No summary available.
ታህሣሥ 26 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካቾች - 1. ወ/ሮ ይሕደጋ ሳሙኤል - አልቀረቡም 2. ወ/ሮ አልጋነሽ ሳሙኤል 3. ወ/ት ዘነበሽ ሳሙኤል - ቀረቡተጠሪዎች - 1. ወ/ሮ አሰፊ ሳሙኤል 2. ወ/ሮ አስኳል ሳሙኤል 3. ወ/ሮ በላይነሽ ሳሙኤል 4. አቶ ሞገስ ሳሙኤል 5. አቶ ሙለ ሳሙኤል 6. ወ/ሮ ንግስቲ ሳሙኤል 7. ወ/ሮ ምልእተ ሳሙኤል አልቀረቡም 8. ወ/ት ዓይንምሸት ሳሙኤል 9. ወ/ሮ ሃና ሳሙኤል 10. አቶ ሰለሞን ሳሙኤል 11. ወ/ሮ ርግበ ሳሙኤል 12. ወ/ሮ ደሞዝ ሳሙኤል **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የፍርድ አፈፃፀም ክርክርን የሚመለከት ነው። ለዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ በአመልካቾች እና በተጠሪዎች መካከል የነበረው የውርስ ንብረት ክፍያ አፈፃፀም ክርክር በፍርድ አፈፃፀም መዝገብ ላይ ሰኔ 29 ቀን 2000 ዓ.ም ትዕዛዝ ተሰጥቶ የአፈፃፀም
በማቅረባቸው ይህንኑ የሥር ፍ/ቤቶች ተቀብለው ትዕዛዝ መስጠታቸውን በመቃወም አመልካቾች የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በአፈፃፀም በተያዘ ጉዲይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 78 መሰረት ጉዲዩ እንደገና እንዱታይ መደረጉ በአግባቡ መሆን /አለመሆኑን ድንጋጌው ተፈፃሚነት አለው ቢባል እንኳን በጉዲዩ ላይ ትዕዛዝ ከተሰጠ ከአንድ ዓመት በኃላ የቀረበ አቤቱታ ተቀባይነት ማግኘቱ በሥነ ሥርዓት ሕግ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ አኳያ የታየ መሆን /አለመሆኑን እንዱሁም ተጠሪዎች ቀደም ሲል ቀርበው የሚፈለገውን ገንዘብ ከፍለው ንብረቱን ለማስቀረት ዲኝነት ጠይቀው ውሣኔ ያረፈበት ከመሆኑ አንፃር ሲታይ የተጠሪዎች የመከራከር መብት አልተጠበቀም ማለት ይቻላልን? የሚለት ነጥቦች ሉመረመሩ የሚገባቸው ሆኖ ስለተገኙ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ተደርጓል።
የተጠሪዎች ጠበቃ ሚያዚያ 4 ቀን 2002 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። በይዘቱም ተጠሪዎች የተለያየ ቦታ ይኖሩ እንደነበር ጠቅሰው በሥር ፍ/ቤት ቀድሞ የተሰጠው ትዕዛዝ እንደማያውቁትና የቤቱ ስመሀብት በአመልካቾች እንዱመዘገብ የተደረገው በ22/06/2001 ዓ.ም በተሰጠ ትዕዛዝ መሆኑን እና እነሱም ይህንን ያወቁት በ15/10/2001 ዓ.ም እንደሆነና ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ያቀረቡትም በ26/10/2001 ዓ.ም ስለመሆኑ ዘርዝረው አቤቱታ ያቀረቡት ጉዲዩን ባወቁ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ እንደሆነ ተከራክረዋል። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 78/1/ ተፈጻሚነት በተመለከተ ጉዲዩ በአፈፃፀም ላይ ያለ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ አመሳስል በመተርጏም መቀበለ አግባብ ነው በሚል እንዱሁም ቀደም ሲል በአፈፃፀም ሂደት ተጠሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበው ክርክር እንዲላቀረቡ ጠቅሰው የሥር ፍ/ቤት ትዕዛዝ እንዱፀና አመልክተዋል።
አመልካቾች ክርክራቸውን አጠናክረው የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር ከፍ ሲል በአጭሩ የተመለከተው ነው። እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት እልባት ሉሰጠው የሚገባው ጉዲዩ ተጠሪዎች ቀደም ሲል በአፈፃፀም ክርክር እንዱቀርቡ ተደርጓል ወይንስ አልተደረገም? ቀርበው እንዱከራከሩ አልተደረገም ከተባለ በአፈፃፀም ጉዲይ ላይ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.
78 ተፈፃሚነት አለው ወይንስ የለውም? ተፈፃሚነት አለው ከተባለ በሥነ ሥርዓት ሕጉ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተፈጻሚነትን በተመለከተ የሥር ፍ/ቤት ከአንድ አመት በኋላ መቀበለ በአግባቡ ነው ወይንስ አይደለም የሚለትን በየተራ እንመለከታለን።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ አመልካቾች አጥብቀው የተከራከሩት ተጠሪዎች ቀደም ሲል በአፈፃፀም ክርክር ላይ ቀርበው የውርስ ንብረት በዓይነት ለማስቀረት እንዱፈቀድላቸው ጠይቀው ተቀባይነት አጥተዋል። በሂደቱም ተከራካሪ የነበሩ ስለመሆኑ በሥር ፍ/ቤት መዝገብ ተረጋግጧል የሚል ነው።
እኛም የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ከዚህ ፍሬ ነገር አንፃር መርምረናል። የአክሱም ከተማ ፍርድ ቤት በመ/ ለዚህ ሰበር አቤቱታ መነሻ በሆነው ፍርድ ላይ እንዲረጋገጠው ከተጠሪዎች ውስጥ 1ኛ - 4ኛ፣ 6ኛ፣ 8ኛ - 10ኛ እና 12ኛ ተጠሪ በአፈፃፀም ክርክር ላይ በተለያዩ ቀናት ችልት ቀርበው የበኩላቸውን ክርክር ያቀረቡ ስለሆነ ነው የተቀሩት ተጠሪዎችም ጥሪ ተደርጏላቸው እንዲልቀረቡ ፍርድ ቤቱ የአፈፃፀም መዝገብ አስቀርቦ መርምሮ እንዲረጋገጠ በውሣኔው አሰፍሯል።
No topics extracted.
በዚህም መነሻ መሰረት ተጠሪዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 78/1/ መሰረት የአፈፃፀም መዝገቡ በ19/10/2000 ዓ.ም በተሰጠ ትዕዛዝ ተዘግቶ ካደረ በኃላ ተጠሪዎች በ26/10/2001 ዓ.ም ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ሲል ውሣኔ የሰጠው። በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የከፍተኛው ፍ/ቤት ተጠሪዎች ቀደም ሲል ቀርበው የተከራከሩ መሆኑን ፍሬ ነገር በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠውን አንዲችም ምክንያት ሳይሰጥ ሸሮታል።
ከዚህ መረዲት እንደሚቻለው ተጠሪዎች ቀደም ሲል የበኩላቸውን ክርክር አቅርበው ተቀባይነት አጥቶ ያደረ ሆኖ ሳለ እንደአዱስ አቤቱታ ማቅረባቸው አግባብ እንዲልሆነ ነው።
በመሰረቱ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ዓላማ ክርክሮች በተወሰነ ደረጃ እና ጊዜ እንዱቋጭ ማስቻል እንጂ ጉዲዩች ያለገደብ በሙግት ላይ ተንጠልጥለው እንዱቆዩ ማድረግ አይደለም። በዚህም የተከራካሪ ወገኖችን እንዱሁም የፍርድ ቤቱን ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘብ ያለአግባብ ብክነት ማስቀረት ነው።
በተያዘው ጉዲይም ቀደም ሲል ስለውርስ ንብረት ክፍያ አፈፃፀም በ19/10/2000 ዓ.ም ትዕዛዝ ተሰጥቶ ካበቃ በኃላ ተጠሪዎች ከአንድ አመት በኃላ በ26/10/2001 ዓ.ም እንደ አዱስ ተከራካሪ ወገን አቤቱታ ማቅረባቸው እና በሥር ፍ/ቤት ተቀባይነት ማግኘቱ ከሥነ ሥርዓት ሕጉ ዓላማና መንፈስ ውጪ በመሆኑ ተቀባይነት ሉኖረው የሚችል አይደለም።
ስለሆነም ከፍ ሲል እንደተጠቀሰው አብዛኛው ወገን በጉዲዩ ላይ የበኩላቸውን ክርክር ያቀረቡ ሆነው ሳለ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 78/1/ አቤቱታ ማቅረባቸው ተገቢነት የለውም ብለናል።
የተቀሩት ሶስት ተጠሪዎችም ቢሆኑ ክርክሩ የውርስ ንብረት ክፍያን የሚመለከት እንደመሆኑና የሁለም ተጠሪዎች መብት በአንድ መስመር የተወሰነ ከመሆኑ አኳያ ሲታይ ከአብዛኞቹ የተለየ ክርክርና መብት አላቸው የሚባልበት ሁኔታ አልተጠቀሰም። ስለሆነም የከፍተኛው ፍ/ቤት እና የክልለ ሰበር በአክሱም ወረዲ ፍ/ቤት ደረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር ከሕጉ ጋር ሳያገናዝቡ ተጠሪዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 78/1/ መሰረት ሉስተናገደ ይገባል ተብል የተሰጠው ውሣኔ ተገቢነት የለውም ብለናል።
ስለዚህም ጉዲዩ በመጀመሪያው ጭብጥ ብቻ እልባት ያገኘ በመሆኑ ወደተከታዮቹ ነጥቦች መግባትና መመርመር አስፈላጊ አይደለም።
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 182/3/ የመጀመሪያ ዐረፍተነገር ይዘት ይህንኑ ያመለክታል።
በመሆኑም በይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠው ውሣኔ ከሥነ ሥርዓት አኳያ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው ሉታረም ይገባል ብለናል።
በመሆኑም ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የትግራይ ብ/ክ/መ የማዕከላዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ9/2/2002 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ እና የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በ14/03/2002 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የአክሱም ከተማ ፍርድ ቤት በመ/ በ13/12/2001 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ ፀንቷል።
በዚህ መዝገብ ላይ የካቲት 24 ቀን 2002 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይፃፍ።
ግራቀኙ ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል። መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ።