No summary available.
ኀዲር 14 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- እነ አቶ ሰናይ ልዐልሰገድ(ሁለት ሰዎች) - ጠበቃ መኮንን ሰሙ - ቀረቡ ተጠሪ፡- እነ ወ/ሮ ትእግስት ኃይላ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የውርስ ይጣራልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። ክርክሩ ሲጀመር አመልካች የነበሩት የአሁኑ አመልካቾች ሲሆኑ የአቤቱታቸው ይዘትም ባጭሩ፡- ወላጅ አባት የሆኑት አቶ ልዐል ሰገድ መዘምር ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውንና የሟቹን ንብረት የአሁኑ ተጠሪዎች ይዘው እንደሚገኙ ገልፀው ተጠሪዎች ተጠርተው ቀርበው የውርስ አጣሪ እንዱሾምና ውርሱ ተጣርቶ ሲቀርብ አስፈላጊው ውሳኔ እንዱሰጣቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው የቀረበለት ፍርድ ቤትም የአመልካቾችን አቤቱታ መርምሮ ውርስ አጣሪ የመሾም ሥልጣን የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ስልጣን ነው በማለት መዝገቡን በትእዛዝ ዘግቶታል። ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የስር ፍርድ ቤትን ትእዛዝ አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካቾች ጠበቃ የካቲት 04 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ አራት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታው ተመርምሮም የውርስ ማጣራት ጉዲይ በአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የዲኝነት ሥረ ነገር ሥልጣን ነው ተብል መወሰኑ ይህ ሰበር ችልት በመ/ ከሰጠው የሕግ ትርጉም አኳያ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጏላቸው ቀርበው ሚያዝያ 22 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። በመልሳቸው ላይም የሰበር ችልቱ በመ/ የሰጠው ትርጉም በመ/ የተለወጠና መለወጡም ባግባቡ መሆኑን ገልጸው የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እንዱፀና ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ይህ ችልት አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41 እና ስለውርስ አጣሪ በ1952 ዓ.ም በወጣው በፍትሐብሕር ሕጉ ውስጥ የተካተቱትን ድንጋጌዎችን በመመርመር ውርስ አጣሪን የመሾም ሥልጣን የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ መሆኑን በመግለጽ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2/4/ መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኘውን ፍርድ ቤት የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም በ
ጥቅምት 13 ቀን 2001 ዓ.ም፣በ
ኀዲር 29 ቀን 2002 ዓ.ም፣በ
ግንቦት 10 ቀን 2002 ዓ.ም እና በላልች በርካታ መዛግብት ሰጥቷል። ይህንኑ የሕግ ትርጉም አለመለወጡንም ይህ ችልት በ
ግንቦት 10 ቀን 2002 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ በግልጽ አረጋግጧል፣ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2/4/ ስር የተመለከተው ድንጋጌ ችልቱ በልላ ጊዜ በተመሳሳይ ጭብጥ የተለየ ትርጉም ላሰጥ እንደሚችል የደነገገ ቢሆንም በዚሁ አግባብ ቀድሞ የተሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም በ
አልተለወጠም። በተያዘው ጉዲይም የስር ፍርድ ቤቶች ይህ ሰበር ችልት ከላይ በተጠቀሱት መዛግብት የሰጠው አስገዲጅ ውሳኔ በሕጉ አግባብ ባልተለወጠበት ሁኔታ ጉዲዩን የማየት የስረ ነገር ዲኝነት ሥልጣን ያላቸው የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ናቸው በማለት የአመልካቾችን አቤቱታ ሳይቀበለ መቅረታቸው ተገቢ ሁኖ አልተገኘም። ማንኛውም ፍርድ ቤት አንድ ጉዲይ ሲቀርብለት ጉዲዩን የማየት ሕጋዊ ስልጣን ያለው መሆኑን በቅድሚያ ሉያረጋግጥ ይገባል። ስልጣኑ የሆነውን ጉዲይ ደግሞ ከሕጉ አግባብ ውጪ በሆነ ምክንያት አልተመለከትም ሉል አይችልም። በመሆኑም የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41/ለ/ሸ/ እና አዋጅ ቁጥር 408/96 መሰረት የወራሽነት የምስክር ወረቀት ከመስጠት በስተቀር ውርስ እንዱጣራ አጣሪውን የመሾም የስረ ነገር ሥልጣን የላለው ስለመሆኑ ተገልፆ በዚህ ሰበር ችልት የተሰጠው የሕግ ትርጉም በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2/4/ መሰረት ባልተለወጠበት ሁኔታ የከተማው ፍርድ ቤት ውርስ አጣሪ የመሾም ሥልጣን አለው ተብል በበታች ፍርድ ቤቶች መወሰኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ አግኝተናል።
የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. በ21/11/2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ እንደዚሁም የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 83998 ታህሳስ 28 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በድምጽ ብልጫ ተሽሯል።
የውርስ አጣሪ የመሾም የስረ ነገር ዲኝነት ሥልጣን የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ነው ብለናል።
የውርስ ይጣራልኝ አቤቱታ የሚቀርበውና ውርስ አጣሪውንም መሾም በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት የሥረነገር ሥልጣን ሥር ስለሚወድቅ የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ጉዲዩን ተቀብል እንዱመለከት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 341 መሰረት ተመልሶለታል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ ይቻቻለ።
No topics extracted.