No summary available.
ታህሳስ 27 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ - ተስፊዬ ምንዲገኝ - ቀረበ ተጠሪ፡- ንጋቱ ወ/ሰንበት - ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ ተጠሪ የሟች ወ/ሮ ፀሐይ በቀለ ባል ነኝ በማለት የሰጠው ውሳኔ የባልና ሚስት ግንኙነት (ጋብቻ) ሳይኖር የተሰጠ በመሆኑ ሉሻር ይገባል በማለት አመልካች ያቀረበውን መቃወሚያ የሚመለከት ነው። ከመዝገቡ እንደሚታየው አመልካች መቃወሚያውን ያቀረበው ተጠሪ የሟች ባል መሆኑን በማረጋገጥ ውሳኔ ለሰጠው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው። ፍ/ቤቱ በመቃወሚያ ሥረ ነገር ላይ ገብቶ ሳያከራክር ተጠሪን መልስ እንዱሰጥ ሳያደርግ አመልካች መቃወሚያውን ለማቅረብ የሚያስችል መብት የለውም በማለት ሳያስተናግደው ቀርቶአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ትዕዛዙን በመቃወም ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ የተሰማ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱም በሥር ፍ/ቤት የተሰጠውን ትዕዛዝ አፅንቶአል። በመጨረሻም አመልካች በተሰጡት ውሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል በማለት ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰበር አቤቱታ ቢያቀርብም፤ የሰበር ችልቱ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም በማለት አቤቱታውን ሰርዞአል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች የካቲት 24 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል የሚልበትን ምክንያት በመግለጽ ስህተቱ ይታረምለት ዘንድ አቤቱታውን አቅርቦአል። በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልቱ እንዱታይ የተደረገው አመልካች ተጠሪ በሰጠው የባልነት ውሳኔ ላይ መቃወሚያ የማቅረብ መብት የለውም በማለት የተሰጠው ውሳኔ አግባብነት ሉመረመር ይገባል በመባለ ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ ግራቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከሥር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር መገንዘብ እንደቻልነው አመልካች መቃወሚያ ሉያቀርብ የቻለው ተጠሪ ሐሰተኛ ማስረጃ በማቅረብ በተሰጠው የባልነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በመጠቀም የጡረታ አበል እንዱከፈለው በማስወሰኑ እና ይህን ውሳኔ መሰረት በማድረግም አበለን መውሰድ በመጀመሩ ነው። በእርግጥም ተጠሪ የሟች ባል ነው ተብል የጡረታ አበል እንዱከፈለው ከተወሰነ አመልካች በውሳኔው መሰረት እንዱፈጽም ይገደዲል። ከዚህ ግዳታ ነፃ ላሆን የሚችለው ተጠሪ የሟች ባል ነው የተባለበትን ውሳኔ ከመሰረቱ ማሻር ሲችል ነው። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 የተመለከተውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ መቃወሚያ ያቀረበውም በዚህ ምክንያት ነው። የሥር ፍ/ቤቶች መቃወሚያውን ሳያስተናግደ የቀሩት ተጠሪ የሟች ባል ነው በመባለ መብቱ (የአመልካች) ተነክቶአል ልባል አይችልም የሚል ምክንያት በመስጠት እንደሆነ ከውሳኔው ይዘት ተገንዝበናል።
በሕግ መሰረት የጡረታ አበል የሚከፈላቸው ሰዎች አበለን የሚያገኙ ከአመልካች ኤጀንሲ እንደሆነ ይታወቃል። አመልካች አበለን መክፈል ያለበት ሕጉን መሰረት በማድረግ ብቻ እንደሆነም አያከራክርም። ይህ ሁኔታ ከላላ አቅጣጫ ሲታይ ደግሞ አመልካች በሕግ የተመሰረተ መብት ለላለው ሰው አበለን አልከፍልም የማለት መብት አለው ማለት ነው። አመልካች በዚህ በያዝነው ጉዲይ እያለ ያለውም ይኸው ነው። በፍ/ቤት የተሰጠ ውሳኔ (ክፈል የሚል) በመኖሩ ግን በራሱ ሥልጣን መክፈል ማቆም ያስቸግረዋል። በመሆኑም ለአበለ ክፍያ መሰረት ሆኖአል ያለውን ውሳኔ ለመቃወም ቀርቦአል። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.358 እንደተደነገገው ቀደም ሲል ለተሰጠው ውሳኔ መሰረት በሆነው ክርክር ተካፊይ ያልነበረ ሰው ውሳኔው እንዱሻርለት መቃወሚያ ማቅረብ የሚችለው ተካፊይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠው ፍርድ (ውሳኔ) መብቱን የሚነካበት እንደሆነ ነው።
ፍርደ መብቱን የሚነካበት ከሆነ ደግሞ በክርክሩ ውስጥ ተካፊይ የመሆን በሥነ ሥርዓት ሕጉ የተረጋገጠለት መብት አለው ማለት ነው። በያዝነው ጉዲይ አመልካች ሕጋዊ መሰረት የላለውን የጡረታ አበል የመክፈል ግዳታ የለበትም ወይም ደግሞ አልከፍልም የማለት መብት አለው የሚል መነሻ ተይዞ ነው መቃወሚያው የቀረበው። በእርግጥም አመልካች መብቱን ማስከበር የሚችለው በክርክሩ ውስጥ በመግባት የበኩለን ክርክር በማቅረብ ነው። የሥር ፍ/ቤቶች መቃወሚያውን ባለማስተናገዲቸው ክርክሩን ለማቅረብ አልቻለም። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች የተከተለት አካሄድ ሕጉንና የሥነ ሥርዓት ደንቦቹን የተከተለ አይደለም። የሰጡት ውሳኔም በሕጉ አተገባበር ረገድ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ነው። ስለዚህም ተከታዩን ወስነናል።
በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ የካ- 1624/98 መጋቢት 10 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ፣ የከተማው አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ. ህዲር 4 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የይግባኝ ሰሚው ሰበር ችልት በመ. የካቲት 4 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.348(1) መሰረት ተሽረዋል።
በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች ያቀረበለትን መቃወሚያ በመቀበል እና ተጠሪ በመቃወሚያው ሥረ ነገር ላይ የሚሰጠውን መልስ በመስማት ግራቀኝ ወገኖቹን በማከራከር ተገቢውን ይወሰን ዘንድ ጉዲዩ ይመለስለት በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.341(1) መሰረት ወሰነናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
ራ/ታ
No topics extracted.