No summary available.
ግንቦት 15 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢ.ፋ.ዱ. ፍትሕ ሚኒስቴር - ዐ/ህግ አልጋነህ ተሾመ - ቀረቡ ተጠሪ፡-
ጉዲዩ በፋደራል ፍርድ ቤቶች ለሚሰሩ ጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥና ምዝገባ በወጣው አዋጅ ቁጥር 199/1992 አንቀፅ 11/2/ ሥር በተመለከተው ድንጋጌ መሰረት ለጥብቅና ሙያ ፈቃድ የሚሰጥበትን አግባብ የሚመለከት ነው።
ይህ አቤቱታ የቀረበው የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የፍትሕ ሚኒስቴር ለተጠሪዎች እያንዲንዲቸው ያለፈተና የጥብቅና ፈቃድ እንደማይሰጣቸው ባሳወቀው ውሣኔ ቅር በመሰኘት በአዋጅ ቁጥር 199/1992 አንቀፅ 29(1) መሰረት ይግባኛቸውን ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪዎች አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን በተለያዩ መዛግብት አከራክሮ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሰጠውን ውሣኔ በመሻር ተጠሪዎች ያለፈተና የጥብቅና ፈቃድ እንዱሰጣቸው ሲል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋደራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቢያቀርብም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈፅሟልና ሉታረም ይገባዋል በማለት ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘት ተጠሪዎች እያንዲንዲቸው በሕግ የመጀመሪያ ዱግሪ ያላቸውና ዱግሪ ከመያዛቸው በፉት የሥራ ልምድ ያላቸው ቢሆንም ከዱግሪ በኋላ የአምስት ዓመት የሥራ ልምድ የላላቸው በመሆኑ በፋደራል ማናቸውም ፍርድ ቤት ለመከራከር የሚያስችል የጥብቅና ፈቃድ የመግቢያ ፈተና ለመቀበል አዋጅ ቁጥር 199/92 አንቀፅ 11(2) የግድ የሚላቸው ሆኖ እያለ ከዱግሪ በፉት ያለው የሥራ ልምድ ሉቆጠር ይገባል ተብል ትርጉም መስጠቱ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከሩን የሚያሣይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮ በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖበት ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጏላቸው ተጠሪዎች ቀርበው ግራ ቀኙ የፅሐፍ ክርክራቸውን አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው 1ኛ ተጠሪ ሐምል 21 ቀን 1996 ዓ.ም ከሮያል ኮላጅ በሕግ ዱፔልማ፣ ሚያዝያ 02 ቀን 2000 ዓ.ም ከሮያል ዩኒቨርሲቲ ኮላጅ በሕግ ባችለር ዱግሪ የተመረቁ ሁነው በሥራ ልምድ ረገድ ደግሞ ከግንቦት 01 ቀን 1993 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 1995 ዓ.ም፣ ከታህሳስ 01 ቀን 1997 ዓ.ም እስከ ዻጉሜ 05 ቀን 2000 ዓ.ም ድረስ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነገረ ፈጅ፣ ከሐምል 11 ቀን 1999 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 03 ቀን 2002 ዓ.ም በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ዐቃቤ ሕግ ሁነው ያገለገለ መሆኑን፣ 2ኛ ተጠሪ (አቶ በለጠ ታፈሰ) በበኩላቸው ሐምል 07 ቀን 1982 ከአዱስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሕግ ዱፔልማ፣ የካቲት 04 ቀን 2000 ዓ.ም ደግሞ ከሮያል ዩኒቨርሲቲ ኮላጅ በሕግ ባችለር ዱግሪ የተመረቁ ሁነው በሥራ ልምድ ረገድም ከሰኔ 14 ቀን 1985 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 21 ቀን 1987 ዓ.ም በኢትዮጵያ የችርቻሮ ንግድ ድርጅት ኮርፕሬሽን ውስጥ በነገረ ፈጅነት፣ ከጥር 15 ቀን 1987 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 14 ቀን 1988 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች ድርጅት ውስጥ በነገረ ፈጅነት፣ ከታህሳስ 10 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምል 6 ቀን 1989 ዓ.ም ድረስ በእርሻ ሰብል ገበያ ኮርፕሬሽን ውስጥ በነገረ ፈጅነት፣ ከሐምል 10 ቀን 1989 ዓ.ም እስከ መስከረም 27 ቀን 1984 ዓ.ም ድረስ በነገረ ፈጅነት፣ ከመስከረም 28 ቀን 1984 ዓ.ም እስከ ሐምል 30 ቀን 1996 ዓ.ም የሕግ አማካሪ ቢሮ ተጠባባቂ ሒላፉ፣ ከነሐሴ 06 ቀን 1996 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 1998 ዓ.ም የሕግ አገልግልት ተጠባባቂ ኃላፉ፣ ከሐምል 01 ቀን 1998 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 08 ቀን 2000 ዓ.ም ድረስ የሕግ አገልግልት ኃላፉ በመሆን በውሃ ሥራዎችና ኮንስትራክሽን ድርጅት ውስጥ የሰሩ መሆኑን፣ 3ኛ ተጠሪ (ሕይወት ሲሳይ) ደግሞ ሐምል 11 ቀን 1994 ዓ.ም ከአዱስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ዱፔልማ፣ እ.ኤ. አቆጣጠር ጁላይ 22 ቀን 2010 ደግሞ ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ባችለር ዱግሪ የተመረቁ ሲሆን በሥራ ልምድ ደግሞ ከነሐሴ 16 ቀን 1995 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2002 ዓ.ም በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ዐቃቤ ህግ ሁነው ያገለገለ መሆኑ የተረጋገጠ መሆኑን፣ 4ኛ ተጠሪ (አቶ ተሾመ አንጀል) ደግሞ በትምህርት ዝግጅት እ.ኤ.አ. ኖቬንበር 11 ቀን 2004 ዓ.ም ከባሕር ዲር ዩኒቨርሲቲ በሕግ ዱፔልማ፣ እ.ኤ.አ. ዱሴምበር 01 ቀን 2009 ደግሞ ከአልፊ ዩኒቨርሲቲ ኮላጅ በሕግ ባችለር ዱግሪ ያላቸው ሁነው በሥራ ልምድ ረገድም ከየካቲት 01 ቀን 1983 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 01 ቀን 1999 ዓ.ም በአማራ ክልል ውስጥ ዐቃቤ ሕግነት፣ ከሰኔ 15 ቀን 1999 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 03 ቀን 2002 ዓ.ም ድረስ ደግሞ በኢ.ፋ.ድ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር አቃቤ ሕግ ሁነው የሰሩ መሆኑ መረጋገጡን፣ 5ኛ ተጠሪ (አቶ መኳንንት ደግነት) በበኩላቸው ነሐሴ 16 ቀን 1993 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮላጅ በሕግ ዱፔልማ፣ ዻጉሜ 01 ቀን 2001 ዓ.ም ደግሞ ከሮያል ዩኒቨርሲቲ ኮላጅ በሕግ ባችለር ዱግሪ የተመረቁ መሆኑንና በሥራ ልምድ ረገድም ከታህሳስ 01 ቀን 1994 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 1994 ዓ.ም ድረስ ደግሞ የዐቃቤ ሕግ ረዲት፣ ከጥር 01 ቀን 1994 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 1998 ዓ.ም ድረስ በዐቃቤ ሕግ ደረጃ አምስት፣ ከሐምል 01 ቀን 1998 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 1999 ዓ.ም ድረስ ደግሞ በዐቃቤ ሕግ ደረጃ አራት፣ ከሐምል 01 ቀን 1999 ዓ.ም እስከ ጥር 30 ቀን 2002 ዓ.ም ድረስ ደግሞ በዐቃቤ ሕግ ደረጃ ሦስት የሰሩ መሆኑ የተረጋገጠ መሆኑን ነው። ተጠሪዎች ያለፈተና የጥብቅና ፈቃድ ሉሰጠን ይገባል በማለት የሚከራከሩት የሥራ ልምዲቸው መያዝ ያለበት ከዱግሪ በሁዋላ ሳይሆን በፉት ያለውም ጭምር ነው በሚል ሲሆን አመልካች ደግሞ የሚከራከረው የሥራ ልምድ ሉያዝ የሚገባው ከዱግሪ ምረቃ በሁዋላ ያለውን ጊዜ ነው በሚል ተገንዝበናል።
ከላይ እንደተጠቀሰው የአመልካች ጥያቄ ያለፈተና ለማናቸውም የፍደራል ፍርድ ቤቶች የጥብቅና ፍቃድ ማግኘት የሚቻለው በአዋጅ ቁጥር 199/1992 አንቀፅ 11 (2) በተመለከተው ሁኔታ ሆኖ ይህ ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 199/1992 አንቀፅ 8 እና 9 ለተመለከቱት ድንጋጌዎች ልዩ ድንጋጌ ነው በሚል ነው።
በአዋጅ ቁጥር 199/92 የፍደራል የጥብቅና ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት ተዘርግቷል። በዚሁ አዋጅ አንቀፅ 8 (1) በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ ለማግኘት የሚቻልባቸው ሁኔታዎች በግልፅ የተዘረዘሩ ሲሆኑ እነዚህም በሕግ ዱፔልማ ያለው፣ የኢትዮጵያ መሰረታዊ ሕጏችን ማወቅ እንዱሁም አግባብነት ባለው ሙያ ቢያንስ 5 ዓመታት ልምድ ያለው ወይም በሕግ ዱግሪ የተመረቀ፣ የኢትዮጵያን መሰረታዊ ሕጏችን የሚያውቅና በሙያው ቢያንስ የሁለት ዓመት ልምድ ያለው፣ ለፍትህ ሥራ አካሄድ መልካም ሥነ ምግባር ያለው፣ ለደረጃው የሚሰጥን የጥብቅና መግቢያ ፈተና ያለፈ፣ ምግባረ ብልሹነትን በሚያመላክት ወንጀል ተከሶ ያልተቀጣ፣ የሙያ ኃላፉነት መድህን ዋስትና መግባቱን የሚያሳይ ማስረጃ ያቀረበ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሚለ ሲሆኑ ለፈቃደ መሰጠት ፈተና መቀመጥንና ማለፍን የግድ የሚል መሆኑ የአዋጁን አንቀፅ 8 ከአዋጁ አንቀፅ 11(1) ጋር አጣምረን በማንበብ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው።
የፍደራል ማናቸውም ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ ለማግኘት ደግሞ በአዋጁ አንቀፅ 9 ሥር የተመለከቱትን መስፈርቶች ማሟሎት ቅድመ ሁኔታ ነው። በዚህ ድንጋጌ መሰረት የፍደራል ማናቸውም ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ የሚሰጠው በሕግ ዕውቅና ካገኘ የትምህርት ተቋም በሕግ ዱግሪ የተመረቀ፣ የኢትዮጵያን መሰረታዊ ሕጏችን የሚያውቅና በሙያው ቢያንስ አምስት ዓመት ልምድ ያለው፣ ለፍትህ ሥራ አካሄድ መልካም ሥነ ምግባር ያለው፣ ለደረጃው የሚሰጠውን የጥብቅና መግቢያ ፈተና ያለፈ፣ ምግባረ ብልሹነቱን በሚያመላክት ወንጀል ተከሶ ያልተቀጣና፣ የሙያ ኃላፉነት መድህን ዋስትና መግባቱን የሚያሳይ ማስረጃ ላቀረበ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነው።
በአዋጁ አንቀፅ 8 እና 9 ድንጋጌዎች የጥብቅና ፈቃድ ደረጃውን የሚለዩ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሁኖ ፈቃደ የሚሰጠው ለደረጃው የሚሰጠውን ፈተና ላለፈ ኢትዮጵያዊ ብቻ መሆኑን ያስገነዝባለ።
በልላ በኩል አዋጁ ያለፈተና የጥብቅና ፈቃድ የሚሰጥባቸውን ሁኔታዎች ለይቶ አስቀምጧል።
ከእነዚህም በአዋጁ አንቀፅ 10 ሥር የተመለከተው የፍደራል ልዩ የጥብቅና ፈቃድ አንደ ሲሆን ላላው በአዋጁ አንቀፅ 11 (2) ሥር የተመለከቱ መስፈርቶችን የሚያሟለ ኢትዮጵያዊያን የሚመለከተው ነው። የአዋጁ አንቀፅ 11 ንዐስ ቁጥር አንድ ድንጋጌ በአዋጁ አንቀፅ 8 እና 9 ሥር የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟላ ማናቸውም ኢትዮጵያዊ የጥብቅና ፈቃድ የሚሰጠው የፈተና መመዝገቢያ ክፍያ ፈፅሞ የጥብቅና ሙያ መግቢያ ፈተና ሲወስድና ፈተናውን ሲያልፍ መሆኑን የሕጉ መንፈስ ያስገነዝባል። የዚህ ንዐስ አንቀፅ ድንጋጌ ከተጠቀሰው አንቀፅ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ጋር ተጣምሮ ሲነበብም ልዩ የጥብቅና ፈቃድ ጠያቂዎች በኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ቢያንስ በረዲት ፔሮፋሰርነት ወይም የመጀመሪያ ዱግሪ ኖሮት በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና ከዚያ በላይ በዲኝነት ወይም በዐቃቤ ሕግነት ወይም በታወቁ የመንግስት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች በሕግ አማካሪነትና በነገረ ፈጅነት ቢያንስ አምስት ዓመት ያገለገለ ማንኛውም ሰው ሥራውን በለቀቀ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የጥብቅና ፈቃድ ማመልከቻ ካቀረበ የጥብቅና መግቢያ ፈተና እንዱወስድ አይገደድም በሚል በኃይለ ቃል የተቀመጠ ሲሆን ይህ ድንጋጌ በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል ክርክር ያስነሣው የሥራ ልምደ ሉቆጠር የሚገባበትን ጊዜ አስመልክቶ ነው። አመልካች የሥራ ልምደ ሉቆጠር የሚገባው ከዱግሪ ምርቃት በኋላ ነው በሚል የሚከራከር ሲሆን ተጠሪዎች በበኩላቸው የሚከራከሩት በዱግሪ ከመመረቃቸው በፉት የነበራቸው የሥራ ልምድ ሉያዝ እንደሚገባ ሕጉም ያሣያል፣ የአመልካች የቆየ አሰራርም ያስረዲል ይህ ሰበር ሰሚ ችልትም አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል በሚል ነው። እኛም የአከራካሪውን ድንጋጌ አቀራረፅ ይዘትና መንፈሱን አይተናል። በዚህም መሰረት የድንጋጌው የአማርኛው ቅጂ ፡- " በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በሕግ ቢያንስ በረዲት ፔሬፋሰርነት ወይም የመጀመሪያ ዱግሪ ኖሮት በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና ከዚያ በላይ በዲኝነት ወይም በዐቃቤ ሕግነት ወይም በታወቁ የመንግስት መሥሪያ ቤቶችና በልማት ድርጅቶች በሕግ አማካሪነት እና በነገረ ፈጅነት ቢያንስ ለአምስት ዓመት ያገለገለ ማንኛውም ሰው ሥራውን በለቀቀ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ የጥብቅና ፈቃድ ማመልከቻ ካቀረበ የጥብቅና መግቢያ ፈተና እንዱወስድ አይገደድም። " በሚል የተቀመጠ ሲሆን የድንጋጌው የእግንሉዝኛ ቅጂ ደግሞ፡- "Any person who has taught law in Ethiopian higher educational institutions at least as an assistant professor or has served, holding degree in law, at least for five years as a judge or public prosecutor in federal first instance court or above, or as a legal consultant and attorney in known government organs and public enterprises may not be required to take an examination, where he applies for a license within a period of one year from the termination of his employment." በሚል የተቀመጠ ነው።
ከላይ የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟለ ፈቃድ ጠያቂዎች ከፈተና ነጻ እንዱሆኑ የተደረገበት ምክንያት ሲታይም የሥራ ፀባይ በሙያው የዲበረ ልምድ የሚያስጨብጣቸውና ስለ ፍርድ ቤቶችም አሰራር በቂ እውቀት ለማግኘት በበቂ ሁኔታ የሚያስችላቸው መሆኑን በመታመኑ ስለመሆኑ የአዋጁ ሐተታ ዘ ምክንያት ያሣያል። ከላይ ከተመለከቱት የድንጋጌው አማርኛ እና እንግሉዝኛ ቅጂዎች ውስጥ እንደ ቅደም ተከተላቸው ….ኖሮት …. እና Holding a degree in law ….. የሚለት ቃላትና ሐረግ ሲታዩ የሥራ ልምድ ዱግሪ ኖሮት እና ከዚህ ጊዜ በኋላ መቆጠር እንዲለበት ለትርጉም በማይጋብዝና ትርጉሙን በማያሻማ ሁኔታ ከትምህርት ዝግጅቱ በሁዋላ ያለው ጊዜ መሆኑን ያስገነዝባለ። ድንጋጌው በአቀራረፁ፣ በይዘቱና በመንፈሱ ሲታይ ግልፅ በመሆኑ ድንጋጌው ግልፅ እስከሆነ ድረስ ትርጉም የማያስፈልገው መሆኑን ተቀባይነት ያላቸው የሕግ አተረጓጏም ደንቦች የሚያሣዩን ጉዲይ ሲሆን ግልፅነት የለውም፣ ትርጉም ያስፈልገዋል ቢባል እንኳን ድንጋጌው በአዋጁ በአንቀፅ 8 እና 9 ጋር ከተቀመጡት ድንጋጌዎች እና የጥብቅና ሙያ ከደረሰበት የእድገት ደረጃ አንፃር የፈቃድ አሰጣጥ መስፈርቶችን ከፍ በማድረግ በዚህ አገልግልት ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሙያዎች የብቃት ደረጃ ከሚሰጡት አገልግልት ጋር ተመጣጣኝ እንዱሆን ለማድረግ ከሚለው የአዋጁ ዓላማ ጋር ተዛምድ መተርጎም ያለበት ነው። የተጠቀሰው አዋጁ በአንቀፅ 8 እና 9 ሥር የሚሰጠው የጥብቅና ሙያ መግቢያ ፈቃድ የትምህርት ዝግጅቱንና የሥራ ልምደ መስፈርቶች ራሣቸውን ችለው የተቀመጡ መሆኑን የሚያሣይ ሲሆን የአገልግልት ዘመኑ መቆጠር ያለበት በዱፔልማ ወይም በዱግሪ ከተመረቁበት ጊዜ ጀምሮ አለመሆኑን ያስገነዝባል። በእነዚህ ድንጋጌዎች አቀራረፅና ይዘት መሰረት የትምህርት ዝግጅቱና የሥራ ልምደ ራሣቸውን ችለው የቆሙ መስፈርቶች ሁነው እኩል ዋጋ ያላቸው ሲሆን እነዚህን መስፈርቶችን የሚያሟላ ፈቃድ ጠያቂ ለደረጃው የሚዘጋጀውን ፈተና ማለፈ ከተረጋገጠ የጥብቅና ሙያ ፈቃድ እንደሚሰጠው ከአንቀፅ 11 (1) ድንጋጌ ጋር ተጣምሮ ሲነበብ ያስረዲል። በመሆኑም በአዋጁ አንቀፅ 8 እና 9 የተቀመጡት ድንጋጌዎች የሥራ ልምድ ዱፔልማ ወይም ዱግሪ ኖሮት በሚል ያስቀመጡ ሣይሆን የሥራ ልምደ ከትምህርት ዝግጅት ጋር በፉትም ቢሆን እንኳን ከትምህርት ዝግጅቱ እኩል ዋጋ የሚሰጠው መሆኑን ለያይተው የሚገልፁ በመሆኑ በአዋጁ አንቀፅ 11 (2) ሥር ከተመለከተው ድንጋጌ ጋር አንድ ናቸው ልባል የሚቻልበት አግባብ የለም። ሕግ አውጪው የትምህርት ዝግጅቱንና የሥራ ልምደን ለያይቶ እኩል ዋጋ በአንደ አንቀፅ ከሰጠ በሁዋላ በተከታዩ ድንጋጌ ተመሣሣይ መንፈስ ያለው አንቀፅ ያስቀምጣል ማለት ትርጉም አልባ ከመሆኑም በላይ የሕጎችን ዐውደ ንባብ (contextual interpretation) ትርጓሜ ያልተከተለ፤ አዋጁ ውጤት እንዱኖረውና በአዎንታዊ መንገድ ታይቶ ሥራ ላይ እንዱውል ለማድረግ የሚያስችል የአተረጓጎም መንገድ ሆኖ አይገኝም። አንድ ድንጋጌ ግልፅነት የሚጎድለው መሆኑ ከታመነበት የድንጋጌው ትክክለኛ ትርጉሙ የሕጉን አጠቃላይ ድንጋጌዎችን በማየት ሉተረጎም እንደሚገባ ተቀባይነት ያላቸው የሕግ አተረጓጎም ደንቦች ያሳያለ።
በመሆኑም በአዋጁ አንቀፅ 11 (2) ሥር የተመለከተው ድንጋጌ በአዋጁ አንቀፅ 8 እና 9 ከተመለከቱት ድንጋጌዎች እና ከላልች የአዋጁ ድንጋጌዎች ጋር ተዛምድ ሲታይ ለተያዘው ጉዲይ ልዩ ድንጋጌ ሲሆን ጉዲዩ መገዛት ያለበትም በዚሁ ልዩ ድንጋጌ መሰረት ነው። የሥር የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአዋጁን አንቀፅ 11(2) ድንጋጌ ከላይ በተመለከተው ሁኔታ በግልፅልነቱ በመቀበል ወይም ልዩ ድንጋጌ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ውጤት ባለው መልኩ በመተርጎም ተግባራዊ ማድረግ ሲገባው በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ የሚተገበረውን የሥራ ልምድ አያያዝ አሰራር በመመርኮዝ የሥራ ልምደ ከዱግሪ ምርቃት በሁዋላ ላሆን አይገባም በማለት የደረሰበት ድምዲሜ የድንጋጌውን ይዘትና መንፈስ እንዱሁም ከላይ ከተጠቀሰው ከአዋጁ አላማ ጋር ተዛምድ ሲታይ ሕጋዊ መሰረት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
የፋደራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለጉዲዩ በዋቢነት የጠቀሰውና በሰ/መ/ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው የሕግ ትርጉምም በመዝገቡ የሰበር አመልካች የነበሩት ግለሰብ የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ መግቢያ ፈተና ለመውሰድ እንዱፈቀድላቸው ቢያመለክቱም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የአመልካች ጥያቄና ማስረጃ በማገናዘብ በሰጠው ውሣኔ አመልካች ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮላጅ ነሐሴ 10 ቀን 1998 ዓ.ም በሕግ ዱፔልማ ከተመረቁ በኋላ በፋደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥ እና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 199/92 አንቀፅ 8/1/ መሰረት በሙያው 5 ዓመት ያላገለገለ ናቸው በማለት የአመልካች ጥያቄን ሳይቀበለው በመቅረቱ በድንጋጌው የተመለከተው የሥራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት እኩል ዋጋ ያላቸው የተለያዩ መስፈርቶች ከሚሆኑ በስተቀር ሁለቱም አንድ ጊዜ እንዱሟለ ሕጉ የግድ አይልም፣ የሰበር አመልካቹ ለፈተና እንዱቀመጡ ሉፈቀድላቸው ይገባል ተብል የተሰጠ ትርጉም ነው እንጂ በአዋጁ አንቀፅ 11(2) ሥር የተመለከቱትን መስፈርቶች ተመልክቶ ትርጉም የሰጠበት መዝገብ አይደለም።
በመሆኑም አንድ የሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው የሕግ ትርጉም በማናቸውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገድደው ተመሣሣይ ለሆኑ ጉዲዮች ነው። የተያዘው ጉዲይ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ን ከሰጠው የሕግ ትርጉም ጋር ተመሣሣይነት የላለው በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት የሰ/መ/ ለውሣኔው በዋቢነት መጠቀሱ አግባብነት የላለው ሆኖ አግኝተናል።
በአጠቃላይ ተጠሪዎች ለጠየቁት የጥብቅና ፈቃድ ደረጃ በሕጉ የተመለከቱትን መስፈርቶች አላሟለም በማለት አመልካች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የሰጠውን ውሣኔ የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች መስፈርቱን እንዲሟለ በማድረግ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ውሣኔ በመሻሩ በሕጉ አተረጓጎምና አተገባበር ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 98707 ታህሳስ 14 ቀን 2003 ዓ.ም፣ በመ/ ታህሳስ 19 ቀን 2003 ዓ.ም ተሰጥተው በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ የፀኑት ውሣኔዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
አመልካች ለተጠሪዎች እያንዲንዲቸው ያሳወቀው ውሣኔ ጸንቷል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
በዚህ መዝገብ የተሰጠው ውሣኔ ግልባጩ ከሰ/መ/ ጋር ይያያዝ ብለናል።
No topics extracted.