No summary available.
ታህሳስ 15 ቀን 2003ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ጠበቃ ሚሉዮን አሰፊ ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በአመልካች የወጣውን መመሪያ ሕጋዊነት አስመልክቶ ተጠሪዎች ያቀረቡትን ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪዎች ባሁኑ አመልካች በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘቱም ባጭሩ ተጠሪዎች የሕብረት ባንክ ባለ አክሲዮኖች መሆናቸውን፣ በ1952ዓ.ም በወጣው የኢትዮጵያ ንግድ ሕግ የአክሲዮን ማህበር አስተዲደር ለማህበረተኞች እንጂ ለላላ ላሰጥ እንደማይችል በአንቀጽ 347/1/ ላይ የተገለፀ፣ ከባለ አክሲዮኖች መካከል በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ማለትም በባለ አክሲዮኖች እንደሚመረጡ በአስተዲደሪነት መመረጥ የሚችለው ለሶስት አመት እንደሆነ ሆኖም ግን የኩባንያው መመስረቻ ጽሐፍ ወይም የመተዲደሪያ ደንብ እስካልከለከለው ድረስ በድጋሚ ለምርጫ መቅረብ እንደሚችል በአንቀጽ 350 ስር መደንገጉን፣ የህብረት ባንክ መመስረቻ ጽሐፍም በድጋሚ መመረጥን እንደሚፈቅድ፣ የባንኩ መተዲደሪያ ደንብም በድጋሚ መመረጥን የሚከለክል ድንጋጌ የላለው መሆኑን፣ 1952ዓ.ም የወጣው የንግድ ሕግ የአንድ ኩባንያ ዲይሬክተር በልላ ኩባንያ ውስጥ በዲይሬክተርነት እንዱያገለግል የሚከለክል ድንጋጌ የላለው መሆኑን፣ አዋጅ ቁጥር 83/1986 እና 84/1986 ስለባንክ ጉዲዮች መውጣታቸውንና ለአመልካች መመሪያ የማውጣት ስልጣን የሰጡት ቢሆንም በንግድ ሕጉ ስለ ዲይሬክተሮች የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ለውጥ ያላደረጉ ወይም ገደብ ያላደረጉ ወይም ላላ ወገን ገደብ እንዱያስቀምጥ ስልጣን ያልሰጡ መሆኑን፣ አመልካች ባንክ የስልጣኑ ምንጭ ሁለት አዋጆች ሆነው እያለ የባንክ ስራ ፍቃድና ቁጥጥር የተሻሻለ የአዱስ ባንክ የስራ ፍቃድና የዲይሬክተሮችና የዋና ስራ አስፈፃሚ ሹመት ማጽደቂያ መመሪያ ቁጥር ኤስቢቢ/39/2006 የሚል በእግሉዝኛ የተፃፈ መመሪያ አውጥቶ በመመሪያው ላይ በአንቀጽ 5.1.4 እና 5.1.5 ስር የተመለከቱት ድንጋጌዎች ገደብ የሚጥለና ከንግድ ሕጉ፣ ከሕብረት ባንክ የመመስረቻ ጹሐፍ ጋር ፍፁም የሚጋጬ መሆናቸውን ዘርዝረው አመልካች ያወጣው መመሪያ እንዱታገድና በስራ ላይ እንዲይውል እንዱወሰን ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካችም ለክሱ በሰጠው መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃሚያና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርቧል። አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም፣ አመልካች ሕገ ወጥ መመሪያ አላወጣም፣ መመሪያው የባለ አክሲዮኖችን የመመረጥና የመምረጥ መብት አላስቀረም የሚለ ምክንያቶችን በመዘርዘር ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ጉዲዩን መርምሮ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 83/86 እና 84/86 መመሪያ የማውጣት ስልጣን የተሰጠው ቢሆንም መመሪያ የሚወጣባቸው ጉዲዮች በአዋጆቹ በተመለከቱት ጉዲዮች ላይ ብቻ በመሆኑ እና በላልች ህጎች በተለይም ከመመሪያው በላይ በሆኑ አዋጆች የተሰጡትን መብቶችና የተመለከቱትን ድንጋጌዎች የማይቃረን መሆን የሚገባው ስለሆነ የተሻሻለው አዱስ የባንክ ሥራ ፈቃድና የዲሬክተሮች፣ የዋና ሥራ አስፈፃሚ ሹመት ማጽደቂያ መመሪያ ቁጥር ኤስቢቢ /39/2006 ላይ በአንቀጽ 5.1.4 እና 5.1.5 ስር የተመለከቱት ድንጋጌዎች ሕጋዊ አይደለም የሚል ምክንያት በመስጠት እነዚህ ድንጋጌዎች ተሽረዋል በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ መጋቢት 04 ቀን 2001ዓ.ም በፃፈት አምስት ገጽ አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ጉዲዩ በፍርድ ቤት ላታይ የማይገባው መሆኑንና አከራካሪው መመሪያም የሕግ አወጣጥ ስርዓቱን መስረት አድርጎ የወጣና ከንግድ ሕጉም በላይ ተፈፃሚነት ያለው መሆኑን ዘርዝረው በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ እንዱሻር ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። ጉዲዩ ተመርምሮም ለሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው ነው ተብል በመታዘዙ ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ጥቅምት 17 ቀን 2002ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰምቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አብይ ነጥብ አመልካች ባወጣው የተሻሻለ አዱስ የባንክ ስራ ፈቃድና የዲይሬክተሮች፣ የዋና ስራ አስፈፃሚ ሹመት ማጽደቂያ መመሪያ ቁጥር ኤስቢቢ /39/2006/ ስር የተመለከቱት አንቀጽ 5.1.4 እና 5.1.5 ድንጋጌዎች ሕጋዊ አይደለም ተብል መሻሩ ተገቢ መሆን ያለመሆኑ ነው።
በመሰረቱ ሕግ የማውጣት ስልጣን በስልጣን ክፍፍል መርህ መሰረት የሕግ አውጪው አካል ስለመሆኑ እሙን ነው። በሕግ አውጪው የመንግስት አካል የሚወጡ ሕጎች ቀዲማዊ /Primary legislations/ ተብለው የሚታወቁ ሲሆን ላልቹ እንደአሰፈላጊነታቸው አግባብ ባለው አካል የሚወጡ የበታች ሕጎች /Subsidiary legislations/ ተብለው የሚታወቁ ናቸው። ሕግ አውጪው የመንግስት አካል በተለያዩ ቴክኒካዊ፤ ሙያዊና ማህበራዊ ምክንያቶች ቀዲሚውን ሕግ ለማስፈፀም የሚያስችለ ዝርዝር ሕጎች ያስፈልጋለ ብል ባመነ ጊዜ ጉዲዩ በቀጥታ የሚመለከተው አካል የበታች ሕጎችን እንዱያወጣ ስልጣን መስጠት የተለመደና ተቀባይነት ያለው አሰራር ነው። ይህ አሰራር በሕግም በምክንያትም የተደገፈ እና የዲበረ ልምድ ስለመሆኑ የታወቀ ነው። አሁን በተግባር ሥራ ላይ ያለው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሕግ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 14/88 አንቀጽ 2/1/ እንደሚያመለክተው ሕግ የሚላቸው አዋጅ ደንብና መመሪያዎችን ነው።
ክርክሩ በተነሳበት ወቅት ተፈፀሚነት የነበረው አዋጅ ቁጥር 83/1986 ሲሆን ይህ አዋጅ ለገንዘብና ለባንክ አዋጅ የተደነገገ ሲሆን በዚህ ላይ የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ከዚህ አዋጅ በፉት የተቋቋመ ሲሆን ባለበት እንዱቀጥል የደነገገ እና ስለ ባንኩ ዓላማዎች፣ ስልጣን እንዱሁም ተግባር በዝርዝር ተመልክቷል። እንዱሁም አዋጅ ቁጥር 84/1986 ደግሞ ለባንክ ስራ ፈቃድ ስለመስጠትና ስለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ነበር። በዚህ አዋጅ የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ የባንክ፣ የኢንሹራንስና የአነስተኛ ገንዘብ ተቋማትን በተመለከተ ለመስራት የሚፈለጉ ሰዎችን ፈቃድ እንዱሰጥ፣ ከፈቃደ በኋላ ቁጥጥር እንደሚያደርግ፣ ለፈቃደ አሰጣጥ በቅድሚያ ሉሟለ የሚችለ ሁኔታዎች ምን ምን እንደሆኑ ያሳያል። አዋጅ ቁጥር 83/1986 አንቀጽ 61 ድንጋጌ ሲታይም ባንኩ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካትና ይህንን አዋጅ በሚገባ በስራ ላይ ለማዋል የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ለማውጣት እንደሚችል ሕግ አውጪው ስልጣን ሰጥቶታል። አዋጁ በአንቀጽ 6 ስር የባንኩ ዓላማዎች የተረጋጋ የገንዘብ ሁኔታ መፍጠር፣ የአገሪቱ ገንዘብ አስተማኝ እንዱሆን ማድረግ፣ አስተማማኝ የፊይናንስ አቅም እንዱኖር ማድረግ እንዱሁም ለኢኮኖሚ እድገት አመቺ የሆኑ የክሬዱትና የምንዛሬ ሁኔታዎች እንዱመቻቹ መጣር መሆናቸውን ደንግጓል። እነዚህን ዓላማዎችን ለማስፈፀምም ብሓራዊ ባንክ ስልጣንና ተግባሩ በአዋጁ አንቀጽ 7 ስር ተመልክቷል። አዋጁ በአንቀጽ 60/2/ ስር ይህን አዋጅ የሚቃረን ማናቸውም ሕግ፣ ደንብ ወይም መመሪያ በዚህ አዋጅ ውስጥ የተመለከቱትን ጉዲዮች በሚመለከት ተፈፃሚነት አይኖረውም በሚል ደንግጓል። አዋጅ ቁጥር 84/1986 አንቀጽ 36 ደግሞ መመሪያ የማውጣት ስልጣንን ለአመልካች ሰጥቶታል። በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 35 ስር ከአዋጁ ጋር የሚቃረኑ ማናቸውም ሕጎች በዚህ አዋጅ የተሸፈኑ ጉዲዮችን በተመለከተ ተፈፃሚነት አይኖራቸውም በማለትም ተደንግጓል።
እንግዱህ አመልካች በሕግ ኃላፉነትና ተግባሩ ተለይቶ የተሰጠው ሲሆን ይህንኑ ተግባርና ኃላፉነት ለመወጣትና ሕጉን ለማስፈፀም መመሪያ የማውጣት ስልጣን በሕግ አውጪው በአዋጅ ቁጥር 83/1986 እና 84/1986 የተሰጠው መሆኑን ከላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። የባንኮችን ሥራ የመቆጣጠር ተግባርና ኃላፉነት ደግሞ እንደማንኛውም ቁጥጥር የማድረጊያ ስርዓት ሉፈፀም የሚችለው የፊይናንስ ተቋሞችንና የባንኮችን ተግባርና ኃላፉነት አስቀድሞ በሕግ በመወሰን፣ ይህንኑ ተግባርና ኃላፉነታቸውን ስራ ላይ የሚያውለበትን ደንብ እንዱኖራቸው በማድረግ እና በአመራራቸውም ላይ በተለያየ ሕጋዊ መንገድች ቁጥጥር በማድረግ ስለመሆኑ ይታመናል። የባንኮችን ስራ የመቆጣጠር ስራ ለጉዲዩ የተለየ እውቀትና ልምድ ያለውን ተቋም /አካል/ ባለሙያ የሚያስፈልግ መሆኑ እሙን ነው። ባንኮችና የፊይናንስ ተቋማት በሰፉው የሕዝብ ጥቅም ያለባቸው መሆኑም ይታወቃል። በ1952ዓ.ም በወጣው የንግድ ሕግ የአንድ ኩባንያ ዲይሬክተር በልላ ኩባንያ ውስጥ በዲይሬክተርነት እንዱያገለግል የሚከለክል ድንጋጌ የላለው መሆኑና አጠቃላይ ስለ ዲይሬክተሮች የተደነገጉት ድንጋጌዎች ተፈፃሚነታቸው የነበረው ከባንክና ከፊይናንስ ተቋማት ላይ ብቻ ሳይሆን በላልች የንግድ ማህበራትም ላይ ጭምር መሆኑ ይታወቃል። ሕግ አውጪው ባንክና የፊይናንስ ተቋማትን በተወሰነ ደረጃ በተለየ የሕግ ማዕቀፍ እንዱገዙ አድርጓል።
በ1952ዓ.ም የወጣው የንግድ ህግ በሕጎች አወጣጥ ደረጃ አዋጅ ሲሆን አዋጅ ቁጥር 83/1986 እና 84/1986ዓ.ም ተመሳሳይ ደረጃ ያላቸው ሕጎች ናቸው። በአዋጅ ቁጥር 83/1986 እና 84/1986 በሚሸፈኑ ጉዲዮች የንግድ ሕጉ የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት የላለው መሆኑ ከሕጉቹ አወጣጥ ቅደም ተከተልና ደረጃ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። አዋጅ ቁጥር 83/1986 እና 84/1986 ከንግድ ሕጉ እኩል ደረጃ ያላቸው በመሆኑና በኋላም የወጡ በመሆኑ በገንዘብና በባንክ እንዱሁም ስለ ባንክ ስራ ፈቃድ ስለመስጠትና ስለመቆጣጠር ቀዲሚ ተፈፃሚነት ያላቸው መሆኑን ከሕጎች አተረጓጎም ደንብ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። ስለሆነም አዋጆቹ ከንግድ ሕጉ ቀድመው የሚፈፀሙ ናቸው ከተባለ አመልካች ያወጣው መመሪያ ቁጥር ኤስቢቢ /39/2006 እነዚህ አዋጆቹን መሰረት አድርጎ የወጣ በመሆኑ ከላይ በተጠቀሱት ጉዲዮች ላይ ከንግድ ሕጉ በላይ የሚፈፀም ይሆናል። የስር ፍ/ቤት ሕጎቹ የወጡበትን ስርዓት፣ ሕጉቹ የሚፈፀሙትን ጉዲይ እና በአፈፃፀም ደረጃ ያላቸውን እርከን በአግባቡ ሳይለይ አመልካች ባወጣው መመሪያ ውስጥ የተካተቱት አንቀጽ 5.1.4 እና 5.1.5 ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት ሉኖራቸው አይገባም በማለት እንዱሻሩ መወሰኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ጥር 02 ቀን 2000ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ታህሳስ 09 ቀን 2001 የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የአመልካች መመሪያ በአዋጅ ቁጥር 83/1986 እና 84/1986 መመሪያውን የማውጣት ስልጣን የተሰጠው በመሆኑ የተሻሻለው አዱስ የባንክ ስራ ፈቃድና የዲይሬክተሮች፣ የዋና ስራ አስፈፃሚ ሹመት ማጽደቂያ መመሪያ ቁጥር ኤስቢቢ /39/2006 አንቀጽ 5.1.4 እና አንቀጽ 5.1.5 ከ1952ቱ የንግድ ሕግ ጋር የሚጋጭ ነው ተብል ሉሻር የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.