No summary available.
ጥር 24 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ አመልካች፡- እነ አቶ ግርማይ ካሕሳይ - ጠበቃ ዜና ደባሱ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሥዩም ታደሰ ሐጎስ - ወኪል ሂሩት ታደሰ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ እጣው ከመድረሱ በፉት አባልነትን ያቋረጠ የእቁብ አባል ለእቁብ የከፈለው ገንዘብ ይመለስልኝ የሚል ጥያቄ ሲያቀርብ ኃላፉነት ያለበትን ወገን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካቾች እና ቀድሞ የእቁቡ ሰብሳቢ ነበሩ በተባለ በአንድ ግለሰብ ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ ተጠሪ አመልካቾች በኃላፉነት በሚሰሩትና በየሳምንቱ በሚጣል እቁብ ውስጥ ማህበርተኛ ሁነው በመመዝገብ 63,300.00(ስልሳ ሦስት ሺህ ሶስት መቶ ብር) መክፈላቸውን፣ ይሁን እንጂ እቁቡ ሳይጠናቀቅ መክፈል ማቆማቸውን፣ ለአመልካቾች የከፈለት ገንዘብ እንዱሰጣቸው ጥያቄ አቅርበውም ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) ከፍሎቸው ቀሪውን ብር 33,300.00(ሰላሳ ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ብር) እቁቡ ሲጠናቀቅ እንደሚከፍሎቸው አመልካቾች የፈረሙላቸው መሆኑን፣ ሆኖም ለመክፈል አመልካቾች ከፈረሙላቸው በኋላ ቀሪውን ገንዘብ እንዱከፍሎቸው ተጠሪ ጥያቄ ቢያቀርቡላቸውም አመልካቾች ያልፈፀሙላቸው መሆኑን ገልፀው ለእቁቡ ከፍለው ያልተመለሰላቸውን ብር 33,000.00 (ሰላሳ ሶስት ሺህ ብር) በአንድነትና በነጠላ ከእነ ሕጋዊ ወለደ እንዱሁም ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዱከፍሎቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የስር 1ኛ ተከሳሽ የነበሩት ግለሰብም ክሱ በቀረበበት ወቅት ከእቁቡ ኃላፉነት የላለባቸው መሆኑንና ጉዲዩ የሚመለከተው የአሁኑን አመልካቾችን መሆኑን ገልፀው በራሳቸው ላይ የቀረበው ክስ ውድቅ እንዱሆን የተከራከሩ ሲሆን የአሁኑ አመልካቾችም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነጥቦችንና የፍሬ ነገር ክርክሮችን አቅርበዋል።
አመልካቾች በመከራከሪያነት ያቀረቡት ነጥብም ተጠሪ አመልካቾችን ለመክሰስ ከውል ወይም ከሕግ የመነጨ መብት የላላቸው መሆኑን፣ በእቁቡ መተዲደሪያ ደንብም አመልካቾች ያለባቸው ኃላፉነትም የተጠሪን ክስ አይነት አለመሆኑን ገልጸው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ የተከራከሩ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የአመልካቾችን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነጥቦችን ውድቅ በማድረግ በዋናው ጉዲይ ላይ የቀረበውን የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ የስር 1ኛ ተከሳሽን ከክሱ ነጻ ሲያወጣ፣ የአሁኑ አመልካቾችን ግን ገንዘቡን ለመክፈል መፈረማቸው ተረጋግጧል በሚል ምክንያት ለክሱ ኃላፉ አድርጎ ለክሱ ምክንያት የሆነውን ገንዘብ ከተለየዩ ወጪና ኪሣራ ጋር በአንድነት እና በነጠላ ለተጠሪ ሉከፍለ ይገባል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር.337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ለተጠሪ የእቁቡን ገንዘብ ለመክፈል ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ ግዳታ ሳይኖርባቸው በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በእቁቡ መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 7.4 ስር የተመለከተውን ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። የሰበር አቤቱታቸው ተመርምሮም አመልካቾች በመተዲደሪያ ደንቡ መሰረት የጎደለውን የእቁብ አባል ክስ መስርተው እየተከራከረ መሆኑ ከታወቀ ከዚህ በማለፍ የመከሰስ ግዳታ ያለባቸው ስለመሆኑ በደንቡ ተሸፍኗል? ወይስ አልተሸፈነም?
የሚለውን ነጥብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ እንዱሁም ያለውን አሰራርና ልምድ መሰረት ያደረገ በመሆኑ ሉፀና ይገባል በማለት የፅሐፍ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካቾች ተጠሪ አባል ሁነው ገንዘብ መክፈላቸው በተረጋገጠው የእቁብ ማህበር ውስጥ በኃላፉነት ቦታ የሚሰሩ መሆኑ፣ ተጠሪ ለእቁቡ ከከፈለት ገንዘብ ውስጥ ብር 30,000.00 ተመልሶላቸው ቀሪ ብር 33,000.00 ያልተከፈላቸው መሆኑን፣ ይህንኑ ቀሪ ገንዘብ ደግሞ አመልካቾች ለተጠሪ ለመክፈል በፊርማ ያረጋገጡላቸው መሆኑ በስር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጡ ነጥቦች መሆናቸውን ነው። የስር ፍርድ ቤት የአመልካቾች ግዳታ ምንጩ የክፍያ ሰነደ ላይ የተቀመጠው ፊርማቸው መሆኑን አረጋግጧል። አመልካቾች በዚህ ረገድ የቀረበውን የተጠሪን ክርክር ያላስተባበለ መሆኑንም የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በግልፅ ያሳያል።
No topics extracted.
አመልካቾች ለተጠሪ ገንዘቡን እንከፍላለን በማለት ግዳታ መግባታቸው ከተረጋገጠ የማይጠየቁበት ሕጋዊ ምክንያት የላለ ሲሆን ከኃላፉነት ነጻ ያደርገናል በማለት የሚጠቅሱት የእቁቡ መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 7.4 ሙለ ይዘቱ ሲታይም ሙለ በሙለ ተጠያቂነትና ኃላፉነት ያለባቸው የእቁቡ ፀሐፉና ዋናው ተቆጣጣሪ መሆናቸውን የሚጠቅስ ሁኖ አግኝተናል። 1ኛው አመልካች የእቁቡ ፀሐፉ፣ ሁለተኛው አመልካች ደግሞ የእቁቡ ተቆጣጣሪ የመሆናቸው ጉዲይ ደግሞ በሚገባ የተረጋገጠ ነጥብ ነው። አመልካቾች ራሳቸው በፊርማቸው አረጋግጠው በሰጡት የሰነድ ማስረጃ ግዳታ ያለባቸው መሆኑ ከመረጋገጡም በላይ ከላይ እንደተጠቀሰው የእቁቡ መተዲደሪያ ደንብም ቢሆን ይዘቱ ሲታይ ከተጠያቂነትና ኃላፉነት ነፃ የማያደርጋቸው ሲሆን አመልካቾች ግዳታውን ባልተወጣው የእቁቡ አባል ላይ ክስ መመስረታቸው በውጤት ደረጃ ተጠሪ አመልካቾችን እንዲይጠይቁ የሚያደርግ አይደለም።
ግዳታውን ባልተወጣው ግለሰብ ላይ አመልካቾች ክስ መመስረታቸውን በስር ፍርድ ቤት ገልፀው ይኸው ተረጋግጦ ጥያቄአቸው ውድቅ መደረጉ ወይም ግዳታውን አልተወጣም የተባለው ግለሰብ ተጠሪ በመሰረቱት ክስ ውስጥ የክርክሩ ተካፊይ ያለመሆኑ ጉዲዩ በአንድ ላይ ቢታይ የክርክሩን አመራር ተገቢ ያደርገው ነበር ከሚባል በስተቀር ተጠሪ በአመልካቾች ላይ በሚኖራቸው መብት፣ አመልካቾች ደግሞ ለተጠሪ በሚወጡት ግዳታ ለሚመለከተው ሰው የተወጡትን ግዳታ እንዱተካላቸው ለመጠየቅ ከሚኖራቸው መብት አንፃር ሲታይ የመብት መጣበብን ሉያስከትል ይችላል ለማለት የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት የላለው በመሆኑ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ በውጤት ደረጃ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም። በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።