No summary available.
ጥቅምት 04 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ወ/ሮ ሰናይት ተመስገን - ጠበቃ አልታዬ ወ/አማኑኤል - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ እጥፍወርቅ በቀለ - ጠበቃ አስናቀ ከፊለ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቤት ይለቀቅልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁኗ ተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ ነው። ክሱ ታህሣሥ 09 ቀን 1993 ዓ.ም የተፃፈ ሁኖ አመልካች የሟች አባታቸው የአቶ ተመስገን በቀለ ወራሽ መሆናቸውን በመግለጽ ሟችና ተጠሪ (በስር ተከሳሽ) በውርስ የተላለፈላቸውን በወረዲ 23፣ቀበላ 13፣የቤት ቁጥር 1597/ለ/ እና /ሀ/ እንዲላቸውና ይህም መጋቢት 22 ቀን 1988 ዓ.ም በተፃፈ የቦታ መለያ ውል ድርሻ ድርሻቸውን ተከፊፍለው ከቆዩ በኋላም ሟች ከሞቱ ጊዜ ጀምሮ ተጠሪ የሟችንም ድርሻ ጠቅልለው በመያዙ ክሱ እስከቀረበበት ጊዜ ድረስ .00(ሰላሳ ሺህ አንድ መቶ ብር) የኪራይ ገቢ እንዲገኙና የሟች የተለያዩ ቁሳቁሶችንም እንደያዙ በመዘርዘር ተጠሪ ክስ የቀረበበትን የኪራይ ገንዘብ እንዱከፍለ እና ቁጥሩ 159/ለ/ የሆነውን እንዱያስረክቡ ይወሰንላቸው ዘንዲ ዲኝነት ጠይቀዋል።
ለማስረጃነትም የሰነድና የሰው ምስክሮችን ዘርዝረው አቅርበዋል። የአሁኗ ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መከላክያ መልስም ክሱ ያለ ማስረጃ የቀረበ ነው፡የውርስ ክፍፍል አላደረግንም፣እንዱያ ቢሆን ኑሮ ላልች ወንድሞቻችን በተካፈለ ነበር፣ መጋቢት 22 ቀን 1988 ዓ.ም የተደረገው የአጥር መለያ ጊዜአዊ ስምምነት ነው፣ ከሳሽን ባለቤትና ባለቦታ የሚያደርግ ካርታ ወይም ደብተር አላቀረቡም፣ክስ የቀረበበትን ቤት ተረክቤ የማስተዲድረው ሆኖ ሳለ ኪራይ ልጠየቅ አይገባም፣የቤት ቁሣቁስ አልተረከብኩም፣ቤቱን ግን ሟች ከሞተበት ጊዜ ጀምሮ ተረክቤ አስተዲድራለሁ፣ የቤት ቁጥር 1597/ለ/ እና /ሀ/ ሟች 600 ካ. ሜትር የቦታ ስፊት ጋር እናቴ ሐምል 3 ቀን 1957 የሰጡኝና ቤቱም በራሴ ገንዘብ የተሰራ በመሆኑ የግል ቤቴ ነው፣ካርታና ደብተር ለመቀበልም በመጠባበቅ ላይ እገኛለሁ በማለት ዘርዝረው የአመልካች ክስ ያለምንም ሕጋዊ ማስረጃ የቀረበ ነው ተብል ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክረዋል። ለማስረጃነትም የሰነድና የሰው ምስክሮችን ዘረዝረው አቅርበዋል።
የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ጉዲዩን ከመመረመረ በሁዋላ ከ600 ካ.ሜትር ውጪ ያረፈውና መጋቢት 22 ቀን 1988 ዓ.ም በአጥር የተለየው አከራካሪው ቤት ቁጥር 1597/ለ/ ወይም 1597/2/ በሚል የሚታወቀው ቤት የሟች አቶ ተመስገን በቀለ በመሆኑ ቤቱን የሟች ወራሽ ለሆኑት የአሁኗ አመልካች ተጠሪ ሉያሰረክቡ ይገባል፣ የኪራይ ገንዘብና የቤት ቁሳቁስን በተመለከተ የቀረበው ክስ ግን በማስረጃ የተደገፈ ስላልሆነ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል።
የአሁኗ ተጠሪ ቤቱን ሉያስረክቡ ይገባል ተብል በተወሰነው የውሳኔ ክፍል፣ የአሁኗ አመልካች ደግሞ የቤት ኪራይ ገንዘብንና የቤት ቁሳቁስን በተመለከተ በተሰጠው የውሳኔ ክፍል ባለመስማማት የየራሳቸውን ይግባኝ ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ እና ተገቢው መጣራት ተደርጏ የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎች ከቀረቡ በሁዋላ የይግባኝ መዛግብቱ ተጣምረው ጉዲዩ ከተመረመረ በሁዋላ አመልካች ያቀረቡት ይግባኝ ውድቅ ሲደረግ የተጠሪ ተቀባይነት አግኝቶ አከራካሪው ቤት የተጠሪ እንጂ የአመልካች አውራሽ አይደለመ ተብል ተወስኗል። አመልካች ቤቱ የተጠሪ ነው ተብል በተሰጠው የውሳኔ ክፍል ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቢያቀርብም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች መጋቢት 11 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት አንድ ገጽ የሰበር አቤቱታ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- አከራካሪው ቤት የአውራሻቸው መሆኑ ተረጋግጦ እያለ ይግባኙን የሰማው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር በመተው እና በይግባኝ ጊዜ ከሥነ ሥርአቱ ውጪ ተጨማሪ ማስረጃ እንዱቀርብ አድርጏ እንዱሁም የተጨማሪ ማስረጃዎችን ይዘት ባግባቡ ባላገናዘበ መልኩ ማስረጃውን መዝኖ የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ መሻሩ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት ውሳኔው ተሽሮ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዱጸናላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮ ተጠሪ አቶ ተመስገን በቀለ ከሞቱ በሁዋላ ያዙት የተባለውና ከይዞታቸው 600 ካ.ሜትር ውጪ ያለ እንዱሁም መጋቢት 22 ቀን 1988 ዓ.ም በተደረገ ስምምነት የተለየው በቀድሞው ወረዲ 23፣ቀበላ 13 ክልል ውስጥ የሚገኘው ቁጥሩ 1597/ለ/ ወይም 1597/2/ የሆነውን ቤት ለአመልካች ሉያስረክቡ አይገባም የተባለው በጉዲዩ ላይ የቀረቡትን ክርክርችንና ማስረጃዎችን ይዘት ባገናዘበ መልኩ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጏ የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ታህሣሥ 01 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰምቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ዲኝነት የጠየቁበት ቤት የአውራሻቸው የሟች አቶ ተመስገን በቀለ መሆኑን ገልጸው ሲሆን ተጠሪ ቤቱን ሟች በሕይወት እያለ ሲኖሩበት የነበረና ከሕልፈተ ሞታቸው በሁዋላ ተረክበው ማስተዲደር የጀመሩት መሆኑን እንዱሁም መጋቢት 22 ቀን 1988 ዓ.ም የተደረገው ስምምነት መኖርን ሳይክደ ቤቱን የሰሩት ሟች ሳይሆኑ ተጠሪ በግል ገንዘባቸው የሰሩት የግል ንብረታቸው መሆኑንና ምንጩም ሐምል 03 ቀነ 1957 ዓ.ም የተሰጣቸው የስጦታ ወለ መሆኑን ገልፀው የሚከራከሩ መሆኑን፣የግራ ቀኙ ምስክሮች በስር ፍርድ ቤት ቀርበው መሰማታቸውን ነው። የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለውሳኔው መሰረት ያደጋቸው ምክንያቶች የተጠሪ ቤት በ600 ካ.ሜትር ቦታ ላይ ማረፈ በቀረበው ካርታ ተረጋግጧል፣በቀበላው የቤት ቁጥር 1597/ለ/ በሚል የሚታወቅ ቤት ከካርታው ክልል ውጪ ያለና ተጠሪ እና የአመልካች አባት መጋቢት 22 ቀን 1988 ዓ.ም የይዞታ ስምምነት ያደረጉበት የአመልካች አውራሽ ቤትና ይዞታ በመሆኑ የተጠሪ ይዞታ አይደለም፣ በ1992 ዓ.ም በቤት ቁጥር 1597/2/ የተሰጠው የግብር ሂሳብ ማስታወቂያ የአመልካች አባት ካፈሩት በኋላ ለተጠሪ መመዝገቡን የሚያስገነዝብ ነው፣ ማስታወቂያው ለአመልካች አባት ይዞታው በ1980 ዓ.ም መሰጠቱንና የተጠሪ ይዞታ ከሆነው ከ600 ካ.ሜትር ውጪ መሆኑን ያሳያል የሚለ መሆናቸውንም ከመዝገቡ ተመልክተናል። በእነዚህ ምክንያቶች የቤት ቁጥር 1597/ለ/ ወይም 1597/2/ የሆነውን ተጠሪ ለአመልካች እንዱያስረክቡ ሲል የሰጠውን ውሳኔ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሻረው በ28/2/92 ዓ.ም በተወሰደ የቦታ ልኬት የቦታ ስፊት ልዩነት መገኘቱ ለአመልካች አውራሽ ለቤት ቁጥር 1597/ለ/ የይዞታ ማረጋገጫ ላሆን እንደማይችል፣ የግብር ማስተወቂያው ለአመልካች አባት በወርስ የተላለፈላቸው ሃብት ስለመኖሩና ለዚሁ የተሰጠ የይዞታ ማረጋገጫ ተደርጏ ለወሰድ የማይችል መሆኑን፣ መጋቢት 22 ቀን 1988 ዓ.ም ተደረገ የተባው ስምምነትም የድንበር መለያ ስምምነት እንጂ የውርስ ሃብት ድርሻ ክፍፍል የተደረገበት አለመሆኑን፣ ቤቱን የአመልካች አባት በውርስ ወይም በስጦታ አግኝተውት ባለሃብት ስለመሆናቸው የቀረበ የማስረጃ የለም፣ የአመልካች አባት በ30/05/1982 ዓ.ም ለሚኖሩበት ሰርቪስ ቤት ቁጥር እንዱሰጥ ጠይቀው በኮሚቴ 1597/ለ/ የሚል ቁጥር መስጠቱና ውሃና መብራት መግባቱም የይዞታ ማስረጃ ላሆን እንደማይችል፣ የንፊስ ስልክ ላፍቶ አስተደደር ጽ/ቤት ኀዲር 20 ቀን 1998 ዓ.ም ለፍርድ ቤቱ በፃፈው ደብዲቤ ለአመልካች አባት በጠየቁት መሰረት ከመፈቀደ ውጪ የቦታ ይዞታ በተጠሪና በባለቤታቸው አቶ ከበደ ወ/ጊዮርጊስ ስም ብቻ መሆኑና በ1967 ዓ.ም የቤት ቁጠር ሲሰጥም የተሰጠው ቁጥር 1597 ሆኖ በተጠሪና በባለቤታቸው ስም መሆኑን ማረጋገጡን፣የክፍለ መሬት አስተዲደር ጽ/ቤት ታህሣሥ 06 ቀን 1998 ዓ.ም ለፍርድ ቤቱ በፃፈው ደብዲቤ የይዞታው አመጣጥ ተጠሪ ከእናታቸው በስጦታ ያገኙት መሆኑና በማህደር ውስጥ የቤት ቁጠር 1597 የሚል ከመሆኑ ውጪ በ/ሀ/ እና በ/ለ/ የተለየ ቤት ቁጥር የሚያሳይ ማስረጃ አለመኖሩን እንዱሁም በአሁኑ ወቅት ይዞታው በካርታ ቁጠር 05/203/11862/00 በተጠሪ፣ በግዛቸው በከበደና በትዘታ አበበ መመዝገቡን ማረጋገጡን፣ተጠሪ ከ1968-1992 ዓ.ም ድረስ በቤት ቁጥር 1597/2/ ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረባቸውን፣ የካቲት 17 ቀን 1998 ዓ.ም የመሬት አስተዲደር ጽ/ቤት ለፍርድ ቤቱ በፃፈው ደብዲቤ በተጠቀሰው ካርታ ውስጥ የቤት ቁጥር 1597/ለ/ የሚል ቤት አለመኖርንና በግቢው ውሥጥ የቤት ቁጠር 1579/2/ ራሱን የቻለ ቤት እንደሚገኝ ሪፕርት የቀረበለት መሆኑን ማረጋገጡን፣የአመልካች ምስክሮች የአመልካች አባት ቤት ሲሰራ አየን ባለበት ግቢ ውስጥ ላልች ቤቶች መኖራቸውን፣የተሰራው ቤት፣የቤት ቁጥር እና ቦታው የማን እንደሆነ እንደማያውቁ የመሰከሩ ናቸው፣በተጠሪ፣በግዛቸው ከበደና ትዝታ አበበ ስም የተመዘገበ የቤት ቁጥር 1597 ካርታ ይዞታ 666 ካ.ሜትር መሆኑ ተረጋግጧል የሚለትን ምክንያቶችን በመያዝ ነው።
እንግዱህ የበታች ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር ደረጃ ያጣሩት ነጥብና ማስረጃውን በመመዘን የደረሱበት ድምዲሜ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችልት ጉዲዩን እንዱመረምር ጉዲዩ ለችልቱ ሲቀርብ የተያዘው ጭብጥ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ያገናዘበ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ተብል ነው። በዚህ ችልት የግራ ቀኙ ክርክር ሲያደርጉ የተጠሪ ጠበቃ የተያዘው ጭብጥ የማስረጃ ጉዲይ በመሆኑ በሰበር ችልት ላታይ የሚገባው አይደለም በማለት ተቃውሞ አቅርበዋል። በእርግጥ ይህ ሰበር ችልት ሉመለከተውና ማረም የሚገባው ጉዲይ የማስረጃን ጉዲይ ሳይሆን በማናቸውም የመጨረሻ ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መፈጸሙ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ድ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 ይዘትና መንፈስ የሚያስገነዝበን ጉዲይ ነው። በተያዘው ጉዲይ የሰበር ችልት እንዱመለከተው የተያዘው ጭብጥ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ በጉዲዩ ላይ የቀረበውን የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ይዘት ባግባቡ ያገናዘበ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር እንጂ የማስረጃውን ክብደት ወይም ታአማኒነት ለመመርመር ተብል አይደለም። አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩትም በጉዲዩ ላይ የቀረቡት የሰው ምስክሮች አከራካሪው ቤት በሟች አባቱ የተሰራ መሆኑን የሚያረጋግጡ ሁነው እያለ እና የሰነድ ማስረጃዎች ይዘትም ይህንኑ የሚደግፍ ሁኖ እያለ በአግባቡ ሳይታይ ታልፎል በሚል ነው። በመሆኑም ሉነሣ እና ላታይ የሚገባው ጭብጥ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ የቀረቡት ማስረጃዎችን ይዘት መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም የሚል ሲሆን ለክርክሩ የቀረቡት ማስረጃዎች ይዘት ወይም በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠው ነጥብ ከሕጉ ጋር በአግባቡ ተዛምድ አልታየም የሚለው ቅሬታ የሕግ ነጥብ እንጂ የማስረጃ ምዘናን የሚመለከት ባለመሆኑ የተጠሪ ጠበቃ ጉዲዩ የማስረጃ ምዝና ስለሆነ በሰበር ችልቱ የሚታይ አይደለም በማለት ያቀረቡትን ክርክር አልተቀበልነውም።
ቀጥለን ተጠሪ ከ600 ካ.ሜትር ውጪ ያለውንና በመጋቢት 22 ቀን 1988 ዓ.ም በተደረገው ስምምነት በአጥር የተለየውን ቁጥሩ 1597/ለ/ ወይም 1597/2/ በሚል የሚታወቀውን ቤት ለአመልካች ሉያስረክቡ አይገባም ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ተመልክተናል።
አከራካሪው ቤት በአመልካች አባት የተሰራ ስለመሆኑ የአመልካች ምስክሮች ማረጋገጣቸውን የበታች ፍርድ ቤቶች የተቀበለት ፍሬ ነገር ነው። ተጠሪ ለአመልካች ክስ መልስ ሲሰጡ ቤቱ በገንዘባቸው የተሰራ መሆኑን ገልፀው የተከራከሩ ሲሆን ምስክሮቻቸው ቤቱ በተጠሪ የግል ገንዘብ የተሰራ መሆኑን አስረድተዋል ወደሚለው ድምዲሜ የስር ፍርድ ቤቶች አልደረሱም። በመሆኑም ቤቱ በአመልካች አባት የተሰራ መሆኑ በሰው ምስክሮች የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። የአመልካች አባት የቦታውና የቤቱ ባለሃብት ስለመሆናቸው የሚያሳይ ማስረጃ የለም ተብል በፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ድምዲሜ የተያዘው የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎችን ይዘት በመመርመር ነው። አከራካሪው ቤት ተጠሪ ከእናታቸው በስጦታ ባገኙት ቦታ የተሰራ መሆኑ የተካደ አይደለም። ሆኖም ዋናው ነገር በቦታው ላይ ያለውን ቤት የሰራው ሰው ተጠሪ ወይስ? የአመልካች አባት? የሚለው ነው። ይህ ፍሬ ጉዲይ ደግሞ አመልካች ባቀረቧቸው የሰው ምስክሮች በሚገባ መረጋገጡን ሁለም የበታች ፍርድ ቤቶች የተቀበለት ነው። በሕጉ አግባብ የሚታወቀው ቦታ ቀድሞ የነበረው ስፊት እንደነበር፣ ስፊቱ በሁዋላ እየተቀነሰ ግብር ሲገበርበት የነበረ መሆኑም በሰነድ ማስረጃ ተረጋግጧል። የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሚመለከታቸው አካላት ተገቢው ማብራሪያ ማስረጃ እንዱቀርብ ትእዛዝ ሰጥቶ እነዚህ አካላት የቦታውን አመጣጥ፣ በቦታው ላይ በማህደር የሚታወቀው ቤት ቁጥር ስንት እንደሆነ፣ ካርታው በማን ስም እንደተመዘገበ እና ስፊቱ ስንት እንደሆነ መግለጫ መስጠታቸውን መሰረት በማድረግ አከራካሪው ቤት የአመልካች አውራሽ ስለመሆኑ ማስረጃ የለም ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰው ቤቱን ማን ሰራው? የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ፣ለጉዲዩ አወሳሰን ቁልፍ የሆነውን ፍሬ ነገርን በተመለከተ የቀረቡትን ማስረጃዎችን ይዘት ባግባቡ ሳይመረመር ነው። ተጠሪ ቦታውን በስጦታ አገኘሁ ከማለት ውጪ ቤቱን በግል ገንዘባቸው የሰሩት መሆኑን አላስረደም። መሬት የኢትዮጵያ ህዝቦችና የመንግስት ብቻ ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40/3/ በግልጽ ተመልክቷል። በልላ በኩል ሕገ መንግስቱ በተጠቀሰው አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ አንድ ስር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የግል ንብረት መሆኑ/መሆኗ በሕግ የተከበረለት መሆኑ የተደነገገ ሲሆን የግል ንብረት በጉልበት፣ በፈጠራ ችልታ ወይም በካፑታል የሚፈራ ስለመሆኑና ጥበቃም የሚደረግለት መሆኑን ንዐስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ያሳያል። ከዚህ ሁለ መገንዘብ የሚቻለው መሬት የመንግስት እና የሕዝብ ብቻ መሆኑን በጉልበት፣ በፈጠራ ችልታ ወይም በካፑታል የተፈራ ንብረት በሕግ ጥበቃ የተደረገ መሆኑ እንዱሁም በሕጉ አግባብ የተገኘ የመሬት ባለይዞታነት የሕግ ጥበቃ የሚደረግለት መሆኑን ነው።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1204 እና 1026 ስር የተመለከቱት ድንጋጌዎችም የባለቤትነት መብት የሕግ ጥበቃ ያለው መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው። በሕጉ አግባብ የተፈራ ንብረት ደግሞ ለሟች ወራሾች በውርስ ሉተላለፍ የሚችል መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 826/2/ ድንጋጌ ያስገነዝባል።
ተጠሪ ቦታውን በስጦታ ከእናታቸው ያገኙት ነው ቢባልም ባድ ቦታውን የአመልካች አውራሽ ይዘው ቤት ሲሰሩ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1178 እና 1179 መሰረት ተቃውሞ ያሰሙ ስለመሆኑ በመግለጽ ያቀረቡት ክርክር የለም። ተጠሪ በሕጉ አግባብ በተሰጣቸው ካርታ ውስጥ አከራካሪው ቤት ተሰርቷል ቢባል እንኳ ቤቱ በአመልካች አውራሽ ጉልበትና ገንዘብ ስለመሰራቱ እንዱሁም ተጠሪ በወቅቱ ተቃውሞ የነበራቸው አለመሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ የቦታው ካርታ አንድ ነው፣ ግብርም በዚሁ ካርታ መሰረት ስለመገበሩ ተረጋግጧል በሚል ምክንያት ብቻ ቤቱ የተጠሪ ነው ልባል የሚችል አይደለም። ተጠሪ ከአመልካች አባት ጋር መጋቢት 22 ቀን 1988 ዓ.ም ያደረጉት ስምምነት ሲታይም የድንበር መለየት ጉዲይን የሚመለከት ቢሆንም በቦታው ላይ ሁለት ቤቶች እንደነበሩ፣ የአመልካች አባት ይዘውት የነበረው ቤት ተጠሪ ከያዙት ከ600 ካ.ሜትር ውጪ ስለመሆኑ የሚያሳይ ሲሆን ስምምነቱ የውርስ ክፍፍል ስለመሆኑ የማያሳይ ቢሆንም አከራካሪው ቤት በአመልካች አባት አልተሰራም ለማለት ግን የሚያስችል አይደለም። ተጠሪ ቤቱን ከአመልካች አባት ሞት በኋላ መረከባቸውን በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክርክር ገልፀዋል፤ ሆኖም ቤቱ የግላቸው ንብረት ስለመሆኑ ግን አላረጋገጡም። በመሆኑም የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አከራካሪው ቤት በአመልካች አባት የተሰራ መሆኑ ስለመረጋገጡ ተቀብል እያለ የውርስ ድርሻ ክፍፍል የተደረገበት ስለመሆኑ አልተረጋገጠም በሚል ምክንያት ቤቱ የአመልካች አባት የግል ንብረት አይደለም ማለቱ በሚመለከታቸው አካላት የተሰጠው የሰነድ መግለጫ ማስረጃም የቦታውን አመጣጥና በቦታው ላይ ያለ ቤቶች በሕጉ አግባብ የተሰጠውን መለያ ቁጥር ከሚገልጽ በስተቀር ቤቱ በማን ተሰራ የሚለውን ጥያቄ በግልጽ ምላሽ ባልሰጠበት ሁኔታ የሥር ፍርድ ቤትን ውሣኔ መሻሩ በጉዲዩ ላይ ግራ ቀኙ ያቀረቡትን ክርክርና ማስረጃ ይዘት ከላይ ከተጠቀሱት የሕገ መንግስት እና የፍትሐብሕር ሕግ ድንጋጌዎች ጋር ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ በመገኘቱ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 21 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲቲ 19 ቀን 2001 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት በከፉል ተሽሯል።
በፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 29 ቀን 1998 ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁጥር 348/1/ ሙለ በመለ ፀንቷል።
ተጠሪ ከአቶ ተመስገን በቀለ ሞት በሁዋላ የያዙትንና ከተጠሪ ይዞታ /600 ካ.ሜትር/ ውጭ ያለውንና መጋቢት 22 ቀን 1998 ዓ.ም በተደረገ ስምምነት ድንበሩ የተለየውን በቀድሞ ወረዲ 23 ቀበላ 13 ክልል ውስጥ የሚገኘውን ቁጥሩ 1597/ለ/ ወይም 1597/2/ የሆነውን ቤት ለአመልካች ሉያስረክቡ ይገባል ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.