No summary available.
የካቲት 10 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የባህር ዲር ከተማ አገልግልት ጽ/ቤት - ዓ/ህግ መቅጫ ለገሰ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡-
የባህር ዲር ጨርቃጨርቅ ፊብሪካ አ.ማ - ነ/ፈጅ ኃይለእየሱስ ደምሴ - ቀረቡ።
ሮማን ገብሩ - የቀረበ የለም።
ማሩ አላምረው - ቀረቡ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በፍትሐብሕር ክርክር ሂደት በፍርድ ቤት የታገደ ንብረት እግደ ተግባራዊ በሆነበት ጊዜ ተሽጦ ሲገኝ እግደን ያሰጠውና የፍርድ ባለመብት የሆነ ወገን ስላለው መፍትሓ የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በመሰረተው ክስ ሲሆን የአሁኑ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በአመልካች ጠያቂነት ወደ ክርክሩ እንዱገቡ የተደረጉ ናቸው። የስር ከሳሽ የክስ ይዘትም አቶ ብርሃኑ ታርቆ የተባለ ግለሰብ በከሳሽ ድርጅት በቋሚ ሰራተኛነት ተቀጥረው ከ1988 ዓ.ም እስከ 1994 ዓ.ም ድረስ በገንዘብ ያዥነት ሲሰሩ በነበረበት ጊዜ የተሰጣቸውን ኃላፉነት በመዘንጋትና አጋጣሚውን በመጠቀም ብር 28,794.70 /ሃያ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና አራት ብር ከሰባ ሳንቲም/ በማጉደላቸውና ለግል ጥቅም በማዋላቸው ይህንን ገንዘብ እንዱከፍለ ለምዕራብ ጎጃም መስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ በመመስረት የመ/ቁጥር 2312 ተከፍቶ ተከሳሽ አቶ ብርሃኑ ታርቆ ተጠርተውና በጉዲዩ ላይ ተከራክረው የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው ፍርድ ቤት መጋቢት ዐ8 ቀን 1997 ዓ.ም በዋለው ችልት አቶ ብርሃኑ ታርቆን ለክሱ ኃላፉ በማድረግ ዋናውን ገንዘብ ከሕጋዊ ወለደና ከተለያዩ ወጪዎች ጋር እንዱከፍል ውሣኔ መስጠቱን፣ ለዚህ ፍርድ ማስፈፀሚያ ይሆን ዘንድ የአቶ ብርሃኑ ታርቆን ቤት የፍርድ ባለመብት የሆነው ድርጅት በዋናው ክርክር ጊዜ እንዲይሸጥ፣ እንዲይለወጥ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ አሰጥቶ ለባህር ዲር ከተማ አገልግልት ጽ/ቤት የእግድ ትዕዛዙን ያደረሰ ቢሆንም እግደ ተጥሶ ቤቱን የፍርድ ባለዕዲው ሽጦ መገኘቱን ገልጾ ማዘጋጃ ቤቱ የፍርደን ገንዘብ እንዱተካለት ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስም በቤቱ ላይ እግድ መሰጠቱን ሳይክድ ሁኔታው የተከሰተው በሰራተኞች ጥፊት መሆኑን ገልጾ መስሪያ ቤቱ ኃላፉነት እንደላለበት፣ ሰራተኞቹም ወደ ክርክሩ እንዱገቡለት ጥያቄ አቅርቧል። የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎችም በአሁኑ አመልካች ጥያቄ መነሻነት በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ወደ ክርክሩ እንዱገቡ ተደርጏ ባቀረቡት መከራከሪያ ለጉዲዩ ኃላፉነት የላለባቸው መሆኑን ገልፀው ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በሁዋላ የአሁኑን አመልካች ለክሱ ኃላፉ በማድረግ ለ1ኛ ተጠሪ የፍርደን ገንዘብ ያህል እንዱከፍል በማለት 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎችን ግን በነፃ በማሰናበት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙንና የሰበር አቤቱታውን ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የሰበር አቤቱታው መሰረታዊ ይዘትም ጥፊቱ ሰራተኛ የሆኑት የ2ኛ እና የ3ኛ ተጠሪዎች ሁኖ እያለ መስሪያ ቤት የሆነው አመልካች ለጉዲዩ ኃላፉ መባለ ተገቢነት የላለው ከመሆኑም በላይ ኃላፉነት አለበት ቢባል ደግሞ የኃላፉነት መጠኑ ላሆን ይገባ የነበረው ቤቱ የተሸጠበት የገንዘብ መጠን እንጂ 1ኛ ተጠሪ በፍርድ ከአቶ ብርሃኑ ታርቆ እንዱከፈለው የተወሰነውን መጠን ያህል ላሆን አይገባም የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች ለጉዲዩ ኃላፉ ተብል ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ለ1ኛ ተጠሪ ይክፈል ተብል የመወሰኑ ሁኔታ ተገቢነት ያለው መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጓል።
በዚህም መሰረት ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጏላቸው ቀርበው የጽሐፍ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው 1ኛ ተጠሪ ከአቶ ብርሃኑ ታርቆ የሚፈልገው የገንዘብ መጠን በፍርድ የተረጋገጠ ሲሆን በዋናው ክርክር ጊዜ ደግሞ የአቶ ብርሃኑ ታርቆ ንብረት የሆነውን ቤት በፍርድ ቤት በማስከበር የእግደን ትዕዛዝ ለአሁኑ አመልካች አድርሶ ባለበት ሁኔታ የቤቱ ባለቤትና የፍርድ ባለዕዲ የሆኑት ግለሰብ ቤቱን ለላላ ሰው ራሳቸው ሸጠው በመገኘታቸው 1ኛ ተጠሪ ፍርደን ሉያስፈጽም የሚችለውን የአቶ ብርሃኑ ታርቆን ንብረት ሉያገኝ ያልቻለ መሆኑን፣ እንዱሁም የቤቱ ሽያጭን በተመለከተ ተገቢ ነው የሚለውን ክርክር 1ኛ ተጠሪ አቅርቦም እስከ መጨረሻው ፍርድ ቤት ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን፣ የአሁኑ አመልካች ሃላፉነት የለብኝም በማለት የሚከራከረውም እግደ ለመስሪያ ቤቱ መድረሱን በመካድ ሳይሆን ተግባሩ የተፈፀመው ሰራተኛ በሆኑት የአሁኑ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጥፊት ነው በማለት መሆኑን ነው። የስር ፍርድ ቤት አመልካችን ለክሱ ኃላፉ ያደረገው የእግድ ትዕዛዙ ደርሶት እያለ ይህንኑ ጥሶ ቤቱ እንዱሸጥ አድርጏአል፣ የሰራተኞች ጥፊት ስለመኖሩም አላስረዲም በሚል ምክንያት ነው። አመልካች ደግሞ አጥብቆ የሚከራከረው ጥፊቱ በሰራተኞች የተፈፀመ እንጂ በመስሪያ ቤቱ የተፈፀመ ነው ልባል የሚችል አይደለም በሚል ነው። ይሁን እንጂ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መደበኛ ችልት የአመልካች ሰራተኛ በሆኑት የአሁኑ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የተፈፀመ ጥፊት ስለመኖሩ አመልካች ያላስረዲ መሆኑን በፍሬ ነገር ደረጃ ድምዲሜ ላይ ደርሰዋል። ይህ ድምዲሜ የማስረጃውን ታዓማኒነት መሰረት ያደረገ መሆን ያለመሆኑን ደግሞ ይህ ችልት ሉመረምር የሚችልበት የሕግ አግባብ የላለ መሆኑን ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 1ዐ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። የእግድ ጥሰት ተግባር የተፈፀመው በሰራተኞች ጥፊት መሆኑን አመልካች ካላስረዲ ደግሞ ራሱ ሃላፉነት የማይወስድበት ምክንያት የለም። ምክንያቱም የፍርድ ቤት እግድ ትዕዛዝ አለማክበር በሕግ ላይ በትክክል ተገልጾ የተደነገገውን ልዩ ደንብና ሥርዓት መጣስ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2028፣2035 እና 2126 መሰረት ኃላፉነትን የሚያስከትል ተግባር ነውና። በመሆኑም አመልካች ለጉዲዩ ኃላፉ ተብል መወሰኑ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃን ከሕጉ ጋር ያገናዘበ እንጂ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የላለበት ሁኖ አግኝተናል።
ላላው አመልካች የሚከራከርበት ነጥብ የካሳ መጠኑን በተመለከተ ሲሆን በዚህ ረገድ አመልካች የሚያቀርበው ክርክር ኃላፉነት መጠኑ ላሆን የሚገባው ቤቱ በእርግጠኝነት የተሸጠበት ዋጋ እንጂ የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ከአቶ ብርሃኑ ታርቆ ላይ የሚፈልገው የፍርድ ገንዘብ መጠን አይደለም በሚል ነው። ይሁን እንጂ ቤቱ በጨረታ ሳይሆን ከዚህ ውጪ የተሸጠ በመሆኑ በትክክል በምን ያህል ዋጋ እንደተሸጠ ተረጋግጧል ለማለት የሚቻልበት አግባብ የለም። ቤቱ የተሸጠው በገበያ ዋጋ ስለመሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ደግሞ አመልካች የኃላፉነት መጠኑን የሚቃወምበት ሕጋዊ ምክንያት ሉኖር አይችልም። በአጠቃላይ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት የሚያስችል ምክንያት የላለ በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.