No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 57ዐ44 ጥር 25 ቀን 2ዐዐ3 ዓ/ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የሁከት ይወገድልኝ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- በወረዲ ዐ3 ቀበላ 47 ክልል ውስጥ የሚገኘውንና ቁጥሩ ዐ4613 የሆነ ቤት ተጠሪ በጨረታ አሸንፈው የገዙት መሆኑን፣ ቤቱ በእርጅና ምክንያት ሉፈርስ በመድረሱ በጊዜአዊነት በላሜራ እንዱያድሱ መስከረም 15 ቀን 2ዐዐ2 ዓ/ም የእድሳት ፈቃድ ተፈቅድላቸው ቤቱን ሰርተው ሲጨርሱ የተሰጠው የጊዜአዊ ግንባታ ፈቃድ ከመመሪያ ውጪ ነው በማለት ግንባታውን እንዱያፈርሱ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑን ገልጸው ተግባሩ ሁከት በመሆኑ እንዱወገድ ዲኝነት ላሰጥ ይገባል በማለት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካቾች ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስም የእድሳት ፈቃድ የተሰጠበት መንገድ ከሕግ ውጪ ነው በመሆኑም ግንባታው እንዱፈርስ ማስጠንቀቂያ ተፅፎል፣ ይህ ደግሞ ሕጋዊ ተግባር እንጂ የሁከት ተግባር አይደለም በማለት ገልፀው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክራዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመመርመር የግንባታ ፈቃደ የተሰጠው ከመመሪያው ውጪና በስህተት መሆኑ ስለተረጋገጠ እና የአመልካቾች እርምጃ ሕጋዊ እንጂ ሁከት ልባል አይችልም በማለት የተጠሪን ክስ ውድቅ በማድረግ ወስኗል። በዚህ ውሣኔ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኙን ለከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ይኸው ፍርድ ቤት ጉዲዩን መርምሮ የግንባታ ፈቃደ ለተጠሪ መሰጠቱ እስከተረጋገጠ ድረስ ተጠሪ በቅን ልቦና የገነቡት ግንባታ የሚፈርስበት ምክንያት የለም፤ የአመልካቾች ተግባር ሁከት ነው በማለት ወስኗል። አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታቸውን ለከተማው ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የሰበር አቤቱታው መሰረታዊ ይዘትም የግንባታ ፈቃደ የተሰጠው ከመመሪያ ውጪ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ የአመልካቾች ተግባር ሁከት ነው ተብል መወሰኑ የአመልካቾችን ኃላፉነት እና ተግባር ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ለተጠሪ የተሰጠው ማስጠንቀቂያ የሁከት ተግባር ነው ተብል መወሰኑ በአግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎአል። በዚህም መሰረት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በሕጋዊ መንገድ ባለንብረት ሁነውና ከመንግስት አካል ጊዜአዊ ፈቃድ ወስደው የገነቡት ግንባታ እንዱፈርስ ማስጠንቀቂያ መጻፍ ሁከት ነው ተብል መወሰኑ ምንም የህግ ስህተት የላለበት በመሆኑ ውሳኔው ሉጸና ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ የተሰጣቸው ጊዜያዊ ግንባታ ፈቃድ ከዓላማው ውጪ በስህተት የተሰጠ መሆኑ በሁለም የበታች ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ ነጥብ መሆኑን ነው። ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው ፍርድ ቤት የተፃፈውን ማስጠንቀቂያ ሁከት ነው ወደሚለው ድምዲሜ ሉደርስ የቻለው ተጠሪ በተሰጣቸው ጊዜያዊ የግንባታ ፈቃድ መሰረት በቅን ልቦና ግንባታ ከአከናወኑ ለስህተቱ ኃላፉነት መውሰድ ያለበት ፈቃደን የሰጠው አካል ነው በሚል ምክንያት ነው።
በመሰረቱ የአንድ ንብረት ባለይዞታ የሆነ ሰው ይዞታውን ለመንጠቅ ወይም በይዞታው ላይ ሁከት ለመፍጠር የሚፈጸምን ማንኛውንም ድርጊት እንዱቆም ወይም ንብረቱ እንዱመለስለት ሕጉ ከሚጠብቃቸው መንገድች አንደ አማራጭ የይዞታ ክስ ማቅረብ (Possessory Action) ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1149(1) ድንጋጌ ያሳያል። በዚሁ ድንጋጌ መሰረት የሁከት ይወገድልኝ ክስ መቅረብ የሚችለው አቤቱታ አቅራቢው ለክርክሩ መነሻ ከሆነው ነገር በቀጥታ ወይም በጠባቂ ይዞታ ሲኖረው ነው። እንዱሁም የይዞታ ክስ የሚቀርበው ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ንብረት በወቅቱ ለመያዝ ምንም አይነት መብት በላለው ሰው ላይ ስለመሆኑም የድንጋጌው መንፈስ ያስረዲል። የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ አቅራቢ በማስረጃ ማረጋገጥ ያለበት ንብረቱ በይዞታው ስር የነበረና የሁከት ድርጊት ፈፃሚው የኃይል ተግባር በመጠቀም ወይም በሚስጢር ንብረቱን የወሰደበት መሆኑን ነው። የሁከት ተግባር የሚኖረው ባለይዞታ የሆነ ሰው በይዞታው ስር በሚገኘው ንብረት እንዲይገለገልበት ላላ ሰው ጣልቃ ገብቶበት መሰናክል ሲሆንበት ወይም ረብሻ ሲፈርጥበት ነው። እንግዱህ የሁከት መፍጠር ድርጊት ትርጓሜና ይዘቱ ከላይ የተመለከተው ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 114ዐ እስከ 1149 ድረስ ከተደነገጉት ድንጋጌዎች መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው። በመሆኑም የሁከት ይወገድልኝ ክስ የሚያቀርበው ሰው ንብረቱ በእርሱ ግልፅ ቁጥጥር ስር መሆኑንና በዚህ ንብረት እንዲይገለገልበት ተከሳሹ ረብሻ የፈጠረበት ወይም መሰናክል የሆነው ስለመሆኑ ከተከሳሽ በተሻለ ማስረጃ የማስረዲት ሸክም አለበት።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም፤ አንድ ባለይዞታ ይዞታውን ከሕጋዊ አካል ከወሰደ በኋላ ይዞታው የተሰጠበት አግባብ ከሕግ ውጪ መሆኑ ከተረጋገጠ ይኸው ስህተት እንዱስተካከልና ሕጋዊ እንዱሆን ለማድረግ የሚከለክል ሕግ የለም። በተሳሳተ መንገድ በተሰጠ አስተዲደራዊ ውሳኔ ቅን ልቦና አድሮበት ለኪሳራ የተዲረገ ሰው ደግሞ በሕጉ አግባብ ተገቢውን ኪሳራ ለመጠየቅ ይችል ይሆናል ከሚባል በስተቀር ቀድሞ በስህተት የተሰጠ ፈቃድ ወይም ላላ ውሳኔ ጸንቶ ሉኖር ይገባል ብል ሉጠይቅ የሚችልበትና ፍርድ ቤትም ይህንኑ ሉቀበል የሚገባበት አግባብ አይኖርም። አንድ የአስተዲደር አካል የሰጠው ውሳኔ ወይም የወሰደው እርምጃ ሕገ ወጥ መሆኑን ከአረጋገጠ ይኸው ውሳኔ እንዱስተካከል የማድረግ ኃላፉነትና ተግባር አለውና። በመሆኑም ለተጠሪ የተሰጠው የግንባታ ፈቃድ ከመመሪያው ዓላማ ውጪ መሆኑ በመረጋገጡ ይህንኑ ሕጋዊ ያልሆነ መመሪያ መሰረት በማድረግ የተሰራ ግንባታ እንዱፈርስ ለተጠሪ የተፃፈው ማስጠንቀቂያ አስተዲደራዊ ኃላፉነትንና ተግባርን ለመወጣት የተደረገ ነው ከሚባል በስተቀር የሁከት ተግባር ላሆን የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። በዚህም ምክንያት የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የአመልካቾች ተግባር ሁከት ነው በማለት የከተማው መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ መሻሩና የከተማው ሰበር ሰሚው ችልትም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ማጽናቱ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በማግኘታችን ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 14 ቀን 2ዐዐ2 ዓ/ም ተሰጥቶ በከተማው ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ሚያዝያ 28 ቀን 2ዐዐ2 ዓ/ም በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት ዐ2 ቀን 2ዐዐ2 ዓ/ም የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
አመልካቾች በተጠሪ ላይ የፈጠሩት ሁከት የለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.