No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 4ዐ945 ጥር 13 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ኮልኔል ግርማ ኃይለሥላሴ - ወኪል ስርጉት በላይ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አስማማው መንግሥቱ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ከሁለት የፍርድ ባለመብቶች መካከል አንደ የፍርድ ባለእዲን ንብረት ቀድሞ ተረክቧል ልባል የሚችልበትን የሥነ ሥርዓት አግባብ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች በአስከፈቱት የአፈፃፀም መዝገብ ነው።
የክርክሩ መነሻና ይዘትም የሚከተለው ነው። አመልካች አቶ ፍስሐ ወረታ የተባለት ግለሰብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አ.አ ቅርንጫፍ ለከባድ የጭነት መኪና መግዣ ብር 291,1ዐዐ.ዐዐ/ ሁለት መቶ ዘጠና አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር/ ሲበደሩ ዋስ በመሆን በአዱስ አበባ ከተማ በድሮው አጠራር ወረዲ 16 ቀበላ 12 / ባሁኑ አጠራር የካ ክፍለ ከተማ ቀበላ 13/14/ ክልል ውስጥ የሚገኝ ቪላ ቤታቸውን በመያዣ ሰጥተው የነበረ ሲሆን ዋናው ተበዲሪ የብድር ገንዘቡን መክፈል ባለመቻላቸው ባንኩ ከአሁኑ አመልካች የያዘውን መያዣ በመሸጥ አመልካች የዋናውን ተበዲሪ እዲ ዋናውን ገንዘብ ከእነ ወለደ ጨምረው ብር 316,3ዐዐ.ዐዐ /ሶስት መቶ አስራ ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ብር/ ለባንኩ ከፍለዋል፣ ባንኩም ይህንኑ አረጋግጦ ለአመልካች ደረሰኝ ሰጥቷል። ከዚህም በኋላ የአሁኑ አመልካች በአቶ ፍስሐ ወረታ ላይ በዋስትናቸው የከፈለትን ገንዘብ እንዱተኩላቸው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክስ አቅርበው ለባንኩ የከፈለትን ገንዘብ ዋናው ተበዲሪ እንዱተካላቸው ፍርድ አግኝተዋል። ይህንኑ ፍርድ መሰረት በማድረግ የአፈፃፀም መዝገብ ከፍተው ፍ/ቤቱ ጉዲዩን መመልከት ጀምሮ የፍርድ ባለእዲ የሆኑትን ግለሰብ /አቶ ፍስሐ ወረታ/ እንደፍርደ እንዱፈጽሙ፣ ወይም የማይፈጽሙበትን ምክንያት ካለ ይህንኑ እንዱያስረደ ተደርጎ ባለእዲው ለአመልካች ገንዘቡን ሉተኩላቸው ወይም ንብረት ካለ እንዱጠቀሙ ሲጠየቁ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የአሁኑ አመልካች የአቶ ፍስሐ ወረታን ንብረት አፈላልገው አፈፃፀሙን ለያዘው ፍርድ ቤት እንዱገልፁ ተደርጎ አመልካች የፍርድ ባለእዲ ባለቤት በሆኑት ወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል ስም የተገዛ ቤት ነው የሚለትን ለፍርድ ቤቱ ገልፀዋል። ፍርድ ቤቱም አመልካች የጠቆሙት ቤት በወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል ስም የሚታወቅ መሆኑን የሚመለከተው አካል አጣርቶ ለፍርድ ቤቱ ውጤቱን እንዱልክ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቶ ጉዲዩ ይመለከተዋል የተባለው የየካ ክፍለ ከተማ ቀበላ 19 አስተዲደር ጽ/ቤት ቤቱ በእርሱ በኩል የማይታወቅና ማህደር የላለው በመሆኑ እንደፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ለመፈፀም የማይችል መሆኑን ገልጿል። የአሁኑ አመልካች ቤቱ የፍርድ ባለእዲው ባለቤት ለመሆኑ ማስረጃ አለኝ በማለትም ግንቦት 11 ቀን 1994 ዓ.ም ተደርጓል ያለትን የሽያጭ ውል አቅርበዋል። የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ጉዲዩን መመርመሮ አለ የተባለው የሽያጭ ውል በሕጉ አግባብ የተደረገ አይደለም፣ የባለእዲው ባለቤት በሻጮች ስም ተተክተው የተመዘገቡና ባለሀብት ስለመሆናቸው አልተረጋገጠም በሚል ምክንያት አለ በተባለው ቤት አፈፃፀሙ ሉቀጥል አይገባም ሲል የአመልካችን አፈፃፀም የፍርድ ባለእዲ ንብረትን አፈላልገው ባቀረቡ ጊዜ የማንቀሣቀስ መብታቸውን በመጠበቅ መዝገቡን ዘግቶታል። አመልካች በዚህ ትእዛዝ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው አመልካችና አቶ ፍስሐ ወረታ ከተከራከሩ በሁዋላ ቤቱ የጨረቃ ቤት በመሆኑ ብቻ በሐራጅ ከማሸጥ የሚከለክል ሕግ የለም በሚል ምክንያት የስር ፍርድ ቤትን ትእዛዝ ሽሮ አፈፃፀሙ አመልካች አለ ባለት የአቶ ፍስሐ ወረታ ባለቤት ቤት ላይ እንዱቀጥል በመ/ ህዲር 19 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ውሣኔ ሰጥቷል። ከዚህ በሁዋላ የአሁኑ ተጠሪ አፈፃፀሙ ይቀጥልበት የተባለው የወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል ቤት ከተጠሪ በነበረባቸውና በፍርድ ቤት በተረጋገጠው እዲ ምክንያት የተረከቡትና የርክክቡ ስምምነትም በፍርድ ቤት የተመዘገበበት ነው በማለት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ እንዱሰርዝላቸው የተቃውሞ አቤቱታቸውን በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 358 መሰረት ለከፍተኛው ፍ/ቤት አቅርበው ከአሁኑ አመልካች ጋር እንዱከራከሩ ከተደረገ በሁዋላ ተጠሪ ከአመልካች ቀድመው አከራካሪውን ቤት በእዲ ምክንያት ከወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል የተረከቡት መሆኑ ተረጋግጧል በሚል ምክንያት የቀድሞውን ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 36ዐ/2/ መሰረት በመሰረዝ ታህሣሥ 24 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በዋለው ችልት ውሣኔ ሰጥቶታል። የአሁኑ አመልካች በዚሁ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የከፍተኛ ፍርድ ቤት አፈፃፀሙ በቤቱ ሉቀጥል አይገባም በማለት የሰጠው ውሣኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
No topics extracted.
በበኩላችን አመልካች ጥቅምት ዐ7 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በተፃፈው ማመልከቻ ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ መሰረት በማድረግ ለተጠሪ ጥሪ አድርገን ክርክሩን በፅሐፍ ሰምተናል፣ ለጉዲዩ አግባብነት አላቸው የተባለትን የበታች ፍርድ ቤቶችን ዋና መዛግብትም በማስቀረብ የክርክሩን አጠቃላይ ሂደት ተመልክተናል። በዚህም መሰረት አመልካች የፍርድ ባለእዲ ባለቤት ስለመግዛታቸው በማረጋገጥ አፈፃፀሙ በቤቱ እንዱቀጥል ያቀረቡት አቤቱታ የአሁኑ ተጠሪ በቤቱ ላይ ቅድሚያ መብት አላቸው ተብል ውድቅ የተደረገው ባግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 74ዐ5 በሆነው መጋቢት ዐ9 ቀን 1994 ዓ.ም ክስ የመሰረቱ ሲሆን ሐምል 12 ቀን 1996 ዓ.ም በዋለው ችልት ሉፈፀም የሚችል ፍርድ በአቶ ፍስሐ ወረታ ላይ ያስፈረደ መሆኑን፣ ይኸው ፍርድ እንዱፈፀምላቸው ፍርደን ለሰጠው ፍርድ ቤት ጥቅምት 16 ቀን 1997 ዓ.ም የተፃፈ ማመልከቻ አቅርበው የአፈፃፀም መዝገብ ቁጥር 23ዐ51 ማስከፈታቸውን፣ አፈፃፀሙን፣ የያዘው ፍርድ ቤትም ለፍርድ ባለእዲ እንደፍርደ እንዱፈጽሙ፣ የማይፈጽሙበት ምክንያት ካለም ቀርበው እንዱያስረደ ትእዛዝ ሰጥቶ የፍርድ ባለእዲ የሆኑት አቶ ፍስሐ ወረታ ፍ/ቤት ቀርበው እንደፍርደ ለመፈፀም የማይችለ መሆኑን ከመግለጽ ውጭ እንደፍርደ ላለመፈፀምያቀረቡት ምክንያት የላለ መሆኑን ፍ/ቤቱ ገልጾ አፈፃፀሙ ከቀጠለ በሁዋላ የአሁኑ አመልካች የፍርድ ባለእዲ ንብረትን በማፈላለግ አሁን አከራካሪ የሆነው ንብረት እንዱከበርላቸው አቤቱታ አቅርበው አፈፃፀሙን የያዘው ፍርድ ቤትም የፍርድ ባለመብት የሆኑት የአሁኑ አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት በየካ ክፍለ ከተማ ቀበላ 19 ክልል ውስጥ የሚገኝ ቁጥር የላለው የፍርድ ባለእዲ ባለቤት በሆኑት የወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል ስም የሚገኝ ቤት ተከብሮ እንዱቆይ በማለት ጥቅምት ዐ8 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችልት ትእዛዝ ሰጥቶ እንደትእዛዙ እንዱፈጽም ለክፍለ ቀበላ ትእዛዙን ሲልክ የክፍለ ቀበላ ቤቱ የለም በማለት ጥቅምት 16 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ ደብዲቤ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል። ፍርድ ቤቱን የፍርድ ባለመብት የሆኑት የአሁኑ አመልካች ማስረጃ ካላቸው እንዱያቀርቡ እና የፍርድ ባለእዲውም አስተያየት እንዱሰጡበት ከአደረገ በሁዋላ የፍርድ ባለመብት በቤቱ ላይ አፈፃፀሙ እንዱቀጥል ያቀረቡት አቤቱታ ቤቱ የጨረቃ ቤት ነው ስለተባለ ተቀባይነት የለውም በማለት ሚያዚያ 17 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችልት ትእዛዝ ሰጥቷል።
የአሁኑ ተጠሪ በአከራካሪው ቤት ባለመብት ሁኜበታለሁ የሚለበት መንገድ የመነጨው በሁለት መዛግብት ሲሆን አንደ፡- በፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መ/ መስከረም 2ዐ ቀን 1997 ዓ.ም በወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል ላይ በመሰረቱት ክስ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አከራክሮ ሚያዚያ ዐ9 ቀን 1998 ዓ.ም በዋለው ችልት ተከሣሽ የነበሩት ወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል ለአሁኑ ተጠሪ ብር 23,752.55 /ሐያ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሣ ሁለት ብር ከአምሣ አምስት ሣንቲም/ ፍርድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ተከፍል እስከሚያልቅ ድረስ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍለ አስወስነው ይኸው ፍርድ እንዱፈፀምላቸው ሰኔ ዐ9 ቀን 1998 ዓ.ም የተፃፈ የአፈፃፀም ማመልከቻ አቅርበው የአፈፃፀሙ ጉዲይ በፋዳራለ የመ/ደ/ፍ/ቤት መ/ በሆነው ተከፍቶ አሁን እያከራከረ ባለው ቤትም ተጠሪ የእግድ ትእዛዝ ታህሣሥ 1ዐ ቀን 1999 ዓ.ም በፍርድ ቤት አሰጥተው ጉዲዩ እየታየ ባለበት ሂደት ግራ ቀኙ ወገኖች ጉዲዩን ግንቦት 25 ቀን 1999 ዓ.ም አቅርበው ፍርድ ቤቱ በእርቅ ስምምነቱ መሰረት አፈፃፀሙ ማለቁን ተገንዝቤአለሁ በማለት የአፈፃፀሙን መዝገብ ሰኔ 22 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችልት ዘግቶታል። ላላው ተጠሪ በወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል ላይ ፍርድ ያገኙ ስለመሆኑ ያሣያል የተባለው ጉዲይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ የታየው ሲሆን ተጠሪ ክስ የመሰረቱት መጋቢት 24 ቀን 1999 ዓ.ም ሁኖ ጉዲዩ ሲታይ ቆይቶ ግራ ቀኙ ሰኔ 18 ቀን 1999 ዓ.ም ጉዲዩን በስምምነት ጨርሰናል በማለት ስምምነቱ በፍርድ ቤቱ እንዱፀድቅላቸው አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱም በስምምነቱ መሰረት ወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል ለአሁኑ ተጠሪ ብር 52,769.73 /ሃምሣ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ስልሣ ጠዘኝ ብር ከሰባ ሶስት ሣንቲም/ በመክፈል መዝገቡ እንዱዘጋላቸው ግራ ቀኙ መስማማታቸውን ገልፀው አቤቱታ አቅርበዋል፣ ስምምነቱም ለሕግና ለሞራል ተቃራኒ አለመሆኑ ተረጋግጧል የሚል ምክንያት በመያዝ ስምምነቱን በማጽደቅ ሰኔ 22 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችልት ውሣኔ ሰጥቷል። ተጠሪ ግንቦት 25 ቀን 1999 ዓ.ም ከወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል ጋር አድርጌአለሁ የሚለት የእርቅ ስምምነት ቤቱን ለሁለም እዲዎች ስለመረከቤ ያረጋግጣል የሚለት ነው። ይህ ችልትም ከላይ ከተጠቀሱት መዛግብት በፍሬ ነገር ደረጃ በተረጋገጡት ነጥቦች መሰረት ጉዲዩን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ ተመልክቷል።
በመሰረቱ ፍርድ እንደፍርደ መፈፀም ያለበት ስለመሆኑ የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ ቁጥር 378 እና ተከታዩቹ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ያሣያል። በአንድ የፍርድ ባለእዲ ንብረት ላይ አፈፃፀሙን የቀጠለ ተራ የፍርድ ባለመብቶች ካለም ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 4ዐ3 ድንጋጌ መሰረት ምላሽ ሉያገኝ እንደሚችል ሕጉ ያሣያል።
እጃችን ወዲለው ጉዲይ ስንመለስም ተጠሪ ሰኔ 22 ቀን 1999 ዓ.ም በፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መ/ ተሰጠ የሚለት ትእዛዝ ሰኔ 18 ቀን 1999 ዓ.ም ከወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል ጋር ያደረጉትን ስምምነት ለሕግ እና ለሞራል ተቃራኒ አለመሆኑን በማረጋገጥ ፍርድ ቤቱ አጽድቆታል የሚለት ሲሆን ፍርድ ቤቱ የመዘገበው ትእዛዝ የሚያሣየው ወ/ሮ አበበች ለአሁኑ ተጠሪ የክርክሩ ምክንያት የሆነውን ገንዘብ የከፈለ መሆኑን እንጂ ለሚፈለግባቸው ገንዘብ አሁን እያከራከረ ያለውን ቤት ለማስረከብ ተስማምተው፣ ስምምነቱም ለሕግና ለሞራል ተቃራኒ አይደለም ተብል የተመዘገበ አለመሆኑን ነው። ተጠሪ በመ/ ባስከፈቱት የአፈፃፀም መዝገብ ሰኔ 22 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችልት የተሰጠው ትእዛዝም ቢሆን እርቁን የመዘገበ ሣይሆን አፈፃፀሙ በእርቅ መሰረት መፈፀሙ ተረጋግጧል በማለት የፍርድ አፈፃፀም መመሪያ የያዘውን አፈፃፀም ሂደት እንዱያቆም የተደረገበት ነው። ከዚህ ሁለ መገንዘብ የሚቻለው አሁን እያከራከረ ያለውና ባለሀብትነቱ የወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል ስለመሆኑ የተረጋገጠውን ቤት ቅድሚያ ያስከበሩት የአሁኑ አመልካች መሆኑን ነው። ተጠሪ በመ/ ላይ በስር ፍርድ ቤት ባሰጡት ትእዛዝ ከወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል የሚፈልጉት ገንዘብ የተከፈላቸው መሆኑን መዘገቡ በግልጽ ያሣያል። ከላይ እንደተገለፀው በመ/ የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ትእዛዝ ተጠሪ አከራካሪውን ቤት ለመውሰድ ያደረጉት ጥረት ስለመኖሩ በማረጋገጥ ይህንኑ ያፀደቀ ሣይሆን አፈፃፀም መቋጨቱን ያረጋገጠበት ነው።
በመ/ የተከፈተው የአፈፃፀም መዝገብ ሲሆን የሚያወሣውም ከመዝገቡ ጋር ተያይዞ የሚገኘውንና ግንቦት 25 ቀን 1999 ዓ.ም በተጠሪና በወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል መካከል ተደረገ የተባለውን የእርቅ ስምምነት ሲሆን በመ/ ለፍርድ ቤቱ ቀረበ የሚባለው ደግሞ ሰኔ 18 ቀን 1999 ዓ.ም ተደረገ የተባለው ስምምነት ሁኖ ወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል ለተጠሪ እዲቸውን የከፈለ መሆኑን የተረጋገጠበት ነው። በመሆኑም ተጠሪ አከራካሪውን ቤት በእዲ ምክንያት ከወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል ሙለ በሙለ ተረክቤአለሁ የሚለት መክፈለ በተረጋገጠበት ገንዘብ ጭምር በመሆኑ ተቀባይነት ሉኖረው አይገባም። በልላ አገላለጽ ተጠሪ አከራካሪውን ቤት ከአመልካች ቀድመው ወስደዋል ለማለት የሚያስችል ሕጋዊ መክንያት የለም። ላላው ተጠሪ በዚህ የሰበር ደረጃ የሚያቀርቡት ክርክር አከራካሪውን ቤት ከወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል በመረከብ ባሁኑ ጊዜ ለላላ ሶስተኛ ወገን ሸጬአለሁ የሚል ነው። ይሁን እንጂ ይህ የክርክር ነጥብ በተጠሪ ሉነሣ የሚችልበት እና ተቀባይነት ሉያገኝ የሚችልበት አግባብ የለም። በአጠቃላይ አከራካሪው ቤት ላይ ተጠሪ ከአመልካች አስቀድመው በእዲ ምክንያት ወስደዋል ተብል የተሰጠው ውሣኔ በእያንዲንደ መዝገብ ላይ ሲደረግ የነበረውን አጠቃላይ የክርክር ሂደት ከጊዜ ቅደም ተከተለና በተለያዩ ጊዜአት ሲሰጡ የነበሩትን ትእዛዝ ይዘት በአግባቡ ያላገናዘበ በመሆኑ ስለፍርድ አፈፃፀም የተመለከቱትን የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎችን የሚጥስና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሣሥ 24 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 16 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 23ዐ35 ሚያዚያ 17 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል። በዚህም መሰረት አፈፃፀሙን እንዱቀጥል የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ታዝዟል። ይፃፍ።
ተጠሪ ከወ/ሮ አበበች ወ/ሚካኤል የሚፈልጉትን ገንዘብ ከመጠየቅ ይህ ፍርድ አያስቀርም ብለናል።
በዚህ ሰበር ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።