No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 15 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበላ ዐ5/06/07 የሚገኝና ቁጥሩ 832 የሆነና በርካታ ክፍልችን የያዘ ህንጻ በአዋጅ ቁጥር 47/67 ተወርሶና ተረክቦት እስከ ህዲር 1992 ዓ.ም እያከራየ ሲጠቀምበት የኖረ መሆኑን ከገለጸ በኋላ ህንጻውን የኢትዮጵያ ፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ በሰጠው ውሣኔ መሰረት ህዲር 24 ቀን 1992 ዓ.ም አስረክቤያቸው ነበር። ሆኖም ቤቱን ተከሣሾች እንዱከራዩ ውሣኔ የተሰጠው በሀሰተኛ ማስረጃ መሆኑን በማረጋገጥ ተከሣሾች ለከሣሽ ቤቱን እንዱያስረክቡ ሀምላ 14 ቀን 1998 ዓ.ም በፔራይቬታይዜሽንና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ወስኗል።
ከሣሽ ከህዲር 1992 ዓ.ም ጀምሮ ቤቱን በማከራየት ያገኘው የነበረው ጥቅም ተቋርጦበታል።
ተከሣሾች የተቋረጠውን ጥቅም /ኪራይ/ ቤቱን እስኪያስረክቡ ድረስ በማሰብ እንዱያስረክቡ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት በአመልካቾችና በላልች አራት ሰዎች ላይ ክስ አቅርቧል። አመልካቾች በተከሣሽነት ቀርበው ከሣሽ አላግባብ በልጽጋችኋል በማለት ያቀረበው ክስ የህግ መሰረት የለውም።
ከሣሽ ከሀምላ 14 ቀን 1998 ዓ.ም በኋላ ያለውን ኪራይ ከሚጠይቅ በስተቀር በውሣኔ ባለመብት ሆነን ቤቱን ከያዝንበት ከህዲር 1992 ዓ.ም ጀምሮ ኪራይ እንድንከፍል ያቀረበው ጥያቄ የህግ መሰረት የለውም።ተከሣሾች ቤቱን ከተረከብን በኋላ ብር 1,63ዐ,ዐዐዐ /አንድ ሚሉዮን ስድስት መቶ ሰላሣ ሺ ብር/ በማውጣት ቤቱን ያሣደስን በመሆኑ ሉቻቻልልን ይገባል የሚል ክርክር አቅርበዋል።
የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተከሣሾች ከሣሽ ቤቱን ካስረከበበት ህዲር 12 ቀን 1992 ዓ.ም ጀምሮ ቤቱን እስከተረከበበት ድረስ ባለት 117 ወራት /አንድ መቶ አስራ ሰባት ወራት/ ቤቱን አከራይቶ ሲያገኝ የነበረውን ገንዘብና የተጨማሪ እሴት ታክስ ስራ ላይ ከዋለ በኋላ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተደምሮበት ለከሣሽ የመክፈል ሀላፉነት አለባቸው በማለት ወስኗል። አመልካቾች ይግባኝ ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል።
ይግባኝ ሰሚ ችልት የአመልካቾችን ይግባኝ በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካቾች መስከረም 14 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ዲኝነት ከጠየቀበት ገንዘብ በላይ እንድንከፍል ወስኖብናል። አመልካቾች ቤቱን ለማሣደስ ከብር 1,63ዐ,ዐዐዐ እንዲወጣን በመግለጽ ያቀረብነውን የመቻቻል ጥያቄ በመቃወም ተጠሪ ያቀረበው ክርክር የለም። ይኸም ተጠሪ የአመልካቾችን ክርክር እንዲመነ የሚያስቆጥረው መሆኑ በፍታብሓር ሥነሥነዓት ህጉ ተደንግጏ እያለ በተጠሪ በታመነው ጉዲይ ላይ ውሣኔ ሣይሰጥበት ማለፊ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። የከፉል አገልግልት ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈልበት አገልግልት አይደለም።
ስለዚህ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዱከፈል የሰጠው ውሣኔ ተገቢነት የለውም ተጠሪ ቤቱን በፉት ከሚያከራይበት በተሻለ ዋጋ ያከራየው ቤቱን እኛ ከተረከብን በኋላ ስላሳደስነው ነው። ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች በእኛ በኩል የቀረቡ መከራከሪያዎችን ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩለ ህዲር 27 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተጻፈ መልስ የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክሯል። አመልካች ታህሣስ 25 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር በግራ ቀኙ የቀረበው የጽሁፍ ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም አመልካቾች ቤቱን በኢትዮጵያ ፔራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ውሣኔ ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ ቤቱን ለተጠሪ እንዱመልሱ እስከተወሰነበት ሀምላ 14 ቀን 1998 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ተጠሪ ቤቱን በማካራየት ሉያገኝ ይችል የነበረውን ገቢ እንዱከፍለ የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
የሚለውን ነጥብ መመለስ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካችና ተጠሪ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2162 ይዘት ትርጉምና የተፈጻሚነት ወሰን አስመልክቶ ሰፉ የህግ ክርክር ያቀረቡ ቢሆንም በዚህ መዝገብ የተያዘውን ጉዲይ ለመወሰን የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 349 ድንጋጌዎች አግባብነት ያላቸው ሆነው አግኝተናቸዋል። የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 349/1/ ጉዲዩን በመጀመሪያ አይቶ የወሰነው ፍርድ ቤት ውሣኔ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የተለወጠ ወይም የተሻረ ሲሆን በተለወጠው ወይም በተሻረው ፍርድ መሰረት የተወሰደ ንብረት የሚመለስበትና የተከራካሪ ወገኖች መብት እንዱስተካከል ፍርድ ቤቱ ተስማሚ መስል የታየውን ትዕዛዝ መስጠት እንዲለበት ይደነግጋል። የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 349 ንኡስ አንቀጽ 2 በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 349 ንኡስ አንቀጽ 1 የተደነገገውን ለማስፈጸም ፍርድ ቤቱ የተወሰደ ገንዘብ እንዱመለስ ወለድ እንዱከፈል ፣ ኪሣራ እንዱወሰን ፣ ካሣና ያላግባብ የተወሰደ ጥቅም እንዱከፈል ወይም በፍርደ መሻሻል ወይም መለወጥ ምክንያት የተካራካሪ ወገኖች መብትን ለማስተካከል ተገቢ መስል የታየውን ትዕዛዝ ለመስጠት የሚችል መሆኑን ይደነግጋል።
የፍታብሓር ህግ ቁጥር 349 በመጀመሪያ ጉዲዩን ባየው ፍርድ ቤት የተሰጠ ውሣኔ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በሚለወጥበት ወይም በሚሻርበት ጊዜ ተፈጻሚ እንደሚሆን ከድንጋጌው ይዘት ለመረዲት ይቻላል። ሆኖም የፍታብሓር ህግ ቁጥር 349 የመጀመሪያ ውሣኔ ወይም ፍርድ በይግባኝ ሲሻርና ሲለወጥ ብቻ ሣይሆን የመጀመሪያውን ውሣኔ የሰጠው ፍርድ ቤት ወይም የዲኝነት ስልጣን በህግ የተሰጠው አካል የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 6 እና ላልች የሥነ- ሥርዓት ህግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ጉዲዩን እንደገና አይቶ ቀደም ብል የሰጠውን ውሣኔ በሚያሻሽልበት ወይም በሚሽርበት ጊዜ ተፈጻሚነት ያለው ድንጋጌ እንደሆነ የድንጋጌውን ርዕስ አቀራራጽና መሰረታዊ ግብና ዓላማ በማገናዘብ ለመረዲት ይቻላል።
ስለሆነም ተጠሪ ቤቱን ለአመልካቾች እንዱያስረክብ በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ወስኖ የነበረው የኢትዮጵያ ፔራይቬታይዜሽንና የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 6 መሰረት እንደገና በማየት ከዚህ በፉት የሰጠውን ውሣኔ ሙለ በሙለ ሰርዞታል።
የኤጀንሲውን ውሣኔ የማስፈጸም ስልጣን የፍ/ቤት መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 193/92 ተደንግጓል። ይህ ከሆነ አመልካቾች ቤቱን ለተጠሪ የማስረከብ ብቻ ሣይሆን ተጠሪ ቤቱን እያከራየ ያገኝ የነበረውን ጥቅም እንዱተኩ የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠው ወሣኔ የፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 349 ንኡስ አንቀጽ 1 እና ንኡስ አንቀጽ 2ን መሰረት ያደረገ በመሆኑ አመልካቾች ቤቱን በህጋዊ ውሣኔ ከተረከብን በኋላ ተጠሪ ያቀረቡትን የቤት ኪራይ እንድንከፍል የተሰጠው ውሣኔ የህግ መሰረት የላለው ነው በማለት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ አልተቀበልነውም።
አመልካቾች ቤቱን እስከሚያስረክቡበት ጊዜ ድረስ ያለው ሂሣብ ታስቦ እንዱከፈለው በግልጽ የዲኝነት ጥያቄ ያቀረበ መሆኑን ከስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ተረድተናል። አመልካቾች ተጠሪ ከጠየቀው የዲኝነት ጥያቄ በላይ የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ሰጥቷል በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
በዚህ መንገድ የሚቀርቡ ክርክሮች በዲኝነት ታይተው ውሣኔ የሚሰጥባቸው በመጀመሪያ የዲኝነት ተከፍልባቸው ሲቀርቡ እንደሆነ ከፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 215 ንኡስ አንቀጽ 1 እና ንኡስ አንቀጽ 2 ተደንግጓል። አመልካቾች ቤቱን ከተረከቡት በኋላ ብር 1,63ዐ,ዐዐዐ /አንድ ሚሉዮን ስድስት መቶ ሰላሣ ሺ ብር/ በማውጣት እንዲሣደሱ በመግለጽ የመቻቻል ጥያቄ ያቀረቡት ከላይ የጠቀስነው የሥነ-ሥርዓት ህግ በሚደነግገው መሰረት የዲኝነት ገንዘብ ከፍለውና ሥርዓቱን አሟልተው ስለ መሆኑ አልተረጋገጠም። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤትም ሆነ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አመልካቾች የዲኝነት ገንዘብ ሣይከፍለና ሥርዓቱን ሣያሟለ ያቀረቡትን የመቻቻል ጥያቄ በጭብጥነት ሣይዙና ውሣኔ ሣይሰጡበት ማለፊቸው የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አላገኘነውም።
ከላይ በዝርዝር በገለጽናቸው ምክንያቶች የስር ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠው ውሣኔ ጸንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሣቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.