No summary available.
መስከረም 26 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- እነ አሰገደች የእናቶች እና የሕጻናት ሆስፑታል - ጠበቃ ብስራት መኮንን ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር - ነ/ፈጅ እድገት ጥላሁን ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአስፈጻሚ አካል ውሳኔ ይሰረዝልን ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካቾች በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአሁኑ ተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ አመልካቾች በሕጉ አግባብ የመከራከር መብት ሳይጠብቅላቸውና ጥፊታቸውም በአግባቡ ሳይረጋገጥ የሙያ ሥነ ምግባር ጉድለት ፈፅመዋል ተብል ድምዲሜ መደረሱም ሆነ የተጣለው ቅጣት ሕጉን ያልጠበቀ ከመሆኑም በላይ የውሳኔው ሀሳብ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤት ያቀረበው አካል ሥልጣን የላለው በመሆኑ ከሕግ ውጪ የተሰጠው ውሳኔ ሉሰረዝ ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስም ውሳኔው በሕጉ አግባብ የተሰጠ በመሆኑ ሉሰረዝ አይገባም በማለት ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በሁዋላ የአስተዲደር መስሪያ ቤቱ ውሳኔ ሕጉን መሰረት አድርጎ የተሰጠ ነው በሚል ምክንያት የአመልካቾችን ክስ ሙለ በሙለ ውድቅ አድርጓል። በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የአስተዲደር መስሪያ ቤቱ ውሳኔ ሕጉን ተከትል የተሰጠ አይደለም በሚል ምክንያት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሙለ በሙለ በመሻር የአስተዲደር መስሪያ ቤቱ ውሳኔን ሰርዞታል። የአሁኑ ተጠሪም በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ የሰጠው ውሳኔ ተሽሮ የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ጸንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካቾች ጠበቃ ሰኔ 04 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈት ሰባት ገጽ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ የአመልካቾች የመከላከል መብት በሕግ አግባብ ሳይጠበቅና ውሳኔው ሥልጣን በላለው አካል የተሰጠ ሆኖ እያለ የአስተዲደር መስሪያ ቤቱ ውሳኔ አይሰረዝም ተብል የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም የሕክምና ሥነ ምግባር ጉድለት ተፈፅሟል? ወይስ አልተፈፀመም? የሚለውን ጉዲይ የጤና ባለሙያዎች መማክርት ጉባኤ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሚመረምርበት ጊዜ ከተራ ቁጥር ሁለት እስከ ስድስት የተዘረዘሩት አመልካቾች ስለጉዲዩ ሙለ የመከራከርና የመሰማት መብታቸው ታልፍ በመታየቱ የተነሳ በየጉዲዩ ውጤት ላይ ለውጥ ያስከትላል ወይስ አያስከትልም? እንዱሁም በዚህ ጉዲይ በፍትሐብሓሩ የካሣ ጥያቄ ቀርቦ አመልካቾች በፍርድ ኃላፉነት የለባቸውም በሚል በነጻ የተሰናበቱ ከመሆኑ አኳያ ጉዲዩን ለማየት ይቻል ዘንድ በሰበር ችልቱ ላቀርብ ይገባዋል ተብል በመታመኑ ለተጠሪ መጥሪያ ተልኮለት ተጠሪ ቀርቦ ሐምል 15 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ተሰምቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር ብቻ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው 1ኛ አመልካች ፈቃድ ተሰጥቶት የሚሰራ የጤና ተቋም ሁኖ ላልች አመልካቾች ደግሞ 1ኛ አመልካች ተቋም ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች መሆናቸውን በ1ኛ አመልካች ውስጥ ህክምና ሲሰጣቸው የነበሩት ወ/ሮ የኔነሽ ደምሰው ለሕልፈት መዲረጋቸውን ለህልፈት የተዲረጉትም ከህክምና ሙያ ሥነ ምግባር ጉድለት ጋር የተያያዘ ነው የሚል አቤቱታ ለተጠሪ ሲቀርብለት የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች መማክርት ጉባኤ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጉዲዩን ሲያጣራ ቆይቶ የካቲት 8 እና 11 ቀን 2000 ዓ.ም ባደረጋቸው ስብሰባዎች በ1ኛ አመልካች ላይ የስድስት ወር የፈቃድ እገዲ በዶ/ር አሰገደች ላቀው ላይ የአንድ ዓመት የስራ ፈቃድ እገዲ፣ በዶ/ር ጌታቸው ተፈራ እና በሲስተር አበባ ኪዲኔ ላይ የስድስት ወር የስራ ፈቃድ እገዲ፣ በሲ/ር ወጋየሁ አለሙና በአቶ አረፊይኔ ገ/እግዚአብሓር ላይ ከፍተኛ የማስጠንቀቂያ ደብዲቤና ቅጣት ውሳኔ አስተላልፍ ተጠሪ መስሪያ ቤት የኮሚቴውን ውሳኔ ተቀብል ማጽደቁን ነው።
No topics extracted.
አመልካቾች በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት የሚለበት አንደ ምክንያት ለ1ኛ አመልካች በተላከው መጥሪያና ክስ ላልች አመልካቾች ቀርበው ለኮሚቴው መልስ ሰጥተው አልተከራከሩም፣ አልተሰሙም በማለት እና ይህ አካሄድ የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎችን መማክርት ጉባኤ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 76/94 አንቀጽ 16 ስር የተመለከተውን ያላሟላ ነው የሚል ነው። ይኸው የተጠቀሰው ደንብ ድንጋጌ የሙያ ሥነ ምግባር ጉዲዮች ንዐስ ኮሚቴ ሥልጣንና ተግባርን ያስቀመጠ ሲሆን በድንጋጌው ንዐስ ቁጥር አንድ ስር የጤና ሙያ የሚጠይቀው ሥነ ምግባር ባለመከበሩ በባለሙያ ላይ የሚቀርብ ክስን ተቀብል ምርመራ እንደሚያካሂድና እንደሚያጣራ የደነገገ ሲሆን የአንቀጹ ንኡስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ደግሞ በንዐስ ቁጥር አንድ መሰረት የሚቀርበውን ክስ ለማየት በቂ ማስረጃ መኖሩን ካረጋገጠ መልሱን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይዞ እንዱቀርብ በመግለጽ ክሱን ክስ ለቀረበበት ባለሙያ ይልካል በሚል አስቀምጧል። እንግዱህ ንዐስ ኮሚቴው ሉከተለው የሚገባውን ሥርዓት ሕጉ ከላይ በተመለከተው መልኩ ያስቀመጠው ሲሆን ይህ ስነ ስርአት የባለሙያውን የመሰማት መብት የሚያስጠብቅ መሆኑ እሙን ነው። በተያዘው ጉዲይ ምላሽ የሚይስፈልገው ነገር ይህ ሥነ ሥርአት በሕጉ መንፈስ መሰረት አልተጠበቀም ለማለት ይቻላልን? የሚለው ነው። የአመልካቾች ጠበቃ የሚከራከሩት በሕጉ መሰረት ለአመልካቾች ክሱና ማስረጃው ደርሷቸው መልስ ሳይሰጡና መልሳቸው ሳይመረመር ውሳኔ ተሰጥቷል በሚል ነው። ይሁን እንጂ 1ኛ አመልካች ክሱ ደርሶት በጹሐፍ መልስ የሰጠበት፣ ላልች አመልካቾች ደግሞ በጹሐፍ መልስ ባያቀርቡም ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ጉዲዩን በያዘው ንዐስ ኮሚቴ ፉት ቀርበው ቃላቸውን የሰጡ ስለመሆኑ የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያረጋገጠው ጉዲይ ከመሆኑም በላይ ይህ ችልትም የስር ፍርድ ቤትን ዋና መዝገብ አስቀርቦ ይህንኑ ተመልክቷል።
በመሆኑም 1ኛ አመልካች ክስና ማስረጃ አልደረሰኝም በማለት የሚያቀርበው ክርክር እውነትነት የላለው በመሆኑ የሥነ ሥርዓት ግድፈት አለበት ለማለት የማይቻል ሲሆን ላልች አመልካቾችን በተመለከተ ደግሞ ምንም እንኳ አመልካቾች በፁሐፍ ክስና ማስረጃ ደርሷቸው ወደ ክርክሩ ሂደት ባይገቡም በንዐስ ኮሚቴ ፉት ቀርበው ግን ተገቢውን ቃላቸውን የሰጡ በመሆኑ እነኚህ አመልካቾች አልተደመጡም ወይም የመሰማት መብታቸው ተነፍጓል ለማለት የሚያስደፍር አይደለም። ከሁለም በላይ ጉዲዩን ሲመለከት የነበረው አካል ሲያካሂዲቸው የነበራቸው ስብሰባዎች በርካታ ጊዜ የተደረጉ፣ በተገቢ ባለሙያዎች አስተያየት የተሰጠበት የነበረ መሆኑን የአስተዲደር ውሳኔ አካሄድና ይዘት ከማሳየቱም በላይ የአስተዲደር መስሪያ ቤቶች ውሳኔ የሚያስተላልፈበት ጥብቅ የሆነ የክርክር ሥርዓትን ጠብቀው ነው ለማለት የማያስደፍር መሆኑን በኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎችን መማክርት ጉባኤ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 76/94 አንቀጽ 16 ስር የተመለከቱት አጠቃላይ የስነ ስርአት ደንቦች አስገዲጅ የሆነ ሥርዓት አለመሆናቸው የድንጋጌዎቹ ይዘታቸውና አቀራረፃቸው የሚያስገነዝብ መሆኑ ጋር ተዲምሮ ሲታይ በአመልካቾች የመሰማት ወይም የመደመጥ መብት ላይ መሰረታዊ የመብት መጣበብ ወይም ግድፈት ያስከተለ ሁኔታ ተፈጽሟል ለማለት የሚያስችል አይደለም። በመሆኑም አመልካቾች ክሱን የመከላከል መብት አልተከበረም በማለት ያቀረቡት ቅሬታ ተቀባይነት ያለው ሁኖ አላገኘነውም።
ላላው ከዚሁ ነጥብ ጋር ተያይዞ በአመልካቾች የቀረበው ቅሬታና በዚህ ችልትም እንዱታይ የተያዘው ጭብጥ አመልካቾች በፍትሐብሕር የካሣ ጥያቄ ቀርቦ አመልካቾች በፍርድ ኃላፉነት የለባቸውም ተብል በነፃ መሰናበታቸው የመከላከል መብታቸው ቢከበር ኑሮ ሉያስከትል ይችል የነበረው ውጤት ነው። በእርግጥ አመልካቾች በፍትሐብሕር የካሣ ጥያቄ በመደበኛው ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦባቸው የመከላከያ ማስረጃ አሰምተው ክሱ ውድቅ ሁኖ በነፃ የተሰናበቱ መሆኑን በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መ/ ግንቦት 03 ቀን 2002 ዓ.ም የተሰጠ ውሳኔ የሚያሳይ ሲሆን ይህ ውሳኔ ለማስረጃነት በስር ፍርድ ቤት ያልቀረበ ከመሆኑም በላይ የመጨረሻ ውሳኔ ያልተሰጠበት ሲሆን በዚህ ሰበር ችልትም በመከራከሪያነት የቀረበው የመከላከል መብት ቢጠበቅ ሉከተል ይችል የነበረውን ውጤት ያሳያል በሚል እምነት በመሆኑ እና ይህ ችልት ደግሞ ከላይ እንደተገለፀው አመልካቾች የመሰማት መብታቸው ተነፍጓል ለማለት አይቻልም ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰ በመሆኑ የስር ፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በፍትሐብሕር የካሣ ጥያቄ ላይ የሰጠው ውሳኔ በአመልካቾች ላይ ተጠሪ ለወሰደው እምርጃ አመልካቾች የመሰማት መብት ቢከበርላቸው ኑሮ የተለየ ውጤት ሉያስከትል ይችል ነበር ለማለት የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት ላሆን የሚችል ሁኖ አልተገኘም። በአጠቃላይ ተጠሪ በሕጉ የተሰጠውን ኃላፉነትና ተግባር ለመወጣት በሕጉ በተዘረጋለት ሥርዓት መሰረት የሰጠው ውሳኔ እንጂ ከሕጉ ውጪ የተሰጠ ነው ለማለት የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት ስላላገኘን በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት 23 ቀን 2002 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
በዚህ ችልት ሐምል 30 ቀን 2002 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል።
ለሚመለከታቸው አካላት ይፃፍ።