No summary available.
የካቲት 9 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኦሮሚያ መንገድች ባለሥልጣን - ሰላማዊት ሀይለ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ከበደ ወዲጆ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት ስላመለከቱ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በወሮጉድሩ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል። ለሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ በከሳሽነት ቀርቦ አመልካች (ተከሳሽ) በጅማ ገነት ወረዲ ውስጥ የገጠር መንገድ ሲጠግን አላግባብ በእርሻ መሬት ይዞታዬ በመግባት የተለያዩ ቋሚ አትክልቶች የሰብል ምርትና ሣር ቤት አውድሞብኛል። ተከሳሽ በቆፈረው ጉድጓድ በሬ ገብቶ ስለሞተብኝ የበሬውንም ዋጋ እንዱከፍለኝ በማለት በአጠቃላይ የጉዲቱን መጠን ብር በመገመት ካሳ እንዱከፈለው ክስ አቅርቧል።
አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ የይርጋ ጊዜው አልፎል። ሥራ ያሰራሁት በክልለ አዋጅ ቁጥር 11/88 በተሰጠኝ ሥልጣንና ሀላፉነት መሰረት ነው። ከሳሽ አለ የሚሎቸው ንብረቶች በቦታው ላይ አልነበረም። የበሬ ዋጋ ልንከፍል አንገደድም የሚል ክርክር አቅርቧል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ አመልካች (ተከሳሽ) በተጠሪ ይዞታ ሥር የነበሩ ግምታቸው ብር 7,850 (ሰባት ሺህ ስምንት መቶ ሀምሳ ብር) ያላቸው የተለያዩ ተክልች አውድሟል። የከሳሽ(ተጠሪ) በሬ ተከሳሽ ከቆፈረው ጉድጓድ ገብቶ የሞተ ስለሆነ ብር 2,500 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) በጠቅላላው ብር 10,350 (አስር ሺ ሶስት መቶ ሀምሳ ብር) አመልካች ለተጠሪ ይክፈል በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ይዞታው የተጠሪ ይዞታ መሆኑ በተጠሪ ይዞታ ላይ ያለው ተክል ላይ አመልካች አላግባብ ጉዲት እንዲደረሰ የተረጋገጠ መሆኑ ስለተረጋገጠ አመልካች ለተጠሪ ብር 7,750 (ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ሀምሳ ብር) እንዱከፍል የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ነው። አመልካች የበሬ ዋጋ ግምት ለተጠሪ እንዱከፍል የሰጠው ውሣኔ ተገቢ አይደለም በማለት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በማሻሻል ወስኗል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ያቀረበ ቢሆንም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የክልለ ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል።
አመልካች ጳጉሜ 2 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የሥር ፍርድ ቤት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2143ን በመጥቀስ ያቀረብነውን የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው አላግባብ ነው።
በመሬቱ ላይ አትክልትና ንብረት እንደላለ ተረጋግጦ እያለና በአዋጅ በተሰጠኝ ሥልጣን መሰረት መንገድ የጠገንኩ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ ካሣ እንድንከፍል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ አመልካች የጠቀሳቸው የይርጋ ድንጋጌዎች ማለትም የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1149(1) እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2143 በእኔና በአመልካች መካከል ባለው ክርክር ተፈፃሚነት የላቸውም።
አመልካች በህጋዊ ይዞታዬ ላይ በነበሩት ቋሚ አትክልቶች ላይ ጉዲት ማድረሱ በማስረጃ ተረጋግጧል። ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው አመልካች ለህዝብ ግልጋልት የሚሰጥ የመንገድ ጥገና ሥራ በሚያከናውንበት ወቅት የተጠሪን ይዞታና በተጠሪ ይዞታ ላይ ያለ የተለያዩ ተክልች ላይ ጉዲት ስላደረሰ ካሣ እንዱከፍላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ከውል ውጭ የሚደርስ ሀላፉነትን የሚመለከት ክስ ሆኖ አላገኘነውም። ተጠሪ ያቀረቡት ጥያቄ አመልካች ይዞታውን ለህዝብ ጥቅምና ግልጋልት የሚውል መንገድ ለመጠገን ከወሰደ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 40 ንዐስ አንቀፅ 8 መሰረት በይዞታው ላይ ለነበረው ንብረት ተመጣጣኝ ካሣ የመክፈል ሀላፉነት አለበት። ስለዚህ በመሬቱ ላይ የነበሩትን ተክልች ዋጋ ይክፈለኝ የሚል ይዘት ያለው ነው። በህገመንግስቱ አንቀፅ 40 ንዐስ አንቀፅ 8 መሰረት ለተወሰደ ንብረት ካሣ እንዱከፈላቸው ተጠሪ የመጠየቅ መብት በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1149 ንዐስ አንቀፅ 1 እና በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2143 ንዐስ አንቀፅ 3 የተደነገገው የሁለት ዓመት የይርጋ የጊዜ ገደብ የማይገደብ መሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት በሰበር መዝገብ አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሰጠበት በመሆኑ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተጠሪ ክስ በሁለት ዓመት የይርጋ የጊዜ ገደብ አይታገድም በማለት የሰጡት ውሣኔ ተገቢና መሰታዊ የህግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪ በይዞታ መሬቴ ላይ ነበሩ ከሚላቸው የተለያዩ አይነት ቋሚ ዛፍችና አትክልቶች ጠቅላላ ግምት ከብር 60,000(ስልሣ ሺህ ብር) በላይ እንደነበርና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣናቸውን ተጠቅመው በተጠሪ ይዞታ ላይ የነበሩትና በአመልካች ጉዲት የደረሰባቸው ተክልችና ዛፍች ግምት 7,750 (ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ሀምሳ ብር) መሆኑን በማረጋገጥ አመልካች ይህንን ገንዘብ ለተጠሪ እንዱከፍል ወስነዋል። አመልካች በቦታው ላይ ምንም አይነት ንብረት የለም በማለት በሰበር አቤቱታው የሚከራከር ቢሆንም ይህ የአመልካች ክርክር የፍሬ ነገር ክርክር ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለሆነም አመልካች የካሣውን መጠን በተመለከተ ያቀረበው አቤቱታ ለሰበር ችልት በህገ መንግስቱ አንቀፅ 80 ንዐስ አንቀፅ 3(ሀ) እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 10 ከተሰጠው ሥልጣን ውጭ የቀረበና ሕጋዊ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
በአጠቃላይ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በማሻሻል የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ጥቅምት 26 ቀን 2003 ዓ.ም የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.