No summary available.
መስከረም 25 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የቀበላ 10 ባለአደራ ቦርድ - ወኪል ታደሰ ሃብቴ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ዲንኤል አድርሴ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የሁከት ይወገድልኝ ክርክርን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- በአዱስ አበባ ከተማ አዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበላ 10/11/12 ክልል ውስጥ የሚገኘውንና አመልካች የሚያስተዲድረውን የሥጋ መሸጫ ቤት ሐምል 01 ቀን 1998 ዓ.ም በተፃፈ የኪራይ ውል በወር ብር 500.00(አምስት መቶ) ተከራይተው እየከፈለ በመስራት ላይ እንዲለ አመልካች በወቅቱ በአቢይ ጾም ምክንያት የሥጋ ቤቱ ለሁለት ወር ስለሚዘጋ ኪራይ እንዱቀንስላቸው ተጠሪ ማመልከታቸውን፣አመልካችም ይህንኑ ተቀብል በወር ብር 105(አንድ መቶ አምስት ብር) ቅናሽ ተደርጏላቸው እየከፈለ ባለበት ሁኔታ ባለአደራ ኮሚቴ በአዱስ ኮሚቴ ተተክቶ ለአዱሱ ኮሚቴም ሁኔታውን ተጠሪ ገልፀው በመነጋገር ላይ እንዲለ የተጠሪ ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቶ ያልሰሩትን የኪራይ ክፍያ ከእነወጪው ብር 2010.00(ሁለት ሺህ አስር ብር) መጋቢት 24 ቀን 1999 ዓ.ም የከፈለ ቢሆንም አመልካች የኪራይ ውለን መጋቢት 22 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ ደብዲቤ በማቋረጥ ስጋ ቤቱን እንዱያስረክቡ መጠየቁን ገልጸው ድርጊቱ ሁከት ስለሆነ ሁከቱ ይወገድልኝ በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም ተጠሪ በኪራይ ውለም ግዳታቸውንም በወቅቱ ባለመወጣታቸው የኪራይ ውለ እንዱቋረጥ መደረጉን ገልፆ ሁከት ልባል ስለማይገባ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመመርመር አመልካች ድርጊቱን የፈጸመው የኪራይ ውልን መስረት በማድረግ በመሆኑ አድራጏቱ ሁከት ነው ልባል የሚችል አይደለም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጏታል። ከዚህም በኋላ የአሁኑ ተጠሪ ይግባኛቸውን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። ከዚህም በኋላ ተጠሪ የሰበር አቤቱታቸውን ለከተማው ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ አመልካች ለመክሰስም ሆነ ለመከሰስ ሕጋዊ ሰውነት የላለው አካል ነው የሚል ምክንያት በመያዝ የበታች ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ሙለ በሙለ ሽሮታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ወኪል መጋቢት 01 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ በከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት የሚልበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ቦርደ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ስለመሆኑ በ1988 ዓ.ም የወጣው መመሪያ የሚያሳይ ሁኖ እያለ ሕጋዊ ሰውነት የለውም ተብል መወሰኑ ያላግባብ በመሆኑ ውሳኔው ሉታረም የሚገባው ነው በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል በመታዘዙ ተጠሪ ቀርበው ሚያዚያ 22 ቀን 2002 ዓ.ም በጠበቃቸው አማካኝነት በተፃፈ ሁለት ገጽ ማመልከቻ አመልካች ሕጋዊ ሰውነት የላለው መሆኑ ተረጋግጦ የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑና መመሪያ የሚባለውም በአመልካቹ በራሱ የወጣ በመሆኑ ተቀባይነት የላለው በመሆኑ የሰበር ቅሬታው ሕጋዊ መሰረት የላለው ስለሆነ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።፡ አመልካች በበኩለ ሰኔ 23 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም አመልካች የሕግ ሰውነት የለውም ተብል የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ መሻሩ ባግባቡ ነውን? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ሉመረመር የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአመልካች ሥልጣንና ተግባር እንዱሁም ዓላማው በ1988 ዓ.ም በወጣው መመሪያ መሰረት ተዘርዝሯል። ከዚህም በተጨማሪ በአዋጅ ቁጥር 361/95 በአንቀጽ 14 ስር በተመለከተው መሰረት የከተማው ምክር ቤት አዋጅ የማውጣት ስልጣን ያለው ሲሆን በአዋጁ አንቀጽ 10/3/ሐ/ ስር የቀበላ ሥልጣን አካላት ስር የቀበላ ቋሚ ኮሚቴ አንደ ስለመሆኑ ተመልክቷል። የከተማው ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 14/1/ረ/ እና 66/2/ መሰረት በተሰጠው ስልጣን ክሱ ሲመሰረት ስራ ላይ የነበረውን የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የአስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግልት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 2/1995 አውጥቷል። በዚህ አዋጅ አንቀጽ 52 ስር በቦርድ ወይም በምክር ቤት (ካውንስል) ስለሚመሩ ማዘጋጃ ቤታዊ ያልሆኑ አስፈፃሚ አካላት የሚደራጁበት ሁኔታ ተመልክቷል። ይህ አዋጅ የሻረው አዋጁን የሚቃረን ማናቸውንም አዋጅ፣ደንብ፣መመሪያ ወይም የአሰራር ልምድ ስለመሆኑ በአንቀጽ 54 ስር በግልጽ አመላክቷል።
ይህም ቀድሞ በመመሪያ የተቋቋመ የቀበላ ባለአደራ ቦርድ ሕልውናው እንዱያከትም የተደረገ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው። በመሆኑም ከላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች አጠቃላይ ይዘትና የቀበላ ባለአደራ ቦርድ ካለው አጠቃላይ ዓላማ እንዱሁም ከሚመራበት አሰራር ስንነሳ የቀበላ ባለአደራ ቦርድ የሕግ ሰውነት ያለው መሆኑን ፍርድ ቤት በራሱ ጊዜ ግንዛቤ የሚወስድበት ጉዲይ(ጉዲዩ የሕግ ጉዲይ በመሆኑ) ሆኖ አግኝተናል። የአዱስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችልት የበታች ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ውድቅ ያደረገው አመልካች ክስ ለማቅረብ ወይም ለመክሰስ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ስለመሆኑ ማስረጃ አላቀረበም በማለት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 397 ድንጋጌን በዋቢነት በመጥቀስ ነው። ይሁን እንጂ አመልካች የሕግ ሰውነት ያለው መሆኑን ፍርድ ቤቱ የራሱን ግንዛቤ(judicial notice) የሚወስድበት ስለመሆኑ ተቀባይነት ያላቸው የማስረጃ ሕግ መርሆዎች የሚያስገነዝቡት ነጥብ እንጂ ተከራካሪ ወገን ለፍርድ ቤት ሕጉን ለማስረጃነት እንዱያቀርብ የሚገደድበት ሁኔታ አይደለም። በአጠቃላይ አመልካች የሕግ ሰውነት የላለው በመሆኑ ሉከሰስ ወይም ሉከስ የሚችል አይደለም ተብል የተሰጠው ውሳኔ ከላይ የተጠቀሱትን ሕጏች ይዘትና መንፈስ እንዱሁም የተጠሪን የክስ አቀራረብ ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ ተገኝቷል።
ላላው በዚህ ችልት መታየት ያለበት ነጥብ የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በዋናው ጉዲይ ላይ ያስተላለፈት ውሳኔ ተገቢነት ያለው መሆን ያለመሆኑ ነው። በእርግጥ የከተማው ሰበር ሰሚ ችልት በዚህ ረገድ ጭብጥ መስርቶ የሰጠው ውሳኔ የለም። ነገር ግን የከተማ ሰበር ሰሚ ችልት በሕግ ተለይቶ የተሰጠው ሥልጣን መሰረታዊ የሕግ ስህተት ማረም በመሆኑ እና ይህም የሕግ ጥያቄ ከፍትሒብሓር ሥነ ሥርአት ህጉ አላማም አንፃር በዚህ ችልት ቢታይ ተገቢ ሁኖ በመገኘቱ ጉዲዩን ለከተማው ሰበር ሰሚ ችልት መመለሱ አስፈላጊ ሁኖ አልተገኘም።
ተጠሪ ክሱን የመሰረቱት አመልካች ሁከት ፈጠረብኝ፣ሉወገድልኝ ይገባል በሚል ነው።
አመልካች ለተጠሪ ክስ በሰጠው መልስ በመካከላቸው ያለው ግንኙነት የኪራይ ውልን መሰረት ያደረገ መሆኑን ጠቅሶ ተጠሪ በውለ መሰረት ግዳታቸውን ስላልተወጡ ተገቢውን መፈጸሙን ገልጾ ተግባሩ ሁከት ልባል የሚገባው አይደለም በሚል ተራክሮ የስር ፍርድ ቤትም ይህንኑ የአመልካችን ክርክር በመቀበል የተጠሪን ክስ ውድቅ አድርጓል። ይህ ችልትም ጉዲዩን ሲመለከተው አመልካችና ተጠሪ ግንኙነታቸው ውል እስከሆነ ድረስ የአመልካች ጥያቄም በውለ መሰረት እንዱፈጸም የሚል በመሆኑ ተጠሪ የአመልካችን እርምጃ ሁከት ነው በማለት ክስ የሚመሰርቱበት የሕግ አግባብ የላለ መሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1140፣1148 እና 1149 ድንጋጌዎች የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። ተጠሪ መብታቸውን ሉያስከብሩ፣ የሚችለት ውላቸውን መሰረት በማድረግ እንጂ በሁከት ይወገድልኝ ክስ አይደለም።
በመሆኑም የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የአመልካች ተግባር ሁከት አይደለም በሚል ምክንያት የተጠሪን ክስ ውድቅ ማድረጋቸው ምንም የሕግ ስህተት የላለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ታህሣሥ 02 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ለመክሰስም ሆነ ለመከሰስ ሕጋዊ ሰውነት አለው ብለናል።
የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 01 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በከተማው የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት መደበኛ ችልት በመ/ ሕዲር 09 ቀን 2001 ዓ.ም በትእዛዝ የጸናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር ግራ ቀኙ ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ት እ ዛ ዝ ይህ ችልት ሚያዝያ 06 ቀን 2002 ዓ.ም ሰጥቶት የነበረው እግድ ተነስቷል ይፃፍ።
ቤ/ኃ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ታህሣሥ 26 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፣ ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች፣ አቶ ጌትነት የኔው - ቀረቡተጠሪ፣ አቶ ኢዩብ ቢንያም ወ/ቢኒያም ዮሐንስ - ቀረቡ መዝገቡን ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ ሁከት ይወገድልኝ ሲል አመልካች ያቀረበውን ክስ የሥር ፍ/ቤት ተቀብል እንደክሱ አቀራረብ ከወሰነ በኃላ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ክሱ በይርጋ ይታገዲል ሲል መሻሩን በመቃወም አመልካች በዚህ ሰበር እንዱታረም ስላመለከተ ነው።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በድሬደዋ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ፍርድ ቤቱም የድሬደዋ ከተማ መሬት አስተዲደር ባለሥልጣን ስለጉዲዩ አጣርቶ መግለጫ እንዱያቀርብ ካደረገ በኃላ በዚሁ መነሻ ተጠሪ በአመልካች ይዞታ ክልል ገብቶ ሁከት ፈጥሯል ሲል ውሣኔ ሰጥቷል።
ይግባኝ የቀረበለት የድሬደዋ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክር ከመረመረ በኃላ ሥር ተከሣሽ /ተጠሪ/ በአከራካሪው ይዞታ ላይ የግንብ አጥር የሰራው በ1987 ዓ.ም መሆኑን አመልካች ደግሞ ክስ ያቀረበው ጥር 14 ቀን 2002 ዓ.ም መሆኑን በማመልከት የአመልካች ክስ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1149/2/ መሰረት በይርጋ ቀሪ ነው ሲል ወስኗል። ከዚህም ባሻገር በፍሬ ነገር ረገድም በይዞታ ላይ ክርክር ሲነሳ ይዞታውን በእጁ አድርጏ በእውነት የሚያዝበት ባለይዞታ ቅድሚያ እንደሚሰጠው የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1144/2/ ይደነግጋል በማለት ይዞታው የተጠሪ ነው ሲል ወስኗል።
ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በአመልካች በኩል የቀረበው የይዞታ ማረጋገጫ ውድቅ ተደርጏ ተጠሪ አከራካሪውን ቦታ ቀደም ሲል ይዞት ነበረ በሚል ይዞታው ለተጠሪ እንዱፀና በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት መወሰኑ በአግባቡ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ተደርጓል።
ተጠሪ ህዲር 29 ቀን 2003 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርቧል በይዘቱም አከራካሪው ይዞታ 52 ካ.ሜ የተባለው የአመልካች ይዞታ ሳይሆን ተጠሪ ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ በእጁ አድርጏ የሚያዝበት ስለመሆኑ በመጥቀስ አመልካች በይዞታው ሥር በልላ ቦታ ሁከት ተፈጥሮብኛል በማለት ያቀረበው ክስ ውድቅ መደረጉ በአግባቡ ነው ሲል ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር ከፍ ሲል በአጭሩ የተመለከተው ነው።
እኛም ጉዲዩን ለዚህ ሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
አመልካች ክስ ባቀረበበት ይዞታ ላይ ባለመብት ስለመሆኑ የይዞታ ማረጋገጫ መጋቢት 10 ቀን 2000 ዓ.ም የተሰጠው ስለመሆኑ ይኸው ማስረጃ ሥር ፍ/ቤት ቀርቦ ተቀባይነት ያገኘ ስለመሆኑ ከመዝገቡ መረዲት ተችሎል። አመልካች በዚሁ የይዞታ ማረጋገጫ የተሰጠው ይዞታ ስፊት 180 ካ.ሜ ሆኖ ከዚህ ውስጥ 52 ካ.ሜ በተጠሪ የተያዘ ስለመሆኑ በሥር ፍ/ቤት በማስረጃ የተረጋገጠ ፍሬነገር ነው።
ተጠሪ ይህንን ይዞታ ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ ይዠዋለሁ ይበል እንጂ የቀበላው አስተዲደር የተጠሪ ይዞታ እና የተሰራው ግንባታ ሕገወጥ ስለመሆኑ በሥር ፍ/ቤት ውሣኔ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው።
ስለሆነም የፍ/ብ/ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 1140 እና 1144/2/ ተጠቅሶ በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ አግባብነት ሲታይ ተጠሪ በሕገወጥ መንገድ ይዞ በእጁ በማድረጉ ለሕገወጥ ተግባር ሕጋዊ ሽፊን እንደመስጠት ያህል መሆኑን መረዲት ተችሎል።
የፍ/ብ/ሕጉ ዓላማ በሕግ አግባብ ባለይዞታ ለሆነው ወገን ጥበቃ ለማድረግ እንጂ ሕገወጥነትን ለማበረታታት እንዲልሆነ ግንዛቤ ሉወሰድበት ይገባል። በዚህ ረገድ አግባብነት ያለው የፍ/ብ/ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 1146/1/ እንደሚያስገነዝበን በስውር ወይም በሚያሻማ አኳኃን የተደረገው ይዞታ ማንኛውንም መብት አይሰጥም።
ስለዚህም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሥር ፍ/ቤት ውሣኔን ለመሻር መሰረት ያደረገው የሕግ ድንጋጌ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተናል።
በልላ በኩል አመልካች በዚህ አከራካሪ ይዞታ ባለመብት ስለመሆኑ በሚመለከተው የአስተዲደር አካል ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጠው መጋቢት 10 ቀን 2000 ዓ.ም ሆኖ ክስ የመሰረተው ጥር 14 ቀን 2002 ዓ.ም መሆኑ ሲታይ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1149/2/ መሰረት የሁለት ዓመት ጊዜ አልፍበታል የሚባልበት ሁኔታ የለም።
በመሆኑም አመልካች ከተጠሪ የተሻለ መብት ያለው መሆኑን ከአስተዲደር አካል የተሰጠውን የምስክር ወረቀት መሰረት አድርጏ ያቀረበው ክስ መታየት የሚገባው ይህንኑ ማስረጃ ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ እንጂ ተጠሪ በሕገወጥ መንገድ ይዞታውን በእጁ ካደረገበት ጊዜ ላሆን አይገባም።
ባጠቃላይ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች ከሕጉ ጋር በአግባቡ ሳያገናዘብ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው ሉታረም ይገባል ብለናል።
ው ሣ ኔ
የድሬዲዋ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመ//2002 ሐምል 27 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የድሬዲዋ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ሰኔ 28 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ለተደረገው ክርክር ግራቀኙ የየራሳቸውን ወጪና ኪሣራ ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.