No summary available.
ጥቅምት 16 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ጌታሁን አበበ ቦጋለ - ጠበቃ ገመዲ ጎንፊ - ቀረበ።
ተጠሪ፡- ሐሰን ገአስ ሁመድ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ውልን መነሻ በማድረግ የተጠየቀውን የገንዘብ ክፍያ ክርክር የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በአፊር ብ/ክ/መ/ በዞን አንድ /የአውሲረሲ/ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን፣ ከሣሽ የነበረው ተጠሪ ነው። ተጠሪው በመልካች ላይ ክስ የመሰረተው የከርሰ ምድር ቁፊሮ ሥራ በጋራ ለመሥራት ውል የተዋዋልን ሲሆን፣ ተከሣሽ /የአሁን አመልካች/ ሥራውን መጀመር ሲገባው ይህን አላደረገም። በመሆኑም ውለን በማፍረሱ ግዳታ የገባበት ብር 2ዐዐ.000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ነው። ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት የሁለቱን ወገኖች ክርክር ከሰማ በኋላ፣ ውለ በስህተት የተደረገ ነው። ስህተቱም የሁለቱ ወገኖች ነው። ከዚህ የተነሣም የክልለ የፊይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ውለን ሰርዞአል የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት ክሱን ውድቅ አድርጎአል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ ውሣኔውን በመቃወም ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ በድጋሚ የተሰማ ሲሆን፣ በመጨረሻም ፍ/ቤቱ በከፍተኛው ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሣኔ በመሻር አመልካችን ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ለተጠሪ እንዱከፍል ወስኖአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች መጋቢት 14 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው አመልካች እንደ ውል አፍራሽ በመቁጠር ክስ የቀረበበትን ገንዘብ እንዱከፍል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ነው። በመሆኑም ይህን ነጥብ በዚህ ረገድ ግራ ቀኝ ወገኖች ካሰሙት ክርክር እና አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከሥር ጀምሮ የተደረገውን የግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር እና የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡትን ውሣኔ በዝርዝር ተመልክተናል። ክርክሩን በመጀመያ ደረጃ የሰማው የአውሲረሲ ከፍተኛ ፍ/ቤት የተጠሪን ክስ ወድቅ ያደረገው ለክሱ መሰረት የተደረገው ውል ተከሣሽን ለማስገደድ የሚችል ሕጋዊ ውል አይደለም እሚል መደምደሚያ ላይ በመድረሱ እንደሆነም ከውሳኔው ይዘት ለመገንዘብ ችለናል።
ተጠሪ የከርሰ ምድር ቁፊሮ ከላልች ሰዎች ጋር ለመሥራት የሚያስችል ፈቃድ ሳይኖረው ውለን እንደተዋዋለና በዚህ ምክንያት የክልለ ፊይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ውለ ሕጋዊ ውጤት እንዲይኖረው እንዲደረገው በፍሬ ነገር ረገድ እንደተረጋገጠም ተመልክተናል። ይግባኙን የሰማው የአፊር ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲሆን ውለ በፊይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ስለመሰረዙ ግንዛቤ እንደወሰደ በውሣኔው አመልክቶአል። በከፍተኛው ፍ/ቤትም የተሰጠውን ውሣኔ የሻረውም ውለ በቢሮው አልተሰረዘም በማለት ሳይሆን፣ ውለ በክልለ ፍትሕ ቢሮ ፉት የተደረገ ነው።
ተዋዋይ ወገኖችም ወደውና ፈቅደው ያደረጉት ነው። የፊይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮው ውለን የመሰረዝ ሥልጣን የለውም የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት ነው።
በበኩላችን እንደምናየው የከርሰ ምድር ቁፊሮ ለማድረግ በቅድሚያ ከሚመለከተው የመንግሥት ተቋም ወይም መሥሪያ ቤት ፈቃድ ሉኖር ይገባል። የመሬት ይዞታ እና በመሬት ውስጥ ያለት ማዕድናት የመንግሥት እና የሕዝብ ሃብቶች እንደመሆናቸው /የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ሕገ መንግሥት አንቀጽ 4ዐ ንዐስ አንቀጽ /3/ ይመለከተዋል/ ከመንግሥት በግልጽ የተሰጠ ፈቃድ ሳይኖር የከርሰ ምድር ቁፊሮ ለመሥራት ግለሰቦች ቢዋዋለ ተግባራዊ ላሆን የሚችል ውል ተዋውለዋል ልባል አይችልም። የአፊር ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ፊይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በዚህ ረገድ የሚመለከተው አካል አይደለም አልተባለም። በአመልካችና በተጠሪ መካከል ተደርጎ የነበረውን ውል ሰርዣለሁ ያለውም በዚህ ምክንያት ማለትም ከቢሮው የተሰጠ ፈቃድ ስለላለ ነው።
በአጠቃላይ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ተደርጎአል የተባለው ውል ተግባራዊ ላሆን ይችል የነበረው ፈቃደ ተሰጥቶ ቢሆን ነበር። ውለ በዚህ ምክንያት ተግባራዊ ላሆን ካልቻለ ደግሞ ለውለ አለመተግበር አመልካች ብቻውን ኃላፉ የሚሆንበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። በመሆኑም የአፊር ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.
በአፊር ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ. 1ዐ98 ጥር 1ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሮአል።
በአፊር ብ/ክ/መ/ የዞን አንድ /አውሲረሲ/ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 122ዐ የካቲት 11 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
ስለዚህም አመልካች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ እንዱከፍል አይገደድም ብለናል።