No summary available.
ሐምል 25 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ቀደመ ተሾመ - አልቀረቡም።
ተጠሪ፡- አቶ ኢብራሂም ሐመደ - ቀረቡ መዝገቡን መርምርን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 30/3/2002 የሰጠውን ፍርድ በአፊር ብ/ክ/መ/ የአውሲረሱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በውክልና እንዱያስፈፅም በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የክልለ ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዱያስፈጽምላቸው የአሁኑ የሰበር አመልካች የአፈፃፀም ክስ ሲያቀርቡ ከፍተኛው ፍ/ቤት የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት የሰጠው ፍርድ ሂሳብ ሳይጣራ የተሰጠ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ለማስፈፀም ይቸገራል በማለት ባለመቀበል ፍርድ በመስጠቱና ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ፍርድ በማፅናቱ ነው።
የአሁኑ የሰበር አመልካችም በሥር ፍ/ቤቶች ፍርድ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል የሰበር አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡ ሲሆን በዋናነት የጠቀሱትም የቅሬታ ነጥብ በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ የተሰጠው ፍርድ የአፈፃፀም ተከሳሾችን መብትና ጥቅም የሚጏዲ ከሆነ በይግባኝ ወይም በፍ/ሥ/ሥ/ሕጉ በተቀመጠው መሰረት መቃወሚያዎችን በማቅረብ ስህተቱ እንዱታረም ከሚያደርጉ በስተቀር እንዱፈፀም የቀረበውን ፍርድ ሂሳብ ሳይጣራ የተሰጠ ፍርድ ነው በሚል በመተቸት ለማስፈፀም የሚያስቸገር ነው መባለ ተገቢነት የለውም የሚል ነው።
ለሰበር አቤቱታው የአሁኑ ተጠሪ /የሥር 2ኛ የአፈፃፀም ተከሳሽ/ በሰጡት መልስ በሥር ከፍተኛ ፍ/ቤትም ሆነ በክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ፍርድ እና ትዕዛዝ ላይ የተፈፀመ የሕግ ስህተት የለም ሲለ ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ አጥሮ የቀረበ ሲሆን እኛም የሥር ፍ/ቤቶች የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት የሰጠው ፍርድ ባልተጣራና ባልተመረመረ ሂሳብ የተሰጠ በመሆኑ በውክልና አፈፃፀሙን ለመቀጠል የሚያስቸግር ነው ያለት በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 371/1/ መሰረት ፍርድ የሚያስፈጽመው ፍርደን የሰጠው ፍ/ቤት ወይም ፍርደን እንዱያስፈፅም የታዘዘ ፍ/ቤት ነው። ፍርደን የሰጠው ፍርድ ቤት ፍርደን እንዱያስፈፅም ለላላ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በሰጠ ጊዜም እንዱያስፈፅም የታዘዘው ፍርድ ቤት ስለ ፍርደ ትክክለኛነት ወይም በግልባጮች ላይ ስለሰፈረው ነገር ላላ መግለጫና ማብራሪያ ሳይጠይቅ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ማስፈፀም እንዲለበት የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 373/2/ ይደነግጋል። ፍርድ እንዱያስፈጽም የታዘዘው ፍ/ቤትም ፍርደን የፈረደው ፍ/ቤት ማረጋገጫ እንዱልክለት የሚጠይቀው የፍርደ ወይም የትዕዛዙ ወይም የግልባጩ ትክክለኛነት የሚያጠራጥር ስለመሆኑ በቂ ምክንያት ካለው ብቻ ነው።
በዚህ በተያዘው ጉዲይ ግን ፍርደን እንዱያስፈፅም የታዘዘው የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ከዚህ በላይ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 373/2/ ከተደነገገው ውጪ ፍርደን የፈረደው ፍ/ቤት የሰጠውን ፍርድ በአግባቡ ሂሳብ ሳይጣራና ሳይመረመር የተሰጠ ነው በማለት በመተቸት ማብራሪያ መጠየቁና የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይኸንኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ፍርድ ማጽናቱ መሰረታዊ የሆነ የሥነ ሥርዓት ሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው። በመሆኑም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የሥር የአውሲረሱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአፈ/መ/ቁ 1917 በቀን 02/11/2002 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ እና የክልለ ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ 2155 በቀን 21/6/2003 የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
የሥር የአውሲረሱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በዚህ ጉዲይ የሰጠውን ፍርድ እንዱያስፈፅም በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት እንዱያስፈፅም በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343/1/ ክርክሩን መልሰናል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ የተዘጋ ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.