No summary available.
ኀዲር ዐ8 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ብርሃኔ ተሰማ - ቀረቡ ተጠሪ፡-
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1225 ስር የተመለከተውን ንውጽውጽታን /Nuisance/ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። የአሁኑ አመልካች የስር ከሣሽ ሲሆኑ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሣሽ ነበሩ ክሱም የካቲት 28 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የተፃፈ ሆኖ ይዘቱም ባጭሩ በመኖሪያነት በተሰጣቸው ቦታ አመልካችና 1ኛ ተጠሪ የገነቡት ቤት ያላቸው ሆኖ ይኸው ተጠሪ በመኖሪያ ቤታቸው ላይ የብየዲ ሥራ በመስራታቸው ጎረቤት በሆኑት አመልካች ላይ የድምጽ ብክለት ሁከት መፍጠራቸውን፣ 2ኛ ተጠሪም የብረታ ብረት ብየዲ ሥራ በኢንደስትሪ ዞን መስጠት ሲገባው ያላግባብ ፈቃደን መስጠቱን ገልፀው የተፈጠረው የድምጽ ሁከት ሉወገድላቸው፣ የሥራ ፈቃድም እንዱሰረዝ እንዱደረግ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው።
የአሁኑ 1ኛ ተጠሪም ጉዲዩን በሁለት ዓመት የይርጋ ጊዜ ሉታገድ እንደሚገባውና የብይዲ ማሽኑ ዝቅተኛ ድምጽ ያለው መሆኑን ገልፀው የተከራከሩ ሲሆን 2ኛ ተጠሪም የሥራ ፈቃደን የሰጠው በሕግ አግባብ ነው ሲል ተከራክሯል። ፍርድ ቤቱም በ1ኛ ተጠሪ ላይ የቀረበው ክስ በሁለት ዓመት ይርጋ የታገደ ነው፣ 2ኛ ተጠሪን በተመለከተ ደግሞ የሰጠውን ፈቃድ የሚሰርዘው ራሱ እንጂ ፍርድ ቤት አይደለም ሲል የአመልካችን ክስ ውድቅ በማድረግ ወስኗል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ሙለ በሙለ አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ ለማስቀየር ነው።
አመልካች ጥር 18 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በፃፈት ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ሁከቱ በክፍለ ደንብ አስከባሪ ትእዛዝ መሰረት ቆሞ ቆይቶ እንደገና ሲፈጠር ክስ ያቀረበ ሆኖ እያለ በሁለት ዓመት የይርጋ ጊዜ ይታገዲል ተብል መወሰኑ የሕግ ግድፈት ያለበት ነው በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ተሽሮ ተገቢው ውሣኔ እንዱሰጥበት ይደረግ ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም አመልካች የተፈጠረው ሁከት ለተወሰነ ጊዜ ከተወገደ በኋላ እንደገና ሁከቱ በመጀመሩ ምክንያት የቀረበው ክስ በይርጋ ሉታገድ ይገባዋል ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጏ ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጏላቸው 1ኛው ተጠሪ ሲቀርቡ 2ኛ ተጠሪ ባለመቅረቡ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል። 1ኛ ተጠሪ ጥቅምት 19 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሦስት ገጽ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- የአመልካች የሰበር ቅሬታ ነጥብ በስር ፍርድ ቤት ያልተነሣ በመሆኑ በሰበር ችልት ሉነሳ አይገባም፣ጉዲዩ በይርጋ የታገደ ነው ተብል መወሰኑም ባግባቡ ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀ ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልቱ ቀርቦ ሉመመርመር ይገባል ተብል ሲታዘዝ ከተያዘው ጭብጥ አኳያ መርምሮታል።
ከመዝገቡ መገንዘብ የተቻለው አመልካችና 1ኛ ተጠሪ ጏረቤት ሆነው በሚኖሩበት አካባቢ 1ኛ ተጠሪ ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ወስደው የብረታ ብረት ብየዲ ሥራ እንደሚሰሩና በስራው ወቅት ጥቅም ላይ የሚውለው ማሽን በሚያሰማው ድምጽ አመልካች ሁከት ተፈጥሮብኛል የሚለ መሆኑን ነው። 1ኛ ተጠሪ የብየዲ ሥራውን ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰሩት መሆኑን በመግለጽ የሚከራከሩ መሆናቸውን ተገንዝበናል።
በመሰረቱ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1225 ስር በባለቤትነት መብት ያለመጠን መገልገልን የሚደነግገው ድንጋጌ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1149 ስር ከተመለከተው በይዞታ ላይ ሁከት ስለመፍጠር እጅጉን የተለየ ነው። በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1225 ስር የተመለከተው ጉዲይ በሰፉ የባለቤትነት መብት ላይ በህጉ ከተመለከቱት ገደቦች መካከል አንደ ነው። ባለቤቱ ድርጊቱን የሚፈጽመው ወይም ሥራውን የሚፈጽመው በራሱ ንብረት ወይም ቤት ውስጥ ቢሆንም የድርጊቱ ወይም የሥራው ውጫዊ መገለጫዎች ላላውን ጏረቤት ወይም ባለቤት፣በልላ ሕጋዊ አግባብ ተጠቃሚ የሆነውን ሰው እንዲይረብሽ፣ እንዲያውክ ወይም በማናቸውም መልኩ ከተገቢው በላይ የሆነ ችግርን እንዲያስከትል በማድረግ መብቱን በልክ ባለቤቱ ይጠቀም ዘንድ ህጉ ያበጀው፣ የባለቤትነት መብትን አጠቃቀም አድማስን የሚወሰን ሥርአት ስለመሆኑ ከአንቀጽ 1226 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ጋር አዛምደን በምናነብበት ጊዜ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው በመሆኑም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1149 ስር የተመለከተው የይርጋ ጊዜ ለጉዲዩ አግባብነት የለውም።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም የክርክሩ ባህርይ የሚያሳየው የአመልካች ጥያቄ በይዞታቸው ላይ የተፈጠረው ሁከት እንዱወገድላቸው ሳይሆን የማሸኑ ድምጽ የፈጠረባቸው ረብሻ እንዱወገድላቸው ነው። የማሽኑ ድምጽ ሥራው እስከተሰራ ድረስ የሚቀጥል መሆኑም ግልጽ ነው።
በልላ አገላለጽ የብየዲው ሥራ ከተጀመረ በኋላ የጊዜ ማለፍ ሁኔታ መኖር በድምጽ ሁከት ተፈጥሮብኛል በማለት ክስ ለማቅረብ የሚገድብ አይደለም። ዋናው ቁልፈ ነገር ድምፁ ከመጠን በማለፈ ረብሻ መፍጠሩን ማረጋገጥ ነው። በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1225 ስር የተመለከተው ድንጋጌ ዓይነተኛ ዓላማውም ባለሐብቱ በመብቱ በሚገለገልበት ጊዜ የጏረቤቱ ርስት ጥቅም የሚቀንስበትን ወይም የሚጏዲበትን ማናቸውንም ከመጠን ያለፈ ነገር ከመስራት መከላከል ነው። አንዳ የተፈጠረ የድምጽ ብክለት እንዱቀጥል የሚደረገበት የሕግ አግባብ የለም። ተከራካሪ ወገኖች የጠቀሱትን ድንጋጌ ብቻ በመያዝ ለፍሬ ጉዲዩ አግባብነት የላለውን ድንጋጌ በመያዝ ውሳኔ መስጠት የዲኝነት አካሄድ የሚፈቅደው አይደለም። ለጉዲዩ አግባብነት ያለውን ድንጋጌ በመለየት ዲኝነት መስጠት የፍርድ ቤት የእለት ተእለት የስራ ድርሻ እንጂ የተከራካሪ ወገኖች አይደለም። ስለሆነም የስር ፍ/ቤት 1ኛ ተጠሪን በተመለከተ የጉዲዩ ይዘት በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1225 እና 1226 ድንጋጌ ስር የተመለከተውን የሚመለከት ሆኖ እያለ በይዞታ ላይ ሁከት ሲፈጠር የይርጋ ጊዜን የሚመለከተውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ውሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተናል።
2ኛ ተጠሪን በተመለከተ የተሰጠውን ውሣኔ ስንመለከተው የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ የሰጠው ተጠሪ ስለንግድ ፈቃድ አሰጣጥና ምዝገባ በወጣው አዋጅ መሰረት መሟላት ያለባቸው ነገሮች ሲሟለ ፈቃድ የመስጠት በኋላም ጉድለት ካገኘ የማገድና የመሰረዝ ሥልጣን አለው እንጂ የከተማውን የቦታና መሬት አጠቃቀም የመወሰን ሥልጣን የለውም በሚል ምክንያት ነው። የአሁኑ አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ላይ የስር ፍርድ ቤት ይርጋን አስመልክቶ የሰጠውን ውሳኔ ስህተት ነው የሚለበትን ምክንያት ከመዘርዘር ውጪ 2ኛ ተጠሪን በተመለከተ የተሰጠው ውሳኔ የሕግ ስህተት ያለበት መሆኑን በመግለጽ ቅሬታቸውን አልዘረዘሩም። በልላ በኩል ይህ ችልት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 67/89 ሲመለከተው የንግድ ፈቃደን የተሰጠው ሰው በልላ ሰው ላይ በስራ በሚፈጥረው ረብሻ የንግድ ፈቃድ የሰጠው አካል ሉሰርዘው የሚገባ ስለመሆኑ የማይደነግግ መሆኑን ከአዋጁ አንቀጽ 10 ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻል መሆኑን ተገንዝቧል። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የደረሰበት መደምደሚያ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አላገኘነውም። ሲጠቃለልም ከላይ በተመለከቱት ሕጋዊ ምክንያቶች ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መ/ ሰኔ 26 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ኀዲር 24 ቀን 2001 ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
የአመልካች ጥያቄ በይርጋ የሚታገድበት ምክንያት ስለላለ 1ኛ ተጠሪ በሚሰሩት የብየዲ ሥራ የሚሰማው ድምጽ ከመጠን በማለፍ ወደ አመልካች መኖሪያ ዘልቆ ሁከት የሚፈጥር መሆን ያለመሆን፣ለመከላከል ያደረጉት ነገር መኖር ያለመኖሩን፣ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1225 ድንጋጌ አኳያ በመመልከት ጉዲዩ ላይ ተገቢው ውሳኔ እዱሰጥበት ለፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341/1/ መሰረት መልሰንለታል።
2ኛውን ተጠሪ በተመለከተ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ተዘገቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.