No summary available.
ጥር 26 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት አመልካቾች ስላመለከቱ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። የክርክሩ መነሻ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው የአፈፃፀም ትእዛዝ እንዱሰረዝላቸው አመልካቾች ያቀረቡት ጥያቄ በየደረጃው ያለ የክልል ፍርድ ቤቶች ህጋዊ መሰረት የለውም በማለት ውድቅ ማድረጋቸው ነው።
የክርክሩ መሰረታዊ ይዘት አንደኛ ተጠሪ ለሁለተኛ ተጠሪ ገንዘብ አበድሮ ያልተከፈለው መሆኑን በመግለጽ ክስ አቅርቦ ሁለተኛ ተጠሪ ከአንደኛ ተጠሪ የተበደሩትን ገንዘብ እንዱከፍለ በፍርድ ተወስኖባቸዋል። ከዚህ በኋላ አንደኛ ተጠሪ የፍርድ ባለመብት ሁለተኛ ተጠሪ የፍርድ ባለዕዲ ሆነው አንደኛ ተጠሪ በአስከፈቱት የአፈፃፀም መዝገብ ተከራክረው ንብረትነቱ የሁለተኛ ተጠሪ ነው የተባለ ቤት በሀራጅ የሚሸጥ መሆኑ በበከልቻ ጋዜጣ የጨረታ ማስታወቂያ ወጥቶ ቤቱ ተሽጦ ለሁለተኛዋ ተጠሪ እዲ መክፈያነት እንዱውል የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰጥቷል። አመልካች ቤቱ ከተሸጠና የአፈፃፀም መዝገቡ ከተዘጋ በኋላ ለሁለተኛ ተጠሪ እዲ መክፈያነት የተሸጠው ቤት የሁለተኛ ተጠሪ የግል ንብረት ሣይሆን የአንደኛ ተጠሪ፣ የሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች የጋራ ንብረት ነው። አንደኛ ተጠሪ ከሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች ጋር በመሆን ህዲር 26 ቀን 1996 ዓ.ም በተፃፈ ውል ለአንደኛ አመልካች የሸጡትና አንደኛ አመልካችም በውለ መሰረት ብር 82,640.29 (ሰማንያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ አርባ ብር ከሃያ ዘጠኝ ሳንቲም) ቤቱን ከባንክ መያዣነት ለማስለቀቅ የከፈለ መሆኑን የቤቱን ስመ ሀብት ወደ ወራሾቹ ለማዛወር ብር 31,884.42 (ሰላሳ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ሰማንያ አራት ብር ከአርባ ሁለት ሳንቲም) የከፈለ መሆኑን ብር 16,799 ለወራሾቹ የከፈለ መሆኑን በመግለጽ ንብረቱ ላይ የተደረገው የሀራጅ ሽያጭ እንዱሰረዝላቸው ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልክተዋል።
አንደኛ ተጠሪ ቤቱ በሀራጅ የሚሸጥ መሆኑ ማስታወቂያው በቤቱ ላይ ያልተለጠፈ መሆኑን በማመን የሀራጅ ማስታወቂያው በጋዜጣ የወጣ በመሆኑ የሽያጩን ሥርአት ለማሰረዝ የሚያበቃ ምክንያት አይደለም። ቤቱ የፍርድ ባለዕዲዋ የሁለተኛ ተጠሪ ንብረት እንደሆነ በክፍለ አስተዲደር ተረጋግጧል። ሽያጩ እንዱሰረዝ ጥያቄው የቀረበው በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 447(1) በተደነገገው የሁለት ወር ጊዜ ካለፈ በኋላ በአምስት ወሩ ነው። አመልካቾች በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 418 መሰረት ጣልቃ መግባት የሚችለት ፍርደ ከመፈፀሙ በፉት ነው።
አንደኛ አመልካች በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1723 መሰረት ቤቱን የገዛ መሆኑን ያቀረበው ማስረጃ ስለላለ የሀራጅ ሽያጩ እንዱሰረዝ ለማመልከት የሚያስችል መብት የለውም በማለት መልስ የሰጠ ሲሆን ሁለተኛ ተጠሪ (የፍርድ ባለዕዲዋ) በበኩሎ ከአንደኛው ተጠሪ የፍርድ ባለመብት ገንዘብ ተበድሬ መክፈል ስላልቻልኩኝ ቤቱ ተሽጦ ተከፍሎል። ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች ከእዲ ቀሪ ከሆነው ገንዘብ ድርሻቸውን እንዱሰጣቸው ከሚጠይቁ በስተቀር ሽያጩ እንዱሰረዝ ለመጠየቅ አይችለም። ቤቱ ከተሸጠና ገንዘቡ ከተከፈለ በኋላ ሁለት ወር አልፍታል በማለት መልስ ሰጥተዋል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካቾችን አቤቱታና የተጠሪዎችን መልስ ከመረመረ በኋላ
የጨረታው ማስታወቂያ በተሸጠው ቤት ላይ ተለጥፎል ወይስ አልተለጠፈም?
የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣ የሀራጅ ማስታወቂያው በሚሸጠው ቤት ላይ መለጠፍ ነበረበት በማለት አቤቱታ አቅራቢዎች (አመልካቾች) የሚያቀርቡት ክርክር ትክክል ነው ወይስ አይደለም?
አቤቱታ አቅራቢዎች የሀራጅ ሽያጩ እንዱሰረዝ ጥያቄ ያቀረቡት ህጉ በሚፈቅደው የጊዜ ገደብ ውስጥ ነው ወይስ አይደለም?
የአንደኛው አቤቱታ አቅራቢ (አመልካች) ቤቱን ለመግዛት ያደረገው ውል በህግ ፉት ተቀባይነት አለው ወይስ የለውም?
በፍርድ አፈፃፀም ሂደት መብታችንና ጥቅማችንን ያሳያል የሚለ ሰዎች የጣልቃ ገብነቱን ጥያቄ መቼ ማቅረብ አለባቸው? የሚለትን ጭብጦች መስርቷል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቤቱ የሀራጅ ማስታወቂያ በቤቱ ላይ ያልተለጠፈ መሆኑን አረጋግጧል። ሆኖም የሀራጅ ማስታወቂያው በጋዜጣ የወጣ በመሆኑ የሀራጅ ማስታወቂያው በሚሸጠው ቤት ላይ አለመለጠፈ የሀራጅ ሽያጩን ለመሰረዝ የሚያበቃ ምክንያት አይደለም በማለት ወስኗል። ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ አመልካቾች ሽያጩ እንዱሰረዝላቸው በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 447(1) የተደነገገው የሁለት ወር የጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ የቀረበ ስለሆነ የአመልካቾች አቤቱታ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል። አራተኛውን ጭብጥ በተመለከተ አንደኛው አመልካች የሁለተኛ ተጠሪ፣ የሁለተኛና የሶስተኛ አመልካች የጋራ ሀብት የሆነውን ቤት በፍ/ብሓር ሕግ ቁጥር 1723 መሰረት የገዛ መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ በቤቱ ላይ የተደረገውን ሽያጭ እንዱሰረዝለት ለመጠየቅ የሚያስችለው መብት የለውም በማለት ብይን የሰጠ ሲሆን አምስተኛውን ጭብጥ በተመለከተ በአፈፃፀም ሂደት በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 418 መሰረት ጣልቃ መግባት የሚቻለው ፍርደ ከመፈፀሙና ንብረቱ ከመሸጡ በፉት በመሆኑ የአመልካቾች ጥያቄ ሥነ ሥርአት ሕግ ድንጋጌው መሰረት አልቀረበም በማለት የአመልካቾችን አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል። ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች የፍርድ ባለዕዲ (ሁለተኛ ተጠሪ) ባመነችው መሰረት ድርሻቸውን ከሚጠይቁ በስተቀር ሽያጩ እንዱሰረዝ ለመጠየቅ አይችለም በማለት ወስኗል።
አመልካቾች የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የአመልካቾችን ይግባኝ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል። አመልካቾች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት የአመልካቾችን አቤቱታ ውድቅ አድርጏታል።
አመልካቾች ሐምል 6 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ሁለተኛ አመልካችና ሶስተኛ አመልካች ከሁለተኛዋ ተጠሪና በዚህ ክርክር ተሳታፉ ካልሆኑት ሄኖክ መኮነን እና ራሄል መኮነን የጋራ ንብረት የሆነ ቤት በቡራዩ ከተማ ነበራቸው። ይህንን የጋራ ንብረት የሆነውን ቤት ህዲር 26 ቀን 1996 ዓ.ም በተፃፈ ውል አንደኛው አመልካች የገዛው ሲሆን ውለ በምዕራብ ሸዋ ዞን ውልና ማስረጃ ጽ/ቤት እንዱመዘገብ ተደርጓል። የፍርድ ባለመብት ነው የተባለው አንደኛው ተጠሪ በሽያጭ ውለ ላይ በምስክርነት የፈረሙ ሲሆን ለሽያጭ ውለ መልካም አፈፃፀም ለሻጮች ሀላፉ እሆናለሁ በማለት የዋስትና ግዳታ ገብቷል። ሁለተኛ ተጠሪ በመዝገብ በመጀመሪያ ለእኔ ከላልቹ በተለየ ሁኔታ ብዙ ገንዘብ ገዥ ሉከፍለኝ ይገባል በማለት ክስ ያቀረቡ ሲሆን ከዚህ በኋላ ክሳቸውን በማሻሻል ውለ ይፍረስልኝ የሚል ክስ አቅርበው ነበር። ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች የሁለተኛ ተጠሪን ክስ በመቃወም በክርክሩ ጣልቃ ከገቡ በኋላ መዝገቡ የዲኝነት ሳይከፈል የተከፈተ በመሆኑ ሁለተኛ ተጠሪ የዲኝነት ከፍለው እንዱቀርቡ ትእዛዝ ተሰጥቶ የዲኝነት ስላልከፈለ የዲኝነት ሲከፈል መዝገቡ እንደሚንቀሳቀስ ገልፆ ሰኔ 18 ቀን 2001 ዓ.ም መዝገቡን ዘግቶ አሰናብቶናል።
ከዚህ በኋላ ሁለተኛ ተጠሪ ክርክራቸው የማያዋጣቸው መሆኑን በመለየት በቤቱ ሽያጭ ላይ በምስክርነት የፈረሙትና ለአፈፃፀሙ ዋስ ከሆኑት አንደኛ ተጠሪ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ለሁለተኛ ተጠሪ እንዲበሩ የሚገልጽ ሁለት የብድር ውል በማዘጋጀት በፍርድ ቤት አንደኛ ተጠሪ በሁለተኛ ተጠሪ ላይ ክስ አቅርበው አስፈርደውና የአፈፃፀም ክስ አቅርበው የሀራጅ ማስታወቂያው ቤቱ ላይ ሳይለጠፍ ሀራጅ እንዱከናወን በማድረግ የአንደኛ ተጠሪ የአክስት ልጅ ቤቱን በሀራጅ እንዱገዛው አድርገዋል። እኛ ቤቱ በሀራጅ የተሸጠ መሆኑን ያወቅነው ከአምስት ወር በኋላ የአንደኛ ተጠሪ የአክስት ልጅ ቤቱን በፍርድ ቤት በወጣ ሀራጅ ስለገዛሁት ልቀቁ ብል ሲጠይቀን ነው። በአንደኛ ተጠሪና በሁለተኛ ተጠሪ መካከል የተደረገው የብድር ውል ሀሰተኛ የብድር ውል መሆኑን ፕሉስ በወንጀል እንዱያጣራልን ጠይቀን የብድር ውለ በሀሰት የተዘጋጀ የብድር ውል መሆኑን በፕሉስ ምርመራ የተረጋገጠ ሲሆን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 447(1)፣ ድንጋጌ ይዘትና ተጠቃሽና ተፈፃሚ የሚሆንበትን ሁኔታና በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 418ን አላግባብ በመተርጎም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል።
ለአመልካች የሰበር አቤቱታ አንደኛ ተጠሪ ህዲር 16 ቀን 2003 ዓ.ም የተፃፈ ሶስት ገጽ መልስ አቅርቧል። አንደኛ ተጠሪ ባቀረበው መልስ አመልካቾች ለሥር ፍርድ ቤት ያላቀረቡትን አዱስ መከራከሪያ በሰበር ያቀረቡ ስለሆነ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 329 መሰረት ውድቅ ይደረግልኝ። አመልካቾች አቤቱታቸውን ያቀረቡት የፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 418 ን በመጥቀስ ነው። ፍርድ ቤቱ በዚህ ድንጋጌ በአፈፃፀም ጣልቃ መግባት የሚችለው ፍርደ ከመፈፀሙ በፉት ነው በማለት የሰጠው ትርጉም ስህተት የለውም። የሀራጅ ማስታወቂያው ቤቱ ላይ አለመለጠፈ የሀራጅ ሽያጩን ለማሰረዝ የሚያስችል ምክንያት አይደለም። አመልካቾች ጥያቄያቸውን በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 447(1) በተደነገገው የጊዜ ገደብ አላቀረቡም። ስለሆነም የሀራጅ ሽያጩ የህጉን ሥርአት ተከትል የተፈፀመ በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል።
ሁለተኛ ተጠሪ በበኩላቸው ህዲር 16 ቀን 2003 ዓ.ም የተፃፈ ሶስት ገጽ መልስ አቅርበዋል።
ሁለተኛ ተጠሪ የጨረታ ማስታወቂያው ቤቱ ላይ አለመለጠፈ የሀራጅ ማስታወቂያው በጋዜጣ የወጣ በመሆኑ የሀራጅ ሽያጩን ለመሰረዝ የሚያበቃ አይደለም። አመልካቾች ጥያቄያቸውን በህግ በተደነገገው የጊዜ ገደብ ውስጥ አላቀረቡም በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች አቤቱታቸውን ውድቅ ያደረጉት በአግባቡ ነው፣ በምዕራብ ሸዋ ዞን ውልና ማስረጃ የተደረገውን ውል ሁለተኛ ተጠሪ የሚያውቁት አይደለም። የብድር ውለ በሀሰት የተደረገ ነው ይበለ እንጂ በፍርድ ቤት ውሣኔ የተረጋገጠ ነው። ቤቱን የገዛው የክርስትና ልጅ ነው ለሚለት የክርስትና ልጅ መሆኑን ማስረጃ አላቀረቡም የክርስትና ልጅ እንዲይገዛ ህጉ አይከለክልም የሚል መልስ አቅርበዋል። አመልካቾች በበኩላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች የፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 425 እና የፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 447 እና ላልች የሕግ ድንጋጌዎች ሲተረጏሙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የሰሩ በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባዋል በማለት ታህሣሥ 15 ቀን 2003 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር በግራ ቀኙ የቀረበው የጽሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ችልት አመልካቾች የሀራጅ ሽያጩ እንዱሰረዝላቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ ያደረጉት በአግባቡና ለጉዲዩ ተጠቃሽና ተፈፃሚ መሆን የሚገባቸውን የፍታብሓር ሥነ ሥርአት ሕግ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን በመጀመሪያ በአፈፃፀም የተሸጠው በቡራዩ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ቤት የማን ንብረት ነው? የሚለውን መለየት አስፈላጊ ነው። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአፈፃፀም እንዱሸጥ ያደረገው ቤት የሁለተኛ ተጠሪ የግል ንብረት አለመሆኑን ሁለተኛ ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤትም ሆነ በሰበር ለዚህ ችልት ባቀረቡት ክርክር ያመኑት ፍሬ ጉዲይ ነው። በአፈፃፀም በሀራጅ የተሸጠው ቤት የሁለተኛ አመልካች፣ የሶስተኛ አመልካች፣ በዚህ ክርክር ተሳታፉ ያልሆኑት ሄኖክ መኮንንና ራሄል መኮንን እና የሁለተኛ ተጠሪ የጋራ ሀብት የነበረ ነው። በቤቱ ላይ ሁለተኛ ተጠሪ ድርሻ የነበራቸው ቢሆንም ይህንን ድርሻቸውን ቤቱ በአንደኛ አመልካች እንዱሸጥ በሰጡት ፈቃድና ስምምነት መሰረት ሸጠዋል የሚለው ነጥብ በሥር ፍርድ ቤት የቀረበና ውለ የህጉን ፍርም አላሟላም በማለት የታለፈ ነው። አንደኛ አመልካች ውለ በምዕራብ ሸዋ ዞን ውልና ማስረጃ ጽ/ቤት የተመዘገበ መሆኑን በመግለጽ ላቀረበው ክርክር ምዕራብ ሸዋ ዞን የተደረገውንና የተመዘገበውን ውል አላውቀውም በማለት ሁለተኛ ተጠሪ በመሸሽ መልክ መልስ የሰጡ ሲሆን ሁለተኛ ተጠሪ ከላልች የቤቱ የጋራ ባለሀብቶች ጋር በመሆን ቤቱን ለአንደኛ አመልካች አልሸጥኩም በማለት የፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 234 ንዐስ አንቀጽ 1(ሰ) መሰረት አልተከራከሩም። ከዚህ የምንረዲው ቤቱ የፍርድ ባለዕዲ የሆኑት የሁለተኛ ተጠሪ የግል ንብረት እንዲልሆነና ሁለተኛ ተጠሪ በቤቱ ላይ ያላቸውን መብት ከላልች የጋራ ባለሀብቶች ጋር በመሆን ለአንደኛ አመልካች ለፍርድ አፈፃፀም ምክንያት የሆነውን የብድር ገንዘብ ከአንደኛ ተጠሪ ከመበደራቸው በፉት የሸጡ መሆኑን በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 234 ንዐስ አንቀጽ 1(ሰ) እና በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 235 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት እንዲመኑ የሚቆጠር ነው። በአፈፃፀም የተሸጠው ቤት የፍርድ ባለዕዲዋ ካልሆነና የፍርድ ባለዕዲዋ በቤቱ ላይ የነበራቸው የጋራ ንብረት ባለቤትነት መብት ከላልች ባለሀብቶች ጋር በመሆን የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1266 በሚደነግገው መሰረት ለአንደኛ አመልካች የሸጠች መሆኑን ክዲ ባልተከራከረችበት ሁኔታ የበታች ፍርድ ቤቶች ለጉዲዩ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 447(1) የተደነገገው የጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ ነው አቤቱታ ያቀረባችሁት በማለት የሰጡት ብይን ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለው መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
አንደኛ አመልካች ንብረቱ የጋራ ባለሀብት ከሆኑ ሰዎች ቤቱን የገዛው መሆኑን ሁለተኛ ተጠሪ በግልጽ ክደው አልተከራከሩም። በአፈፃፀም የተሸጠው ቤት የጋራ ባለሀብት የሆኑት ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች አንደኛ አመልካች ቤቱ ላይ በባንክ የሚፈለገውን እዲ በመክፈልና የማዘጋጃ ቤትን ዕዲ በመክፈል ቤቱን ነፃ ያደረገ መሆኑንና ከሁለተኛ ተጠሪና ከላልች የጋራ ባለሀብቶች በሙለ ፈቃድና ስምምነት ገብቶ ቤቱን ይዞ የሚገኝ መሆኑን በመግለጽ ተከራክረዋል። በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 447 ንዐስ አንቀጽ 1 የተደነገገው የሁለት ወር ጊዜ ገደብ በአፈፃፀሙ ሂደት ተከራካሪ የነበሩት የፍርድ ባለዕዲው ወይም የፍርድ ባለመብቱ ወይም በሀራጅ ጨረታው ተሳትፍ ቤቱን የገዛው ሰውና ለአፈፃፀሙ ሙለ እውቀት የነበራቸው ላልች በጉዲዩ ይገባናል የሚለ ሰዎች የሀራጅ ጨረታውን ለማስፈረስ በቂ ምክንያት ካላቸው ሽያጩ እንዱሰረዝላቸው በሁለት ወር ውስጥ ማመልከት ያለባቸው መሆኑን የሚደነግግ ነው። በአፈፃፀም በሀራጅ በተሸጠው ቤት ላይ መብት ያለውን ሶስተኛ ወገን በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 447 ንዐስ አንቀጽ 1 በተደነገገው የሁለት ወር ጊዜ ገደብ ውስጥ አላመለከትክም ብል አቤቱታውን ውድቅ ለማድረግ በመጀመሪያ ቤቱ በፍርድ ምክንያት እግድ የተሰጠበት መሆኑና ሀራጅ ማስታወቂያ የወጣበት መሆኑን በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 414 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት በቤቱ ላይ የተለጠፈ መሆኑን ማረጋገጥ የግድ የሚያስፈልግ መሆኑ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 425 ንዐስ አንቀጽ 1 ተደንግጓል። በያዝነው ጉዲይ የሁለተኛ ተጠሪ የግል ሀብት ያልሆነው ቤት የሀራጅ ማስታወቂያ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 414 ንዐስ አንቀጽ 2 እና የፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 425 ንዐስ አንቀጽ 1 በሚደነግገው መሰረት በቤቱ ላይ አልተለጠፈም። ይኼም በመሆኑ ቤቱን ከሁለተኛ ተጠሪና ከላልች የቤቱ የጋራ ባለሀብቶች ገዝቶ የያዘው አንደኛ አመልካችና ቤቱን ከሁለተኛ ተጠሪ ጋር በመሆን ለአንደኛ አመልካች የሸጡት የቤቱ የጋራ ባለሀብት የሆኑት ሁለተኛ እና ሶስተኛ አመልካቾች ቤቱ በሁለተኛ ተጠሪ እዲ ምክንያት እግድ የተሰጠበትና የሀራጅ ጨረታ የወጣበት መሆኑን ለማወቅ የሚያስችላቸው ሁኔታ አልነበረም።
ሕግ አውጪው የማይንቀሳቀስ ንብረት የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 423 የተደነገገውን ሁኔታ አሟልቶ በጋዜጣ እንዱወጣ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 425 ንዐስ አንቀጽ 2 ከተደነገገው በተጨማሪ የሀራጅ ማስታወቂያው በሚሸጠው የማይንቀሳቀስ ቤት ላይ እንዱለጠፍ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 414 ንዐስ አንቀጽ 2 እና በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 425 ንዐስ አንቀጽ 1 የደነገገበት የራሱ የሆነ መሰረታዊ ምክንያት አለው። ይኸው የእግድ ትእዛዝ የተሰጠበት ወይም የሀራጅ ማስታወቂያ የወጣበት የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ መብት ያላቸው ሰዎች ንብረቱ የእግድ ትእዛዝ የተሰጠበት ወይም ለሀራጅ ማስታወቂያ የወጣበት መሆኑን በመገንዘብ በአፈፃፀሙ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 418 መሰረት ጣልቃ ገብተው መብታቸውን እንዱያስከብሩ ለማድረግ ንብረቱ የጋራ ባለሀብቶች በሆነ ጊዜ የንብረቱ የጋራ ባለሀብቶች በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 443 የተጠበቀላቸውን መብት እንዱያስከብሩ ንብረቱ በሀራጅ የሚሸጥ መሆኑን እንዱያውቁት ለማድረግና በመጨረሻም የሀራጁን ሂደት በመከታተል በሂደቱ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 445 የተደነገጉት ሕገ ወጥና የማጭበርበር ተግባራት ከተፈፀሙ የሀራጅ ሽያጩ እንዱሰረዝ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 447 ንዐስ አንቀጽ 1 በተደነገገው ጊዜ ውስጥ ለማመልከት እንዱችለ ነው። ህግ አውጭው ከላይ የተዘረዘሩትን ዓላማዎች የማሳካት ሀሳብና ፍላጏት ባይኖረው ኖሮ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያውና በማይንቀሳቀስ ንብረት በፍርድ በተወሰነ እዲ ምክንያት የእግድ ትእዛዝ ሲሰጥ በማይንቀሳቀሰው ቤት ላይ እንዱለጠፍ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 414 ንዐስ አንቀጽ 2 እና በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 425 ንዐስ አንቀጽ 1 አይደነግግም ነበር። ስለሆነም የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያው በሚሸጠው ቤት ላይ አለመለጠፍን እንደ ቀላል የሥነ ሥርአት ግድፈት በመቁጠር የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ትርጓሜ ከላይ በዝርዝር የተገለፀውንና ህግ አውጭው ሉያሳካቸው የሚፈልጋቸውን ግቦች ያላገናዘበ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የሀራጅ ማስታወቂያው በማይንቀሳቀሰው ንብረት ላይ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 425 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት ሣይለጠፍ የያዙት የማይንቀሳቀስ ንብረት በአፈፃፀም ምክንያት የእግድ ትእዛዝ በልላ ወይም የሀራጅ ማስታወቂያ የወጣበት መሆኑን ሳያውቅ በልላ ሰው እዲ ምክንያት የያዙት ንብረት በሀራጅ የተሸጠባቸው ሰዎች በምን መንገድና መቼ የሀራጅ ሽያጭ እንዱሰረዝላቸው ለማመልከትና በንብረት ላይ አለን የሚለትን የንብረት ባለቤትና ላልች ተዛማጅ መብቶች ለማስከበር ይችላለ? የሚለው ነጥብ የያዝነውን ጉዲይ ለመወሰን መመለስ ያለበት ጥያቄ ነው። የማይንቀሳቀስ ንብረት በሀራጅ ከተሸጠ በኋላ በንብረቱ ላይ መብት ያለው ሰው ንብረቱን ለገዢው እንዱያስረክብ ሲጠየቅ ንብረቱን መልቀቅ አይገባኝም በማለት አቤቱታውን ሉያቀርብ እንደሚችል የፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 453 ንዐስ አንቀጽ 1 የሚደነግግ ሲሆን እንደዚህ በሚሆን ጊዜ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር የሚሰማበትን ቀነ ቀጠሮ በመያዝ መስማት እንዲለበት ይደነግጋል።
በዚህ ሂደት አመልካች ንብረቱን የያዘው በራሱ መብትና ከላላ ሰው በተላለፈለት መብት መሆኑን ፍርድ ቤቱ ከተረዲው ንብረቱ እንዱመለስለት ለመወሰን እንደሚቻል የፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 453 ንዐስ አንቀጽ 3 ይደነግጋል።
በያዝነው ጉዲይ አመልካቾች የሀራጅ ሽያጩ እንዱሰረዝላቸው የጠየቁት አንደኛ አመልካች ከሁለተኛ ተጠሪ /የፍርድ ባለዕዲ/ እና ከላልቹ ባለሀብቶች ገዝቶ የያዘውን ቤት በሀራጅ ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ስለገዛሁት ልቀቅልኝ በማለት ገዥው ሀራጁ ከተከናወነ በኋላ ከአምስት ወር በኋላ ሲጠይቀው መሆኑ በሥር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። የሥር ፍርድ ቤት የአመልካቾችን አቤቱታ የፍታብሓር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 453 ድንጋጌን መሰረት በማድረግ ማስተናገድና ውሣኔ መስጠት ሲገባው ለጉዲዩ አግባብነት የላላቸው የፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 418 እና የፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 447 ንዐስ አንቀጽ 1 ን በመጥቀስ የአመልካቾችን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ችልት ይህንን ውሣኔ ማጽናታቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
በምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያከናወነው የሀራጅ ሽያጭ ማጭበርበር የተፈፀመበትና የህጉን ሥርአት ያልተከተለና የፍርድ ባለዕዲ ያልሆኑትን የአንደኛ አመልካችንና የላልች አመልካቾችን መብት የሚጎዲ በመሆኑ የሀራጅ ሽያጩ ሉሰረዝ ይገባዋል በማለት ወስነናል።
በዚህ መዝገብ ያወጡትን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻቻለ ብለናል።
መዝገቡ ወደ መ/ቤት ይመለስ።
ሃ/ዓ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.