No summary available.
ሰኔ 15 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ አሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ዓለም ባህታ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- ወ/ሮ ኑኑሽ ሸህምል - አልቀረቡም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለውን ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ አመልካች ተሰጠ የተባለውን የፍርድ አፈጻጸም አደናቅፍአል በማለት የፋ/የመ/ደረጃ/ፍ/ቤት በአምስት ወር እስራት እንዱቀጣ መወሰኑና ይሄው ውሣኔ በፋ/ከ/ፍ/ቤት በመጽናቱ የቀረበ ቅሬታ ነው።
አመልካች በተፈረደበት የፍርድ አፈጻጸም ማሰናከል ቅጣት ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል ያለውን ታህሣስ 14 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው ቅሬታ ያመለከተ ሲሆን መሰረታዊ ፍሬ ሃሣቡ አመልካች አፈጻጸም በማሰናከል ከዚህ በፉት በ5 ወራት የእስራት ቅጣት የተቀጣ ሲሆን ይሄ ውሣኔ ይግባኝ ቀርቦበት በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በመ/ቁ. 73402 የተሻረ ሆኖ እያለ አዱስ ፍሬ ነገር ሣይኖር እንደገና በዚህ ጉዲይ ፍርድ አሰናክሎል በማለት ቅጣት መጣለ ያለአግባብ ነው አመልካችም የፈጸሙት የማሰናከል ተግባር ባለመኖሩ እና አመልካቹ ላይ የተጣለውም ቅጣት የከበደ በመሆኑ የተሰጠው ቅጣት እንዱሻርልን በማለት የቀረበ ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ በተጠሪ ጠበቃ በኩል በመጋቢት 5 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተጻፈ መልስ፡- ቀድሞ የተቀጣበት የፍርድ አፈጻጸም ማሰናከል ጉዲይ ከአሁን ጋር የማይገናኝ በመሆኑና በውሣኔ ያለቀ ጉዲይ የማይባል በመሆኑ ፣ በዚህ ጉዲይ ላይ የፍርድ ማሰናከል ተግባር ተፈጽሟል እና የተጣለበት ቅጣትም የከበደ ባለመሆኑ የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል።
በግራ ቀኙ የተደረገው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የቀረበውን ክርክር ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል።
እንደመረመረውም በዚህ ጉዲይ ላይ መፍትሄ ማግኘት ያለበት፡-
በዚሁ መሰረት ወደ መጀመሪያው ጭብጥ ስንመለስ አሁን ለዚህ ክርክር መነሻ ከሆነው ቅጣት በፉት አመልካች በፍርድ ማሰናከል ተግባር ኃላፉ ተብለው በአምስት ወር እስራት የተቀጡ የነበርና ጉዲዩ በይግባኝ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርቦ በመዝገብ የተሻረ መሆኑን ግራቀኙ አልተካካደም። አከራካሪው ጉዲይ ቀድሞ ከተጣለው ቅጣት በኋላ አዱስ የማሰናከል ተግባር ስላልተፈጠረ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 መሰረት አዱስ ኃላፉነት ሉጣል አይገባም በማለት የአመልካች ጠበቃ ሲከራከሩ በተጠሪ በኩል ደግሞ በቀድሞው የፍርድ ማሰናከል ተግባር ኋላፉ የተደረጉበት ምክንያት ከአሁኑ ጋር የተለየ በመሆኑ ጉዲዩ በውሣኔ የተቋጨ ነው ለማለት የማይችል ባለመሆኑና በሁለቱም ጊዜ ሉያዝ የሚገባው ጭብጥ የተለያየ በመሆኑ ውሣኔ ያገኘና የተቋጨ ጉዲይ ነው ለማለት የሚቻል አይደለም የሚል ነው።
አሁን እየቀረበ ካለው ክርክር አኳያ ጉዲዩን ስንመረምረው የቀድሞው የፍርድ ማሰናከል ኃላፉነት በአመልካች ላይ የተወሰነው ለፍርድ አፈጻጸም እንዱውል የታገደው የሰላዲ ቁ. 3-27755 የሆነ መኪና አመልካች በቃለ መሀላ ስር ሆነው መኪናውን ገዝተው እንዲላቸው ከገለጸ በኋላ መኪናውን በወ/ሮ ደብሪቱ ውክልና ነው የገዛሁት በማለታቸው እንደሆነ የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔ ያስረዲል። በአሁኑ ጉዲይ ግን በልላ ችልት ተጠይቀው ከላይ የተጠቀሰውን መኪና ከአቶ ተስፊዬ ሞላ የገዙት መሆኑን እንደገና የገለጸ ሲሆን በዚህ መሰረት እንዱፈጽሙ ሲጠየቁ ግዢውን አፍርሽያለሁ ያፈረስኩትም ስመንብረቱን ወደ ራሴ ስም ማዛወር ስላልቻልኩ ነው ከሻጭ ወኪል 100.000 /አንድ መቶ ሺህ/ ብር ተቀብዬ መኪናውን መልሼለታለሁ የተቀበልኩትንም ገንዘብ ተጠቅሜበታለሁ በማለት በማቅረቡ እንደሆነ ተረድተናል።ከዚህ መረዲት የሚቻለው አሁን ለቀረበው ጉዲይ አመልካች ገዝቶ የነበረውን መኪና የተሰጠው እግድ ሳይነሣ መኪናውን ለሻጭ በመመለስ የገዛበትን ገንዘብ መልሶ የተቀበለ ሲሆን ገንዘቡንም ተጠቅሜበታለሁ ማለቱ ከቀድሞ ጉዲይ ጋር አንድ ዓይነት ጭብጥ የሚያዝበት ባለመሆኑ ጉዲዩ ቀድሞ በፍርድ ያለቀ ነው ልባል አይችልም ብለናል።
No topics extracted.
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ በመኪናው ላይ የተላለፈው እግድ ሣይነሣ አመልካች መኪናውን ገዝቶ እያለ ስመ ንብረቱ ወደ እሱ ያለመዞሩን አጋጣሚ በመጠቀም መኪናውን ለሻጭ በመመለስ የገዛበትን ገንዘብ መቀበለን ገልጿል። መልሶ በተቀበለው ገንዘብ ላይ አፈጻጸሙ እንዲይቀጥል /እንዲይከፍል/ ደግሞ ተጠቅሞበታል ወይም ገንዘቡ የለም ማለቱ የፍርድ ባለዕዲው ለአፈጻጸሙ የታገደውን መኪና ከማሸሹም በላይ ቢያንስ የተቀበለውን ገንዘብ እንኳ ለዕዲው አለማቅረቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 389/1/ /ሀ/ /ለ/ መሰረት ያለበቂ ምክንያት ፍርደን ላለመፈጸም ከመንቀሣቀሱ በላይ ፍርደ ያልተፈጸመው አመልካች ፍቃደኛ ባለመሆኑ ብቻ የተለያዩ መሰናክልችን በመፍጠሩ መሆኑን ያረጋግጣል። በመሆኑም አመልካች የፍርደን አፈጻጸም አላሰናከልኩም በማለት ያነሱት ክርክር ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ሶስተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡- በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ 389 /1/ /ለ/ መሰረት እስከ 6 /ስድስት/ ወር ሉደርስ በሚችል እስራት ሉቀጣ እንደሚችል ስለሚደነግግ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው ፍ/ቤት የጉዲዩን አጠቃላይ ሂደት በማመዛዘን በ 5 ወራት እስራት የቀጣው መሆኑ ሲታይ የከበደ ቅጣት ነው የሚያሰኝ ባለመሆኑ የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ባጠቃላይ ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች የበታች ፍ/ቤቶች አመልካች የፍርድ አፈጻጸም አደናቆፍአል በማለት የሰጡት የእስራት ቅጣት መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝ/ቁ. 89236 በቀን 26-01-2003 ዓ.ም እና የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በመዝ/ቁ. 115299 በቀን 13-5-02 ዓ.ም በዋለት ችልት የሰጡት ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
አመልካች የፍርድ አፈጻጸም አደናቅፈዋል በማለት የተላለፈባቸው የ5 ወራት የእስራት ቅጣት በአግባቡ በመሆኑ የሚነቀፍ አይደለም ብለናል።
በዚህ ችልት የካቲት 16 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በዋለው ችልት የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።ለሚመለከተው ይጻፍ ብለናል።
በዚህ ችልት በግራቀኙ ላይ ለደረሰው ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡን ዘግተናል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።