No summary available.
መጋቢት 9 ቀን 2003ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድማ አመልካቾች፡-
አመልካቾች በተናጠል ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር መዝገብ የአሁን ተጠሪ አመልካች የአሁን አመልካቾች ተጠሪዎች ሆነው ያቀረቡትን ክርክር መርምሮ ጉዲዩን የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንደገና አይቶ እንዱወሰን ጥር 14 ቀን 2001 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ መሰረት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግራቀኛችንን ክርክር በመስማት ህዲር 24 ቀን 2002ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በይግባኝ አይቶ መጋቢት 28 ቀን 2002ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል።
የክርክሩ መነሻ የአሁን ተጠሪ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግንቦት 22 ቀን 1994 ዓ.ም ያቀረቡት የክስ ማመልከቻ ነው። ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት በተከሳሽነት ቀርበው ሁለተኛ አመልካች አዱስ አበባ ከተማ ወረዲ 16 ቀበላ 03 የቤት ቁጥር 314 የሚገኘውን ቤቱን ከታህሣሥ 23 ቀን 1991ዓ.ም ጀምሮ በየወሩ ብር 3‚000/ሦስት ሺ ብር/ ኪራይ ለመክፈል ተስማምተው ተከራይተውታል። በውላችን መሰረት ያልከፈለኝ ብር 117‚000 /አንድ መቶ አሥራ ሰባት ሺ ብር/ የቤት ኪራይ ያለባቸው ስለሆነ እንዱከፍለ ይወሰንልኝ።
አንደኛው አመልካች ህግና መመሪያ ሣይከተል ቁጥሩ ከፍ ብል የተጠቀሰውን ቤት ለሁለተኛ አመልካች ነሐሴ 28 ቀን 1993 ዓ.ም በተፃፈ የሽያጭ ውል ሸጧል። አመልካቾች በአንድነትና በነጠላ ከነሐሴ 28 ቀን 1993 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን የቤቱን ኪራይ እንዱከፍለና ቤቱንም ለቅቀው እንዱያስረክቡኝ በማለት ያቀረቡት ክስ ነው። አንደኛ አመልካች ቤቱን ለሁለተኛ አመልከች የሸጠው ቤቱ የኤርትራዊያን ንብረት መሆኑ በወቅቱ በተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ተጣርቶ ስለቀረበለት መሆኑን ገልጾ የተጠሪ ክስ ተገቢ አይደለም የሚል ክርክር አቅርቧል። ሁለተኛ አመልካችም መንግስት ባወጣው የጨረታ ማስታወቂያ መሰረት በህጋዊ መንገድ የገዛሁ በመሆኑ የሽያጭ ውለ የሚፈርስበትም ሆነ ቤቱን የምለቅበት ምክንያት የለም። የቤት ኪራይ ለተጠሪ ወኪል ከፍያለሁ የሚል ይዘት ያለው ክርክር አቅርበዋል።
የሥር ፍርድ ቤት አንደኛ አመልካች ለሁለተኛ አመልካች የተጠሪን ንብረት የሸጠው ከህግ ውጭ ነው። ስለዚህ ቤቱን ለሁለተኛ ተጠሪ ያስረክቡ። የቤት ኪራይ ከነሐሴ 28 ቀን 1993 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን በአንድነትና በነጠላ አመልካቾች ለተጠሪ እንዱከፍለ በማለት በመዝገብ ታህሣሥ 28 ቀን 97 ዓ.ም ውሣኔ ሰጥቷል፣፣ አመልካቾች ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበው የከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ ተጠሪ በአመልካቾች ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችላቸው መብትና ጥቅም የላቸውም በማለት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በይግባኝ መዝገብ ሀምላ 12 ቀን 1998 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ ሽሮታል። ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት የተጠሪን ይግባኝ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 337 መሰረት በመዝገብ የካቲት 2 ቀን 1999 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ ስርዞታል። ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አቅርበው የሰበር ችልቱ የግራቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡትን ውሣኔ በመሻር የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተጠሪ በመዝገብ አለ የሚለትን የሚስትነትና የልጆቻቸውን የወራሽነት ማስረጃ በማስቀረብና ተገቢውን በመፈፀም እንደዚሁም ተገቢነት አላቸው የሚላቸውን ማስረጃዎች ሁለ በማስቀረብ በግራ ቀኙ የመከራከሪያ ነጥቦች ላይ ውሣኔ እንዱሰጥበት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343/1/ መሰረት በሰበር መዝገብ ጥር 14 ቀን 2001 ውሣኔ ሰጥቷል። ተጠሪ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ጥር 14 ቀን 2001ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ መሰረት ጉዲዩን በማንቀሣቀሥ አጣርቶ እንዱወሰንላቸው የካቲት 16 ቀን 2001 ዓ.ም ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መሰረት መዝገቡን በማንቀሣቀሥ ሉቀርቡ ይገባቸዋል የሚላቸውን ማስረጃዎች በማስቀረብ 24-3-2002 ዓ.ም ውሣኔ ሰጥቷል። የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ክስ በቀረበበት ጉዲይ ላይ ለመክሰስ የሚያስችል መብት አላቸው ወይስ የላቸውም; አመልካቾች ክስ የቀረበበትን ቤት ለተጠሪ ሉያስረክቡ ይገባል ወይስ አይገባም; ተጠሪ ክስ ያቀረቡበትን የኪራይ ገንዘብ በይርጋ ይታገዲል ወይስ አይታገድም; አመልካቾች ተጠሪ የጠየቁትን የቤት ኪራይ የመክፈል ሀላፉነት አለባቸው ወይስ የላበቸውም; የሚለትን ጭብጦች መሥርቷል።
ክርክር የተነሳበት ቤት በብርጋዳር ጄኔራል ገብረአብ ወልዲይ ስም የተመዘገበ ነው። ተጠሪ የሟች ብርጋዳር ጄኔራል ገብርአብ ወልዲይ ሚስት መሆናቸው በሥር ፍይል መዝገብ ቁጥር 79/83 ተረጋግጦ በፍርድ ተወስኗል። የቤቱ ስመ ሀብት በብርጋዳር ጄኔራል ገብረአብ ወልዲይ ስም የተመዘገበ ቢሆንም ተጠሪ ቤቱን በጋብቻ ያፈሩት የጋራ ሀብታቸው በመሆኑ ክስ የማቅረብ መብት አላቸው። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ አገር ዜጋ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሥልጣን ባለው የመንግስት አካል የተሰጣቸው በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 470/94 አንቀፅ 5/4/ መሰረት ክስ ማቅረብ ይችላለ በማለት ወስኗል። ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ አንደኛ አመልካች ቤቱን ለሁለተኛ አመልካች የሸጥኩት የክልል 14 መስተዲድር ጽ/ቤት መጋቢት 15 ቀን 1992ዓ.ም በቁጥር አመ/አአ 73/6/53 በፃፈው ደብዲቤና ባወጣው መመሪያ መሰረት ነው በማለት የሚከራከር ቢሆንም መመሪያው በወቅቱ በመንግስት ውሣኔ ከአገር እንዱወጡ የተደረጉት ኤርትራዊያን ንብረት በጨረታ የሚሸጥበትን ሁኔታ የሚመለከት ነው። ብርጋዳር ጄኔራል ገብረአብ ወልዲይ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ግንቦት 23 ቀን 1983 ዓ.ም መሆኑና በኢትዮጵያ ውስጥ የተቀበሩ መሆኑ ተረጋግጧል። ብ/ር ጄኔራለ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣን የነበሩና ተጠሪ አሁንም ከኢትዮጵያ መንግስት ጡረታ በሟች ስም እየተቀበለ መሆናቸው ተገልጿል።
የቤቱ ባለንብረት ኢትዮጵያዊ ሆነው እያለ በተሣሣተ መረጃ አንደኛ አመልካች ቤቱ የኤርትራዊና በመንግስት ውሣኔ ከአገር እንዱወጡ የተደረጉ ሰው ንብረት እንደሆነ በመቁጠር ለሁለተኛው አመልካች የፈፀመው ሽያጭ ፈራሽ ነው።
ስለዚህ አመልካቾች ቤቱን ለተጠሪ የማስረከብ ግዳታና ሀላፉነት አለባቸው በማለት ወስኗል።
ሦስተኛውን ጭብጥ በተመለከተ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት በመዝገብ በሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም መሰረት ሁለተኛ አመልካች ከመጋቢት 20 ቀን 1992 በፉት የነበረውን የቤት ኪራይ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2024 መሰረት እንደተከፈለ የሚገመት በመሆኑ ሁለተኛ አመልካች ከመጋቢት 20 ቀን 1992 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 26 ቀን 1993 ዓ.ም ያለትን አሥራ ስምንት ወራት ኪራይ ብቻ በብር 3‚000 ተሰርቶ ብር 54‚000 ሉከፍለ ይገባል በማለት ወስኗል። አራተኛውን ጭብጥ በተመለከተ ከነሐሴ 28 ቀን 1993ዓ.ም ጀምሮ ሁለተኛ ተጠሪ ቤቱን የያዙት በሽያጭ ውል በመሆኑ ለተጠሪ ኪራይ የመክፈል ሀላፉነት የለባቸውም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አንደኛ አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታውን አቅርቧል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኙን የሚጣራ ፍሬ ነጥብ የለውም በማለት በመዝገብ መጋቢት 28 ቀን 2002 በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 ሰርዟል። ሁለተኛ አመልካች በበኩላቸው ይግባኝ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኙ የሚጣራ ነጥብ የለውም በማለት በመዝገብ መጋቢት 28 ቀን 2002 ዓ.ም በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አንደኛው አመልካች የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔና የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት። ቤቱን ለሁለተኛ አመልካች የሸጥነው መንግስት የኤርትራዊያን ንብረት እንዱሸጥ ባወጣው መመሪያ መሰረት ነው። ተጠሪ ሽያጩ ሲከናወን ኢትዩጵያዊ የነበሩ መሆኑን አላስረደም። ተጠሪ ኢትዩጵያዊ ባለመሆናቸው በባንክ የተቀመጠውን ገንዘብ ከሚጠይቁ በስተቀር የቤት ሽያጩ ውለ እንዱፈርስ መጠይቅ አይችለም።
የሥር ፍርድ ቤት በወቅቱ ያልወጣውን አዋጅ ቁጥር 270/94 በመጥቀስ መወሰኑ የህግ ስህተት አለበት በማለት ሚያዚያ 18 ቀን 2002 ዓ.ም ፅፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የተከራከረ ሲሆን ሁለተኛ አመልካች በበኩላቸው የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔና ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ መዝገብ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት። ተጠሪ የሟች ብ/ር ጄኔራል ገብረአብ ሚስት ቢሆኑም ኤርትራዊ ዜግነት ያልያዙ እንደነበሩ ባላሥረደበት ሁኔታ መንግስት ባወጣው መመሪያ መሰረት የገዛሁትን ቤት እንዲስረክብ መወሰኑ የህግ ስህተት ያለበት ነው። የቤቱ ስመ ሀብት በገዥዋ በሁለተኛ አመልካች ስም የተዛወረና ውለ የተፈፀመ በመሆኑ ውለ ፈራሽ ነው መባለ ተገቢ አይደለም። ተጠሪ ኢትዩጵያዊ ስለመሆናቸው ያቀረቡት ማስረጃ የለም።
ቤቱን ከገዛሁ በኃላ ከብር 500‚000 በላይ ወጭ በማድረግ የግንባታ ሥራ አከናውኛለሁ። የሥር ፍርድ ቤት የሰበር ችልቱን ትዕዛዝ በመከተል አጣርቶ አልወሰነም። የውጭ ዜጋ ንብረቱን ለኢትዩጵያዊ እንዱያስተላለፍ ማስገደድ እንደሚችለ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 390 እና በፍታብሓር ህግ ቁጥር 391 የተደነገገ በመሆኑ አንደኛ አመልካች ቤቱን ለእኔ ለመሸጥ ሥልጣን አለው ስለዚህ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ በመሻር የተፈፀመውን የህግ ስህተት እንዱያርሙልኝ በማለት ከዚህ መዝገብ ጋር በተጣመረው በሰበር መዝገብ ሚያዚያ 8 ቀን 2002ዓ/ም ፅፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ አመልክተዋል።
ተጠሪ አመልካቾች በተናጥል ባቀረቡት መልስ ቤቱ የሟች ብ/ር ጄኔራል ገብረአብ ወልዲይ ቤት ነው። ሟች የኢትዮጵያ የጦር መኮንንና ኢትዮጵያዊ ናቸው። መንግስት የጡረታ አበል እየከፈለኝ መሆኑን በቂ ማስረጃ አቅርቤለሁ። እኔም የሟች ሚስት መሆኔን በማስረጃ ተረጋግጧል።
አመልካቾች የኤርትራዊ ንብረት ነው ከሚለት ውጭ ቤቱ በመንግስት ውሣኔ ከአገር የተባረሩ ኤርትራዊ ንብረት መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አላቀረቡም። ስለሆነም አንደኛ አመልካች ለሁለተኛ አመልካች ቤቱን ለመሸጥ የሚያስችል ምክንያትና ሥልጣን ሣይኖረው ሟች ብ/ር ጄኔራል ገብረአብ ወልዲይ በመንግስት ውሣኔ ከአገር የተባረሩ ኤርትራዊ ናቸው በሚል ምክንያት ቤቱን መሸጡ የተረጋገጠ ስለሆነ ሽያጩ እንዱፈርስ የተሰጠው ውሣኔ መሰታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ስኔ 16 ቀን 2002 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። አመልካቾች በተናጠል የመልስ መልስ አቅርበዋል።
አመልካቾችና ተጠሪ ከዚህ በፉት ያደረጉት ክርክር ያለፈበት ሂደትና ጉዲዩ የተመለሰለት የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔና ግራቀኙ በተጣመሩት መዝገቦች በሰበር ያቀረቡት ክርክር ይዘት ከላይ በአጭሩ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የበታች ፍርድ ቤቶች አንደኛ አመልካች በቀድሞው ወረዲ 16 ቀበላ 03 የቤት ቁጥር 314 ለሁለተኛ አመልካች ለመሸጥ ያደረገው ውል ፈራሽ ነው በማለት የሰጡት ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም; የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የክርክሩ መነሻ የሆነው የቤት ቁጥር 314 አንደኛ አመልካች ነሐሴ 28 ቀን 1993 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ውል ለመሸጥ ህጋዊ መሰረት ያደረገው የክልል 14 መስተዲድር ጽ/ቤት መጋቢት 15 ዓ.ም በቁጥር አመ/አስ 73/6/53 ያፃፈውን ደብዲቤና በመንግስት ከአገር እንዱወጡ የተደረጉ ኤርትራዊያን ንብረት ስለሚሸጥበት ሁኔታ የወጣውን መመሪያ ነው። መመሪያው አስተዲደሩ በመንግስት ውሣኔ ከአገር እንዱወጡ የተደረጉ ኤርትራዊያን ንብረት እንዱሸጥ ሥልጣን የሚሰጥ ነው። አንደኛ አመልካች ተጠሪ የሚከራከሩበትን ቤት ለሁለተኛ አመልካች የሸጠው ቤቱ በስማቸው የተመዘገበው አቶ ገብረአብ ወልዲዊ ከአገር የተባረሩ ኤርትራዊ ናቸው በማለት እንደሆነ በሥር ፍርድ ቤት አንደኛ አመልካች በማስረጃነት ያቀረበው ሰነድ ጭምር ተረጋግጣል።
አንደኛ አመልካች ከአገር የተባረሩ ኤርትራዊ ናቸው በማለት ቃለ ጉባኤ ይዞ ንብረታቸው እንዱሸጥ የወሰነባቸው ብርጋዳል ጄኔራል ገብረአብ ወልዲዊ ኤትርራዊ ዜግነት የላላቸው ኢትዮጵያዊ የጦር መኮንን እንደነበሩና ግንባት 23 ቀን 1983 ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ መሆኑን ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። ይህም አንደኛ አመልካች በህግ ከተሰጠው ሥልጣን ውጭ ከሁለተኛ አመልካች ጋር የቤት ሽያጭ ውል ያደረገ መሆኑን የሚያሣይ ነው።
በልላ በኩል ተጠሪ የሟች ብርጋዳር ጄኔራል ገብረአብ ወልዲይ ሚስት መሆናቸውንና የኢትዮጵያ መንግስት የጡረታ አበል እስካሁን ድረስ የሚከፍላቸው መሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። ተጠሪ በመንግስት ውሣኔ ከአገር የተባረሩ ኤርትራዊ መሆናቸውን አመልካቾች ለበታች ፍርድ ቤቶች ያቀረቡት ማስረጃ የለም። በአንፃሩ ተጠሪ በትውልድ ኢትዩጵያዊ የሆኑ የላላ አገር ዜግነት ያላቸው መሆኑን የሚያስረዲ በውጭ ጉዲይ ሚኒስትር የመታወቂያ ካርድ የተሰጣቸው መሆኑን ለሥር ፍርድ ቤት ማስረጃ አቅርበዋል። ‟የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ዜጋ‟ የሚል መታወቂያ የሚሰጠው አንድ ሰው በአዋጅ ቁጥር 270/1994 አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀፅ 2ን ለሚያሟላ የውጭ አገር ዜጋ መሆኑ በደንብ ቁጥር 101/96 አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀፅ 1 ይደንግጓል።
የኢትዮጵያን ዜግነት በመተው የኤርትራን ዜግነት መርጦ የያዘ ሰው ‟የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ዜጋ‟ የሚለውን ትርጉም የማይሸፍን ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 270/94 አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀጽ 1 በግልጽ ተደንግጓል። ተጠሪ ‟የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጋ‟ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የመታወቂያ ካርድ ከኢፋዱሪ ውጭ ጉዲይ ሚኒስትር የተሰጣቸው መሆኑን ያረጋገጡ በመሆኑ የኢትዮጵያን ዜግነት በመተው የኤርትራ ዜግነት መርጠው ይዘው ያልነበረ ስለመሆኑ የሚያሣይ ነው። ስለሆነም አንደኛ አመልካች በህግ ከተሰጠው ሥልጣን ውጭ ንበረትነቱ የኢትዮጵያዊው ብርጋዳር ጄኔራል ገብረአብ ወልዲይና የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑት የተጠሪን ንብረት ለሁለተኛ አመልካች ለመሸጥ ነሐሴ 28 ቀን 1993 ዓ.ም ያደረገው የሽያጭ ውል ፈራሽና ህጋዊ ውጤት የላለው ነው በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ህገ መንግስቱ ለግል ንብረት ባለቤትነት በአንቀጽ 40/1/ የሰጠውን ጥበቃና ዋስትና መሰረት ያደረገና የህግ ስህተት የላለበት ነው።
የሥር ፍርድ ቤት ሁለተኛ አመልካች ቤቱን ከመግዛታቸው በፉት ያለትን አስራስምንት ወራት የቤት ኪራይ ሁለተኛ አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍለ የሰጠው ውሣኔም በሁለተኛ አመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገውን የኪራይ ውል መሰረት ያደረገና የህግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል። አንደኛ አመልካች በዚህ መዝገብ የሸጠውና ክርክር ያቀረበበት ኢትዮጵያዊ ዜግነት የነበራቸውን ብርጋዳል ጄኔራል ገብረአብ ወልዲይንና የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑትን የተጠሪን የጋራ ሀብት መሆኑ ስለተረጋገጠ ይህ የሰበር ችልት በመዝገብ አከራክሮ ውሣኔ ከሰጠበት ጉዲይ ጋር ተመሣሣይነት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም በሰበር መዝገብ የተደረገው ክርክርም ሆነ የሰበር ችልቱ የሰጠው ውሣኔ ለዚህ ጉዲይ አግባብነት የላለው በመሆኑ ይህንን መዝገብ በመጥቀስ ያቀረበው ክርክር ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
ከላይ በዝርዝር በገለፅናቸው ምክንያቶች የሥር ፍርድ ቤት አንደኛ አመልካችና ሁለተኛ አመልካች ነሐሴ 28 ቀን 1993ዓ.ም ያደረጉት የቤት ሽያጭ ውል ፈራሽ በመሆኑ አመልካቾች ቤቱን ለተጠሪ እንዱያስረክቡ በማለት የሰጠውን ውሣኔ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ሁለተኛ አመልካች ቤቱን ከገዛሁ በኃላ ከብር 500‚000/አምስት መቶ ሽ ብር/ በላይ ወጭ በማድረግ የግንባታ ሥራ አከናውኛለሁ በማለት በሰበር አቤቱታቸው ቅሬታ አቅርበዋል። ሁለተኛ አመልካች ቤቱን ከተረከቡ በኃላ ያደረጉት ግንባታ ስለመኖሩ በሥር ፍርድ ቤት አንስተው ያልተከራከሩ መሆኑን የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የመዝገብ በማስቀረብ ለመረዲት ችለናል። ሁለተኛ አመልካች በሥር ያልተከራከሩበትን አዱስ ፍሬ ጉዲይ በሰበር ደረጃ ማንሳታቸው በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 329 ንዐስ አንቀፅ 1 የተደነገገውን መሰረታዊ መርህ የሚጥስ በመሆኑ አልተቀበልነውም።
በአጠቃላይ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ በመንግስት ውሣኔ ከአገር እንዱወጡ የተደረጉ ኤርትራዊያን ንብረትን ለመሽጥ ያወጣውን መመሪያ ይዘትና የተፈፃሚነት ወሰን ያገናዘብና መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ህዲር 24 ቀን 2002ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ እና በመዝገብ መጋቢት 28 ቀን 2002ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ግራቀኙ ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ
No topics extracted.