No summary available.
ጥር 24 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡
ተጠሪ፡
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የሰበር አቤቱታው በቀጥታ ለፍ/ቤት በቀረበ ክስ መነሻ ፍትህ ሚኒስቴር ለአሁኑ ተጠሪ የጥብቅና ፈቃድ በመስጠት እንዱመዘግባቸው በማለት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በሚል በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10(3) መሰረት የቀረበ ነው።
በዚህ ጉዲይ የአሁኑ ተጠሪ የጥብቅና ፈቃድ ይሰጠኝ የሚል ጥያቄ ለፍትህ ሚኒስቴር አቅርበው በፋዳራል ፍርድ ቤቶች ስለሚሰሩ ጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥና ምዝገባ በሚመለከት በወጣው አዋጅ ቁጥር 199/1992 አንቀጽ 21 መሰረት በጥብቅና ገምጋሚ ኮሚቴ ተመርምሮ የተሰጠው የውሣኔ ሃሳብ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 26 መሰረት ለሚኒስትሩ ቀርቦ የጥብቅና ፈቃድ እንዲይሰጣቸው ተብል በመወሰኑ በአዋጅ አንቀጽ 29(1) በሚደነግገው መሰረት የጥብቅና ፈቃድ ጠያቂው ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበው ክርክሩ ከተሰማ በኋላ ፍ/ቤቱ መርምሮ በዚሁ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ ‛2“ መሰረት በሕጉ ጉዲይ ላይ ውሣኔ በመስጠት መታየት ይገባዋል ባለው ፍሬ ነገር ላይ ሚኒስትሩ አይቶ በ30 ቀን ውስጥ ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥበት ብል የመለሰው ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ሚኒስትሩ ከፍተኛው ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ መሰረት ለመፈፀም ፈቃደኛ ባለመሆን ለ40 ቀናት ውሣኔ ሳይሰጥበት በማቆየት የጥብቅና ፈቃድ እንዲላገኝ ስላደረገ ክልከላው ተወግድ የጥብቅና ፈቃድ እንዱሰጠኝ ይታዘዝ በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 314(1) መሰረት በቀጥታ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበዋል። በዚህ የክልከላ ይወገድ ክስ ተከሳሽ የሆነው የፍትህ ሚኒስቴር ወኪል ቀርበው ጉዲዩን ገምጋሚ ኮሚቴ ተመልክቶ ውሣኔ እንዱሰጥበት አስተላልፈናል የሚል መልስ እንደሰጡ ተመዝግቦ ፍ/ቤቱ መርምሮ ፍትህ ሚኒስቴር ጉዲዩን ለማየት ፈቃደኛ መሆኑን ከመግለጽ በቀር ክልከላው የማይወገድበት ምክንያት ስለመኖሩ ስላላስረዲ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 314(2) መሰረት ክልከላው ተወግድ ለከሣሹ የጥብቅና ፈቃድ በመስጠት ይመዝግባቸው በሚል ውሣኔ ሰጥቷል።
የአሁኑ አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኙን ሉያቀርብ የቻለ ቢሆንም ከፍተኛው ፍ/ቤትም በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሳይቀበለው ቀርቷል።
የሰበር አቤቱታው በዚህ ምክንያት የቀረበ ሲሆን ተመርምሮ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ ይታይ ተብል ስለታዘዘ ማመልከቻው ለተጠሪው ተልኮ ቀርበው መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
በዚህም መሰረት ተጠሪው ታህሣሥ 21 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ መልስ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም፣ የአመልካቹ አቤቱታ ተቀባይነት ሉሰጠው አይገባም የሚለባቸውን ምክንያቶች ገልፀው አቅርበዋል። አመልካች በተጠሪው በኩል የተሰጠውን መልስ በማስመልከት የመልስ መልስ እሰጣለሁ ካለ ይቅረብ የተባለ ቢሆንም ከመዝገቡ እንደሚታየው ያቀረበው የመልስ መልስ የለም።
ሰበር ችልቱም ጉዲዩን መርምሯል።
የአሁኑ ተጠሪ ያቀረቡት የጥብቅና ፈቃድ ይሰጠኝ ጥያቄ በፋዳራል ፍ/ቤቶች ስለሚሰሩ ጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥና ምዝገባ በሚመለከት በተለይ በወጣው በአዋጅ ቁጥር 199/1992 አንቀጽ 20፣21 እና 26 መሰረት ታይቶ ሚኒስትሩ የጥብቅና ፈቃድ እንዲይሰጥ ብል በሰጠው ውሣኔ ላይ ፈቃድ ጠያቂው በተጠቀሰው በዚህ አዋጅ አንቀጽ 29(1) መሰረት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ክርክሩ ከተሰማ በኋላ ፍ/ቤቱ መርምሮ የሕግ ጉዲይ ነው ባለው ነጥብ ላይ ውሣኔ በመስጠት በዚሁ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ ‛2“ መሰረት በቀሪው ፍሬ ነገር ላይ ሚኒስትሩ አጣርቶ በ30 ቀን ውስጥ ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥበት ብል መልሶት ሚኒስትሩ ውሣኔ ሳይሰጥበት ጉዲዩ በእንጥልጥል ላይ እያለ ተጠሪው ሚኒስትሩ በተባለው 30 ቀን ውስጥ ውሣኔውን ባለመስጠቱ ምክንያት የአሁኑ አመልካች ያደረገብኝ የጥብቅና ክልከላ ይወገድ በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.314(1) መሰረት ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክስ ያቀረቡት በሕጉ አግባብ ነው ወይንስ አይደለም?
የአሁኑ ተጠሪ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሣኔ መሰረት ፍትህ ሚኒስቴር በ30 ቀን ውስጥ በጉዲዩ ላይ ውሣኔ ሳይሰጥ ቢቀርና ቢያዘገየው ምን ማድረግ አለባቸው? የሚለት ጥያቄዎች ሲታዩ፡ - በፋዳራል ፍ/ቤቶች ለመስራት የሚቀርብ የጥብቅና ፈቃድ መስጠትና ምዝገባ ጥያቄን በአዋጅ ቁጥር 199/1992 አንቀጽ 19 መሰረት አይቶ የመወሰን ስልጣን የተሰጠው ለፍትሕ ሚኒስቴር ነው።
በመጀመሪያ በአዋጁ አንቀጽ 20 እና 21 መሰረት የአመልካቹን የጥብቅና ፈቃድ ጥያቄ አይቶ ማስረጃዎቹን በመመርመር ፈቃድ እንዱሰጠው ወይም እንዲይሰጠው ለሚኒስትሩ የውሣኔ ሃሣብ የሚያቀርበው የጥብቅና ገምጋሚ ኮሚቴ ነው። በአንቀጽ 26 ላይ እንደተመለከተው የጥብቅናው ፈቃድ ይሰጥ ወይንስ አይሰጥ የሚለውን የመጨረሻውን ውሣኔ የሚሰጠው ሚኒስትሩ ነው። ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የሚኖረው ከዚህ የሚኒስትሩ ውሣኔ በኋላ በአዋጅ አንቀጽ 29 መሰረት በይግባኝ ደረጃ ብቻ ነው። የመጀመሪያውን ይግባኝ የሚያየው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። ሚኒስትሩ የጥብቅና ፈቃድ እንዲይሰጥ በማለት በሰጠው ውሣኔ መነሻ በቀጥታ ለፍ/ቤት የሚቀርብ ክስ አይኖርም። በሕጉ ይግባኝ እንዱባልበት ብቻ የተፈቀደ ነው።
በአሁኑም ጉዲይ ተጠሪው አዋጁን በተከተለ መንገድ የጥብቅና ፈቃድ ይሰጠኝ ጥያቄ ለፍትሕ ሚኒስቴር አቅርበው ታይቶ ሚኒስትሩ የጥብቅና ፈቃድ እንዲይሰጥ የሚል ውሣኔ በመሰጠቱ በሕጉ በተፈቀደው የይግባኝ ሥርዓት በመጠቀም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው ክርክሩ ተሰምቶ ፍ/ቤቱ መርምሮ በሕጉ ጉዲይ የራሱን ውሣኔ ሰጥቶበት በቀሪ ፍሬ ነገር ላይ ራሱ ፍትህ ሚኒስቴር አይቶ ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥበት የመለሰው መሆኑ ተረጋግጧል። ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ወደ ፍትህ ሚኒስቴር የመለሰው በ30 ቀን ውስጥ አይቶ ውሣኔ እንዱሰጥበት ነው። ሆኖም ፍትሕ ሚኒስቴር ከፍተኛው ፍ/ቤት በአጭር ጊዜ ውስጥ ታይቶ እንዱወሰን በመፈለግ ውሣኔው በ30 ቀን ውስጥ አይቶ በጉዲዩ ላይ ውሣኔ እንዱሰጥበት ባዘዘው መሰረት ሳይፈጽም ቆይቷል። ጉዲዩም ገና በእንጥልጥል ላይ ስለሚገኝ ውጤቱ ምን እንደሚሆን አይታወቅም።
የአሁኑ ተጠሪ በዚህ ሁኔታ ምን ማድረግ ይችላለ? በሕጉ ክስ ማቅረብ ይችላለ ወይ?
የሚለውን በተመለከተ ከፍ ሲል እንደተገለፀው በቀጥታ ክስ ለፍ/ቤት ቀርቦ የሚታይ ጉዲይ አይደለም። የጥብቅና ክልከላ ጉዲይ በአዋጅ ቁጥር 199/1992 አንቀጽ 29(1) መሰረት ሥልጣኑ ለሚመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ ደረጃ ቀርቦ ታይቶ የሚወሰን እንጂ ክልከላ ይወገድ በሚል በቀጥታ ለፍ/ቤት አቤቱታ የሚቀርብበት ባለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.314 ድንጋጌ በእንዱህ አይነቱ ጉዲይ ተፈፃሚነት አይኖረውም። ተጠሪ የአሁኑ አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ መሰረት እንደገና ጉዲዩን አይቶ ተገቢውን ውሣኔ ለመስጠት ባለመፈለግ የሚያዘገየው ከሆነ በውሣኔው መሰረት እንዱፈፀምላቸው ማመልከት ያለባቸው ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። በውሣኔው መሰረት እንዱፈጸም ሉያስገድደው የሚችለውም ይኼው ውሣኔውን የሰጠው ፍ/ቤት ነው። የአሁኑ ተጠሪ በዚህ መንገድ በመጠየቅ በጥብቅና ፈቃድ ጥያቄው ላይ ውሣኔ እንዱሰጥ ማድረግ ሲገባቸው አመልካች የጥብቅና ፈቃድ ክልከላ አድርጏብኛል በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.314(1) መሰረት ክልከላው ይወገድ በሚል በቀጥታ ለፍ/ቤት የክስ አቤቱታ ያቀረቡት በሕጉ አግባብ ስላልሆነ ተቀባይነት የለውም። የሥር ፍ/ቤትም የጥብቅና ፈቃድ ጉዲይን በተመለከተ በተለይ በወጣው አዋጅ ቁጥር 199/1992 በተደነገጉት ድንጋጌዎች መሰረት ታይቶ የሚወሰንና ለፍ/ቤትም የሚቀርበው በይግባኝ ደረጃ ብቻ መሆኑ እየታወቀ የጥብቅና ፈቃድ ክልከላ ተደርጓል በሚል ምክንያት በቀጥታ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.314 መሰረት የቀረበውን ክስ በመቀበል የአሁኑ አመልካች ለተጠሪው የጥብቅና ፈቃድ በመስጠት እንዱመዘግባቸው በሚል የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስለተገኘ የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ.166328 በ25/8/2002 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 94250 በ27/09/2002 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
በዚህ መዝገብ የተሰጠው ፍርድ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይተላለፍ።
No topics extracted.