No summary available.
ግንቦት 16 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጉስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሤ አመልካችቾች፡- 1. ኤርሰዳ ንግድ ኃ/የተ/የግል ማህበር - ጠበቃ አቶ አብደርማን መሀመድ - ቀረቡ 2. አቶ ፀደቀ ማርቆስ - ጠበቃ አቶ ዲንኤል ወ/ጊዮርጊስ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ዐ/ሕግ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምር የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የአሁን ተጠሪ ለሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ያቀረባቸው ሁለት የወንጀል ክሶችን ሲሆን 1ኛ ክስ በሥር 1ኛ ተከሳሽ /በአሁን 1ኛ አመልካች/ ላይ የቀረበ ነው። የክሱ ፍሬ ቃልም ተከሳሹ በ1996 ዓ/ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 34/1/ እና የቡና ጥራት ቁጥጥር እና ግብይት አዋጅ ቁጥር 602/2000 አንቀጽ 14/3/ እና 15/3/ በመተላለፍ የቡና ላኪነት ፈቃድ አውጥቶ በቡና ግብይት ሥራ ላይ ተሰማርቶ ሲንቀሳቀስ በአንድ የምርት ዘመን ከጨረታ ማዕከላትና ከኢት/የምርት ገበያ የገዛውን ቡና የሚቀጥለው የምርት ዘመን ከመድረሱ በፉት በሚመለከተው ገበያ አቅርቦ መሸጥ ሲገባው መጋቢት 23 እና 30/2001 የቡና ክምችቶ ቆጠራ በተደረገበት ወቅት በድርጅቱ መጋዘኖች ከተገኘው 203‚577 ኪል ግራም ውስጥ ለኤክፕርት የተዘጋጀ 101‚580 ኪ.ግ የከረመ ቡና ለገበያ ሳያቀርብና ለሚመለከተው አካል ሳያሳውቅ ቡና አከማችቱ በመገኘቱ ተከሷል የሚል ሲሆን፣ 2ኛ ክስ በሥር 2ኛ ተከሳሽ /በአሁኑ 2ኛ አመልካች/ ላይ የቀረበ ነው። 2ኛ የሥር ተከሳሽ የ1ኛ ተከሳሽ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 602/2000 አንቀጽ 14/3/ እና 15/3/ ሥር በ1ኛ ክስ የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት በመፈፀሙ ተከሷል የሚል ነው።
የሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከቀረቡት ማስረጃዎች አንፃር በመመርመር በሰጠው ፍርድ 1ኛ ተከሳሽን ክስ በቀረበበት የወንጀል ህግ አንቀጽ 34/1/ እና በአዋጅ ቁጥር 602/2000 አንቀጽ 15/3/ ሥር ጥፊተኛ ነው በማለት በብር 40‚000 እንዱቀጣ የወሰነ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በመሆኑ በአዋጅ አንቀጽ 15/3/ ሥር ጥፊተኛ ሆኖ በ1 ዓመት ቀላል እሥራት እና በብር 30‚000 የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጣ ወስኖበታል።
በዚሁ በፋ/የመ/ደረጃ ፍ/ቤት ውሳኔ የሥር ተከሳሾች ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለሥር የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ከፍተኛ ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ተከራካሪዎች ካከራከረ በኋላ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 195/2/ /ለ/ /2/ መሰረት የሥር የመ/ደ/ፍ/ቤትን የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሳኔን አጽንቷል።
የሰበር አቤቱታም የቀረበው በሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን አመልካቾች በዋናነት የጠቀሱአቸው የቅሬታ ነጥቦችም፡የተጠሪ ክስ አቀራረብ ከአዋጅ ቁጥር 602/2000 አንቀጽ 15/3/ አባባል ጋር ተጣጥሞ ባለመቅረቡ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 130/1/ መሰረትም የአመልካቾችን የመከላከል መብት የሚያጣብብ በመሆኑ ክሱ ተሻሽል እንዱቀርብ ያቀረብነውን ተቃውሞ የሥር ፍ/ቤት ውድቅ ማድረጉ ያለአግባብ ነው፤
የወንጀለ አፈፃፀም ከጥርጣሬ በፀዲ መልኩ ሳይረጋገጥ የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሣኔ መሰጠቱ ተገቢነት የለውም፤
ከረመ የተባለው ቡና የምርት ዘመኑ ሳያልፍ ጥር 10 ቀን 2001 ዓ/ም ተሸጦ የውል መፈፀሚያው ቀን የክፍያ ማረጋገጫ የቀረበበት ቀን ተደርጏ መወሰደ ያለአግባብ ነው የሚለ ናቸው።
ለሰበር አቤቱታ ተጠሪው በሰጠው መልስ አመልካቾች ክሱ ተጠቅሶ የቀረበብንን የአዋጅ ቁጥር 602/2000 አንቀጽ 15/3/ ዝርዝር ሁኔታን አያሟላም በማለት በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 130/1/ እና 119 መቃወሚያ በማቅረብ ተሻሽል እንዱቀርብ ጠይቀን ታልፍብናል ያለትን በሚመለከት የሥር ፍ/ቤት ምላሽ እንድንሰጥበት በጊዜው ጠይቆን አመልካቾች ቡናን ወደ ውጪ ሀገር ለመላክ ፈቃድ አውጥተው የሚንቀሣቀሱ እንደመሆናቸው መጠን ቡናን ለማገበያየት ፈቃድ ካለው አካል የገዙትን ያልተዘጋጀ ቡና ለኤክስፕርት በሚመጥን መልኩ አዘጋጅተው ወደ ውጪ ሀገር ከሚልኩ በስተቀር ቡናውን ለላላ አላማ ሉያውለት እንደማይችለና የተከማቸውም ቡና ለግብይት የሚውል መሆኑን አስረድተናል። አመልካቾች የሽያጩ ጊዜ ከማለፈ በፉት ሽያጩ ተከናውኗል ያለትም ቢሆን ገዥ ነው የተባለው ኩባንያ የግዥ ማረጋገጫ የላከው የካቲት 26 ቀን 2001 መሆኑን አመልካቾች ያልካደት ሲሆን ይህም የሚያሳየው ሽያጩ የተጠናቀቀው የካቲት 26 ቀን 2001 ዓ/ም መሆኑን ነው።
ስለሆነም የቡና ጥራት ቁጥጥርና ግብይት አዋጅ ቁጥር 602/2000ን ተከትል የወጣው መመሪያ ላይ ላልታጠበ ቡና የተመለከተው የጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ የተከናወነ ሽያጭ ነው። በማለት የአመልካቾች አቤቱታ ውድቅ እንዱደረግና የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ እንዱፀና ጠይቋል።
አመልካቾች በሰጡት የመልስ መልስ ክርክራቸውን በማጠናከር አቅርበዋል። የግራቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ በተገለፀው አኳኋን የቀረበ ሲሆን እኛም በሥር ፍ/ቤቶች የጥፊተኛነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል ወይስ አልተፈፀመም የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
ተጠሪ በመጋቢት 23 ቀን 2001 እና መጋቢት 30/2001 ዓ/ም በአመልካቾች መጋዘን ባደረገው ቆጠራ 42‚646 ኪል ግራም የከረመ ያልታጠበ ቡና ተከማችቶ የተገኘ ሲሆን ተጠሪዎች ግን ተከማችቶ ተገኝቷል የተባለው ቡና በጀርመን ሀገር የሚገኝው ሀምቡርግ የተባለው ኩባንያ ጥር 10 ቀን 2001 ዓ/ም በቃል በተደረገ ስምምነት መግዛቱንና የካቲት 26 ቀን 2001 ዓ/ም የስምምነት ደብዲቤ መላኩና ቡናውም ሳይጫን የዘገየው ገዥው ተግባሩን ባለመወጣቱ ምክንያት ነው በሚል ተከራክሯዋል። ይሁን እንጂ ተጠሪዎች ቡናው በመጋዘናቸው ተከማችቶ የቆየ ስላለመሆኑ ክደው አልተከራከሩም።
ይህ የከረመው ቡና ያልታጠበ እስከሆነ ድረስ ኢዱስ አመት ከገባ ከየካቲት 01 ቀን እስከ ሚቀጥለው ጥር 30 ድረስ ወደ ገበያ ወጥቶ መሸጥ የነበረበት መሆኑን የሥር ፍ/ቤት የፍሬ ነገርን ክርክር በሚያጣራበት ጊዜ የተጠሪ ምስክሮች ቀርበው ሙያዊ ምስክርነት የሰጡ ሲሆን ቡናው በተለያዩ ችግሮች ለገበያ ካልቀረበ ደግሞ ለሚመለከተው አካል የማስታወቅ ግዳታ አመልካቾች ያለባቸው መሆኑን አዋጅ ቁጥር 602/2000 እና ይኸንኑ አዋጅ ለማስፈፀም የወጣው ደንብ ቁጥር 159/2001 እንዱሁም የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር ያወጣው መመሪያ ይደነግጋለ።
በመሆኑም ቡናው ስለመክረሙ በሕጉ በተጣለባቸው ግዳታ መሰረት አግባብ ላለው የመንግስት አካል አመልካቾች እስካላሳወቁ ድረስ የተጠቀሰባቸውን የቡና ጥራት ቁጥጥርና ግብይት አዋጅ ጥሰው ተገኝተዋል በማለት የጥፊተኛነት እና የቅጣት ውሳኔ የተሰጠባቸው በአግባቡ ስለሆነ በሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አላገኘንም።
የሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 160177 በቀን 07/8/2002 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ እንዱሁም የፋዳራል የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 91949 በቀን 21/10/2002 ዓ/ም የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የላለባቸው በመሆኑ በወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 195/2/ /ለ-2/ ፀንቷል።
መዝገቡ የተዘጋ ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ተመላሽ ይሁን።
No topics extracted.