No summary available.
ሰኔ 13 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ አሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- ወ/ሮ ኡልባሬ ሰማን - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው።
ክርክሩ የአፈጻጸም ክርክር ነው። የክርክሩ አመጣጥ አመልካች ከአቶ ሁሴን መሐመድ ጋር የነበረውን የብድር ውል አቶ ሁሴን መሐመድ በብድር ውለ መሰረት ያልፈጸሙ መሆኑን ገልጾ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሣኔ ሰጥቷል።
የብድር ውለን በተመለከተ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሣኔ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ ቀርቦ ይግባኝ ሰሚው ችልት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በማሻሻል አቶ ሁሴን መሐመድ ብር 6ዐ1154.55 /ስድስት መቶ አንድ ሺ አንድ መቶ ሀምሣ አራት ብር ከሀምሣ አምስት ሣንቲም/ ለአመልካች እንዱከፍለ ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች ይህንን ፍርድ ለማስፈጸም የአፈጻጸም ክስ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአፈጻጸም ክስ አቅርቧል። የአመልካች የአፈጻጸም ክስ የቀረበለት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት የፍርድ ባለዕዲ ንብረት የሆነውና በአቶ ሁሴን መሐመድ ሚስት በወ/ሮ ከድጃ አወል ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ቁጥሩ 425 የሆነ ቤት ተሽጦ ለፍርድ ማስፈጸሚያ እንዱሆን በአፈጻጸም መዝገብ መጋቢት 4 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ትዕዛዝ ሰጥቷል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ንብረቱ የሚገኝበት የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሻሸመኔ ከተማ በዱዲ ቦቄ ቀበላ የሚገኘውንና ቁጥሩ 425 የሆነውን ቤት በመሸጥ ፍርደን እንዱያስፈጽም ትዕዛዝ ሰጥቷል።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠውን የአፈጻጸም ትዕዛዝ መሰረት በማድረግ የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሻሸመኔ ከተማ በዱዲ ቦቄ ቀበላ የሚገኘውና በወ/ሮ ከድጃ አወል ስም ተመዝግቦ ያለውን ቁጥሩ 425 የሆነው ቤት በሀራጅ እንዱሽጥ ትዕዛዝ ሰጥቶ የሀራጅ ማስታወቂያ ወጥቷል።
ከዚህ በኋላ የአሁን ተጠሪ የሀራጅ ማስታወቂያ የወጣበትን ቤት ከወ/ሮ ከድጃ አወል ሀምላ 6 ቀን 1996 ዓ.ም በተደረገ ውል ገዝተው በእጃቸው አድርገው እየተጠቀሙበት መሆኑን በመግለጽና የቤቱን የሀራጅ ሽያጭ በመቃወም በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 418 መሰረት አቤቱታ አቅርበዋል። የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችንና የተጠሪን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተጠሪ ቤቱን የገዙት በመሆኑ ለፍርድ ማስፈጸሚያ ሉሸጥ አይገባውም በማለት ትዕዛዝ ሰጠ። አመልካች የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቀረበ። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን የአፈጻጸም ትዕዛዝ በመሻር ቤቱ ተሽጦ ለፍርድ ማስፈጸሚያ ሉውል ይገባዋል በማለት ውሣኔ ሰጠ።
ተጠሪ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቀረቡ።፡ ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችንና የተጠሪን ክርክር ሰምቶ ብይን የሰጠው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርደን እንዱያስፈጽም በሰጠው የውክልና ስልጣን ነው። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ብይን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሰጠው ብይን የሚቆጠር በመሆኑ ይግባኝ መቅረብ ያለበት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ነው። ስለዚህ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የላለውን የይግባኝ ስልጣን በመጠቀም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ መሻሩ ተገቢ አይደለም በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል።
አመልካች ጥር 12 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 374 /1/ን በመተርጉም የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው የአፈጻጸም ትዕዛዝ የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 372 /ሐ/ ድንጋጌን ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ መጋቢት 23 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተጻፈ መልስ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ ፍርደን በውክልና የሚያስፈጽም ፍርድ ቤት የሚሰጠው የአፈጻጸም ትዕዛዝ የሚኖረውን ውጤትና በትዕዛዝ ይግባኝ ስለሚባልበት ሁኔታ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር የተደነገጉ ድንጋጌዎችን ያገናዘበ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ተከራክሯል። አመልካች የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አከራክሮ ውሣኔ ላሰጥበት የማይችለውን የተጠሪን ጣልቃገብነት ጥያቄ በመቀበል የሰጠው ውሣኔ ከስልጣኑ ወሰን ያለፈ ነው።
ስለሆነም የውክልና ስልጣኑን በማለፍ የሰጠውን ትዕዛዝ በይግባኝ አይቶ የማረም ስልጣን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው በማለት ሚያዝያ 17 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ተጠሪ በአፈጻጸሙ ሂደት ያቀረቡትን የጣልቃ ገብነት ጥያቄ በመቀበል የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ አይቶ የመወሰን ስልጣን የለውም በማለት ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ሰባተኛ መጽሐፍ ማለትም ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 371 እስከ ፍታብሓር ሥነ ሥዓርት ህግ ቁጥር 455 የተደነገጉትን የሥነ ሥርዓት ህግ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ በኢትዮጵያ ግዛት የተሰጠን ፍርድ የማስፈጸም ስልጣን ፍርደን የሰጠው ፍርድ ቤት ወይም ፍርደን እንዱያስፈጽም የታዘዘው ፍርድ ቤት መሆኑን በዚህ ምዕራፍ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት ፍርድ የሚያስፈጽመው ፍርደን የሰጠው ፍርድ ቤት ወይም እንደፍርደ እንዱያስፈጽም የታዘዘው ፍርድ ቤት ነው በማለት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 371 ንኡስ አንቀጽ 1 በግልጽ ተደንግጓል። ፍርደን ያልሰጠው ፍርድ ቤት በልላ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሣኔ ተከታትል እንዱያስፈጽም ፍርደን የሰጠው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መስጠት የሚችል ስለመሆኑና ፍርደን የሰጠው ፍርድ ቤት ፍርደን ያልሰጠው ፍርድ ቤት አፈጻጸሙን ተከታትል እንዱያስፈጽምለት ትዕዛዝ ላሰጥ የሚችልባቸው ሁኔታዎች በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 372 ተደንግጓል።
ከዚህ በተጨማሪ ፍርደን የሰጠው ፍርድ ቤት ፍርደን ያልሰጠው ላላ ፍርድ ቤት ውሣኔውን ተከታትል እንዱያስፈጽምለት ትዕዛዝ በሚያስተላልፍበት ጊዜ አብሮ ሉገልጻቸውና ሉልካቸው የሚገቡ ጉዲዮች በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 373 የተደነገገ ሲሆን ‛ፍርደን አስፈጻሚው ፍርድ ቤት ስለፍርደ አፈጻጸም የሚሰጠው ትዕዛዝና በትዕዛዙም ይግባኝ ስለሚባልበት ሁኔታ ያለው ስልጣን ዋናውን ፍርድ ከወሰነው ፍርድ ቤት ስልጣን ጋር እኩል ሆኖ ይቆጠራል በማለት የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 374 ንኡስ አንቀጽ 1 ይደነግጋል።
ከላይ ከተገለጹት ድንጋጌዎች ፍርድን በሰጠው ፍርድ ቤት ውሣኔውን ተከታትል እንዱያስፈጽምለት ለላላ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለመስጠት ስለሚችልበት ሁኔታ ትዕዛዙን የሚሰጠው ፍርድ ቤት ሉያሟላቸው ስለሚገቡ ሥነ ሥርዓቶችና ፍርድ እንዱያስፈጽም በልላ ፍርድ ቤት የታዘዘው ፍርድ ቤት በአፈጻጸም ሂደት ስላለው ስልጣን የሚደነግጉ ተያያዥነት ያላቸው ድንጋጌዎች ናቸው። ስለሆነም አመልካች የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 372 ከፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 374/1/ ጋር ተያያዥነት የላለውና ራሱን የቻለ ድንጋጌ ነው በማለት አመልካች ያቀረበው ክርክር ከላይ የተገለጹትን ድንጋጌዎች ይዘት መንፈስና ዓላማ ያላገናዘበና የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
ሆኖም ይህ የተጠሪ ክርክር የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 375 ድንጋጌዎች መሰረታዊ ባህሪና ላልች አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች ያገናዘበ ሆኖ አላገኘነውም። ምክንያቱም በመጀመሪያ ደረጃ የአመልካች ክርክር ፍርድ እንዱያስፈጽም የታዘዘው ፍርድ ቤት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህጉ ሰባተኛ መጽሐፍ በምዕራፍ አንድ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ማለትም ከፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 371 እስከ ፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 455 የተደነገጉትን ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ፍርደን የማስፈጸም ስልጣን እንዲለው በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 371 ንኡስ አንቀጽ 1 የተደነገገውን መሰረታዊ መርህ ግንዛቤ ውስጥ የማያስገባ በመሆኑ ነው።
በሁለተኛ ደረጃ የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 375 በመሰረታዊ ባህሪው ፍርድ እንዱያስፈጽም የታዘዘው ፍርድ ቤት ውሣኔ የሚሰጥባቸውን ጉዲዮች ምንምን እንደሆኑ የሚያመላክት ድንጋጌ /indicative provision of law/ እንጂ ፍርድን እንዱያስፈጽም የታዘዘው ፍርድ ቤት የሚያቸውን ጉዲዮች በሙለ የሚዘረዝር ድንጋጌ /conclusive provision of law/ አለመሆኑ ነው። የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 375 ድንጋጌዎችን አመላካች የህግ ድንጋጌ መሆኑን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 418 ንኡስ አንቀጽ 1 በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት ንብረት እንዲይያዝ ወይም እንዲይከበር የመቃወም አቤቱታ ሲቀርብ ወይም በዚሁ ንብረት ላይ ቀዲሚ መብት አለኝ የሚል ተቃዋሚ አቤቱታ ያቀረበ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ መቃወሚያ ያቀረቡት ወይም እንዱያዝ በታዘዘው ንብረት ላይ ተቀዲሚ መብት አለን የሚለ ወገኖች በመጀመሪያው ክርክር ተካፊይ ባይሆኑም በያዝነው ንብረት ላይ መብት እንዲላቸው በመቁጠር የሚያቀርቡትን መቃወሚያ አቤቱታ ተቀብል መመርመር አለበት በማለት አስገዲጅነት ባለው ሁኔታ ህግ አውጭው የደነገገውን ድንጋጌና ከዚህ በላይ ባለው ንኡስ ቁጥር የተነገረው መቃወሚያ ወይም አቤቱታ የሚቀርበው በጽሁፍ ሆኖ ፍርድን ለሚያስፈጽመው ፍርድ ቤት ነው በማለት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 418 ንኡስ አንቀጽ 2 የተደነገገውን በማየት ለመገንዘብ ይቻላል።
ስለሆነም የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪን በአፈጻጸሙ ጣልቃ በመግባት ያቀረቡትን ክርክርና ማስረጃ በመመርምር ውሣኔ የሰጠው በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 418 ንኡስ አንቀጽ 1 እና ንኡስ አንቀጽ 2ን መሰረት በማድረግ በመሆኑ አመልካች የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 375 በመጥቀስ ያቀረበውን ክርክር አልተቀበልነውም።
በመሆኑም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ እንዱያስፈጽም ያዘዘው የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን የአፈጻጸም ትዕዛዝ በይግባኝ አይቶ የመወሰን ስልጣን የለውም በማለት ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠው ውሣኔ ከላይ የተገለጹትን ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ነው በማለት ወስነናል፡ ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ ጸንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ጥር 24 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል ይጻፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ ለየራሣቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.