No summary available.
ሐምል 01 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡-
ለዚህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነው የአሁኑ ተጠሪ መ/ቤት የዱስኘሉን ኮሚቴ የሰጠው የዱስኘሉን ውሣኔ ሲሆን ውሣኔውም ለተጠሪ መ/ቤት የበላይ ሀላፉ ቀርቦ ይፈፀም በመባለ ምክንያት ለከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ በአሁኑ አመልካች ይግባኝ ጠያቂነት ቀርቦ ከፍተኛው ፍ/ቤትም መልስ ሰጪውን መጥራት ሳያስፈልግ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት የይግባኙን መዝገብ በመዝጋት ይግባኝ ባዩን በማሰናበቱ ለዚህ ችልት ቀርቧል።
ለዱስኘሉን ኮሚቴ ውሣኔ መነሻ የሆነውን አቤቱታ ለተጠሪ መ/ቤት ያቀረቡት ወ/ሮ ዮላንዲ ካፐሲ ሲሆኑ የአቤቱታውም ፍሬ ቃል ከአቶ ሩፊኤል ዳልጋውዱ ከተባለው ጋር ባልና ሚስት ሆነን ከቆየን በኋላ በመካከላችን በተፈጠረው አለመግባባት በፍ/ቤት ጉዲያችን እየታየ ባለበት ወቅት ባለቤቴ የጋራ ሃብታችንን በሙለ በእጁ በማድረጉ የንብረት ክፍፍለ እስከሚደረግ ድረስ ለወደፉት ከንብረቱ ከሚደርሰኝ የሚታሰብ በየወሩ ብር 1ዐ,ዐዐዐ እንዱከፍለኝ ተወስኖልኝ ሲከፍለኝ ከቆየ በኋላ ተጠሪው /የአሁኑ አመልካች / የባለቤቴ ጠበቃ በመሆናቸው ለፍ/ቤቱ የካቲት ዐ2 ቀን 1999 ዓ/ም በሰጡት የመልስ መልስ እኔ ‛ ኢንተርናሸናል ቢዝነስ ግሩኘ“ የሚባል የግል ድርጅት ሳይኖረኝ እንዲለኝ በማስመሰል ሐሰተኛ የቢዝነስ ካርድ በማዘጋጀት አቅርበው በፈፀሙት ህገወጥ ድርጊት ከፍተኛ እንግልትና ጉዲት ያደረሱብኝ ስለሆነ በዱስኘሉን ኮሚቴ ይጠየቅልኝ የሚል ነው።
የሥር ተጠሪውም /የአሁኑ አመልካች/ በሰጡት መልስ የአቤቱታ አቅራቢዋ ባለቤት የቢዝነስ ካርደን ስለሰጣቸው ለፍ/ቤቱ እንዲቀረቡ ገልፀዋል።
የሥር የዱስኘሉን ኮሚቴውም የአሁኑ አመልካች የፋዳራል ፍ/ቤቶች የጠበቆች ሥነ ምግባር ደንብ ቁጥር 57/92 አንቀጽ 29/2/ እና አንቀጽ 56/4/6/ ላይ የተደነገጉትን የሥነ ምግባር ድንጋጌዎች ጥሰዋል በማለት በብር 10,000 /አሥር ሺህ / እንዱቀጡ ወስኖባቸዋል። የአሁኑ አመልካችም በተጠሪ መ/ቤት የዱስኘሉን ኮሚቴ ውሣኔና በሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ያለ ሲሆን በዋናነት የጠቀሱአቸው የቅሬታ ነጥቦችም፡የተጠሪ የዱስኘሉን ኮሚቴ ለውሣኔው መሰረት ያደረጋቸው ድንጋጌዎች ላይ ያለት ነጥቦች ስለመኖራቸው አልተረጋገጠም ፣ የዱስኘሉን ኮሚቴው ማስረጃዬን ሳይሰማና ሳይመረምር ውሣኔ መስጠቱ ያለአግባብ ነው፣ በደንበኛዬ ትክክለኛ መሆኑ ተገልጾ የተሰጠኝ ሰነድ ሀሰተኛ መሆን አለመሆኑን የማጣራት ግዳታ የላለብኝ ሆኖ ሣለ ጥፊተኛ መባላ ያለአግባብ ነው የሚለ ናቸው።
ለአመልካች የሰበር አቤቱታ ተጠሪው በሰጠው መልስ ለሥር የዱስኘሉን ኮሚቴ አቤቱታው እንዱታይ የጠየቁት ግለሰብ የንግድ ድርጅት ያላቸው ስለመሆኑ ምንም አይነት ህጋዊ ሰነድ ከአመልካች ደንበኛ ሳይቀርብላቸውና በቢዝነስ ካርደ የተመለከቱት ዝርዝር ሁኔታዎችን በአግባቡ ሳያረጋግጡ አመልካች ካርደን ለፍ/ቤቱ በማቅረብ ለግለሰቧ የሚከፈለው ቀለብ እንዱቋረጥ ማድረጋቸው ከቅን ልቦና ውጪ የፈፀሙት መሆኑን የሚያሣይ ነው። ይህ ሆኖ ሣለ አመልካች የሰነደን ሀሰተኛነት አላውቅም ያለት ከተጣለባቸው ሙያዊ ግዳታ አንፃር ተቀባይነት የላለው ነው። አመልካች በሰበር ቅሬታቸው ማስረጃቸው ያልተሰሙ መሆናቸውን ቢገልጹም የተጠሪ የዱስኝሉን ኮሚቴ 7 የአመልካች ማስረጃዎችን አቅርቦ የሰማ በመሆኑ በዚህ ረገድ ያቀረቡት ቅሬታ ተቀባይነት የለውም በማለት የዱስኘሉን ኮሚቴውም ሆነ የሥር የፋ/ከ/ፍ/ቤት በውሣኔያቸው የፈፀሙት የህግ ስህተት የለም በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ የተገለፀ ሲሆን እኛም አመልካች በተከሰሱበት የዱስኘሉን ክስ ጥፊተኛ ናቸው ተብለው በገንዘብ የተቀጡት በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
የተጠሪ መ/ቤት የዱስኘሉን ኮሚቴ ውሣኔ እንደሚያመለክተው አመልካች ጠበቃ ሆነው ሲከራከሩ የነበሩት የወ/ሮ ዩላንዲ ካፐሲ ባለቤት ወክልአቸው ሲሆን አመልካች የተባለውን የቢዝነስ ካርድ ያገኙት ከደንበኛቸው መሆኑን እና ለፍ/ቤቱ ግለሰቧ የንግድ ድርጅት እንዲላቸው ካርደን በማቅረብ ጭምር የገለጹት ይኸው ደንበኛቸው በሰጡት መረጃ መሰረት ነው ብሎዋል። ይበለ እንጂ ደንበኛው ያቀረባቸውን ማስረጃዎች ባለሙያው /ጠበቃው/ እንዲለ ተቀብል ለፍ/ቤት ማቅረብ አለበት?
ወይስ የለበትም የሚለውን ነጥብ መመለስ ተገቢነት ያለው ይሆናል። ለዚህም በመጀመሪያ የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 92/1/ን መመልከት የሚገባ ሲሆን የተጠቀሰው የሥነ ሥርዓት ህግ ድንጋጌ ስለማናቸውም ጉዲይ የሚቀርብ አቤቱታ በልላ ሁኔታ እንዱቀርብ የሚያዝ ድንጋጌ ከላለ በቀር በአቤቱታው ማመልከቻ ላይ የተገለፀው ነገር አቤት ባዩ ወይም ነገሩን የሚያውቅ ላላ ሰው በአቤቱታው ግርጌ ይህ የቀረበው አቤቱታ እውነት መሆኑን ማረጋገጥ አለበት ይላል። ከዚህ ከህጉ መንፈስ መረዲት እንደሚቻለው አቤቱታ አቅራቢው ያቀረበው አቤቱታ እውነት ስለመሆኑ የማረጋገጥ የህግ ግዳታ አለበት። በዚህ በተያዘውም ጉዲይ ቢሆን ደንበኛቸውን በመወከል ግለሰቧ የንግድ ድርጅት ያላቸው ስለመሆኑ አመልካች ካርደን ጭምር ይዘው ለፍ/ቤት የቀረቡ ሲሆን ይህ አለ የተባለው የንግድ ድርጅት ስለመኖሩ ደግሞ አስቀድሞ በእርግጠኝነት ሉያውቁ ይገባ ነበር።
ይህ ሆኖ ሣለ አመልካች በእርግጠኛነት የሚያውቁትን ጉዲይ ብቻ ክርክሩን ለያዘው ፍርድ ቤት ማቅረብ ሲገባቸው የቢዝነስ ካርደን ሐሰተኛ መሆንና አለመሆን የማጣራት ግዳታ የለብኝም ያለት ከተጠቀሰው የሥነ ሥርዓት ህግ ውጪ በመሆኑ ተቀባይነት ሉኖረው የሚገባ አይደለም።
በልላ በኩል የፋዳራል ፍርድ ቤቶች የጠበቆች የሥነ ምግባር ደንብ ቁጥር 57/92 አንቀጽ 3 በመርህ ደረጃ ማንኛውም ጠበቃ በተለይም ለደንበኛው፣ ለላልች የህግ ሙያተኞችና ተከራካሪ ወገኖች፣ ለፍርድ ቤት፣ ለሙያው እና በአጠቃላይ ለህብረተሰቡ ያለበትን የሙያ ሃላፉነት በቅንነት፣ በታማኝነት እና በእውነተኛነት መውጣት እንዲለበት የተደነገገ ሲሆን በደንቡ አንቀጽ 29/2/ ደግሞ ማስረጃን ማሳሳት ወይም ላልች ሰዎች ይህን መሰል አድራጏት እንዱፈጽሙ መምከር ወይም መርዲት የተከለከለ ተግባር እንደሆነ በግልጽ ተቀምጧል። ከዚህ በተጨማሪ በደንቡ አንቀጽ 56/4/ ሆን ብል ፍርድ ቤትን የሚያሳስት ወይም የተጋነነ ጽሁፍችንና ንግግር ማድረግ ፣ እንዱሁም በአንቀጽ 56/6/ እንደተደነገገው ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን ማስረጃ አግባብነት እንዲለው አስመስል ማቅረብ የማይፈቀደ ድርጊቶች እንደሆኑ ተጠቅሰዋል።
ይህ ሆኖ ሣለ አመልካች ከፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 92/1/ ውጪ እና ከዚህ በላይ ከተጠቀሰው የጠበቆች የሥነ ምግባር ደንብ በሚቃረን መልኩ የደንበኛቸው ባለቤት የነበሩት ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ግሩኘ የሚባል የንግድ ድርጅት ሳይኖራቸው አላቸው በማለት በሐሰት የተዘጋጀ የቢዝነስ ካርድ ለሥር ፍ/ቤት በማቅረብ ፍ/ቤቱን በማሳሳት ከቅን ልቦና ውጪ ለግለሰቧ እንዱከፈላቸው ተወስኖ የነበረውን ቀለብ እንዱቋረጥ ማድረጋቸው በተጠሪ የዱስኘሉን ኮሚቴ በማስረጃ ከተረጋገጠ በኋላ አመልካችንም ባቀረቡአቸው የመከላከያ ማስረጃዎች ማስተባበል ባለመቻላቸው ጥፊተኛ ተደርገው የቅጣት ውሣኔ የተላለፈባቸው እንዱሁም የተጠሪው የዱሲኘሉን ኮሚቴ ውሣኔ በይግባኝ ቀርቦ መጽናቱ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም። በመሆኑም የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የተጠሪ መ/ቤት የዱስኘሉን ኮሚቴ በ14/05/2002 ዓ/ም ባደረገው ስብሰባ የሰጠው ውሣኔ እንዱሁም የሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 26/04/2003 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
አመልካች የመቀጮ ገንዘብ ብር 1ዐ,ዐዐዐ /አሥር ሺህ / ለመንግስት ገቢ እንዱያደርጉ የተወሰነው በአግባቡ ነው ብለናል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች ይቻቻለ።
መዝገቡ የተዘጋ ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.