No summary available.
ህዲር 01 ቀን 2003ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- ሲ.ኤ.ኤስ - ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ሳልዝጊተር ጂ.ኤም.ቢ.ኤች ጠበቃ ፍቃደ ሞላ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ካሳሁን ተወልደብርሃን ጠበቃ ፈቃደ አስፊው ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ አዋጅ ቁጥር 377/96"ን" መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክር የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው። ክርክሩ ሲጀመር ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ ሲሆን የአሁኑ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ ነበር። የስር ከሳሽ ክስ ይዘት ሲታይም ከአመልካች ድርጅት ጋር የመሰረቱት የቅጥር ውል ከሕግ ውጪ የተቋረጠባቸው መሆኑን ገልፀው የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፍሎቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም፣ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርቧል። አመልካቹ የስራ መሪ መሆናቸውንና የግራ ቀኙ ስምምነት ጉዲዩ በጀርመን ሕግ እንደሚዲኝ የሚገልጽ መሆኑን በመጥቀስ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት የስረ ነገር ዲኝነት ስልጣን የላለው መሆኑን በመግለጽ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ የስራ መሪ ስለመሆናቸው አልተረጋገጠም ብል ከደመደመ በኋላ በቅጥር ስምምነቱ ላይ ጉዲዩ በጀርመን ሕግ እንደሚታይ መስማማታቸውን ገልጾና የግለሰብ የአለም አቀፍ ሕግ የሚያስነሳ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 11/2/ሀ/ መሰረት ጉዲዩን የማየት ስልጣን የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው ሲል ክሱን ዘግቶታል። በዚህ ውሳኔ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲያቀርቡ አመልካችም ተጠሪ የስራ መሪ አይደለም ተብል የተሰጠው ብይን ላይ መስቀለኛ ይግባኝ አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ተጠሪ ጉዲዩን የማየት ስልጣን የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መሆኑን፣ ተጠሪ የስራ መሪ ስለመሆናቸው ግን አለመረጋገጡን ገልጾ የስር ፍ/ቤት በዋናው ጉዲይ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 341 መሰረት ተመልሶለታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ መጋቢት 14 ቀን 2002ዓ.ም በፃፈት የሰበር ማመልከቻ በበታች ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል።
ይዘቱም ባጭሩ ጉዲዩ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግ የሚያስነሳ ስለሆነ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተመልክቶ ብይን ይስጥበት ተብል በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተሰጥቶ ይኽው ትዕዛዝ በይግባኝ መሻሩ ያላግባብ መሆኑን ማስረጃ ሳይሰማ ተጠሪ የስራ መሪ አይደለም ተብል መወሰኑም ተገቢነት የላለው መሆኑን በመዘርዘር ውሳኔው ሉታረም ይገባዋል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታቸውም ተመርምሮ ክሱን የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ማየት አለበት ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጓል የተጠሪ ጠበቃ ቀርበው መስከረም 21 ቀን 2003ዓ.ም በተፃፈ አራት ገጽ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የአመልካች ጠበቃ በበኩላቸው ጥቅምት 15 ቀን 2003ዓ.ም የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩ የሚገዛው ግራ ቀኙ ባደረጉት ስምምነት መሰረት ሳይሆን በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ነው ብል ጉዲዩን የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣን እንዱመለከተው መመለሱ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ ምላሽ የሚያስፈልገው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክር ሑደት መገንዘብ የተቻለው ግራ ቀኙ መስከረም 20 ቀን 2001ዓ.ም ባደረጉት ስምምነት መሰረት በመካከላቸው የሚነሳው አለመግባባት በጀርመን ሕግ የሚታይ መሆኑን መስማማታቸውን፣ በመካከላቸው የነበረው ግንኙነትም የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት መሆኑን፣ ተጠሪ ኢትዮጵያዊ ሆነው የሚኖሩትና ስራውን ለመስራት ግዳታ የገቡት በኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን፣ አመልካች የውጪ ድርጅት ሆኖ የተመዘገበውና ስራውን የሚሰራው በኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 11/2/ሀ/ ስር የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግ (Private International Law) የሚመለከቱ ጉዲዩች በሚኖሩ ጊዜ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የፍትሐብሕር የዲኝነት ስልጣን እንደሚኖረው ተደንግጓል። አዋጁ ይህን ድንጋጌ ሲያስቀምጥ የራሱ የሆነ ምክንያት አለው ተብል ይታሰባል። በዚህም መሰረት ሕግ አውጪው ይህንን ድንጋጌ ያስቀመጠው አንድም ወደ ፉት በስራ ላይ የሚውለውን የአገሪቱን የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግ በሕግ አውጪው አካል ፀድቆ በስራ ላይ ሲውል በዚህ ረገድ የሚነሱ የህግ ክርክሮች የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመጀመሪያ ደረጃ የዲኝነት ስልጣን አይቶ እንዱወስን ወይም አሁን ባለው ሁኔታ በኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ለዲኝነት በቀረበ አንድ ጉዲይ ላይ ከተከራካሪ ወገኖች አንደ የኢትዮጵያ ሕግ ከአመልካቹ አገር ሕግ ወይም ከላላ አገር ሕግ ጋር ይጋጫል ወይም ይቃረናል በማለት በኢትዮጵያ ሕግ እንዲይዲኝ ወይም በራሱ ወይም በልላ አገር ሕግ ጉዲይ እንዱታይና እንዱወሰንለት ሲያመለክት ነው። በልላ አገላለጽ ለዲኝነት የቀረበው ጉዲይ በባህርይው ከአንድ በላይ የሆኑ የሕግ ስርዓቶችን ለጉዲዩ አወሳሰን የሚጋብዝና የየትኛው ሥርዓት ሕግ ተመራጭ ላሆን ይገባል የሚለው ክርክር ሲነሳ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመጀመሪያ ደረጃ የፍትሐብሕር የዲኝነት ስልጣን አይቶ እንዱወሰን ከመደረጉ ውጪ በማናቸውም ሁኔታ ተከራካሪዎች የአገሪቱን ሕግ በሚፃረር መልኩ ስምምነት አድርገው ሲገኙ ሁለ ተከራካሪ ወገን ክርክር ስላነሳ ብቻ የግለሰብ አለም አቀፍ ሕግ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው ልባል የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም። ከዚህ አንፃር ግራ ቀኙ አደረጉ የተባለትን ስምምነት ስንመለከት የኢትዮጵያ አሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ሕግ ተፈፃሚነት እንዲይኖረው የሚያደርግ መሆኑ ሲታይ ስምምነቱ ተቀባይነት አለው ልባል የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት አለመኖሩን ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ዓላማ እና መንግስት አዋጁ ላይ ካለው ጠቅላላ ፍላጎት አንፃር የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ የመንግስትም ፍላጎት የሚንፀባረቅበት ሕግ ሲሆን ይህን አዋጅ የሚመለከቱ ስምምነቶች ሕጋዊ እና የሕዝብን ጥቅም የማይፃረሩ መሆን ይገባቸዋል። የሚኒስተሮች ምክር ቤት በደንብ ካልወሰነ በስተቀር አዋጅ ቁጥር 377/96 የውጪ አገር ድርጅት ሆኖ በኢትዮጵያ ተመዝግቦ በሚሰራ ድርጅት ላይ ተፈፃሚነት ያለው ስለመሆኑ ከአዋጁ ድንጋጌ 3/3/ለ/ ይዘት የምንገነዘበው ነጥብ ነው። በዚህ ረገድ የወጣ ደንብ የለም።
እንዱህ ከሆነ አዋጅ ቁጥር 377/96 ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለው በመሆኑ ጉዲዩ የግለሰብ አለም አቀፍ ሕግ ጥያቄን ስምምነቱን መሰረት አድርጎ ያስነሳል ልባል የሚችልበት ምክንያት የለም። በመሆኑም የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ለጉዲዩ አዋጅ ቁጥር 377/96 ተፈፃሚነት እንዲለው በመግለጽ ጉዲዩን ለፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መመለሱ ምንም የሕግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተናል።
ተጠሪ የስራ መሪ ናቸው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ በሰበር ችልት እንዱታይ በጭብጥነት ያልተያዘ በመሆኑና ከአመልካች የመልስ መልስ ክርክር ላይም ያልተነሳ በመሆኑ መመልከቱ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
1/ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/
No topics extracted.