No summary available.
ሰኔ 2 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የእንግሉዝ ህጻናት አድን ድርጅት - ጠበቃ ጥላዬ ተገኝ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ገአስ ኡስማን - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የተያዘው ክርክር በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሣኝ ቦርድ የተጀመረ ነው። ጉዲዩ አሰሪ የሆነው የአሁን አመልካች ሰራተኛ በሆኑት በአሁን ተጠሪ ላይ የወሰደውን የስንብት እርምጃ የሚመለከት ነው። ተጠሪ በአመልካች ድርጅት የተወሰደብኝ እርምጃ ህገ ወጥ በመሆኑ የተቋረጠብኝ ክፍያ ተሰጥቶኝ ወደ ስራዬ እንድመለስ ይወሰንልኝ ሲለ በአመልካች ላይ ክስ መስርተዋል።
አመልካች ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጏ በውሣኔው ላይ ቢገለጽም ተወካዮቹ ቀርበው በጽሁፍ መልስ የሰጡ ስለመሆኑ ግን የክርክሩ ሂደት ያሣያል። የአመልካች የመከላከያ መልስ ክርክርም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የስንብቱን ተገቢነት ይገልጻል የሚለውን መልስ አቅርቦ የተከራከረ መሆኑን የክርክሩ ሂደት ያሣያል። ክሱ የቀረበለት የአፊር ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ዞን አራት ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ጉዲዩ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣኑ መታየቱ ፍርድ ቤቱ ክሱን አዛውሮ ከማየት ስልጣኑ አንጻር ተገቢ ነው የሚለውን ምክንያት በመስጠት በስልጣን ረገድ የተነሣውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ከአለፈው በሁዋላ ዋናውን ጉዲይ በተመለከተም መርምሮ ስንብቱ ህገ ወጥ ነው ወደሚለው ድምዲሜ ደርሶ አመልካች ድርጅት ተጠሪን አሰናበተ ከተባለበት ከጥቅምት ወር 2ዐዐ1 ዓ.ም እስከ ጥር 26 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም እንዱሁም ከጥር 27 ቀን 2ዐዐ2 እስከ የካቲት 29 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ድረስ ያለውን ውዝፍ ደመወዝ ከቆላ አበለ ጋር የደመወዝ ጭማሪ እንዱሁም ላልች ጥቅማጥቅሞችን በመክፈል ወደ ቀድሞው የስራ መደብ እንዱመልሰው በማለት ወስኗል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ጉዲዩን በይግባኝ የመመልከት ስልጣን የላለው መሆኑን ጠቅሶ መዝገቡን ዘግቶታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘቱም ጉዲዩ በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣኑ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መመልከቱም ሆነ ጉዲዩን የመራበት ስርዓት የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህጉን የተከተለ ባለመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮ በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖበት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጏላቸው ቀርበው የጽሁፍ መልስ የሰጡ ሲሆን በመልሣቸው ላይም የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት ሉያገኝ አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
ይህም ችልት በቅድሚያ ምላሽ ሉሰጠው የሚገባው አቢይ የህግ ነጥብ ላይ ብቻ በማተኮር መዝገቡን መርምሯል። በዋነኛነት ሉፈታ የሚገባው የነገሩ ጭብጥ፡የአሰሪና ሰራተኛን ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 ‛ን“ መሰረት አድርጏ የሚነሣውን የግል የስራ ክርክር በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣኑ በማየት የመዲኘት ስልጣን የማነው? የክልለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው? ወይስ የክልለ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት? የሚለው መሆኑን ተገንዝቧል።
ለተያዘው ጭብጥ ምላሽ የማግኘቱ ጉዲይ ስለ ስራ ክርክር ስለ ቦርድና ስለ ፍርድ ቤት ስልጣን የሚገልጹትን የአዋጅ ቁ. 377/96 ድንጋጌዎችን ተመስርቶ ጭብጡን መመርመርን ይጠይቃል።
አዋጅ ቁጥር 377/96 ከአዋጅ ቁ. 25/1988 በኋላ የወጣ ሲሆን በአንቀጽ 136/3/ ስለ ስራ ክርክር ምንነት ትርጓሜ የሚሰጥ ድንጋጌ ከመያዙም በላይ የዚሁ አዋጅ አንቀጽ 147 ስለቦርድ ስልጣን የሚደነግገው ሲሆን የፍ/ቤት ስልጣንን ደግሞ የሚደነግገው የአዋጁ አንቀጽ 138/2/ ነው። በአዋጁ አንቀጽ 138/1/ የተዘረዘሩትንና መሰል የግል የስራ ክርክሮችን የመዲኘት ስልጣን ለፍ/ቤት መስጠቱን ከዚህ ድንጋጌ መረዲት ይቻላል። አዋጁ የስራ ክርክርን የክልልና የፋዳራል ጉዲይ ነው የሚል መለኪያ በመስጠት የስነ-ነገር የዲኝነት ስልጣን መከፊፈለን በግልጽ አያሣይም። በአዋጅ ቁጥር 322/95 ‛ም“ ሆነ በህገ መንግስቱ መሰረት የክልለ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስራ ክርክርን አስመልክቶ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስልጣንን በውክልና ሉመለከት ይችላል የሚባልበት አግባብም የለም። በአዋጁ አንቀጽ 138/1/ ድንጋጌ መሰረት ለፍ/ቤት የሰጡትን የስራ ክርክሮችን በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣን የማየት የስረ ነገር ስልጣን የክልለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መሆኑ በግልጽ ተቀምጧል። የአዋጁ አንቀጽ 139/1/ /ሀ/ ደግሞ በክልለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በስራ ክርክር ችልት የተሰጡ ውሣኔዎች ላይ የክልለ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የስራ ክርክር ችልት የይግባኝ ስልጣን እንዲለው ያሣያል፡ በመሆኑም የክልለ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የስራ ክርክር ችልት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 138 መሰረት በክልለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሚታዩት ጉዲዮች ላይ የይግባኝ ስልጣን ያለው መሆኑን የአዋጁ አንቀጽ 139/1/ሀ/ በግልጽ ያሣያል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ የተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ የስራ ውል ከህግ ውጭ የተቋረጠ ስለሆነ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍል ወደ ቀድሞው ስራ እንዱመለስ ፣ ጭማሪ ደመወዝ እንዱከፈለኝ ፣ የቆላ አበል እና ላልች ጥቅማጥቅሞች እንዱከፈለኝ ይወሰንልኝ የሚል ሲሆን በይዘቱ በአዋጅ አንቀጽ 138/1/ለ/ መሰረት የሚታይ የግል የስራ ክርክር ሁኖ በጉዲዩ ላይ በሚሰጠው ውሣኔ ቅሬታ ያለው ወገን ይግባኙን ለክልለ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የስራ ክርክር ችልት በአንቀጽ 139/1ሀ/ መሰረት አቅርቦ የሚያሣይበት ጉዲይ ነው። የአፊር ክልል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣኑ ሉመለከት የቻለው ጉዲዩን ለማየት ስልጣኑ በህጉ በግልጽ ተሰጥቶኛል በሚል ምክንያት ሣይሆን የክስ መዛወር ጥያቄ ሲቀርብ ለማስተናገድ የምችለው እኔ ነኝ በሚል ምክንያት ስለመሆኑ ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ ችለናል። ይሁን እንጂ የክስ ይዛወርልኝ ጥያቄ /Change of Venue/ የሚስተናገድበትን አግባብ ህጉ የዘረጋው ስርዓት ያለ ሲሆን የስር የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለብይኑ ዋቢ ያደረገው በ1958ቱ የፍትሐብሕር ስነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 31 ስር የተመለከተው አንደ ሲሆን ከዚህ ህግ በሁዋላ በፋዳራልም ሆነ በክልልች የወጡት የፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጆችም ተመሣሣይ ይዘት ያለውን ድንጋጌ ስራ ላይ አውለው ይገኛለ። አንድ ክስ ወደ ላላ ስፍራ ሉዛወር የሚችልበትን አግባብ ከሚደነግጉት የስነ ስርዓት ህግ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው ደግሞ ጥያቄው ከተከራካሪ ወገኖች የሚቀርብ መሆኑና ህጋዊ ምክንያቶች ተብለው በህጉ ከተመለከቱት ሁኔታዎች ውስጥ አንደ መሟላት ያለበት መሆኑን ነው። በተያዘው ጉዲይ ግን የአፊር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ወደራሱ ያዞረው በተከራካሪ ወገኖች የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታ ቀርቦለትና በህጉ ስር የተመለከቱት ቅድመ ሁኔታዎችም ተሟልተው ስለመሆኑ የክርክሩ ሂደት የማያሣይ መሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ወደ ራሱ አዙሮ የተመለከተው ህጋዊ ስርዓቱን ተከትል አይደለም ፣ በውጤቱም በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣኑ እንዱመለከተው በህጉ ያልተሰጠውን ስልጣን በመውሰድ ጉዲዩን በማየት በህጉ ጥበቃ ያገኘነው የተከራካሪ ወገኖች የይግባኝ መብት ያጣበበ ሁኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ሁኖ ስለተገኘ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በአፊር ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ዞን አራት ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት 29 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ጉዲዩ በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣን ላታይ የሚገባው በክልለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣኑ ላታይ የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት/አግባብ የለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የራሣቸውን ይቻለ ብልናል።
No topics extracted.