No summary available.
ግንቦት 04 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- መምህርት አታቱ ከበደ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ስቴኘስ አት.ኢደኬሽናል ኃ.የተ.የግል ማህበር - በላለበት የሚታይ ነው **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ አዋጅ ቁጥር 377/1996“ን“ መሰረት አድርጎ የቀረበን የአሰሪና ሰራተኛ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ አመልካች በስቴኘስ ትምህርት ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- ከስቴኘስ ት/ቤት ጋር በመምርነት ስራ ከመሰከረም 1998 ዓ/ም ጀምሮ የስራ ውል ግንኙነት በመመስረት እስከ ጥቅምት 23 ቀን 2002 ዓ/ም ድረስ በወር ብር 1‚050.00 እየተከፈላቸው ሲሰሩ ቆይተው ከህግ ውጪ በተከሳሽ እንደተሰናበቱ ገልጸው የተለያዩ ክፍያዎች እንዱክፍለቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የማያሳይ ነው። የስር ተከሳሽ ለክሱ በሰጠው መልስም አመልካች ተቀጠርኩበት በሚለበት ጊዜ ስቴኘስ ት/ቤት በልላ ሰው ስም የነበረ መሆኑን ገልጾ በጠየቁበት ዘመን በስቴኘስ ት/ቤት እንዲልሰሩ ክሱም ላቀርብ የሚገባው ስቴፔስ አት ኢደኬሽናል ኃ.የተ.የግል ማህበር በመሆኑ እንዱሻሻል በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የገለጸ ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃ ስቴፔስ አት ኢደኬሽናል ኃ.የተ.የግል ማህበር የፈረሰና የተዘጋ መሆኑን ተረጋግጦ በድርሻቸው መልስ እንደሚሰጡ ጠቅሰው ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤትም የባልና ሚስት የጋራ ንብረት የነበረው ትምህርት ቤት ጋብቻው ፈርሶ ሲከፊፈል አመልካች ወደ ሴትየዋ ሄደው መስራቱን መቀጠላቸው መረጋገጡንና ከዚህ በሁዋላም ሴትየዋ አመልካችን አላሰናበትኩም የሚል ክርክር የላለው መሆኑን በመጥቀስ ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ወደሚለው ድምዲሜ ደርሶ ለአመልካች የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፍሎቸው ዘርዝሮ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት ተጠሪ ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ስቴኘስ አት ኢደኬሽናል የተባለ ትምህርት ቤት የንግድ ፈቃደ መሰረዙ መረጋገጡን በመግለፅ አመልካች ክሱን ከትምህርት ቤቱ ስራ አስኪያጅና ከላልች ባለአክሲዮኖች ተነጥለው ሉከሰሱ አይገባም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሽሮታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በስር ፍርድ ቤት ክስ የቀረበበትን ትምህርት ቤትና ስራውን ሲያሰራ የነበረን ትምህርት ቤት ከጋብቻው መፍረስ በሁዋላ የንግድ ፈቃደ ተሰርዟል ከተባለው የስቴኘስ አት ኢደኬሽናል ትምህርት ቤት ጋር አንድ አድርጎ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ መሻሩ የክስ አቅራረቡንና በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠውን ሁኔታ ባግባቡ ሳያገናዝብ በመሆኑ ውሳኔው ሉታረም የሚገባው ነው በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ተጠሪ ድርጅት መደበኛ ስራውን እያከናወነ አይደለም የሚለውን ብቻ በመያዝ ሉከሰስ አይችልም በሚል የሰጠው ውሳኔ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ድርጅት መጥሪያው ተልኮለት ሉቀበል አለመቻለ ተረጋግጦ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል።
የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም በጉዲዩ ላይ የተሰጠውን ውሳኔ በስር ፍርድ ቤት ከተረጋገጠው ፍሬ ነገርና ከሕጉ ጋር አገናዝቦ ጉዲዩን ለሰበር ችልት ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገዝነብ የተቻለው አመልካች ክስ የመሰረቱት ስቴኘስ ት/ቤት በሚል ሲሆን ይህ ትምህርት ቤት ሉከሰስ እንደማይገባ ፣ አመልካች ስራውን የጀመሩት ስቴኘስ አት ኢጁኬሽናለ ኃ.የተ.የግል ማህበር ጋር ሆኖ ይህ ትምህርት ቤት በባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክርክር ምክንያት የተከፊፈለ በመሆኑ ክሱ ላቀርብ የሚገባው በዚሀ ትምርት ቤት መሆኑን የስቴኘስ ት/ቤት ባለቤት ተብለው የተከሰሱት ግለሰብ ጠቅሰው መከራከራቸውን፣ የስር ፍርድ ቤት የባልና ሚስት ንብረት የተከፊፈለ ቢሆንም የአሁኗ አመልካች የመምህርነት ስራውን የሴትዬዋ /ማዲም ፐሽ ፕላታ/ ንብረት በሆነው ስቴኘስ ት/ቤት መቀጠላቸው መረጋገጡን፣ ይህ ትምርት ቤትም አመልካችን አላሰናበትኩም የሚል ክርክር የላለው መሆኑን በፍሬ ነገር ደረጃ አረጋገጦ ለአመልካች የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፍሎቸው የወሰነ መሆኑን ፣ ይህ ውሳኔ በየትኛውም እርከን በሚገኝ ፍርድ ቤት አለመለወጡንና ለስር ፍርድ ቤት የአፈጻጸም አቤቱታ ቀርቦለትም በመ/ በሆነው የአፈጻጸም መዝገብ ተከፍቶ የፍርድ ባለእዲ የሆነው ስቴኘስ ት/ቤት ፍርደን እንዱፈጽም ትዕዛዝ መሰጠቱን፣ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤት ዋናው ፍርድ እንዱፈጸም በሰጠው ትእዛዝ ይግባኝ ቀርቦለት አመልካችንና ስቴኘስ አት.ኢደኬሽናል ኃ.የተ.የግል ትምህርት ቤት የተባለውን በይግባኝ ባይነት አከራክሮ ይኸው ድርጅት የንግድ ፈቃደ መሰረዙ ተረጋግጧል፣ ስራውን ባቆመ ድርጅት ስራ አሰኪያጅ የነበረ በመሆኑ ብቻ ተጠያቂ መሆን የለባቸውም በሚል ምክንያት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን የአፈጻጸም ትዕዛዝ ሙለ በሙለ ሽሮታል። እንግዱህ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ ባይ የተጠቀሰው ድርጅት እና የስር ፍርድ ቤት በዋናው ክርክር ኃላፉ አድርጎ አፈጻጸሙን የቀጠለበት ድርጅት የተለያዩ መሆናቸውን የክርክሩ ሂደት በግልጽ ያሳያል።
No topics extracted.
በመሰረቱ አንድ ፍርድ ሉፈጸም የሚገባው እንደፍርደ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 378 እና ተከታዩቹ ቁጥሮች የተመለከቱትና አፈጻጸምን የሚገዙ ድንጋጌዎች ያሳዩናል። ስለሆነም አንድ የፍርድ አፈጻጸም የሚመራው እንደፍርደ ነው። አንድ ፍርድ እንደፍርደ የማይፈፀመው ፍርደ በይግባኝ ሥርዓት የተለወጠ የሆነ እንደሆነ ወይም ፍርደን ለመፈፀም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 386 መሰረት ሕጋዊ ምክንያቶች ያለ ስለመሆኑ ከተረጋገጠ ነው። ፍርደ ተለውጧል ልባል የሚችለውና ለአፈጻጸም መሰረት ላሆን የማይችለው ደግሞ ዋናው ክርክር ላይ የተሰጠው ውሳኔ ስህተት ነው በማለት ሳይሆን ዋናው ክርክር ላይ የተሰጠውን ውሳኔ በይግባኝ/ሰበር ስርዓት ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት በማስለውጥ ነው። በተያዘው ጉዲይ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤትን የአፈጻጸም ትዕዛዝ የሻረው የንግድ ስራውን ባቆመ ድርጅት ስራ አስኪያጁ ብቻውን ሉጠየቅ አይችልም በሚል ምክንያት ሲሆን ይህ ምክንያት ይዘቱ ሲታይ ከዋናው ፍርድ ይዘት ውጪ የሆነ፣ በዋናው ክርክር ጊዜ ቀርቦ በስር ፍርድ ቤት ተቀባይነት ያጣና በሥርዓቱ መሰረት በበላይ ፍርድ ቤት ያልተለወጠ በመሆኑ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ በዋናው ክርክር የተሰጠውን ፍርድ በአፈፃፀም መዝገብ የሚሽርና አፈጻጸም ከሚመራበት ስርዓት ውጪ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ስለአፈጻጸም የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሰኔ 24 ቀን 2002 ዓ/ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ የተሰጠው የአፈጻጸም ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል። በመሆኑም ይኸው ፍርድ ቤት በዚሁ አፈጻፀም መዝገብ በጀመረው መሰረት አፈጻጸሙን በመቀጠል እንደዋናው ፍርድ እንዱያስፈጽም ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343/1/ መልሰንለታል። ይፃፍ።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ አመልካች የራሳቸውን ይቻለ ብለናል።