.18ዐ2 እንደተመለከተው ግዳታው ይሆናል።
ከዚህ አንፃር የደረሰውን የጉዲት ልክ አወሳሰን ከተያዘው ጉዲይ አንፃር በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 179ዐ፤18ዐ2 የተመለከተውን መሰረት በማድረግ ሉወስን ሲገባ ይህንን በገዥው በኩል የታየው የጥንቃቄ ጉድለት ሳይታይ የሽያጩ ውል የተደረገበትንና ዕግደ የተነሣበትን ጊዜ መነሻ በማድረግ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2ዐ91 በተመለከተው ድንጋጌ ብቻ በማየት ውሣኔ መስጠቱ በሥር ፍ/ቤቶች በጉዲት ካሣው አወሳሰን ረገድ ስህተት መፈፀማቸውን ተገንዝበናል።
ው ሣ ኔ 1/ የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት እንደቅደም ተከተለ በመ/ቁ.
ዐ5183 21/6/2ዐዐዐ በመ/ቁ. 64263 በ22/ዐ4/ዐ2 የሰጡትን ውሣኔዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
348/1/ አሻሽለን ወስነናል።
አመልካች በተጠሪ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት አለበት ብለናል።
የተከሰተውን ጉዲት በጊዜው እንዱስተካክል ማድረግ ሲገባ ይህን ካልፈፀመ ከተያዘው ጉዲይ አንፃር ጊዜ በረዘመ ቁጥር የጉዲቱ ስላት በዚሁ ልክ እያደገ እንደሚሄድ ማወቅ ሲገባው ይህንን ሣያደርግ ያሳየውን የጥንቃቄ ጉድለት ሁለ በማየት ለደረሰበት የጉዲት ልክ በርትዕ ብር 21,ዐዐዐ.ዐዐ /ሃያ አንድ ሺህ/ ብር ይከፈለው ብለናል።
በሥር ፍ/ቤት የተወሰነው ወጭና ኪሣራ ስላቱ መሰረት ይኸው የጉዲት ገንዘብ ይሁን፤
በዚህ ችልት የተደረገው ክርክር ስለተሰጠው ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ መዝገቡ ተዘግቷል።