No summary available.
ጥቅምት 29 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች - የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ነ/ፈጅ ወንድወሰን ጥሩነህ ቀረቡተጠሪዎች - እነ አቶ ዲንኤል ካሣ /ሃያ ሁለት ሰዎች/ - ቀረቡ
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የኪራይ ውል ይሞላልን ጥያቄን መሰረት ያደረገ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኑ ተጠሪዎች በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአሁኑ አመልካች ላይ የካቲት 27 ቀን 1999 ዓ.ም በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- አመልካች የሚያስተዲድራቸውን የመንግስት ቤቶች ያለውል በቁልፍ ሽያጭ ወይም በውክልና በመያዝ ከሶስት እስከ አስር አመት ድረስ በቤቶቹ ቤተሰብ አፍርተው እየኖሩ እንደሚገኙ የኪራይ ቤቶች አስተዲደር የስራ አመራር ቦርድ 94ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በተጠሪዎች ሁኔታ የሚኖሩ ግለሰቦች ሕጋዊ ተከራይ እንዱሆኑ ውሣኔ ማሳለፈን፣ የተጠሪዎች ሁኔታ ውሣኔ ያረፈበት በመሆኑ የኪራይ ውል አመልካች እንዱያስሞላቸው ቢጠይቁ ከሰባት መቶ ሁለት ሰዎች ዝርዝር ውስጥ የላላችሁ በመሆኑ ውል አላስሞላችሁም በማለት የመለሳቸው መሆኑን ተጠሪዎች ከእነዚህ ሰባት መቶ ሁለት ከተባለ ግለሰቦች ጋር ሲመዘገቡ አቅርቡ የተባለትን ማስረጃ ሲያቀርቡ ቆይተው በአመልካች ድርጅት አስተዲደራዊ ችግር ባለመመዝገባቸው ሁለንም ዜጋ እኩል ያላስተናገደና ተጠሪዎችን የጎዲ መሆኑንና የአመልካች ድርጅት ድርጊት ኢፍትሐዊና አድል ያለበት በመሆኑ ሉታረም እንደሚገባው ገልፀው ጥቅምት 03 ቀን 1998 ዓ.ም በተሰጠው ውሣኔ መሰረት ተጠቃሚ መሆናቸው እንዱረጋገጥ በኤጀንሲው የስራ ኃላፉዎች በኩል የተከሰተው አፈፃፀም ችግር የተጠሪዎችን በሕግ ፉት በእኩል የመታየት ሕገ መንግስታዊ መብት የጣሰና የመልካም አስተዲደር መርህን ያልተከተለ አሰራር ነው ተብል በአመልካች ቤቶች ላይ ሕጋዊ ውል እንዲይሞለ የተደረገው ክልከላ ተነስቶ በቦርደ ውሣኔ መሰረት ሕጋዊ ውለ እንዱሞላ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም ተጠሪዎች በአመልካች ላይ ክስ ለመመስረት የሚያስችላቸው ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ መብት የላላቸው መሆኑን ተጠሪዎች ሰባት መቶ ሁለት ሰዎች በመባል ውል እንዱሞለ ከተፈቀደላቸው ሰዎች መሐል ስማቸው እንደማይገኝ በተደረገው 105ኛ ስብሰባ በኤጀንሲው ሰባት መቶ ሁለት ሰዎች በመባል ከሚታወቁት ባለጉዲዩች በቀር ሉስተናገደ እንደማይገባ በመወሰኑ የተጠሪዎችን ጉዲይ ማስተናገድ እንደማይቻል፣ ተጠሪዎች ከፉለ ከመጋቢት 04 ቀን 1997 ዓ.ም በፉት ጉዲያቸው ውሣኔ ያገኘ በመሆኑ 94ኛ ስብሰባ በተደረገው ውሣኔ መሰረት ሉስተናገደ የማይገባ ከፉለ ደግሞ ውዝፍ ኪራይ ባለመክፈላቸው ምክንያት ውሣኔ ያገኘ በመሆኑ በአንድነት ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት እንደላለው እንዱሁም ውል አመልካች ሉዋዋል የሚችለው በሙለ ፍላጎት እንጂ ተገድ አለመሆኑን በመዘርዘር ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል።
የስር ፍ/ቤት የግራቀኙን ክርክር እና ማስረጃ በመመርመር የአመልካችን ክርክር በከፉል ውድቅ አድርጏ የአሁኑ ተጠሪዎች ጥቅምት 03 በቀን 1998 ዓ.ም በተሰጠው ውሣኔ መሰረት ተጠቃሚዎች በመሆናቸው በውሣኔው መሰረት ተጠቃሚ እንዱሆኑ ሲል ወስኗል በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነገረፈጅ ታህሣሥ 03 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈት ሶስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ጉዲዩ ተመርምሮም አመልካች ከተጠሪዎች ጋር የኪራይ ውል ማድረግ አለበት ወይስ የለበትም? የሚለው ነጥብ በፍርድ ሉያልቅ የሚችል ጉዲይ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎአል። የግራቀኙ የቃል ክርክርም ጥቅምት 23 ቀን 2002 ዓ.ም ተሰምቷል።
የክርክሩ አመጣጥ ከላይ ባጭሩ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የተጠሪዎች የዲኝነት ጥያቄ አመልካች በቤቶቹ ላይ ውል አስሞልቷቸው የተከራይነት መብት እንዱረጋገጥላቸው ሲሆን ለጥያቄው መሰረት ያደረጉትም የአመልካች ቦርድ ውሣኔ ተጠቃሚ የሚያደርጋቸው መሆኑን አመልካች ከተጠሪዎች ጋር ተመሳሳይ ሁኔታ ያላቸውን ላልች በርካታ ሰዎችን የኪራይ ውል እንዱሞለ ሲያደርግ ተጠሪዎሪችን በሕገ መንግስቱ የተጠበቀላቸውን የእኩልነት መብት ግንዛቤ ውስጥ ባላስገባ መልኩ አድል ፈጥሯል የሚለትን ምክንያቶችን መሆኑን ነው። አመልካች በበኩለ ተጠሪዎች ተመሳሳይ ሁኔታ ያላቸው ሰዎች የኪራይ ውል እንዱሞለ ተደርጓል የሚለት ለተጠሪዎች መብት የማይሰጥ መሆኑንና የቀድሞው የቦርድ ውሣኔ በልላ ውሣኔ መተካቱን እንዱሁም የኪራይ ውል መደረግ ያለበት በተዋዋይ ወገኖች ሙለ ፈቃድ እንጂ በግዳታ አለመሆኑን ጠቅሶ የተጠሪዎች የዲኝነት ጥያቄ የህግ ወይም የውል መሰረት የለውም በማለት መከራከሩን ተገንዝበናል።
በመሰረቱ በፋዳራልም ሆነ በክልል የዲኝነት ስልጣን የፍ/ቤቶች ብቻ ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 79/1/ ተደንግጓል የሕገመንግስቱ አንቀጽ 37 ድንጋጌ ሲታይ ደግሞ ፍ/ቤቶች በማናቸውም ጉዲይ ገደብ የለሽ ስልጣን የላላቸው መሆኑን ተመልክቷል። በዚህም መሰረት የሕገመንግስቱ አንቀጽ 79/1/ እና 37 አንድ ላይ ሲታዩ ፍ/ቤቶች አንድን ጉዲይ ተቀብለው ለማየትና ለመወሰን ሥልጣን የሚኖራቸው ጉዲዩ በፍርድ ሉወሰን የሚገባው /Justiciable matter/ ሆኖ ከተገኘ ብቻ መሆኑን ያስገነዝባለ። የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 37 ድንጋጌ ንዐስ ቁጥር 1 ‛ማንኛውም ሰው በፍርድ ሉወሰን የሚገባውን ጉዲይ ለፍርድ ቤት ወይም ለላላ በህግ የዲኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሣኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት አለው።“ በሚል ከተደነገገው ‛..... ወይም ለላላ በህግ የዲኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል…“ የሚለው፤ እንዱሁም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 4 በልላ አኳኋን እንዱፈፀም በህግ ካልተገለፀ፤ ክሱን ተቀብል ለማከራከር ሥልጣን ያለው ፍ/ቤት ብቻ ነው በሚል መደንገጉ በፍርድ ሉወሰን በሚችለው ጉዲይ ፍ/ቤቶች ብቸኛ ስልጣን የላላቸው መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው። በመሆኑም ፍ/ቤቶች አንድን ጉዲይ ተቀብለው ማየት የሚችለት ጉዲዩ በፍርድ የሚያልቅ ሲሆንና በልላ አኳኋን እንዱታይ በሕግ እስካልተወሰነ ጊዜ ድረስ ብቻ ነው። ጉዲዩ በፍርድ ሉያልቅ የሚችል ነው ልባል የሚችለው ደግሞ የክርክሩ መሰረት በሕግ ጥበቃ ያገኘ መብት ወይም ግዳታ ሲሆን ወይም ለመብቱ ወይም ግዳታው መሰረት የሚሆን ውል መኖሩ ሲረጋገጥ ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ተጠሪዎች ከአመልካች ጋር የመሰረቱት ሕጋዊ ውል የላላቸው መሆኑን ራሳቸው ክሱን ሲመሰርቱም ቢሆን አረጋግጠው የቀረቡት ጉዲይ ሲሆን አመልካች የሚያስተዲድረውን ቤት የኪራይ ውለ ከተጠሪዎች ጋር እንዱገባ ይደረግላቸው ዘንድ ዲኝነት የሚጠይቁት አመልካች ከተጠሪዎች ጋር ተመሳሳይ ሁኔታ ያላቸውን ሰዎች ኪራይ እንዱሞለ በቦርድ ተወስኖ በቁጥር ሰባት መቶ የሆኑት ሰዎች የውሣኔው ተጠቃሚ ሲሆኑ ተጠሪዎች ላይ አድል በመፈፀም በቦርደ ውሣኔ ተጠቃሚ እንዲይሆኑ ማድረጉ ከመንግስት መስሪያ ቤት የማይጠበቅ ነው በሚል ነው።
በመሰረቱ አመልካች የራሱ የሆነ ሕጋዊ ስልጣን ያለው፣ የመንግስት ቤቶችን የማስተዲደር ኃላፉነት የተሰጠው ሲሆን እንደማንኛውም ባለሃብት ቤቶቹን ለፈለገው ሰው የማከራየት ሕጋዊ መብት ያለው አካል መሆኑ የሚያከራክር አይደለም። ከዚህም በተጨማሪ የራሱን ሥርዓት በመዘርጋት የሚያስተዲድራቸውን ቤቶች ለሕብረተሰቡ በተከራይነት እንዱጠቀሙ የሚያደርግ መሆኑ ይታመናል። ኪራይ ደግሞ ውል ከሚባለት ሕጋዊ ተግባራት አንደ ሲሆን በሕግ ጥበቃ የሚደረግለት የኪራይ ውል የውል አመሰራረት መሰረታዊ ነጥቦችን አሟልቶ መገኘትን የግድ ይላል። ለውል አመሰራረት መሰረታዊ ነጥቦች ናቸው ከሚባለት መካከል ደግሞ አንደ የመዋዋል ነፃነት /Freedom of contract/ ነው። የመዋዋል ነፃነት ሲባልም ተዋዋይ ወገኖች በሙለ ፈቃዲቸውና ፍላጎታቸው ውል የማድረግ መብት ያላቸው መሆኑን የሚያሳይ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው ሕግ ጥበቃ የሚያደርገው በሕጉ አግባብ የተመሰረተን ውል እንጂ ከመነሻው ተዋዋይ ወገኖች በግድ በውል ግዳታ ውስጥ እንዱገቡ ማድረግን አለመሆኑን ነው።
የተጠሪዎች ጥያቄ ሲታይም በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 25፣ 41፣ 89 እና 90 ድንጋጌዎች ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች መንፈስ የሚጠቅስ ቢሆንም አመልካች በሕጉ ከተሰጠው ሥልጣን እና ተግባር እንዱሁም ከውለ አመሰራረት መሰረተ ሃሳቦች አንፃር ሲታይ የተጠሪዎች የእኩልነት እና መጠለያ የማግኘት መብት ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የተያያዘ ነው ልባል የሚችል አይደለም። ከሁለም በላይ ከተጠሪዎች ጋር ተመሳሳይ ሁኔታ ያላቸውን ሰዎች የኪራይ ተጠቃሚነት ወሰነ የተባለው የአመልካች መስሪያ ቤት የስራ አመራር ቦርድ የተጠሪዎች ጥያቄ ከሰባት መቶ ሰዎች ጋር ተመሳሳይ አለመሆኑን በ105ኛው መደበኛ ስብሰባ አረጋግጦ የወሰነ ሲሆን ተጠሪዎች ጉዲዩ ተመሳሳይ ነው፣ ወይም ተመሳሳይ እንዲይሆን በአመልካች የአስተዲደር ችግር ተፈጥሯል የሚለ ከሆነም ጥያቄውን ማቅረብና መስተናገድ ያለባቸው በፍርድ ቤት ክስ በመመስረት ላሆን አይችልም። በመሆኑም የተጠሪዎች ጥያቄ በሕግ አግባብ የተቋቋመ የኪራይ ውል አፈፃፀም ጋር የተገናኘ ባለመሆኑ አመልካች ከተጠሪዎች ጋር በፍርድ ኃይል የኪራይ ውል እንዱዋዋል የሚደረግበት ሕጋዊ ምክንያት የላለ ሲሆን ጉዲዩ በፍርድ ሉያልቅ የማይችል ሆኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች ክሱን በመቀበል ውሣኔ መስጠታቸው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል ው ሣ ኔ
በፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሕዲር 03 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 25 ቀን 2001 ዓ.ም የጸናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት በድምፅ ብልጫ ተሽሯል።
ተጠሪዎች ከአመልካች ጋር ያቋቁሙት ሕጋዊ የኪራይ ውል በላለበት ሁኔታ አመልካች ከተጠሪዎች ጋር የኪራይ ውል ለማድረግ በፍርድ ኃይል የሚገደድበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.