No summary available.
ግንቦት 2 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ መልድ አልማው ወላ አሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሤ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤላክትሪክ ኃይል ኮርፕሬሽን ነገረፈጅ ተስፊዬ ከርጋ - ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡-
አቶ ወልደ በየነ ቀረቡ።
አቶ ታምሩ አያለው - ቀረቡ።
አቶ አየለ ዋቀዮ በ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ተወካይነት ቀረቡ።
አቶ ተስፊዬ በዲዲ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የደሞዝ ጨማሪን የሚመለከት ክርክር ሲሆን የአሁን ተጠሪዎች በበታች ፍ/ቤት ከሣሾችና አመልካች ደግሞ ተከሣሽ ነበር። ክሱ የቀረበው በኦሮሚያ ብሓ/ክ/መንግሥት የምሥረቅ ኦሮሚያ አሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ ሲሆን ቀርቦ የነበረው ክስ በጡረታ እድሜያችን የጡረታ አበል ያገኙ የነበረና ተከሣሽ በኮንትራት ሲቀጥረን በጡረታ በምናገኘው ክፍያ ላይ 291 ብር ጨምሮ ይከፍለን የነበረና የጡረታ ደብተራችንም የተመለሰ መሆኑ ይሁን እንጂ የጡረታ እና ዋስትና ባለሥልጣን ከሐምል 1999 ዓ.ም ጀምሮ ጭማሪ ቢያደርግም የአሁን ተከሣሽ በደሞዛችን ላይ እንዱጨምርልን ስንጠይቅ መልስ ሣይሰጠን ቆይቶ ከጥር 1 ቀን 2001 ዓ.ም እስከ ግንቦት 30 ቀን 2001 ዓ.ም ድረስ ያለውን ብቻ ከፍልናል። ስለዚህ ከሐምል 1 ቀን 1999 ዓ.ም እስከ ታህሣሥ 30 ቀን 2001 ዓ.ም ድረስ ያለውን የ18 ወር ውዝፍ እንዱከፍል የሚል ነበር።
ተከሣሽ በበኩለ በሰጠው ከሣሾች በጡረታ ላይ የነበሩ ቢሆንም በግልፅ ውል በአዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 4 መሰረት ተቀጥረው እንደማንኛውም ሰራተኛ የሚመለከታቸውን ደሞዝና ጥቅማጥቅም እያገኙ ነው፣ ማህበርዊ ዋስትና በኑሮ ውድነት ምክንያት ደሞዝ ሲጨምር እኛም መጨመር እንዲለብን የተደረገ ስምምነት የለም። እንዱሁም ክሱ በይርጋ ቀሪ የሆናል በማለት ተከራክሯል።
ቦርደ ከላይ እንደተመለከተው ከክርክር በኋላ የቀረበው ክስ የሕግ ድጋፍ የለውም በማለት ውድቅ አድርጓል። በዚህ ውሣኔ የአሁን ተጠሪዎች ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብለው ፍ/ቤቱ ከክርክር በኋላ የአሁን አመልካች ከሐምል 1 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ መንግሥት በጨመረው መሰረት ለአሁን ተጠሪዎች ሉከፍላቸው ይገባል በማለት የቦርደን ውሣኔ በመሻር ውሣኔ ሰጥቷል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ ከዚሁ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሣኔ ሲሆን በ03/13/2003 2 ገጽ በተፃፈ አቤቱታ መንግሥት የሰጠውን ጭማሪ አስቀምጦ በውላችን ውስጥ የካተተ ነገር ባለመኖሩ ልንከፍል አየገባም። በተጨማሪም ክሱ በይርጋ ይታገዲል በማለት አመልክቷል። ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል በመባለ ተጠሪዎች በ29/03/2003 ዓ.ም 2 ገጽ ላይ ጽፈው ባቀረቡት መልስ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ በአግባቡ በመሆኑ እንድፀና የሚል ነበር። ከዚህ በኋላ አመልካች የመልስ መልስ እንድያቀርብ በተቀጠረበት ባለመቅረቡ መዝገቡ ለምርመራ አድሯል።
በግራ ቀኙ የተደረገው የክርክር ሂደቶች ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የቀረበውን ቅሬታ ከተያዘው ጭብጥና ከሚመለከታቸው ሕጎች ጋር መርምሮአል። እንደመረመርነውም ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ሲባል የክፍያውን አግባብነት በግራ ቀኙ መካከል ከተመሰረተው የሥራ ውል አኳያ ለመመርመር ነው። ችልቱም ጉዲዩን ከዚህ አኳያ መርምሮታል።
በመጀመሪያ ደረጃ የአሁን ተጠሪዎች በጡረታ ላይ የነበሩ ሰዎች ሆነው የቅጥር ውል ከአሁን አመልካች ጋር የፈፀሙ ስለመናቸው አላከራከረም። ይሄ የሥራ ውል ግንኙነት በመፈጠሩ ምክንያት የጡረታ ደብተራቸውን ለሚመለከተው የመንግሥት አካል የመለሱ መሆናቸውን ተጠሪዎች ራሣቸው አመልክተዋል። በግራ ቀኙ የሥራ ውል ውስጥ አመልካች ለአሁን ክስ ምክንያት የሆነውን ክፍያ ለመክፈል የገባው ግዳታ ያለመኖሩን አመልካች የተከራከረ ሲሆን ተጠሪዎችም በውላቸው ውስጥ የተቀመጠ ግዳታ ስለመኖሩ ያነሱት ነገር ካለመኖሩም በላይ እንደዚህ ዓይነት ግዳታ በመካከላቸው ያለመኖሩን የበታች ፍርድ ቤት አረጋግጧል።
በልላ በኩል አንድ ጡረታ የወጣ ሰው ተመልሶ ብቀጠር እንደማንኛውም ተቀጣሪ ሰራተኛ ማግኘት ያለበትን ክፍያ ከመጠየቅ ባለፈ ለጡረተኞች የክፍያ ጭማሪ በማደረጉ ብቻ አመልካች የተደረገውን ጭማሪ እንድከፍል የሚያሰገድድ የህግ ማዕቀፍ የለም። በመሆኑም አመልካች መንግሥት ለጡረተኞች ያደረገውን የደመወዝ ጭማሪ ለተጠሪዎች እንዱከፍል በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ብሓ/ክ/መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ/93661 በ29/10/2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የምሥራቅ ኦሮሚያ አሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ በቁጥር 664/01/2002 በ26/6/2002 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
ተጠሪዎች ጡረታኝነታቸውን በመተው የሥራ ቅጥር ውል ከአመልካች ጋር ከፈፀሙ በኋላ መንግሥት ለጡረተኞች በኑሮ ውድነት ምክንያት ደሞዝ ጨምሯል በሚል አመልካች ጭማሪውን እንዱከፍል ለመጠየቅ የሚያስችል ከውል ወይም ከህግ የሚመነጭ መብት የለም ብለናል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ላይ የደረሰውን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡን ዘግተን ወደ መዝገብ ቤት መልስናል።
No topics extracted.