No summary available.
ኀዲር 2 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ሻገረ ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የአ/አ ከተማ አስተዲደር ዋና ኦዱተር መ/ቤት ነ/ፈጅ ማህላት ዲዊት ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1ኛ. አቶ ኤሣው መዓዛ 2ኛ. አቶ ዘርሁን ሙላት ጠ/መስፍን ደምሴ ጋር ቀረቡ 3ኛ. ወ/ሮ ተስፊነሽ ተሰማ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የዋስትና ግዳታን የሚመለከት ነው። ለዚህ ክርክር መነሻ የሆነው ክስ የቀረበው በአመልካች በኩል ነው። የክሱ ይዘት ባጭሩ ሲታይ 1ኛ ተጠሪ የአመልካች ሰራተኛ ሁኖ ለ7 ዓመታት ያህል ትምህርት እንዱከታተል እና ትምህርቱን ሲያጠናቅቅ ለ6 ዓመት ያህል ለማገልገል ግዳታ ገብቶ ለ5 ዓመታት ያሕል ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ትምህርቱንና ሥራውን ስላቋረጠ ለትምህርት የወጣውን ወጪ እንዱተካ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች (ተጠሪዎችም) ለዚሁ ውል አፈፃፀም እስከ ብር 50,000 ድረስ የዋስትና ግዳታ የገቡ ስለሆነ ክስ የቀረበበትን ብር 29,497.03 ባልተነጣጠለ ሃላፉነት እንዱከፍለ እንዱወሰን ዲኝነት ጠይቋል።
የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ የመረመረው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት 1ኛ ተከሳሽ(ተጠሪ) ክስ የቀረበበትን ገንዘብ እንዱከፍል ሲወስን፣2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የዋስትና ግዳታ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1925/2/ መሰረት አስቀድመው አስቀርተዋል በሚል ከክሱ በነፃ እንዱሰናበቱ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝቶ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካራከረ በኋላ የሥር ፍ/ቤትን ውሳኔ በፍርድ አጽንቷል።
ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ የሥር ፍ/ቤቶች የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1925/2/ የሰጡት ትርጉም መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ነው በማለት እንዱታረም ጠይቋል።
የሰበር ችልቱም አቤቱታውን መርምሮ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1925/2/ መሰረት ከዋስትና ግዳታቸው ነፃ ናቸው ተብል መወሰኑ በአግባቡ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ አዝዟል።
የ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጠበቃ የካቲት 29 ቀን 2002 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርቧል።
በይዘቱም ተጠሪዎች የገቡት ግዳታ ወደፉት ይደርሳል ተብል ለሚታሰብ ሁኔታ ስለመሆኑ ጠቅሶ ይህ ሃላፉነት ከመድረሱ በፉት የዋስትና ግዳታቸውን ማውረዲቸው በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1925/2/ የሚሸፈን ስለመሆኑ በመግለጽ በዝርዝር ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ከፍ ሲል የተመለከተው ሲሆን እኛም ጉዲዩን ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
የዚህ ሰበር ችልት ውሳኔ የሚያሳየው ነጥብ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የዋስትና ግዳታ አውርደዋል ተብል የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 125/2/ ተጠቅሶ የተሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ነው ወይንስ አይደለም? የሚለው ነው።
ከግራ ቀኙ ክርክር ላይ እንደተረዲነው 1ኛ ተጠሪ በአመልካች እስፕንሰርንት ከፍተኛ ትምህርት ተከታትል አጠናቆ ሲመለስ ለ6 ዓመት ለማገልገል፣ ይህንን ካልፈፀመ ደግሞ አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ ያወጣውን የትምህርት ወጪዎች ሉተካ የውል ግዳታ የገባ ስለመሆኑ ተረጋግጧል።
2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎችም 1ኛ ተጠሪ በውል የገባውን ግዳታ ካልፈፀመ እስከ ብር ሃምሣ ሺህ ባልተነጣጠለ ኃላፉነት ለመክፈል የዋስትና ግዳታ መፈረማቸውም አላከራከረም።
በዚሁ አግባብ አመልካች ይህንኑ ውለታ መነሻ በማድረግ 1ኛ ተጠሪ እንደውለ ግዳታውን ባለመፈፀሙ ተጠሪዎች በአንድነትና በነጠላ ብር 29,497.03 እንዱከፍለ እንዱወሰን ዲኝነት በመጠየቁ የሥር ፍ/ቤትም 1ኛ ተጠሪን ሃላፉ በማድረግ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ እንዱከፍል ወስኗል።
በልላ በኩል 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የዋስትና ግዳታ ውል የገቡ ቢሆንም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1925/2/ መሰረት የዋስትና ግዳታቸውን አስቀድመው አውርደዋል በሚል ከክሱ በነፃ አሰናብቷቸዋል።
የሥር ፍ/ቤት ለውሳኔው ምርኩዝ ያደረገው የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1925/2/ ወደፉት ስለሚሆን ወይም በአንድ ዓይነት ሁኔታ ስለሚመጣ ግዳታ ዋስ ስለመሆን አስመልክቶ የዋስትና ግዳታው ለስንት ጊዜ እንደሚረጋ በስምምነቱ ያልተመለከተ እንደሆነ የዋናው እዲ ተጠያቂነት ከመድረሱ በፉት ዋሱ ዋስትናውን ሉያስቀር እንደሚችል ያመለክታል።
No topics extracted.
ከዚህ ድንጋጌ ይዘት መረዲት የሚቻለው ዋናው ግዳታ ወደፉት ሉደርስ ወይም ላይደርስ በሚችል ሁኔታ ላይ (uncertain event) የተመሰረተ በሆነ ጊዜ ዋሱ ዋናው ግዳታ ከመድረሱ በፉት የዋስትና ግዳታውን ማስቀረት የሚችልበት አግባብ ስለመኖሩ ነው።
የዚህ ድንጋጌ መንፈስ ዋናው ግዳታ በሁኔታ ላይ የተመሰረተ መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ሉፈጸም የሚችል ስለመሆኑ ከይዘቱ መረዲት ይቻላል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ የአመልካች ግዳታ 1ኛ ተጠሪ ከሥራ ውጪ ሆኖ ትምህርት እንዱከታተል መፍቀድ እና ለትምህርቱም አስፈላጊውን ወጪ መሸፈን ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ደግሞ ትምህርቱን ተከታትል እንዲጠናቀቀ በውለ ለተመለከተው ጊዜ ያሕል ለአመልካች አግልግልት መስጠት አሉያም ለትምህርት የወጣውን ወጪ መተካት ስለመሆኑ ከግራ ቀኙ ክርክር መረዲት ተችሎል። ይህ ከሆነ ደግሞ የዋናው ውል ግዳታ ወደፉት በሚደርስ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ እርግጠኛ ያልሆነ (uncertain event) ሁኔታ ላይ የተንጠለጠለ ነው ተብል በፍ/ብ/ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 1925 ሥር የሚሸፈን አለመሆኑን መረዲት ይቻላል።
በአመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገው ዋና ግዳታ ወደፉት ሉደረስ ወይም ላይደርስ የሚችል ሁኔታ (conditional) ነው የማይሰኝ ነው ከተባለ ደግሞ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የዋስትና ግዳታ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1925/2/ መሰረት የዋናው ግዳታ ተጠያቂነት ከመድረሱ በፉት አስቀርተዋል ተብል ተቀባይነት ሉያገኝ አይችልም።
ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቶች 2ኛ ና 3ኛ ተጠሪዎች የዋስትና ግዳታ የ1ኛ ተጠሪ ግዳታ ከመድረሱ በፉት ቀሪ ሆኗል በሚል ምክንያት ተጠሪዎች አላፉነት የለባቸውም ሲል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1925/2/ በመጥቀስ የሰጠው ፍርድ የድንጋጌውን ይዘትና መንፈስ በአግባቡ ያላገናዘበና የግራ ቀኙን የውል ግዳታ በውል ያላመነ ስለሆነ ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል።
ስለሆነም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 110168 በ01/09/2000 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ እና በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 70425 በ16/10/2000 ዓ.ም የተሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በገቡት የዋስትና ግዳታ ውል መሰረት ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ባልተነጣጠለ ኃላፉነት ለአመልካች የመክፈል ግዳታ አለባቸው ብለናል።
የሥር ፍ/ቤት በዚሁ መሰረት ያስፈጽም። ይፃፍ።