No summary available.
ህዲር 30 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ቄስ ገ/ሚካኤል አለምነው - ጠበቃ ታደሰ ወ/ጊዮርጊስ ቀረበ ተጠሪ፡- ወ/ሮ መልኬ ደምሴ ቀረበች መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ከሕግ ውጪ የተያዘብኝ ቤት ይለቀቅልኝ በማለት ተጠሪ በአመልካች ላይ በመሰረተችው ክስ መነሻነት የተደረገውን ክርክር የሚመለከት ነው። በተጠሪ ክስ እንደተገለጸው አመልካች ቤቱን አለቅም ያለው ከተጠሪ አውራሽ ላይ በውል ገዝቼ ነው የያዝኩት በማለት ነው።
ተጠሪ ይህን ሁኔታ በማወቅዋም ውለ በሕጉ የተመለከተውን መስፈርት /ፍርማሉቲ/ አሟልቶ የተደረገ አይደለም የሚል የመከራከሪያ ነጥብ በክስዋ አንስታለች። በመጨረሻም የጠየቀችው ዲኝነትም ውለ በሕግ ውጤት የለውም እንዱባል እና አመልካችም ቤቱን እንዱያስረክቧት ነው።
አመልካች ደግሞ ለክሱ በሰጠው መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የስረነገር የመከራከሪያ ነጥቦችን አንስቶአል። ከመቃወሚያዎቹ አንደ ክሱ በፍ/ብ/ሕግ ቁ.1000 መሰረት በይርጋ ቀሪ ሆኖአል የሚል ሆኖ ሥረ ነገርን በሚመለከትም ውለ የሚፈርስበት ምክንያት የለም። የገዛሁት ጅምር ቤት ስለነበር በእንጨት ተሰርቶ የነበረውን ጅምር በማፍረስ ህንፃ ሰርቻለሁ። እንደከሳሽ ጥያቄ ቤቱን አስረክብ ብባል የማስረክበው የገዛሁትን ሳይሆን በራሴ ገንዘብ የሰራሁትን ህንፃ ነው የሚለትን መከራከሪያዎች አቅርቦአል። ይህን የመሰለ ክርክር የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአንድ በኩል ለይርጋ መቃወሚያው አግባብነት አለው ተብል የተጠቀሰው የፍ/ብ/ሕግ ቁ.
1000 በወራሾች መካከል ለሚነሳ ክርክር ነው አግባባነት የሚኖረው በማለት በልላ በኩል ደግሞ የሺያጭ ውለ በተደረገበት እና ክሱ በቀረበበት መካከል ያለው ጊዜ ሰባት ዓመት በመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1845 ከተቀመጠው የጊዜ ወሰን አንፃር ሲታይ ይርጋው አላለፈም የሚል ምክንያት በመስጠት የአመልካችን የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ አድርጎታል። በሥረ ነገር ረገድ የቀረበው ክርክር የሽያጭ ውለ በፍ/ሕ/ቁ. 1723 የተመለከተውን መስፈርት ወይም /ፍርም/ አያሟላም የሚል ምክንያት በመስጠት ብቻ ውድቅ አድርጏታል። በእርግጥ አመልካች በቤቱ ላይ ወጪ አድርጌአለሁ ካለ ወጪው እንዱመለስለት ስለ አላግባብ መበልፀግ በሚመለከቱት የሕግ ድንጋጌዎች መሰረት የመጠየቅ መብቱ ተጠብቆአል የሚል ትችት በውሳኔው መጨረሻ ላይ አስፍሮአል። በመጨረሻም በክሱ የተመለከተውን ቤት አመልካች ለተጠሪ እንዱያስረክብ ወስኖአል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሳኔውን አጽንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ሐምል 17 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተደረገው አመልካች የገዛሁትን ጅምር ቤት በመገንባት ህንፃ ሰርቻለሁ በማለት ያቀረበው ክርክር እና ማስረጃ የመታለፈ አግባባነት ሉመረመር ይገባል በመባለ ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
እንደምንመለከተው ክርክሩ የተነሳው በወራሾች መካከል ባለመሆኑ እና ክሱም የቀረበው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 የተመለከተውን የይርጋ ወሰን ከማለፈ በፉት ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ረገድ በመረጋገጡ አመልካች ያቀረበው የይርጋ መቃወሚያ በሥር ፍ/ቤቶች ውድቅ የተደረገው በአግባቡ ነው። ወደ ጉዲዩ ሥረ ነገር ስንመጣ ተጠሪ ቤቱን ልረከብ የምትለው የቤት ሺያጭ ውለ ሕጋዊ አይደለም ወይም የተደረገው ከሕግ ውጪ ነው በማለት እንደሆነ ነው የምንገነዘበው። ውለ ውጤት የለውም ለማለት የሰጠችው ምክንያትም በፍ/ብ/ሕግ ቁ.1723 የተመለከተውን የውል አጻጻፍ ፍርም አያሟላም በማለት ነው። በፍትሐብሕር ሕጉ አራተኛ መጽሐፍ አንቀጽ 12 በምዕራፍ 3 ሥር ስለግዳታዎች መቅረት በሚመለከት ዝርዝር ድንጋጌዎች ተቀምጠዋል። የዚህ ምዕራፍ ክፍል 1‘ም’ ውልችን ስለመሰረዝና ስለማፍረስ በሚል የተደነገገ ሲሆን በዚህ መዝገብ ለያዝነው ጉዲይ አወሳሰን ተገቢነት ያለው በዚህ ክፍል ሥር ከተካተቱት ድንጋጌዎች አንደ የሆነው በቁጥር 1808 የተመለከተው ድንጋጌ እንደሆነም እንገነዘባለን። በዚህ ድንጋጌ ንኡስ ቁ(2) እንደተመለከተው ውለ ለውለ አጻጻፍ የተደነገገውን ፍርም አልጠበቀም የሚል መከራከሪያ ያለው ተዋዋይ ወገን ወይም ማንኛውም ከውለ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ጥቅም ያለው ሰው ውለ እንዱሰረዝ ለመጠየቅ ይችላል።
በያዝነው ጉዲይ በእርግጥ ተጠሪ ውለ ይሰረዝልኝ የሚል ክስ ባትመሰርትም የውለን መኖር ተገንዝባ ለውለ አጻጻፍ የተደነገገውን ፍርም አልጠበቀም የሚል መከራከሪያ አንስታለች።
No topics extracted.
አመልካች ደግሞ ውለ ሳይነካ በራሴ ጥረት እና ገንዘብ የሰራሁትን ቤት ይዤ መቅረት አለብኝ በማለት ተከራክሮአል። በዚህ ምክንያትም አመልካች ቤቱን ለተጠሪ ሉያስረክብ ይገባል ወይስ አይገባም በሚለው ነጥብ ላይ ውሳኔ ከመስጠት በፉት ውለ የሚሰረዝ ነው ወይስ አይደለም?
በሚለው ጭብጥ ላይ ውሳኔ መስጠት አግባብ ይሆናል። በዚህ አካሄድ በመጨረሻ ውለ ይሰረዛል የሚባል ቢሆን እንኳ አመልካች ቤቱን አስረክበህ ሂድ የሚባልበት አግባብ ይኖራል ማለት አይደለም። በፍ/ብ/ሕግ/ቁ 1815 (1) እንደተደነገገው ውል ሲሰረዝ ወይም ሲፈርስ ተዋዋዮቹ በተቻለ መጠን ውለ ከመደረጉ በፉት እንደነበሩት ሁኔታ እንዱመለሱ የግድ ነው። በዚህ መንገድ መፈፀም ካልተቻለም በፍ/ብ/ሕግ ቁ1817 የተመለከተውን ደንብ መከተል እንደሚገባ ሕጉ ያመለክታል።
ጉዲዮን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የፋዳራል መጀመያ ደረጃ ፍ/ቤትም ሆነ ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍ/ቤት ከጅምሩ ውል እንደላለ በመቁጠራቸው የውልን መፍረስ ወይም መሰረዝ ተከትል ስለሚኖረው ውጤት በተመለከተ ውሳኔ ሉሰጡ አልቻለም ተጠሪ ልረከብ የምትለው ቤት እኔ የሰራሁት ነው የሚለው የአመልካችን ክርክር በጭብጥነት ይዘው በማስረጃ ሳያጣሩ ያለፈትም በዚህ ምክንያት ነው የሚመስለው። እንደ ሕጉ ከሆነ ግን ክርክሩ የውል መፍረስ ወይም መሰረዝንም የሚመለከት በመሆኑ ቀጥል ስለሚመጣው ውጤት በተመለከተ ተገቢውን መወሰን ይቻል ዘንድ በእርግጥ ቤቱ አመልካቹ የሰራው ነው? ቤቱ በጅምር የነበረ ነው ከተባለስ አመልካች ምን ያህለን ሰራ፣ ወዘተ የሚለትን ነጥቦች አስቀድሞ በማስረጃ ማንጠር አስፈላጊ ነው የሚሆነው። ይህ ሁኔታ በሕጉ አግባብ ውል ይፈርሳል ወይም ይሰረዛል የሚል ውሳኔ ቢሰጥ ሉከተል ስለሚገባው ውጤት ወሳኝ ሚና የሚኖረው የፍሬ ነገር ጉዲይ ነው። የሥር ፍ/ቤቶች ክርክሩን በዚህ አግባብ አልመሩም።
በመሆኑም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ በሕጉ አተገባበር /አተረጓጏም/ ረገድ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።