No summary available.
ጥቅምት 1 ቀን 2003 ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጰያ ልማት ባንክ - ነ/ፈጅ አክሉለ ተስፊዬ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ተክላ ዋከኔ -- ዋከኔ ቶላ - ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር የመያዣ ውል የሚመለከት ነው። ለዚህ ክርክር መነሻ የሆነው ክስ የቀረበው በተጠሪ ነው። የክሱ ምክንያት በአበዲሪ /አመልካች/ እና ተበዲሪ በአቶ ሽፈራው ቡል መካከል በ24/12/1987 ዓ.ም በተደረገ የብድር ውል የቤት ቁጥር 870 የሆነውን መኖሪያ ቤት ለብድር አከፊፈል ዋስትና መያዣ ያደረገ መሆኑን ጠቅሶ የብድር ውለም ሆነ የመያዣ ውለ ሳይታደስ አሥራ ሦስት /13/ ዓመት ስለሆነ የመያዣ ውለ በፍ/ብ/ሕግ/ ቁጥር 3058 መሰረት ቀሪ ሆኖ አመልካች የያዘውን የቤቱን ካርታና ፔላን እንዱመልስ እንዱወሰን የሚል ነበር።
አመልካች ሥር ፍ/ቤት ያቀረበው ክርክር ታህሳስ 19 ቀን 1988 የተፈረመው የመያዣ ውል ጥቅምት 9 ቀን 1998 ዓ.ም ለነቀምቴ ከተማ አስተዲደር በተፃፈ ደብዲቤ ለቀጣይ 10 ዓመት እንዱታደስ የተደረገ መሆኑን ጠቅሶ ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ጠይቋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የዲኝነት ሥልጣን ያከራከረው የምሥራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ስለ ውለ መታደስ ከማዘጋጃው መግለጫ ከጠየቀ በኋላ ውለ የታደሰው ከሳሹ /ተጠሪ/ በላለበት ነው በማለት ይህ የዋሱን ሃላፉነት የሚለወጠው ያለእሱ እውቅና የተደረገ ነው በሚል የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1928/2/ን በመጥቀስ የመያዣ ውለ እንደታደሰ አይቆጠርም በማለት የመያዣ ውለ ሳይታደስ 1ዐ/አሥር/ ዓመት አልፍበታል በሚል ተጠሪ የዋስትና ሃላፉነት የለበትም ሲል ፈርዶል።
አመልካች በውሳኔው ቅር ተሰኝቶ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኙን ሰርዞታል።
ለዚህ ሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው። የአመልካች ነ/ፈጅ ለሰበር የቀረበው አቤቱታ ይዘት ባጭሩ አመልካች ለሰጠው ብድር ተጠሪ መያዣ መስጠቱን፣ የመያዣ ውል ከሰው ዋስትና የተለየ መሆኑን የሥር ፍ/ቤቶች ባለመገንዘብ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1928/2/ን ጠቅሰው መወሰናቸው ስሕተት ስለመሆኑ እና የመያዣ ውለ የተጠሪን ስምምነት ሳይጠይቅ ሉታደስ መቻለን የፍ/ብ/ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 3058/2/ ድንጋጌ ባለማገናዘብ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት እንዱሻር አመልክተዋል። የሰበር ችልት አቤቱታውን መርምሮ የተጠሪን ስምምነት ሳያገኝ ውለ መታደሱ ተቀባይነት የለውም ሲለ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ በአግባቡ ስለመሆኑ ለመመርመር ሲባል ተጠሪ እንዱቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ተጠሪም ግንቦት 11 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በዋለው ችልት ቀርበው ክርክራቸውን አሰምተዋል።
የክርክራቸው ይዘትም ማዘጋጃ ቤቱ የመያዣ ውለን አላደሰም የሚልና ቀርበው ስምምነት ያልሰጡ መሆኑን ጠቅሰው የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱፀና ጠይቀዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ከፍ ሲል በአጭሩ የተመለከትነው ሆኖ እኛም ጉዲዩን ከሕጉ አገናዝበን መርምረናል። በዚህ ሰበር ችልት ውሳኔ የሚያስፈልገው ጭብጥ የመያዣ ውልን ለማደስ የተጠሪው ስምምነት አስፈላጊ ነው ወይስ አይደለም; የሚለው ነው።ከመዝገቡ መረዲት እንደቻለው አመልካች ለአቶ ሽፈራው ቡል ለሰጠው ብድር ተጠሪ በነቀምት ከተማ ቀበላ 04 ክልል የሚገኘው ቁጥሩ 870 የሆነ መኖሪያ ቤቱን በዋስትና መያዣ መስጠቱን አላከራከረም።
የመያዣ ውለም በክፍለ አስተዲደር ተመዝግቦ የቆየ ስለመሆኑ ተረጋግጧል። የመያዣ ውል ተመዝግቦ ካለ ለቀጣይ አሥር ዓመት ያህል ሕጋዊ ውጤት የሚኖረው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 3058/1/ ድንጋጌ ያመለክታል። ይህ ጊዜ ከማለፊ በፉት ለተጨማሪ ጊዜ ውጤት እንዱኖረው ለማድረግ ውለን ማደስ አስፈላጊ እንደሆነም የፍ/ብ/ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 3058/2/ ይጠቅሳል።
በተያዘው ጉዲይ የመያዣ ውለ እንዱታደስ የአሥር ዓመት ጊዜ ከማለፊ በፉት አመልካች ለክፍለ መሬት አስተዲደር /ማዘጋጃ ቤት/ በደብዲቤ ያሳወቀ ስለመሆኑ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው። የሥር ፍ/ቤት ይህንን ፍሬ ነገር ካረጋገጠ በኋላ የመያዥ ውለ እንዱታደስ የአስያዡ ፈቃድ አልተገለፀም በሚል ምክንያት መያዣ ውለ እንደታደሰ አይቆጠርም በማለት ውለን ውጤት አልባ ማድረጉን ተረድተናል።
የመያዣ ውል ከተመዘገበ ይህው ውል እንዱታደስ ጥያቄ የሚቀርበው በመያዣ ውለ መብት ተጠቃሚ በሆነው ወገን መሆኑን መረዲት አዲጋች አይደለም። የፍ/ብ/ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 3058/2/ መንፈስ መረዲት የሚቻለውም ይኸው ሀሳብ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ይበልጥ ግልፅ የሚሆነው የመያዣ ውል ከመዝገብ ሉሰረዝ የሚቻልባቸው ሁኔታዎች እና የሥልጣኑን ጉዲይ አስመልክቶ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1632/2/ ጋር በማገናዘብ ሲታይ ነው።
No topics extracted.
እነዚህ ድንጋጌዎች የሚያስገነዝቡት የተመዘገበው መብት ጊዜ ተወስኖለት የተደረገ እንደሆነ ጊዜው ሲያበቃ ይኸው እንዱሰረዝ አቤቱታ ላቀርብ ሳያስፈልግ ባለሥልጣኑ ከመዝገብ መሰረዝ እንደሚችል ያመለክታል። በልላ በኩል በተመዘገበው መብት ተጠቃሚ የሆነው ወገን ይኸው የተወሰነ ጊዜ ከማለፊ በፉት እንዱታደስለት ከጠየቀ ውል እንዱታደስ መመዝገብ የሚችል መሆኑን ያመለክታል።
ከእነዚህ ድንጋጌዎች አቀራረፅና ይዘት መረዲት የሚቻለው የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዥ ውል አንዳ ከተመዘገበ ይህንኑ ውል የማደስ ተግባር ለመፈጸም የአስያዡ ፈቃድ እንደገና መረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ የሚያሣይ አንቀጽ አለመሆኑን ነው።
ስለሆነም አመልካች የመያዣ ውለ እንዱታደስ ለማዘጋጃ ቤቱ በሕጉ በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ጥያቄ ማቅረቡ እስከተረጋገጠ እና ማዘጋጃ ቤቱም ይህንኑ መፈፀሙ እስከታመነ ጊዜ ድረስ ተጠሪ ውለ እንዱታደስ ፈቃደን አለመግለፅ የመያዣ ውለን ጊዜ ሉያራዝም አይችልም በማለት የሥር ፍ/ቤቶች የደረሱበት ድምዲሜ የሕጉን መንፈስና ይዘት በአግባቡ ያላገናዘበ ሆኖ ተገኝቷል።
ስለዚህም የመያዣ ውለ የአሥር አመት ጊዜ አልፍበታል ከዚያ በኋላም አልታደሰም በማለት የተጠሪን ክስ ተቀብለው የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል ብለናል።
ው ሣ ኔ
የምሥራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ4/7/2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በ4/11/2000 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው የመያዣ ውል ለተጨማሪ 10 ዓመት ጊዜ የታደሰ በመሆኑ የተጠሪ ክስ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።