No summary available.
ግንቦት 04 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ባልቻ ወ/ፃድቅ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ግርማ ቀለታ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለው ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልካች ቃረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ያቀረበ ነው አመልካችና ተጠሪ የሚከራከሩት የጥበቅና ግልጋልት አሰጣጥን በሚመለከት ጉዲይ ነው። አመልካች ከወ/ሮ እታገኘሁ በሻህ ጋር በአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የነበረኝን የፍታብሓር ክርክር ለመከታተልና ጉዲዩን እስከሰበር ችልት ድረስ እኔን በመወከል ሉከራከሩልኝ ከተጠሪ ጋር ውል ተዋውለናል። ከሳሽ በውል ከተስማማነው ብር 2‚000 /ሁለት ሺ ብር/ ውስጥ ብር 1‚000 /አንድ ሺ ብር/ ለተከሳሽ ከፍያለሁ። ተከሳሽ ተገቢውን የጥብቅና አገልግልት ያልሰጡኝ በመሆኑ የከፈልኩትን ገንዘብ ከነኪሣራው እንዱመልስ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። የማህበራዊ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ተጠሪ ለአመልካች ብር 2‚000 /ሁለት ሺ ብር/ ይክፈለ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ተጠሪ ይግባኝ አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከአመልካች ጋር የጥብቅና አገልግልት ለመስጠት የተዋዋለው በአዱስ አበባ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለመከራከር እንጂ በይግባኝና በሰበር ለመከራከር አይደለም በማለት የማህበራዊ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ለከተማው ሰበር ችልት አቅርቦ የሰበር አቤቱታው ውድቅ ተደርጎባቸዋል።
አመልካች ተጠሪ ጋር ያደረግሁት የጥብቅና አገልግልት ውል ተጠሪ እኔ ከወ/ሮ እታገኘሁ በሻህ ጋር ባለኝ የፍታብሓር ክርክር በአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በይግባኝና በሰበር ሉቆሙልኝ መሆኑ በውለ ተገልፆ እያለ የማህበራዊ ፍርድ ቤት ውሣኔ በይግባኝ ያየው የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከተማው ሰበር ችልት ውለ በአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ብቻ ለመከራከር የተደረገነው በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩላቸው ውለ በአዱስ አበባ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የጥብቅና ግልጋልት ለመስጠት የተደረገ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሣኔ ላይ ይግባኝ ማቅረቡ የማይጠቅማቸው መሆኑን መክሬአቸዋለሁ። አመልካች ከሙያ አንፃር የማያዋጣውንና የማላምንበትን ጉዲይ ይግባኝ ካላቀረብክ በማለት ያቀረቡት ክስ የህግ መሰረት የለውም በማለት ተከራክሯል። አመልካች የመልስ መልስ በፅሐፍ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥ በሰበር ግራ ቀኙ ያቀረቡት የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከተማው ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
በአመልካችና በተጠሪ መካከል ሰኔ 12 ቀን 2000 ዓ.ም የተደረገው የጥብቅና አገልግልት ውል ስምምነት ‛እኔ ውል ሰጭ ከወ/ሮ እታገኘሁ በሻህ ጋር በአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስላለኝ የቦታ ክርክር ጉዲይ ውል ተቀባይ ባላቸው የጥብቅና ሙያ ጉዲዬን እስከ መጨረሻ ድረስ ሉከራከርልኝ ለዚህ አገልግልታቸው ብር 2‚000 /ሁለት ሺ ብር/ ልከፍላቸው የተሰማማን ሲሆን“ በሚል መንገድ በተራ ቁጥር 1 የአመልካችን ግዳታ የሚገልፅ ሲሆን በተራ ቁጥር 2 ‛እኔም ውል ተቀባይ በተራ ቁጥር 1 ላይ በተገለፀው መሰረት የውል ሰጭው ጉዲይ እስከመጨረሻ ድረስ ልከራከርላቸው ተስማምተን በቅደሚያ ብር /አንድ ሺ ብር/ ተቀብያለሁ“ በሚል መንገድ የተጠሪን ግዳታ የሚገልጽ ሆኖ አግኝተናል። በአመልካች እና ተጠሪ መካከል በተደረገው ውል ውስጥ ‛ እስከመጨረሻ ድረስ ሉከራከሩልኝ“ የሚለውና ‛እስከ መጨረሻ ድረስ ልከራከርላቸው“ የሚለው ቃል ተጠሪ በአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ብቻ ለመከራከር የውል ግዳታ እንደገቡ በማድረግ የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ትርጉም የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1732 እና የጥብቅና አገልግልት በደንብ ቁጥር 57/1992 አንቀፅ 8/2/ የተደነገገውን ያላገናዘበና የአተረጓጉም ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለዚህ ‛እስከ መጨረሻ ድረስ“ ልከራከርላቸው በማለት ተጠሪ የገቡት ውል ይዘት አመልካች ከሙያ አንፃር የሚያዋጣ ከሆነ ይግባኝ አቅርቦ የመከራከርና በሰበር አቤቱታ አቅርቦ መከራከረን የሚጨምር በመሆኑ በዚህ በኩል የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከተማው በሰበር ችልት የሰጡት ትርጉም ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም በመሆኑም ተጠሪ በአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ብቻ ለመከራከር ነው በጥብቅና አገልግልት ውለ የተስማማሁት በማለት ያቀረቡትን መከራከሪያ አልተቀበልነውም።
የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከተማው ሰበር ችልት የአመልካችንና የተጠሪን ውል ሲተረጉሙ ስህተት የሰራ ሲሆን ተጠሪ ያቀረበው ሁለተኛ መከራከሪያ ስንመለከተው ፍርድ ቤቶቹ የደረሱበትን መደምደሚያ የሚያስለውጥ ሆኖ አላገኘነውም። ተጠሪ ከሙያ አንፃር አመልካች ከህግ አንፃር ማድረግ የሚገባቸውን የማስረዲትና ግልፅ የማድረግና የማማከር ግዳታና አከሪካሪ ጉዲይ በላለበት ክስና ክርክር ያለማቅረብ ግዳታ እንዲለበት በደንብ ቁጥር 57/92 አንቀፅ 28 በግልፅ ተደንግጓል። በአመልካችና በወ/ሮ እታገኘሁ በሻህ መካከል በአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የነበረው ክርክር የቦታ ይዞታ ክርክር ሲሆን በጉዲዩ አመልካች የሁከት ይወገድልኝ ክስ አቅርበው ነበር። በክርክሩ ሂደት ክርክር የተነሳበት ቦታ የማናቸው ይዞታ እንደሆነ አጣርቶ እንዱገልፅ የአቃቂ ቃሉቲ ክፍለ ከተማ አስተዲዲር ተጠይቆ ተከሳሽ ወ/ሮ እታገኘሁ የአመልካችን ቦታ አልፍ እንዲልያዘ እና በተቃራኒው አመልካች የወ/ሮ እታገኘሁን ህጋዊ ይዞታ አልፍ የያዘ መሆኑን በማረጋገጡ የአመልካች ክስ ውድቅ መሆኑን የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሀምላ 9 ቀን 2000 ዓ.ም ከሰጠው ውሣኔ ተገንዝበናል። ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ ባይ የሰበር አቤቱታ ማቅረብ ከሙያ አንፃር እንደማያዋጣ የምክር አገልግልት ከሰጠ ለአመልካች የይግባኝ አቤቱታ የማቅረብ ግዳታ የለበትም። አመልካች የተጠሪን ምክር ወደጎን በመተው ይግባኝ አቅርቦ ይግባኙ የተሰረዘበት ሲሆን የሰበር አቤቱታው ውድቅ ተደርጎበታል።
ስለሆነም ተጠሪ ተገቢ የሆነ የሙያ ግልጋልትና ምክር ለአመልካች የሰጠ በመሆኑ በውጤት ደረጃ የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከተማው የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና የከተማው ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ምክንያቱ ተለውጦ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ
No topics extracted.