No summary available.
ጥቅምት 16 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የቦላ ክ/ከ/ገቢዎች መምሪያ ነ/ፈጅ ታደሰ አንዲርጌ - ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡-
አቶ መዓዛ ሽፈራው - ጠበቃ ወርቅነሽ መንግሥቱ - ቀረቡ።
ወ/ሮ ስብለ ከፈለኝ - ቀረቡ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ይህ አቤቱታ የቀረበው በተጠሪዎች መካከል የንብረት ክፍፍል ከመደረጉ በፉት የቀዲሚነት መብት ይፈጽምልኝ ሲል አመልካች ያቀረበውን አቤቱታ የሥር ፍ/ቤቶች ባለመቀበላቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ይታረምልኝ በማለት አመልካች ስለጠየቀ ነው።
አመልካች ለሰበር ችልቱ ያቀረበው አቤቱታ ይዘት ሲታይ 1ኛ ተጠሪ በኮንስትራክሽን ሙያ የተሰማሩ ነጋዳ ስለመሆናቸው፣ አመልካችም በአዋጅ ቁጥር 286/94 እና 285/94 መሰረት የንግድ ትርፍ ገቢ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከ1997 እስከ 2ዐዐዐ ዓ.ም. ያለባቸው የመንግሥት እዲ ብር 4ዐ5,ዐ7ዐ.88 እንዱከፍለ ማስታወቂያ ደርሷቸው ባለመክፈላቸው በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ለማስፈጸም እንደሚችል፣ 1ኛ ተጠሪ በተጨማሪ እሴት ታክስ የሰበሰቡት ገንዘብ ብር 4ዐ,140.63 ጭምር መታገደን በመግለጽ ይህንኑ ለማስፈጸም ያቀረበውን የጣልቃ ገብነት አቤቱታ የሥር ፍ/ቤት አለመቀበለ ስሕተት ነው ተብል እንዱታረም በሚል ነው።
የሰበር ችልቱም የአመልካች አቤቱታ ውድቅ የተደረገው በሕጉ አግባብ ነው ወይንስ አይደለም? የሚለውን ለመመርመር ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ አዟል።
1ኛ/ ተጠሪ በ24/ዐ6/2ዐዐ2 ዓ.ም. ባቀረበው የጽሁፍ መልስ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በነበረው ክርክር ንብረቶቹ በመታገዲቸው የመንግሥት እዲ /ግብር/ ለመክፈል አለመቻለን ገልፆ በዚህም ምክንያት የሥራ ፈቃደም እንዲልታደሰ በመዘርዘር የሥር ፍ/ቤት ትዕዛዝ እንዱታረም ጠይቋል።
2ኛ ተጠሪ በበኩሎ በ18/5/2ዐዐ2 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ አቅርባለች። ይዘቱም የአመልካች አቤቱታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 418 መሰረት ተቀባይነት እንደላለው ከ1ኛ ተጠሪ የሚፈለገው የግብር ገንዘብ መጠን በ1999 እና 2ዐዐዐ ዓ.ም. የተከፊፈለ በመሆኑ ተጠሪዋ ደግሞ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር የነበራት ግንኙነት በ1999 ዓ.ም. የተቋረጠ በመሆኑ የጋራ እዲ ልባል እንደማይገባ በዚህም ምክንያት የጋራ ሀብት ሉያዝ እና ሉፈፀምበት እንደማይገባ በመዘርዘር የሥር ፍ/ቤት ትእዛዝ እንዱፀና ጠይቃለች።
አመልካች ክርክሩን በማጠናቀር የመልስ መልስ ሰጥቷል። የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ከፍ ሲል የተመለከተው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል።
ከመዝገቡ እንደተረዲነው በ1ኛ ተጠሪ እና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የንብረት ክፍፍልን በተወሰነው መሰረት አፈፃፀሙ በ2ኛ ተጠሪ አመልካችነት መዝገብ ተከፍቶ በሂደት ላይ ባለበት ሁኔታ ግራ ቀኙ ንብረቱን ከመከፊፈላቸው በፉት ከ1ኛ ተጠሪ የሚፈለግ ግብር እና ተጨማሪ እሴት ታክስ በቀዲሚነት ለማስፈጸም አመልካች አቤቱታ ያቀረበ ስለመሆኑ ነው።
አመልካች ለአቤቱታው መሰረት ያደረገው መሰረታዊ ሕግ አዋጅ ቁጥር 285/94 እና አዋጅ ቁጥር 286/94ን ስለመሆኑ ግልጽ ነው።
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 32/1/ እና የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 8ዐ/1/ ላይ እንደተደነገገው ዋስትና የተሰጣቸው የላልች አበዲሪዎች የቅድሚያ መብት እንደተጠበቀ ሆኖ ታክስ ወይም ግብሩ ተከፍል እስከአለቀበት ጊዜ ድረስ ታክስ ወይም ግብር የመክፈል ግዳታ ያለበት ሰው ሀብት ላይ ባለሥልጣኑ ከማናቸውም ላልች እዲዎች የቀደምትነት መብት እንዲለው ተመልክቷል። በዚህ ረገድ የሕጉ አገላለጽ ግልጽ ነው።
በተያዘው ጉዲይ በተጠሪዎች መካከል ንብረት ክፍፍል እንዱደረግ መወሰኑን ተከትል የፍርድ ባለመብት የሆነችው 2ኛ ተጠሪ ባስከፈተችው የአፈፃፀም መዝገብ በ2ኛ ተጠሪ ስም አለ የተባለን ሀብት ያስከበረች ስለመሆኑ መዝገቡ ያስረዲል። በፍርድ ባለእዲ ጥያቄ የታገደና የተከበሩት የ2ኛ ተጠሪ ሀብቶች አንድም በዓይነት አልያም ተሸጠው ለፍርድ ባለመብት የሚከፈል መሆኑ ግልጽ ነው። ስለሆነም ንብረቱ ለፍርድ ባለመብት ከመከፈለ በፉት አመልካች በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት መብቱን ለማስከበር እና ለማስፈጸም አፈፃፀሙን ለያዘው ፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረቡ ሲታይ ከሕግ የመነጨ መሰረት ያለው መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
አመልካች በአፈፃፀም በተያዘ ንብረት ላይ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 418 ጠቅሶ አቤቱታ ማቅረቡም ቢሆን በሥነ ሥርዓት ሕጉ እንደተደነገገው የቀዲሚነት መብቱን መሰረት /መነሻ/ ምክንያት ማስረዲት የሚጠበቅበት እንጂ በዋናው ውሣኔ እንዱከራከር አያስገድደውም።
ስለሆነም አመልካች ያቀረበውን አቤቱታ የሥር ፍ/ቤቶች ውድቅ ማድረጋቸው የሕጉን ዓላማና ይዘት ያገናዘበ ባለመሆኑ ሉታረም የሚገባ ሆኖ ተገኝቷል።
በልላ በኩል 2ኛዋ ተጠሪ የጋራ አፈፃፀም አይመለከተኝም የሚል ክርክር በዚህ ሰበር ችልት በአማራጭ አቅርባለች። በመሰረቱ ከ1ኛ ተጠሪ የሚፈለገው የተከሣሽ እና የግብር እዲ የግል ወይንስ የጋራ? የሚከፈለውስ ከግል ሀብት ወይንስ ከጋራ ሀብት የሚለት እና ተያያዥ ጭብጦች በሥር ፍ/ቤት ተመርምሮ ውሣኔ ያልተሰጠባቸው ስለሆነ በዚህ ሰበር ችልት የሚመረመርበት የሕግ አግባብ የለም።
ስለሆነም በዚህ ረገድ ጉዲዩ እልባት ሉያገኝ የሚገባው የሥር ፍ/ቤት ተመልሶ ግራ ቀኙ በሚያቀርቡት ክርክር እና ማስረጃ መሆን እንዲለበት ታምኗል።
ስለሆነም አመልካች ያቀረበውን የቀዲሚነት መብት ይከበርልኝ ጥያቄ የሥር ፍ/ቤት ሳይቀበል መቅረቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ በማረም ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ትዕዛዝ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህንኑ ትዕዛዝ በመ/ቁ. 81ዐ55 ነሐሴ 11 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በማጽናት የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
No topics extracted.