No summary available.
ሰኔ 15 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- 1- አቶ ብርሀን ገ/እግዚአብሓር 2- ወ/ሮ አልጋነሽ ገ/እግዚአብሓር 3- ወ/ሮ ዝማም ገ/እግዚአብሓር 4- ወ/ሮ ሙለ ገ/እግዚአብሓር 5- ወ/ሮ አልማዝ ገ/እግዚአብሓር 6- ወ/ሪት ገነት ገ/እግዚአብሓር 7- የአቶ አበበ ገ/እግዚአብሓር ወራሾች /ወ/ሪት ትከሻዬ አበበ ና አቶ ዮሐንስ አበበ 8- ወ/ሪት ሉንዲ ገ/እግዚአብሓር - ቀረቡ 9- ወ/ሮ ምፅላል ገ/እግዚአብሓር 1ዐ- ወ/ሮ ፅጌወይኒ ገ/እግዚአብሓር 11- አቶ ሀይለ ገ/እግዚአብሓር 12- አቶ ግዛቸው ገ/እግዚአብሓር ተጠሪ፡- ወ/ሮ ለታይ ገ/ጊዮርጊስ ጠበቃ አቶ ደረጀ ወረቁ ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
1ኛ እስከ 7ኛ ተራ ቁጥር ለተጠቀሱት ጠበቃ አቶ ደስታ በርሄ ቀረቡ ከዘጠነኛ እስከ አስራ ሁለተኛ ቀረቡ የተጠቀሱት ወኪል አንደኛ ተጠሪ
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት የአፈፃፀም ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ የአፈፃፀም ክርክር ነው። የክርክሩ መነሻ በቦላ ክፍለ ከተማ በቀድሞው ወረዲ 17 ቀበላ 24 የቤት ቀጥር 166 ሥር የመኖሪያ ቤትና መጋዘን ያለ ሲሆን መኖሪያ ቤቱ የአመልካቾች አውራሽና የተጠሪ የጋራ ሃብት መሆኑ በፍርድ የተወሰነ ሲሆን መጋዘኑ የአመልካቾች አውራሽ የግል ንብረት መሆኑ ተወስኗል።
አመልካቾችና ተጠሪ የሚከራከሩት በግቢው ውስጥ የሚገኘው ባድ ቦታ የመኖሪያ ቤቱ ነው ወይስ የመጋዘኑ ነው በሚለው ነጥብ ላይ ነው። አፈፃፀሙን የያዘው የሥር ፍርድ ቤት የቦላ ክፍለ ከተማ ቦታው በባለሙያ እንዱታይ ካደረገ በኋላ ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት ቦታ የሚጠቃለለው ወደ መኖሪያ ቤቱ መሆኑን ወይም ወደ መጋዘኑ መሆኑን ወይም መኖሪያ ቤቱና መጋዘኑ የየራሳቸው ይዞታ ካላቸው የይዞታቸውን ስፊት ምን ያህል መሆኑን ለይቶ የእስኬች ማብራሪያ እንዱልክ ትዕዛዝ ሰጥቷል። የቦላ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዲደር ጽ/ቤት ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት ቦታ ለመጋዘን ይሁን ለመኖሪያ ቤቱ ለማሳወቅ የሚቸገር እንደሆነና ቀደም ሲል በነበረው ካርታ ይዞታው ተለይቶ ያልተቀመጠ መሆኑንና ለአመልካቾች አውራሽ 1973 ዓ.ም ቦታው የተሰጣቸው የመኖሪያ ቤት በመሥራት እንዱገለገለበት መሆኑን በመግለፅ ምላሽ ሰጥቷል።
የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና የቀረበለትን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ባድ ቦታው ወደ መኖሪያ ቤቱ እንዱጠቃለልና አፈፃፀሙ እንዱቀጥል ትዕዛዝ ሰጥቷል። አመልካቾች በዚህ ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ አፅንቶታል።
አመልካቾች ፍርደን የሚያስፈፅመው ፍርድ ቤት ተጨማሪ ማብራሪያ መጠየቅ አልነበረበትም መጋዘኑ ኤል ሼኘ በመሆኑ ቦታውን ለአመልካቾች ማስረከብ ነበረበት። መጋዘኑ የተሰራው 1973 ዓ.ም ሲሆን የመኖሪያ ቤቱ የተሰራው 1978 ዓ.ም ነው። ተጠሪ በመ.
ባቀረቡት ክስ ቦታው የመጋዘኑ አካል መሆኑን በማመን ገልፀው እያለ በፍርደ መሰረት ባድ ቦታውን በእጅ ማስረከብ ሲገባው ከመኖሪያ ቤቱ ጋር እንዱጠቃለል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ህዲር 24 ቀን 2003 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። ተጠሪ በበኩላቸው መጋቢት 2 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተፃፈ መልስ የሥር ፍርድ ቤት ጉዲዩን በባለሙያ በኩል እንዱጣራ በማድረግ የሰጠው ትዕዛዝ የህግ ስህተት የለበትም በመዝገብ የአጥር ግንባታ የተገነባበትን ግምት ከሚጠይቅ ውጭ ስለቦታ የቀረበ ክርክርና የተሰጠ ውሣኔ የለም። የአመልካቶች አቤቱታ የበታች ፍርድ ቤቶች መሰረታዊ የህግ ስህተት የፈፀመ መሆኑን የማያሣይ ከመሆኑም በላይ ዕውነታውን የሚያንፀባርቅ አይደለም በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካቾች መጋቢት 17 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የአፈፃፀም ትዕዛዝ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካችና ተጠሪ የሚከራከሩት የመኖሪያ ቤቱና መጋዘኑ ከተሰራበትና በአንድ ካርታ በተጠቃለለው ይዞታ ቦታ ላይ የሚገኘው ባድ ቦታ የመኖሪያ ቤቱ ነው ወይስ የመጋዘኑ ነው በሚለው ነጥብ ላይ ነው። አመልካቾች ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት ባድ ቦታ በመጋዘኑ ሉጠቃለል እንደሚገባ ውሣኔ እንደተሰጠበት በማንሣት የሚከራከሩ ቢሆንም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ውሣኔ የሰጠው መጋዘኑ የአመልካች አውራሽ የግል ንብረት መሆኑን እንጅ በግቢው የሚገኘው ባድ ቦታ ከመጋዘኑ ጋር ሉጠቃለልና ለአመልካቾች ላሰጥ የሚገባው መሆኑን አልወሰነም። በልላ በኩል በመዝገብ ተጠሪ ከጋብቻ በኋላ አጥር በማጠር ወለል ሉሾ በማድረግ ያወጡትን ገንዘብ ጠይቀው ውሣኔ የተሰጠበት ሲሆን የባድ ቦታ ክርክር አቅርበው የተወሰነ ውሣኔ የላለ መሆኑን ተገንዝበናል።
No topics extracted.
አመልካችና ተጠሪ የሚከራከሩበት ቦድ ቦታ ከዚህ በፉት በፍርድ ያልተወሰነ በመሆኑ ፍርደን በማስፈፀሙ ሂደት ቦታው መጠቃለል ያለበት ከመኖሪያ ቤቱ ጋር ነው ወይስ ከመጋዘኑ ጋር የሚለው ጥያቄ ሲነሳ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የቦላ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዲደር ቦታውን በማየት ካርታውን በመመርመር መግለጫ እንዱሰጥበት አድርጓል። በዚህ መሰረት ቦታው የመጋዘኑ ነው ወይም የመኖሪያ ቤቱ ነው ብል ለመለየት ያልተቻለና በካርታውም ላይ ያልተመለከተ መሆኑ ተረጋግጧል። በልላ በኩል የአመልካቾች አውራሽ በ1973 ዓ.ም ቦታውን የተመሩት ለመኖሪያ ቤት አገልግልት መሆኑን የቦላ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዲደር ጽ/ቤት ያረጋገጠ በመሆኑ ተጠሪ ከመኖሪያ ቤቱ ጋር እንዱጠቃለል ትዕዛዝ ሰጥቷል። ፍርደን የሚያስፈፅመው ፍርድ ቤት ፍርደን ለማስፈፀም ተስማሚ ነው ብል የሚገምተውን ትዕዛዝ የመስጠት ሥልጣን ያለው መሆኑን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 392 ንዐስ አንቀፅ 1 ተደንግጓል። የከፍተኛ ፍርድ ቤት በዚህ ድንጋጌ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት የአመልካቾች አውራሽ ቦታውን የመኖሪያ ቤት ለመሥራት የተመሩት መሆኑን ከክፍለ አስተዲደር የቀረበለትን ማረጋገጫ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ቦታው ወደ መኖሪያ ቤቱ እንዱጠቃለል የሰጠውን ትዕዛዝ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ማፅናቱ ስለፍርድ አፈፃፀም በተለይም የፍታብሓር ሥነ ሥርዐት ሕግ 392 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌን መሰረት በማድረግ የተሰጠና መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።