No summary available.
ጥቅምት 18 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- ዓብደል መሐመድ - ጠበቃ አሰፊ መኮንን - ቀረበ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዘበናይ ኃይላ - ቀረበች።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የቤት ሽያጭ ውልን መሰረት ያደረገ ክርክርን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ ከሣሽ የነበረችው ተጠሪ ናት። ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተችው ከሟች እህቴ በኑዛዜ የወረስኩትን ቤት ከሕግ ውጪ ይዞ ስለሚገኝ ለቆ ያስረክበኝ ዘንድ ይወሰንልኝ በማለት ነው።
አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የሥረ ነገር ክርክር አቅርበዋል።
መቃወሚያዎቹ ተጠሪ ክስ ለመመስረት የሚያስችል መብት የላትም እንዱሁም ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል የሚለ ሲሆን፣ ሥረ ነገርን በተመለከተም ቤቱ ከወ/ሮ ንጋቷ /ሟች/ በብር 25ዐ000 በውል ገዝቼዋለሁ። ከዋጋው ውስጥ ብር 24ዐ000 በመክፈል ቤቱን ተረክቤአለሁ። ከሣሽም ጉዲዩን /ውለን/ ለማስፈጸም ብር 4ዐ000 ከኔ ወስዲለች የሚለትን ነጥቦች ማንሳቱን ተመልክተናል። ከዚህም በተጨማሪ የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ አቅርቦ ተጠሪ በውለ መሰረት የማስፈጸም ግዳታ ያለበት በመሆኑ የቤቱን የባለቤትነት መብት እና ካርታ በስሜ እንድታስተላልፍ ይወስንልኝ በማለት ዲኝነት ስለመጠየቁ ከመዝገቡ አረጋግጠናል። ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ የሁለቱንም ወገኖች ክርክር መርምሮአል።
በመቀጠልም የአመልካችን ክርክር ሙለ በሙለ ውድቅ በማድረግ ቤቱን ለተጠሪ እንዱያስረክብ በማለት ወስኖአል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይግባኝ የተባለበት ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሰርዞታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች የካቲት 22 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል የሚልበትን ምክንያት በመግለጽ ስህተቱ ይታረምለት ዘንድ አቤቱታ አቅርቦአል። እኛም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተደረገው አመልካች ያቀረበውን የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ ለሕጉ የተሰጠው ትርጓሜን አግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም አመልካች እና ተጠሪ በጭብጥነት የተያዘውን ነጥብ በሚመለከት ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
እንደምንመለከተው አመልካች ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል በማለት መቃወሚያ ያቀረበው ከሟች ጋር በተደረገው የቤት ሽያጭ ውል መሰረት ገንዘቡን ከፍዬ ቤቱን ተረክቤያለሁ የሚልበትን ጊዜ መነሻ በማድረግ ነው። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሰጠው ውሣኔ ይዘት መገንዘብ እንደቻልነው የቤት ሽያጭ ውለ የተደረገው በ1988 ዓ.ም. ሆኖ ተጠሪ ክስ የመሰረተችው ደግሞ በ2ዐዐ1 ዓ.ም. ነው። ተጠሪ ክሱን የመሰረተችው የሽያጭ ውለን ሳታስፈርስ እንደሆነም መዝገቡ ያመለክታል። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካችን የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1168 በተደነገገው መሰረት ለ15 ዓመት ግብር በተከታታይ ከፍል ቤቱን ስለመያዙ አላስረዲም የሚል ምክንያት በመስጠት እንደሆነም ከውሣኔው ለመገንዘብ ችለናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቤቱን ይዞ የሚገኘው አመልካች ላቀረበው የይርጋ መቃወሚያ አወሳሰን ተገቢነት አለው በማለት የጠቀሰው የፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1168 ‛ስለግል ሃብት“ በተመለከተ በተደነገገው በፍትሐብሕር ሕግ በአንቀጽ 7 ሥር ነው የሚገኘው። የዚህ አንቀጽ አንደኛው ክፍል የሆነው ምዕራፍ 1 ሀብት ስለሚገኝበት ሁኔታ፣ ሀብትን ስለማስተላለፍ እንዱሁም ሀብት ስለሚቀርበት እና ስለ ሀብትነት ማስረጃ የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን አካቶ የያዘ ሲሆን፣ ከፍ ሲል የተጠቀሰው ቁ. 1168 በተለይ የሚገኝበት የምዕራፈ ክፍል 1 ደግሞ ሀብት ስለሚገኝበት ሁኔታ የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን ይዞአል። በዚህ መሰረትም የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለይዞታ የሆነ ሰው በንብረቱ ላይ የባሃብትነት መብት የሚያገኝበት ሁኔታ በቁጥር 1168 ተደንግጎአል። በዚህ ድንጋጌ የተቀመጠው መርህ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት በይዞታው ሥር ያደረገው ሰው የዚህኑ ንብረት ግብር ባለማቋረጥ አሥራ አምስት /15/ ዓመት በስሙ ከከፈለ የንብረቱ ባለቤት እንደሚሆን ነው የሚያመለክተው። በመሆኑም የማይንቀሳቀሰውን ንብረት የያዘው ሰው ንብረቱን እንዱለቅ ሲከሰስ ድንጋጌውን በመጥቀስ ሉከራከር የሚችለው በድንጋጌው የተመለከቱትን ሁኔታዎች አሟልቶ በመያዙ የንብረቱ ባለሃብት መሆኑን ለማረጋገጥ እንጂ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል ለማለት አይደለም። የይርጋ መርህ ክስን በተወሰነ የጊዜ ገደብ ቀሪ የሚሆንበትን አግባብ የሚመለከት በመሆኑ ንብረትን በመያዝ ወይም ባለይዞታ በመሆን የባለሃብትነት መብት ከሚገኝበት መርህ ወይም አግባብ የተለየ ነው።
No topics extracted.
ስለዚህም የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1168/1/ የተመለከተውን ድንጋጌ ለይርጋው መቃወሚያ አወሳሰን መሰረት ማድረጉ ትክክል ሆኖ አላገኘነውም።
በመቀጠል የተመለከትነው አመልካች ያቀረበው የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ የሚደረግበት የሕግ ምክንያት አለ ወይ? የሚለው ነጥብ ነው። አመልካች ቤቱን የያዘው ከሟች ወ/ሮ ንጋቷ ሃይላ (ተጠሪ አውራሼ ናት የምትላት) ጋር በ1988 ዓ.ም ባደረገው የቤት ሽያጭ ውል መሰረት ነው። ይህ ፍሬ ነገር በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ግንዛቤ እንደተወሰደበት ከውሳኔው ለመገንዘብ ችለናል።
በልላ በኩል ግን የሺያጭ ውለ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723 በተደነገገው መሰረት በውል አዋዋይ ፉት ያልተመዘገበ በመሆኑ ለአመልካች የሚሰጠው መብት የለም፤በሻጭም ሆነ በወራሽ (ተጠሪ) ላይም የሚያስከትለው ግዳታ የለም፤ በአጠቃላይ ውለ ሕጋዊ ውጤት የለውም የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት ፍ/ቤቱ የአመልካችን ክርክር ውድቅ አድርጏአል። በእርግጥ ፍ/ቤቱ የይርጋውን መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው ከላይ በተገለጸው ምክንያት በመሆኑ ውለ በሕጉ የተቀመጡትን የፍርም ሁኔታዎች (መስፈርቶች) አያሟላም ከሚለው ትችቱ ጋር አላያያዘውም። ይሁንና ትችቱ የሽያጭ ውል መደረጉን ስለሚያመላክት የአመልካችን የይርጋ መቃወሚያ በመወሰን ረገድ ጠቃሚ ፍሬ ነገር ነው።
ቀደም ሲል እንዲመለከትነው ተጠሪ በክስዋ ያቀረበችው የዲኝነት ጥያቄ አመልካች ቤቱን ያስረክበኝ የሚል ነው። አመልካች ደግሞ ተጠሪ ቤቱን ልትረከብ ይገባል ወይስ አይገባም የሚለው የሥረ ነገር ጭብጥ ከመታየቱ በፉት ውሳኔ ሉያገኝ የሚገባው የይርጋ መቃወሚያ አቅርቦአል።
በመሆኑም ተጠሪ የአመልካችን የይረጋ መቃወሚያ ውድቅ ታስደርግ ዘንድ በቅድሚያ ይጠበቅባታል።
አመልካች ቤቱን የያዘው በውል እንደመሆኑ ውለ ፈራሽ ነው ወይም ተሰርዞአል ሳይባል እንዱለቅ የሚደረግበት አግባብ የለም። በእርግጥ አመልካች በመከራከሪያነት ያቀረበው ውለ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723 በተደነገገው መሰረት አልተደረገም ተብልአል። የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትን ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል በጽሐፍ እና ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው ሰው ፉት ወይም በፍ/ቤት ካልተደረገ ውጤት እንደማይኖረው የተጠቀሰው ድንጋጌ ያመልክታል። በልላ በኩል ደግሞ በሕጉ የተመለከተውን የአፃፃፍ ሥርአት አለመከተል የሚያስከትለው ውጤት ምን እንደሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1808/2/ ተደንግጏአል። በዚህም መሰረት ይህን የመሰለ ውል የሚፈርሰው ከተዋዋዮቹ አንደ ወይም ማናቸውም ጥቅም ያለው ሰው ሲጠይቅ እንደሆነ ሕጉ ያመለክታል። ይህም የሚያስገነዝበን የአፃፃፍ ሥርአትን ያላሟላ ነው የተባለው ውል በሕጉ በተመለከቱት ሰዎች እንዱፈረስ ጥያቄ እስካልቀረበበት ድረስ ከጅምሩ ፈራሽ ነው ልባል እንደማይችል ነው። ውለ እንዱፈርስ የሚቀርበው ጥያቄም በጊዜ የተገደበ ነው። የአፃፃፍ ሥርአቱን ያልተከተለ ውል እንዱፈረስ ጥያቄው መቅረብ ያለበት በአሥር /10/ ዓመት ጊዜ ውስጥ ስለመሆኑም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1808/2/ እና 1845 ከተቀመጡት ድንጋጌዎች መንፈስ እና ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስ የቤት ሽያጭ ውለ የተደረገው መስከረም 12 ቀን 88 ሆኖ ተጠሪ ክስ የመሰረተችው ደግሞ ጥር 12 ቀን 2001 ዓ.ም እንደሆነ መዝገቡ ያመለክታል። ይህም ማለት ክሱ የቀረበው ውለ ከተደረገ ከ13/ አሥራ ሦስት/ ዓመት በኋላ ነው ማለት ነው። ክሱን የሰማው ፍ/ቤት አመልካች ያቀረበውን የይርጋ መቃወሚያ አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች መሰረት አድርጏ ባለማየቱ ከተሳሳተ መደምደሚያ ላይ ሉደርስ ችልአል። ከፍ ሲል እንደገለጽነው ለተያዘው ክርክር አወሳሰን ተገቢነት ያላቸው ድንጋጌዎች የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1808/2/ እና 1845 በመሆናቸው አመልካች ያቀረበው መቃወሚያ ውድቅ የሚሆንበት ምክንያት የለም። ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ በሕጉ አተረጓጏም ረገድ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።