No summary available.
ሐምል 27 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ- - አቶ እሸቱ በቀለ /ነገረ ፈጅ/ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ ንጉሴ በያን - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ለባንክ ብድር መያዣ የሰጠበት የማይንቀሳቀስ ንብረት በመያዣው ከመያዙ በፉት በሽያጭ ለሶስተኛ ወገን ተላልፍና ስመ ሀብቱም ከመያዣው በኋላ ለገዥው ዙሮ ሲገኝ ያለውን ውጤት የሚመለከት ነው። የክርክሩ መነሻና ይዘትም የሚከተለው ነው። አመልካች ለአቶ አያላው መንገሻ የሰጠውን ብድር ተበዲሪው ባለመመሰለ ምክንያት እና ተበዲሪው በውለ መሰረት የወሰደውን ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ክስ አቅርቦባቸው ውሳኔ እንዲገኘ በውሳኔው መሰረት እንዱፈጸምለት ለምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአፈፃፀም ማመልከቻ አቅርቦ በቅድሚያ በዋስትና የተያዘ ቤት በአገምሳ ከተማ ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥሩ 026 እና 96 የሆነ ተገምቶ በጨረታ በሐራጅ እንዱሸጥ አፈጻጸሙን ለያዘው ፍርድ ቤት ጥያቄ አቅርቧል። ፍርድ ቤቱም ቤቶቹ በሐራጅ እንዱሸጡ ትእዛዝ ሰጥቶ ከተሸጡ በሁዋላ የአሁኑ ተጠሪ ይህ ቤት አመልካች በዋስትና ከመያዙ በፉት በውል ስምምነት ገዝቼ የንብረት ባለቤትነት ስም ወደ ስሜ ተዛውሮ የሚገኝ መሆኑን ገልፀው የሐራጅ ሽያጩ ውድቅ እንዱሆንላቸው አቤቱታ አቅርበዋል። አቤቱታው የቀረበለት ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ቤቱ በሽያጭ ስምምነት ለተጠሪ መዛወሩና ስም በተዛወረበት ወቅትም የአሁኑ አመልካች ያቀረበው ወይም ያነሳው ተቃውሞ የለም በሚል ምክንያት የሐራጅ ሽያጩን ውድቅ አድርጎ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ አከራካሪው ቤት በ10/10/1988 ዓ/ም በዋስትና መያዙ ተረጋግጧል፣ ስመ ሀብቱ ለተጠሪ የዞረውም በ1992 ዓ/ም ውስጥ ነው የሚለትን ምክንያቶችን በመያዝ አመልካች በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 3059(1) ድንጋጌ የቅድሚያ መብት አለው በማለት ሽያጩ ሉቀጥል ይገባል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ተጠሪ ቤቱን በ01/10/1988 ዓ/ም ገዝተው ሲገዙ ከነበረበት ከአስር ቆርቆሮ ወደ አንድ መቶ ቆርቆሮ በማሳደግ ግንባታ ያከናወኑ መሆኑ መረጋገጡን፣ ስመ ሃብቱ ሲዞርም በቤቱ ላይ እዲና እገዲ የላለው መሆኑን የሚመለከተው ቀበላ አስተዲደር መገለጹን እንዱሁም ተጠሪ ቤቱን የገዙት ከባለእዲው ጋር ተመሳጥረው ለማሸሽ ነው አለመባለን በምክንያትነት ይዞ ቤቱ ከተሸጠ በኋላ በመያዣነት ተይዞ ብድር በባለእዲው መወሰደን ከክርክሩ ሂደት መገንዘቡን ጠቅሶ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቶታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪ ቤቱን በ01/10/1988 ዓ/ም ገዛሁ ቢለም ስመ ሀብቱ የዞረው በ1992 ዓ/ም ሁኖ አመልካች ቤቱን በመያዣ የያዘው በ10/10/1988 ዓ/ም መሆኑ ተረጋግጦ እያለ አመልካች የቅድሚያ መብት የለውም ተብል መወሰኑ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተምርምሮም ክርክር የተነሳበት ቤት ተጠሪ አመልካች በመያዣ ከመያዙ በፉት ነው የተገዛው ተብል ለተጠሪ የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን በዚሁ መሰረት ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ቤቱን ገዛሁ የሚለት ጊዜ በ01/10/1988 ዓ/ም ሁኖ ስመ ሀብቱ የዞረው በ1992 ዓ/ም መሆኑን፣ ስመ ሀብቱ ሲዞርም በቤቱ ላይ እዲና እገዲ የላለው መሆኑን የክፍለ ቀበላ ማረጋገጡና ተጠሪ አስር ቆርቆሮ ቤት ገዝተው ባሁኑ ጊዜ አንድ መቶ ቆርቆሮ በማድረግ ይዘው የሚጠቀሙበት መሆኑን፣ ተጠሪ ቤቱን ይዘው ግንባታ ሲያከናውኑም አመልካች ያነሳው ተቃውሞ የላለ ሁኖ ሽያጩን ያከናወኑትም ከባለእዲው ጋር ተመሳጥረው ስለመሆኑ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ክርክር ያላቀረበበትና ይህንኑ የሚያሳይ ሁኔታም አለመኖሩን፣ ቤቱ እንዱታገድ በ10/10/1988 ዓ/ም ቀበላው ሰጠ የተባለው የአመልካች የሰነድ ማስረጃም ቀበላው በሁዋላ ስመ ሀብቱ ወደ ተጠሪ ሲዞር በቤቱ ላይ እዲና እገዲ የላለ መሆኑን በ25/2/1992 ዓ/ም ከገለፀበት ማስረጃ አንፃር ሲታይ ተጠሪ ቤቱን እዲና እገዲ እያለ ገዝተዋል ለማለት የሚያስችል አለመሆኑን የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍሬ ነገርን ሲያጣራና ማስረጃን ሲመዘን ያረጋገጣቸውና ለውሳኔው መሰረት ያደረጋቸው ምክንያቶች መሆናቸውን ነው። ከዚህ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በግልፅ መረዲት የሚቻለው በሕግ አግባብ የተቋቋመ የመያዣ ውል በአከራካሪው ቤት ላይ አለመደረጉን ፍርድ ቤቱ ፍሬ ጉዲዩን በማጣራትና ማስረጃውን በመመዘን የደመደመው ጉዲይ መሆኑን ነው። በልላ አገላለፅ አመልካች በቤቱ ላይ የመያዣ ውለን በሕጉ አግባብ ስለማቋቋሙ ሉታመን በሚችል ማስረጃ አለማስረዲቱን የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚያስገነዝብ ሁኖ አግኝተናል። አመልካች ቤቱን በመያዣነት የያዘው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 3051(2) ድንጋጌ መሰረት በቅን ልቦና ነው ለማለት የሚያስችል ፍሬ ነገርም በክርክሩ ሂደት አለመረጋገጡን ተገንዝበናል። ስለሆነም ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት ተጠሪ አመልካች በመያዣ ከመያዙ በፉት ነው የተገዛው ተብል ሐራጁ በቤቱ ሉቀጥል አይገባም ተብል የተወሰነው ፍሬ ነገሩና ማስረጃው ተመዝኖ በመሆኑና ይህ ፍሬ ነገርና ማስረጃ ምዘና ጉዲይ ደግሞ በዚህ ችልት ላታይ የሚችልበት አግባብ የላለ መሆኑን ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎችን ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ሕዲር 24 ቀን 2003 ዓ/ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.