No summary available.
መጋቢት 5 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ አሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዐቃቤ ሕግ ታደሰ ተስፊዬ - ቀረበ።
ተጠሪ፡- አይንሸምስ ሁሴን አብደላ - ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ ለሰበር የቀረበው ክርክር በወንጀል ክስ ምክንያት በኤግዚቢትነት ተይዞ የቆየውና በኋላ ከወንጀለ ክስ በነፃ ለተሰናበቱት ለአሁኑ ተጠሪ ይመለስ የተባለው የአፈር ወርቅ ይዞት በቆየው አካል በአሁኑ አመልካች ተሸጦ ከተገኘ ለወርቁ ባለቤት ሉከፈል የሚገባው ተሸጧል የተባለበት ዋጋ መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነው።
የአሁኑ ተጠሪ 2512 ግራም የአፈር ወርቅ በህገወጥ መንገድ ደብቆ ሉያሣልፍ ሲል ተይዟል ተብል በቀረበበት የወንጀል ክስ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክርክርና ማስረጃዎቹን መርምሮ ወንጀለን መፈፀሙ ተረጋግጧል ብል ጥፊተኛ በማድረግ በኤግዚቢትነት የተያዘው የአፈር ወርቅም እንዱወረስ ወስኖ የነበረ ቢሆንም ጉዲዩን በይግባኝ ያየው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሣኔ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በመሻር ከክሱ በነፃ እንዲዱሰናበት ፣ በኤግዚቢትነት ተይዞ የቆየው የአፈር ወርቅም ለአሁኑ ተጠሪ እንዱመለስለት ወስኗል።
ይህ የከፍተኛው ፍ/ቤት ውሣኔ ይግባኝ ተብልበት የተለወጠ ባለመሆኑ ኤግዚቢቱ ይመለስልኝ የሚለውን ጥያቄ የአሁኑ ተጠሪ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረበው ሲሆን የአሁኑ አመልካች ቀርቦ ሲጠየቅ የአፈር ወርቁን በወቅቱ በነበረው ዋጋ እክፍላለሁ የሚል መልስ ሰጥቷል። የአሁኑ ተጠሪ አመልካች የአፈር ወርቁን ዋጋ እከፍላለሁ ያለውን ቢቀበለትም የሚከፈለው በወቅቱ በነበረው ዋጋ ነው በሚለው ላይ ሣይስማሙ ቀርተዋል። ፍ/ቤቱም የአሁኑ አመልካች ገንዘቡን የምከፍለው በወቅቱ በነበረው ዋጋ ነው ያለው ተገቢ አይደለም በማለት ታህሣሥ 1ዐ ቀን 2000 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ዋጋው ታስቦ ለአሁኑ ተጠሪ መክፈል ይገባዋል የሚል ትእዛዝ ሰጥቷል።
በዚህ ትዕዛዝ ላይ ይግባኙ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ግራቀኙ እንዱቀርቡ አድርጏ በጉዲዩ ላይ ካከራከረ በኋላ መርምሮ በሰጠው ፍርድ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠው ትዕዛዝ ጉድለት የለበትም በማለት አጽንቶታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ አመልካች የአፈር ወርቁን ዋጋ መክፈል ያለበት በወቅቱ በነበረው ዋጋ መሰረት ሣይሆን በኋላ ትዕዛዝ በተሰጠበት ጊዜ በነበረው የገበያ ዋጋ መሰረት ነው በሚል የተሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት የቀረበ ሲሆን አቤቱታው ተመርምሮ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ ተብል በመታዘዙ ማመልከቻው ለአሁኑ ተጠሪ ተልኮ ቀርቦ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጓል። በዚህም መሰረት ተጠሪ በጽሐፍ በሰጠው መልስ የአሁኑ አመልካች በወቅቱ የአፈር ወርቁ የተሸጠበትን ዋጋ እከፍላለሁ በማለት የጠየቀው ተቀባይነት ሉሰጠው አይገባም፣ ወርቁን በአይነት መመለስ ካልቻለ በጊዜው በወጣው የብሓራዊ ባንክ በሚሰጠው ዋጋ መሰረት መክፈል ይኖርበታል በማለት ተከራክሯል። በተጠሪ በኩል በጽሐፍ የተሰጠው መልስ ለአመልካች የተሰጠ ቢሆንም ከመዝገቡ እንደሚታየው በጽሐፍ ያቀረበው የመልስ መልስ የለም።
የጉዲዩ አመጣጥና የክርክሩ ይዘት ከዚህ በላይ እንደተመለከተው ሲሆን ይህ የሰበር ችልቱም ጉዲዩን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
የአሁኑ አመልካች ለአሁኑ ተጠሪ መክፈል የሚገባው የኤግዚቢቱ የአፈር ወርቅ ዋጋ በወቅቱ ሽጫለው የሚልበትን ዋጋ ነው ወይንስ በኋላ ፍ/ቤት ወርቁን መመለስ አለበት የሚል ትዕዛዝ በሰጠበት ጊዜ የነበረውን ዋጋ ነው? የሚለውን ዋናውን የክርክር ጭብጥ በተመለከተ፡የአሁኑ አመልካች ሐምል 27 ቀን 2002 ዓ.ም ተጽፍ ባቀረበው የሰበር ማመልከቻው ላይ በኤግዚቢትነት ተይዞ የቆየውን የአፈር ወርቅ ሉሸጠው የቻለው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁኑን ተጠሪ በወንጅለ ጥፊተኛ በማድረግ መጋቢት 22 ቀን 1997 ዓ.ም ወርቁ እንዱወረስ በማለት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት መሆኑንና ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ወርቁ እንዲይሸጥ የሚል ትዕዛዝ ያስተላለፈው ወርቁ በውርስ ውሣኔው መሰረት እንዱሸጥ ከተደረገ በኋላ ሰኔ 15 ቀን 1997 ዓ.ም እንደሆነ የገለጹ ሲሆን የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም የካቲት 29 ቀን 2002 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል። የአሁኑ ተጠሪ ይህንን በሚመለከት በጽሐፍ ባመጣው መልስ ላይ የአሁኑ አመልካች ወርቁን የሸጠው መቼ ነው? ከፍ/ቤቱ ዕግድ በኋላ ወይንስ በፉት? የሸጠውስ በምን ያህል ነው? የሚለውን በሚስጥር ይዞ ስለማቆየቱና ክርክሩም በማስረጃ የተደገፈ እንዲልሆነ ገልጿል ከማለት በቀር አመልካች ወርቁን የሸጠው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዲይሸጥ የሚል የዕግድ ትዕዛዝ ከሰጠና ከደረሰው በኋላ ነው በሚል በግልጽ ያቀረበው ክርክር የለም በግልጽ ያልተካደ ፍሬ ነገር ደግሞ በሕጉ እንደታመነ የሚቆጠር ነው።
አመልካች በኤግዚቢትነት ይዞ የቆየውን የአፈር ወርቅ ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ወርቁ እንዲይሸጥ በማለት የዕግድ ትዕዛዝ ከመስጠቱ በፉት አሰቀድሞ የፋዳራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪን በወንጀለ ጥፊተኛ በማድረግ ወርቁ ይወረስ ብል በሰጠው የውርስ ወሣኔ መሰረት የሸጠው መሆኑ የታመነ ሆኖ ከተገኘ አመልካች ለተጠሪ ለመክፈል የሚገደደው በወቅቱ ወርቁን የሸጠበትን ዋጋ ነው።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን በይግባኝ አይቶ ተጠሪን ከወንጀል ክሱ በነፃ በማሰናበት ወርቁ ይመለስለት ብል ባዘዘበት ጊዜ በነበረው የገበያ ዋጋ መከፈል አለበት በሚል የቀረበው ክርክር በሕጉ ተቀባይነት የሚሰጠው አይደለም። የሥር ፍ/ቤቶች በዚህ ረገድ የሰጡት ውሣኔም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስለተገኘ ሉታረም የሚገባው ነው። በዚህም ምክንያት የሚከተለው ተወስኗል።
1ኛ) የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ/43191 የካቲት 29 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ እና 2ኛ) የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮ/መ/ቁ. 90395
No topics extracted.