No summary available.
መስከረም 25 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው አልማው ወላ በላቸው አንሺሶ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ሚ/ር ካርል ካስቴሉ ተጠሪ፡- የወ/ሮ ዘውዳ ደሚኒኮ ውርስ አጣሪ አቶ ታምራት ኪዲነ ማርያም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 7 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና ከውሣኔው በፉት ባቀረብኩት የመጀመሪያ የክስ መቃወሚያ ላይ የሰጠው ብይን እንደዚሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት በመዝገብ ግንቦት 2 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ሀምላ 24 ቀን 1999 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው። የክርክሩ መነሻ የወ/ሮ ዘውዳ ድሜንኮ የውርስ አጣሪ ሆነው ወ/ሮ ዘውዳ ድሜንኮ በአሜሪካን አገር በእንግሉዘኛ ቋንቋ እንደ አውሮፒውያን አቆጣጠር ፋብሪዋሪ 6 ቀን 2005 ዓ.ም በአደረጉት ግልፅ ኑዛዜ የተሾሙ መሆኑን በመግለፅ የአሁን አመልካች ከሟች ወ/ሮ ዘውዳ ድሚኒኮ ጋር መስከረም 29 ቀን 1990 ዓ.ም በተደረገ የኪራይ ውል በአዱስ አበባ ከተማ በቀድሞው ወረዲ 23 ቀበላ 13 የቤት ቁጥር 1822 በወር ብር 6500 (ስድስት ሺ አምስት መቶ ብር) ለመክፈል ተስማምተዋል ስለዚህ የኪራይ ገንዘቡን እንዱከፍለና ቤቱን እንዱያስረክቡ በማለት አቶ ታምራት ኪዲነማርያም ያቀረቡት ክስ ነው። አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ የመጀመሪያ የክስ መቃወሚያ አቅርቧል።
አመልካች አቶ ታምራት ኪዲነማርያም በውርስ አጣሪነት ተሹሜበታለሁ የሚለት ኑዛዜ በውጭ አገር የተደረገ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም ቆንሲላ ጽ/ቤት ትክክለኛነቱ ያልተረጋገጠ በመሆኑ ህጋዊ ውጤት የለውም ስለዚህ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል ሥልጣን ስለላለው ክስ ሉያቀርብብኝ አይገባም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል። የከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የአመልካችን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ግንቦት 28 ቀን 1998 ዓ.ም በሰጠው ብይን ውድቅ በማድረግ በፍሬ ጉዲዩ በማከራከር አመልካች ተጠሪ ክስ ያቀረበበትን ቤት ለውርስ አጣሪው እንዱያስረክብ የቤቱን ኪራይ እንዱከፍል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው ይግባኝ ሰሚው ችልት በሥር ፍርድ ቤት የተፈፀመ የህግ ወይም የፍሬ ጉዲይ ስህተት የለም በማለት ይግባኙን ሰርዞታል። አመልካች ለዚህ ችልት ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በውጭ ቋንቋ ተፅፈው ከውጭ አገር ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ሰነድች በኢትዮጵያ ቆንጺላ ጽ/ቤቶች ተረጋግጠው ካልገቡ በስተቀር ውጤት እንደማይኖራቸው የሰነድች ምዝገባ አዋጅ 334/95 አንቀፅ 2 አንቀፅ 26 እና አንቀፅ 27(1)ን አጣምሮ በማንበብ ለመገንዘብ እየተቻለ በኢትዮጵያ ቆንጺላ ባልተረጋገጠና ሟች ወ/ሮ ዘውዳ አሜሪካን አገር አድርገውታል ተብል በቀረበ ኑዛዜ የውርስ አጣሪ ሆኖ ተሹሟል በሚል ምክንያት ክስ ለማቅረብ የሚያስችል ሥልጣን ሣይኖረው ያቀረበውን ክስ ተቀብል ማስተናገደና ውሣኔ መስጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሥለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ ሟች ወ/ሮ ዘውዳ ድሚኒኮ በውጭ የኢትዮጵያ ቆንጺላ ጽ/ቤቶች አለመረጋገጡ ሰነደን ህጋዊ ውጤት እንዲይኖረው የሚያደርግ ምክንያት አይደለም።
ህጋዊ ውጤት እንዱኖራቸው የግዳታ መመዝገብና መረጋገጥ የሚገባቸው ሰነድች ዝርዝር በአዋጅ ቁጥር 334/1995 አንቀፅ 5 ተደንግጓል። የኑዛዜ ሰነድ ህጋዊ ውጤት ለማግኘት መመዝገብና መረጋገጥ ያለበት ሰነድ ስለመሆኑ በአንቀፅ 5 አልተደነገገም። ስለሆነም አመልካች ሟች ዘውዳ ድሜንኮ በአሜሪካን አገር ያደረጉት ግልፅ ኑዛዜ ሰነድ የመመዝገብና የማረጋገጥ ሥልጣን ባላቸው የኢትዮጵያ ቆንጺላ ጽ/ቤት ያልተረጋገጠ ስለሆነ ህጋዊ ውጤት የለውም በማለት ያቀረበው ክርክር የህግ ድጋፍ የለውም የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል። አመልካችና ተጠሪ በፅሐፍ ካደረጉት ክርክር በተጨማሪ ችልቱ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የፅሐፍ ክርክር በአጭሩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን የሟችን ወራሾች በመወከል በአመልካች ላይ ክስ ያቀረበውና የውርስ አጣሪ ሆኜ ተሹሜአለሁ የሚለው ሰው የውርስ አጣሪ ሆኖ የተሾመበት የወ/ሮ ዘውዳ ድሜንኮ በውጭ አገር አድርገውታል የተባለው ግልፅ ኑዛዜ ሰነድ ክስ ለማቅረብ የሚያስችለው ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን እንደመረመርነው ሟች ወ/ሮ ዘውዳ ድሜኒኮ እንደ አውሮፒ አቆጣጠር ፋብሪዋሪ 6 ቀን 2005 ዓ.ም በአሜሪካን አገር ሆነው በእንግሉዘኛ ቋንቋ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 881 መሰረት ባደረጉት ግልፅ ኑዛዜ ክስ የቀረበበትን ቤት በኤርትራ ግዛት አሥመራ ከተማ ውስጥ የእየሱስ ኦርቶድክስ ቤተክርስቲያን ደቂ ገብሩ ለሚገኝና አብርሀበሀታ አይነስውራን ትምህርት ቤት ሙለ የባለቤትነት መብቱ እንዱዛወር የተናዘዙ መሆኑንና ይህንንና ላልች የኑዛዜ ቃልችን እንዱያስፈፅም አቶ ታምራት ኪዲነማርያም በውርስ አጣሪነት የሾሙ መሆኑን የሚገልፅ ሰነድ ነው። ተጠሪ የሚከራከሩት ይህ ኑዛዜ በሰነድች ማረጋገጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 334/1995 አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀፅ 2 ሰነድ በሚለው ትርጉም ሥር የሚወድቅ ቢሆንም ሰነደ በውጭ አገር የኢትዮጵያ ቆንጺላ ጽ/ቤቶች አለመመዝገቡና አለመረጋገጡ ህጋዊ ውጤት አያሳጣውም። ምክንያቱም ‛ኑዛዜ“ ካልተረጋገጠና ካልተመዘገበ ህጋዊ ውጤት ከማይኖራቸው ሰነድች አንደኛው አለመሆኑን ከአዋጁ አንቀፅ 5 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ መረዲት የሚቻል በመሆኑ የሚል ሲሆን የከፍተኛው ፍርድ ቤት እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይህንን አተረጓጎም በመከተል ሟች በውጭ አገር አድርገውታል የተባለው የኑዛዜ ሰነድ ህጋዊ ውጤት አለው ከሚል መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል።
በእኛ በኩል ተጠሪ ያቀረበው የኑዛዜ ሰነድ ወ/ሮ ዘውዳ ድሜንኮ ኢትዮጵያ ውስጥ ያደረጉት የኑዛዜ ሰነድ ቢሆን ከላይ የተሰጠው የህግ ትርጉም ተገቢነት ያለው ነው። ሆኖም ተጠሪ ያቀረበው ሟች ኢትዮጵያ ውስጥ ያደረጉትን የኑዛዜ ሰነድ ሣይሆን በአሜሪካን አገር ፈፅመውታል የተባለውን የኑዛዜ ሰነድ በልላ አነጋገር የውጭ አገር ሰነድ (Foreign document) ነው። አንድ ሰነድ የውጭ አገር ሰነድ (Foreign document) የሚባለው በውጭ አገር ተፅፍ ተዘጋጅቶ ከውጭ አገር የተላከና ወደ አገር ውስጥ የገባ ሲሆን ነው። ይኸም በመሆኑ በውጭ አገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም ቆንሲላ ጽ/ቤቶች ትክክለኛነቱ ያልተረጋገጠና ያልተመዘገበ የውጭ አገር ሰነድ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ቢቀርብ ህጋዊ ውጤት ይኖረዋል ወይ? የሚለውን ጥያቄ የሚያስነሳ ነው።
አዋጅ ቁጥር 334/1995 በውጭ አገር የተደረጉ ሰነድች በአዋጁ መሰረት ካልተመዘገቡና ካልተረጋገጡ ህጋዊ ተቀባይነትና ውጤት አይኖራቸውም በማለት ያስቀመጠው ራሱን የቻለ ግልፅ ድንጋጌ የለም። አዋጁ ስለ ‛ውጭ ሰነድች“ መረጋገጥና ህጋዊ ውጤት ስለሚያገኙበት ሁኔታ ከላይ በተገለፀው መንገድ በግልፅ ያልደነገገ ቢሆንም በውጭ አገር ተደርጓል ተብል የቀረበ ኑዛዜ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ወይም ቆንጺላ ጽ/ቤቶች ባይረጋገጥም በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ፉት ሲቀርብ ህጋዊ ውጤት ይኖረዋል ከሚለው መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ አይደለም። ምክንያቱም ከውጭ አገር የሚገቡ የመንግስትም ሆነ የግል ሰነድች ትክክለኛነታቸው በኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽ/ቤቶችና በውጭ በሚገኙ የኢትዮጵያ ቆንጺላ ጽ/ቤቶች እየተረጋገጡና እየተመዘገቡ መግባት ያለባቸው መሆኑን አዋጅ ቁጥር 334/1995 አንቀፅ 26 ንዐስ አንቀፅ 1 ‛በውጭ አገር የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንጺላ ጽ/ቤቶች ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ሰነድችን ያረጋግጣለ“ በሚል መንገድ የደነገገና ይኸም ድንጋጌ አስገዲጅ የህግ ድንጋጌ መሆኑን በድንጋጌው የእንግሉዘኛ ቅጅ ‛Ethiopian Embassies and Consular offices shall authenticate documents entering in to Ethiopia“ በማለት ከውጭ አገር የሚገቡ ሰነድች ትክክለኛነት በኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም ቆንሲላ ጽ/ቤት ትክክለኛነታቸው መረጋገጥ ያለበት መሆኑ አስፈላጊና የግድ መፈፀም የሚገባው ተግባር መሆኑን የሚደነግግ በመሆኑ ነው።
ስለሆነም ተጠሪ የውርስ አጣሪ ሆኜ ተሹሜበታለሁ የሚለው በውጭ አገር ሟች አድርገውታል የተባለው የኑዛዜ ሰነድ የአዋጅ ቁጥር 334/95 አንቀፅ 26 ንዐስ አንቀፅ 1 በሚደነግገው መሰረት አሜሪካን አገር በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትክክለኛነቱ ተረጋግጦና ተመዝግቦ የመጣ ሰነድ አይደለም። ሰነደ በህጉ በአስገዲጅነት የተቀመጠውን መስፈርት ማለትም በውጭ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም ቆንሲላ ጽ/ቤት ትክክለኛ ሰነድ መሆኑ ተረጋግጦና ተመዝግቦ ያልቀረበ በመሆኑ ህጋዊ ውጤት ሉሰጠው ስለማይገባ ተጠሪ የውርስ አጣሪ ሆኜ ተሹሜበታለሁ በማለት ያቀረበው ሰነድ አመልካችን በፍርድ ቤት ከስሶ ለመከራከር የሚያስችለው ሰነድ ሆኖ አላገኘነውም።
በመሆኑም የከፍተኛው ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጠሪ ክስ ለማቅረብ ሥልጣን አግኝቼበታለሁ በማለት ያቀረበው ኑዛዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የተደረገ ሣይሆን በውጭ አገር ተደረገ ተብል የቀረበና ኑዛዜው የሟች ወ/ሮ ዘውዳ ድሜንኮ ትክክለኛ የኑዛዜ ቃል ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 334/95 አንቀፅ 26 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት በአሜሪካን አገር በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያልተረጋገጠና ያልተመዘገበና ይኸም በመሆኑ ህጋዊ ውጤት የላለው መሆኑን ሣያገናዝቡ ተጠሪ ያቀረበውን ክስ በመቀበል አከራካሪውን ውሣኔ መስጠታቸው ከላይ የተጠቀሰውን የህግ ድንጋጌ ይዘት መንፈስ ዓላማና የሚያስከትለውን ህጋዊ ውጤት ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 7 ቀን 1999 የሰጠው ውሣኔና ግንቦት 28 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ብይን ሙለ ለሙለ ተሽሯል።
የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት ግንቦት 2 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
ሟች ወ/ሮ ዘውዳ ድሜንኮ በአሜሪካን አገር አድርገውታል የተባለው ኑዛዜ ትክክለኛነት አሜሪካን በሚገኘው በኢትዮጵያ ኤምባሲ ያልተረጋገጠና ያልተመዘገበ በመሆኑ ህጋዊ ውጤት የላለውና ተጠሪን ክስ ለማቅረብ የሚያስችል አይደለም ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምፅ ተሰጠ።
No topics extracted.